tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29707
Last Update:
"ርእሰ አንቀጽ"
"…ንጉሡ አንድ ትእዛዝ ያዝዛሉ አሉ። በግዛታቸው በአስተዳደር ክልላቸው ውስጥ የሚኖሩ ዐዋቂ የተባሉ ሁሉ እንዲሰበሰቡ ያደርጋሉ። ዐዋቂ የተባሉትም በሙሉ ከያሉበት ሰበሰቡ። የንጉሥ ትእዛዝ ነውና አንድም የቀረ ሰው የለም። ዐዋቂ የተባሉት ሁሉ መሰብሰባቸውን ባረጋገጡም ጊዜ ንጉሡ እንዲህ አሉ። ከእናንተ ውስጥ እኔ የምሞትበትን ቀን አስረግጦ የሚነግረኝ ሰው እፈልጋለሁ። እርግጠኛውን ቀን የማይነግረኝ ዐዋቂ ካለም ከፍ ብዬ አንገቱን፣ ዝቅ ብዬ ደግሞ ባቱን ነው በሰይፍ የማስቆርጠው በማለት ጥያቄ ያቀርባሉ አሉ። ምድረ ዐዋቂ ነኝ ባይ ሁላ ተጨነቀ። ደነገጠም። እሺ መልካም አስበንበት እንምጣም ብለው ጠየቁ። የጠየቁት ተፈቀደላቸው። የማሰቢያው ጊዜ አልቆም ወደ ንጉሡ ዙፋን ችሎት ፊት መጡ። ሁሉም ግን የንጉሡን መሞቻ ቀን ሊያውቁ ስላልቻሉ በዚህ ምክንያት የንጉሡን ትእዛዝ ባለመፈጸማቸው የሚደርስባቸውን የሞት ቅጣት እንዴት እንደሚጎነጩት በማሰብ እየተጨነቁም ነበር ወደ ንጉሡ የፍርድ ዙፋን ፊት የቀረቡት። ንጉሡም እህሳ እጃችሁ ከምን አሉ። ሁሉም አንገቱን ደፍቶ ዝም። በሉ እንጂ ምን ይዘጋችኋል ተናገሩ እንጂ። ቁጣቸው በረታ፣ ፀጥታም ሰፈነ፣ ቁጣውም በረታ፣ ጭንቅ በጭንቅም ሆኑ። በዚህ ጭንቅ መሃል ነው ዐዋቂ ከተባሉት መሃል አንደኛው የእኔ ቢጤው ኮስማና እጁን አውጥቶ ከፍ ባለ ድምጽ እኔ ዐውቃለሁ ብሎ ጮክ ብሎ የተናገረው።
• ንጉሥ ሆይ ሺ ዓመት ይንገሡ። እኔ እርስዎ የሚሞቱበትን ቀን ተመራምሬ ዐውቄ ደርሼበታለሁ ይላል።
~ ንጉሡም በል ና ወዲህ፣ እንግዲያው በሁሉ ፊት ተናገር። መቼ ነው የምሞተው? ብሎ ይጠይቀዋል አሉ።
• ዐዋቂውም መለሰ እንዲህም አለ። "ንጉሥ ሆይ እርስዎ የሚሞቱት እኔ በሞትኩ በማግሥቱ ነው" ብሎ ፍርጥ አድርጎ ነገራቸው አሉ። ንጉሡም ደነገጡ። ፈሩም። ቀጥሎ የሆነው ምንድነው? ንጉሡ እንዳይሞቱ ሲሉ ዐዋቂውን መንከባከብ ያዙ። እንዲያውም ቤተ መንግሥት አስገቡት። ማረፊያም በዚያ ሰጡት። ጠባቂ ተንከባካቢም አስመደቡለት። ንጉሡ ይሄን ያደረጉት ግን ለራሳቸው ሕይወት ሲሉ ነበር። ዐዋቂው ሞቶ በማግሥቱ እንዳይሞቱ ሲሉ ኢንቨስት አደረጉበት። እና ምን ለማለት ፈልጌ ነው መሰላችሁ የጎጃም ጉብኝቴ እንደቀጠለ ነው ለማለት ፈልጌ ነው። ይሄ ተረት ዋሸራ ደርሼ የቅኔ ተማሪዎቹን በጎበኘሁ ጊዜ የሰማሁት ተረት ነው።
