tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29739
Last Update:
• ጥያቄ እኮ ነው የጠየቅኩት…
"…ትናንት ባሕርዳር ዊኪሊክ ለሀገሯ ልጅ ለጠበቃ አስረስ ማዕረይ ጥብቅና ቆማ እኔ ዘመዴን የሐረርጌ ቆቱ መራታ ነው፣ በጎጃም ከእኛ ሰፈር ዘመድም፣ ወገንም፣ ጓደኛም የለውም ብለ በስሱ ወቅሳኝ ነበር። እኔም ፈጣሪ ያውቅልኛል ብዬ እንባዬን ወደ ሰማይ ረጭቼ ዝም አልኩ። ብዙዎች ግን በኮመንት መስጫው ላይ ሲከራከሩልኝ ሳይ ግን ዐማራ ፍትሕ ዐዋቂ ነው የሚለውን ቃል አስታወሼ ተጽናናሁ።
"…ከወኪ ሊኪ ዘገባ ግን እኔን የሳበኝ "…ምናልባት ግላዊ ህይወቱንም መዳሰስ ካስፈለ… አስረስ ማረ ዳምጤ ጥሩ ገቢ የነበረው ጠበቃ ነበር። አስረስ ልጆቹና ሚስቱ ወዳሉበት አሜሪካን አገር ለመምጣት የአሜሪካ ኤምባሲ ቀጠሮው ደርሶ ቀናቶች ሲቀሩት ጫካን የመረጠ የትውልዱ የነጻነት ፋኖስ ነው።" የሚለው አረፍተ ነገር ነው። "በተለይ ልጆቹና ሚስቱ ወዳሉበት አሜሪካን አገር" የምትለዋ አፈዘዘችኝ።
"…አስረስ ቢያንስ ዘር ተክቷል። ሚስቱና ልጆቹንም አሽሽቷል ማለት ነው አይደል? መልካም የእኔ ጥያቄ አስረስን ትላንት አናድዶት መሳይ መኮንን ቤት ሄዶ እኔን እንዲሳደብ ያስገደደው ነገር "በጎጃም የዐማራ መምህራን ለምን ይገደላሉ? በጎጃም የሚፈጸመውን የመምህራን ግድያ አቁሙ ማለቴም ነው።
"…ዲግሪ አለው። የተስተማረ ነው። ፍልስስ ያለ መኪና ነበረው። ቆንጅዬም ውብም ነው ወዘተ ብሎ መከራከር ይበጃችኋል ወይ? ጥያቄው እኮ እሱ አይደለም።
• የመምህራን ግድያን አስረስ መዓረይ ያስቁም። ይሄ እናንተን ቢደብራችሁም የእኔ ጥያቄ ነው።
BY Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Share with your friend now:
tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29739