tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29728
Last Update:
ተቀብያለሁ ቤቲሻ…😂
"…የጎጃም ጉብኝቴን እንደቀጠለ ነው። ጎጃም በጣም ነው የተመቸኝ። እንግዳ አቀባበሉም ግሩም ነው። እስከአሁን ያደረግኩትን መስቀል አይተው ከሚያጓሩብኝ ጥቂት የአየር ላይ የቲክቶክና የፌስቡክ አጋንንቶች በቀር የጎጃም ምድር ሳር ቅጠሉ ሁሉ ነው የተቀበለኝ።
"…በቶሎ ካለቀልኝ እስከ ልደት፣ ካላለቀልኝ እስከ ጥምቀት፣ ግፋ ቢል እስከ አስተርዕዮ ጥር ማርያም በዓል እቆያለሁ ብዬ አስቤ ነበር። ነገር ግን ሳስበው የጎጃም ፍቅር ስለበረታብኝ ጾመ ኢየሱስን ሁዳዴ ጾምን ሁላ ሱባኤ ገብቼ እስከ ፋሲካም ድረስ ሳልቆይ አልቀርም።
"…ወደ ጎጃም ስገባ ወትውቶ ደውሎ፣ ምነው በጥንስሱ መጣህ ብሎ የተቀበለኝ፣ ፋኖ አስረስ መዓረይ ብዙ፣ ብዙ ምስጢር ከነገረኝ በኋላ እኔ የመረጃ ቴቪ ሰዓቴ ደርሶ ይብቃኝ ብዬ ለሰኞ ከተቀጣጠርን በኋላ አሁን ሚዲያ ላይ ወጥቶ እንዲህ 😡 ጓ ብው ማለቱ ግን አስደንቆኛል። ሆኖም ግን አስረስን ከማያገኘው ከድሮን ጥቃት ለማምለጥ እየተሽለኮለኩም ቢሆን በጎጃም መቆየቴ ግድ ነው።
"…3 ዓመት ሙሉ አርበኛ ዘመነ ካሤ በስኳድ፣ በፌክ ኢትዮጵያኒስት፣ በግንቦት 7፣ በወያኔ፣ በኦነግ፣ በብልፅግና፣ በዋን አዋራ፣ በብአዴን፣ በግንባሩ፣ በክፍት አፉ ሁሉ ሲሰደብ፣ ሲወቀጥ "መሪዬ ለምን ተነካ? ለምን ተሰደበ? ብሎ ትንፍሽ ያላለው አስረስ መዓረይ አሁን እኔ ገና በስሱ ወንድማዊ ጥያቄ በጨዋታ መልክ ስላነሣሁበት የሌለ ከእሱ በማይጠበቅ መልኩ ከመሬት ተነሥቶ እኔ ወዳጁን፣ እኔ"የንስሀ አባቱን" በስንት ውትወታና አማላጅነት አውራኝ፣ አናግረኝ ብሎ ፈልጎ ያገኘኝን ወንድሙን የሌለ ክስ ሲከሰኝ ማየት ያሳፍራል።
"…ምንም የተለየ ነገር አይመጣም። ተልባ ቢንጫጫ በአንድ ሙቀጫ። በሰጨኝ ብዬ አውቶሚክ ቦንቤን በቶሎ አላፈነዳም። ግን ሁሉንም በዝረራ አሸንፋቸዋለሁ።
• ጃል ቆቱ ነኝ ከዲማ…🙏
BY Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Share with your friend now:
tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29728