"…ጎጃም ከገባሁ የፊታችን ማክሰኞ ሁለት ሳምንት ይሆነኛል ማለት ነው። የእስካሁኑ ጉብኝቴ እጅግ ግሩም ጉብኝት ነው። 1ቢልዮን ዶላር ቢከፍሉኝ እንኳ የማያዋጣኝን ምክር ነው እኔ ጃል ቆቱው ለጎጃም ዐማራ ፋኖዎች ከፈጣሪ አገኘዋለሁ ብዬ ፈጣሪን ተስፋ በማድረግ በብላሽ ምክሬን እየለገስኳቸው የምገኘው። ከጥቂቶች ጥቂት ፍሬ በቀር ሙላው ጎጃም እየመረቀኝ ነው። ክፋቱ የእኔ ምክር እንደ አይስክሬም አይጣፍጥም። እንደ ማር እንደ ስኳርም አይጥምም። የእኔ ምክር ኮሶ ነው። ይጎመዝዛል። ይቆመጭጫል፣ ይኮመጥጣልም። ያንዘረዝራልም። ግፍግፍ ነው የሚያደርገው። ጨክኖ ታግሶ ለጠጣው ግን ፍቱን መድኀኒት ነው። ጨክነው ከጠጡት፣ ከተጋቱትም ፈውሱ ቅርብ ነው። ወዲያው ያሽራል። ያስተነፍሳልም። የስኳር ውጤቱ ቁጫጭና ወስፋት በሆድ ውስጥ ማርባት ነው። የኮሶ መድኃኒት ግን ለጊዜው ቢመር ቢያንገሸግሽም ዶሮ ማታ ዶሮ ማታ እያሉ ጨክኖ መጨለጥ ነው። በውጤቱም ትላትል፣ የኮሶም ሆነ የሌላ ስም ያለው ትላትል ማስወገድ ነው። ውልቅ፣ ትንፍስ ማድረግ ነው። አይደለም እንዴ? እየጠላኸኝ የግድህን ለምታነብበኝ ለአንተ ነው የምጽፈው።
"…ጎጃም ከገባሁ በኋላ ከታዋቂዋ ድልብ ሸንጎ ኦሮሞዋ ብሪቱ አልማዝ ባለ ጭራዋ በቀር የጎጃም ዐማራ ሆኖ የተቃውሞ ስሜት ያንፀባረቀብኝ አንድም ሰው አልገጠመኝም። የጎጃም የቲክቶክ ሮናልዶና ሜሲዎቹ ዓባይና ጣና፣ ኢትኤል፣ ሔኖኬም ወዘተ የማኅበራዊ ሚዲያ አንቂዎች ጭምር አንዳቸውም ዘመዴ ስህተት ሠርቷል አላሉኝም። እንዲያውም ቄጤማ ጎዝጉዘው፣ ፍራሽ አንጥፈው፣ እንግዳ ክቡር ነው በማለት ነው ተቀብለው እንዳሻህ ሁን፣ ዘመዴ ጎጃም ነፃ ምድር ነው ተንፈላሰስበት ብለው አንቀባርረው የያዙኝ። ሌላው ሲተች ቆይቶ እኛ የማንተችበት ምንም ምክንያት የለም፣ ማንም ከማንም አይበልጥም ነበር ያሉኝ። ሌላው ቀርቶ የቆየ ወዳጄ የሆነው የአልማዝ ባለጭራዋ ወዳጅ ወዳጄ ዩሪ ታደሰ እንኳ ዝም ነው ያለው። መማር ደጉ ማለት ይሄን ጊዜ እኮ ነው። ሁላችሁም ክበሩልኝ።
"…እኔ ጎጃም ምድር ከገባሁ በኋላ በአየርም፣ በምድርም ከባድ ለውጥ ነው እየመጣ ያለው። በኔትወርክ ተደራጅቶ ሲስተማቲካል በሆነ መንገድ አርበኛ ዘመነ ካሤን ይሰድብ የነበረ መንጋ ሁሉ ነው አሁን ክንፉን እንደተመታ ዶሮ ጭጭ ምጭጭ ያለው። ከምር ግን ስለ እውነት ምንም አልታዘባችሁም ማኅበራዊ ሚዲያውን? በጥላሁን አበጀ አዛዥነት በአልማዝ ባለጭራዋ ፖፔትነት፣ በአስረስ ማረ በላየሁም፣ አልሰማሁም ሙድ እሷ ሚዲያ ላይ ወጥታ በጎጃም ዐማራ ስም ጎንደርን፣ ወሎንና ሸዋን ሞልጫ በመሳደብ ለጎጃም ዐማራ ጠላት በመግዛት፣ ስኳድ 24/7 በዚች ጋለሞታ ምክንያት የተከበረውን