tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29751
Last Update:
መልካም…
"…በክርስቶስ ቅዱስ መስቀል መረገጥ ኢትዮጵያ በመሬት መንቀጥቀጥ እየተናጠች ነው። በተለይ 4 ኪሎ በሚገኘው በቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ለጥር 7 ቅዱስ ፓትርያርኩ፣ ብፁዓን ሊቃነ ጳጳሳት፣ ካህናት፣ ዲያቆናትና ምእመናን በተገኙበት በኢትዮጵያ ምድር በታላቅ ክብር የቆየውን ቅዱስ መስቀል በይፋ በመርገጥ ቤተ ክርስቲያን ፀረ ክርስቶስነቷን በይፋ የምታወጅበት ዕለት ይሆናል ተብሎ ስለሚጠበቅ የመሬት መንቀጥቀጡ ይቀጥላል። እርግፍግፍ፣ ውድም ያደርገናል። ምህላ የሚኖረው የሃይማኖት አባቶቹ በእግዚአብሔር መኖር ሲያምኑ እኮ ነው። ምህላም የለም ይቅርታ ምህረትም የለም። መስቀሉን እንዳዋረድነው እንዋረዳለን። በራብ፣ በጦርነት፣ በጭንቅም እንኖራለን።
"…ሌላው እኔ ዘመዴ ከሸዋ፣ ከወሎና ከጎንደር መልስ ጎጃም ለጉብኝት መግባቴ ሰማይ ምድሩን በአዋራ አንቀጥቅጦታል። ጫጫታው በዝቷል። ግን ምንም መፍጠር አይችሉም። ጎጃም እቆያለሁ። እበድ፣ ፍረጥ፣ ዝለል፣ ጩህ፣ አጓራ ደንታዬ አይደለም። "ደመቀ ዘውዱን፣ እስክንድር ነጋን፣ ሃብታሙ አያሌውን፣ አበበ በለውን፣ የጎንደርን ስኳድ ስነካ ከተፈጠረው ጫጫታና ግርግር አይበልጥም የጎጃሙ። በመጨረሻ ዘመዴ እውነቱን ነው ብለህ ልትፀፀት አጉል ደርሰህ አትንፈራገጥ። የእስክንድር ነጋ ጠባቂ ጎጃም ምን ይሠራል? እስክንድርስ ደቡብ ጎንደር ምን ይሠራል? አርበኛ ዘመነ ካሤ ይሄ ሁሉ ድራማ በዙሪያው ሲሠራ ያውቃል? የዛሬው የመረጃ ቲቪ ዝግጅቴ ልዩ ነው የሚሆነው። እስከዚያው ላታስቆሙኝ ተንጫጩ።
"…እያየኸኝ፣ እየሰማኸኝ በዝረራ አሸንፍህሃለሁ። ወላዲተ አምላክ ምስክሬ ናት። የጎጃም ፋኖን ከከበበው ጭራቅ እታደገዋለሁ። ባህርዳር፣ ኢንጂባራና ደብረ ማርቆስ ዩኒቨርሲቲ፣ ጫካና አሜሪካ የመሸገውን ፀረ ጎጃም ዐማራ ሁሉ አውጥቼ አሰጣዋለሁ። ማርያምን ብዬ ማልኩ እኮ። አለቀ።
BY Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Share with your friend now:
tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29751