የጎጃም ሕዝብ ከነ መሪው አርበኛ ዘመነ ካሤ ጭምር ሲሳደብ እንዲውል ይደረግ የነበረው አሁን አለ? የለም። ዛሬ ይሄን በመጻፌ ግንባሩና ስኳድ ዘመነንም ጎጃምንም መሳደብ ካልጀመሩ በቀር ዘመነን መስደብ ለጊዜው ቆሟል። የዘንዶውን ማንቁርት ነው ያነቅሁት። እንዲያውም ስኳድ ከዘመነ እና ከጎጃም ይልቅ ወደ ወሎ ጄነራል አሳምነው ጽጌና ወደ ጎንደሬው አርበኛ ሀብቴ ወልዴ ነው የዞረው።
"…እኔ ጎጃም ምድር ከገባሁ ወዲህ ሌላው ትልቁ የተፈጠረው ነገር ከእኔ ምንም ያጣው ስኳድ፣ ዘመዴ ጎጃምን ይሰድባል፣ በምላሱም የጎጃምን ፋኖ ያውካል፣ ፋፍዴንና ስኳድን ጎንደር ገብቶ እንደናደው ጎጃም ገብቶ የጎጃም ፋኖን ይንዳል። መሪያቸው አርበኛ ዘመነ ካሤንም ያዋርዳል ብለው ቢጠብቁም እሁድ ዕለት በነበረው የመረጃ ቲቪ መርሀ ግብሬም ላይ አንዳች ብናገኝበት ብለው መቀስ ይዘው ሰፍ ብለው ቢጠብቁም፣ ምንም የፈለጉትን ነገር ከእኔ ከዘመዴ ባለማግኘታቸው ምክንያት በማግስቱ ጀምሮ በዶር ደረጄ ቤት የቲክቶክ አዳራሽ በመክፈት እነ ፓስተር ምስጋናው፣ እነ መሳፍንት ባዘዘው፣ እነ ባናና፣ እነ እሸቱ ገጠሬው፣ እነ ሰሎሞን ባለ ሃውልቱ፣ እነ ርስተይ ተስፋይ ሁላቸውም ተሰባስበው ዋይ ዋይ ብለው እንደ አዲስ ማልቀስ ጀመሩ። ቆይተውም "ገዳይነታቸውን፣ አረመኔነታቸውን፣ አራጅ ሳዲስትነታቸው ሁሉ የተገለጸበትና በራሳቸው ላይ የፖለቲካ ሞት የፈረዱበትን የጎጃም ተወላጁን የሻምበል መማር ጌትነትን እስከዛሬ ድረስ አፍነው የያዙትን ቪድዮ ለቀቁ።"
"…በእነሱ ቤት ቪድዮው ሲለቀቅ ዘመዴ የጎጃም ጉብኝቱን ትቶ፣ አቋርጦም ለእነርሱ ቀሽም የሴራ አጀንዳ ምላሽ ይሰጣል። የጎጃም ዐማራም ቪድዮ አለኝ ሲል የነበረው ዘመድኩን አሁን ይሄ ቪድዮ ሲለቀቅ በዘመዴ ላይ ይዞርበታል። ከዚያ ጎጃምና ጎንደር ሲጨቃጨቅ፣ ዘመድኩንም ምላሽ ለመስጠት ሲንገታገት እኛ በመሃል አፈር ልሰን እንነሣለን ብለው ነበር ቁማሯን የሠሯት። የፈበረኳትም። ጎጄ መለኛው ግን ነቃ። ባነነ። እንዲያውም ባልታሰበ መንገድ እንኳንም ገዳይ መሆናችሁን ዐወቅነ፣ እሸቱ ገጠሬው ጠብቅ እንፋረድሃለን፣ ጠብቅ እናሳይሃለን ብለው ወረዱበት። ስኳድ ደነገጠ። እሸቱ ገጠሬውም ጭዳ መሆኑን በማወቁ የለጠፈውን ቪድዮ አነሣው። ሰለሞን ቦጋለ ባለ ሃውልቱም ቀባጠረ። ነፍስ ግቢ ነፍስ ውጪ ሆነ።👇①✍✍✍
BY Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Share with your friend now:
tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29707