tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29764
Last Update:
መልእክቱ ደርሶኛል…!
"…ብዙ ሰዎች ይህን ዛሬ በማኅበራዊ ሚዲያ ሲዘዋወር የዋለ ቪድዮ ልክለውልኝ አይቼዋለሁ። ተመልክቼዋለሁም። ከቪድዮው የተመለከትኩት አካላዊ እንቅስቃሴ ለእኔ ለዘመዴ የገባኝ ነገር በደንብ ገብቶኛል። ግልፅም ነው። በፋኖ ስለሺ፣ በፋኖ ጠበቃ አስረስ እና በፋኖ ማርሸት የተከበበው አርበኛ ዘመነ ካሤም እንደወትሮው አንበሳ ሆኖ ስላላየሁት ያለበትንም ሁኔታ አሳምሬ እረዳለሁ። አሁን ላይ በዚህ ቪድዮ ዙሪያ ምንም አልልም። ምንም።
"…ሌላው ደስ ያለኝ የቀድሞው የአሚኮ ጋዜጠኛ ግማሽ ትግራዋዩና ግማሽ አገው ሸንጎው ወንድሜና ወዳጄ ጋዜጠኛ ተስፋዬ ወልደሥላሴ እንዲህ ጮቤ መርገጥ ነው። ከተስፍሽም ጋር ሒሳብ የምናወራርድበት ቀን ደረሰ ማለት ነው። እግዚአብሔር ይመስገን። ከጀመርነው አይቀር የበረከት ስምዖን ቀኘ እጅ ስለሆነው የራህናይ ሆቴል ባለቤት ስለ አገው ተወላጁ አበበ ይመኑ እና ስለ ሚስቱ መርድያ እንድሪስም እናወጋለን።
"…በቀደም ዕለት ድብቅ ስብሰባ ነበር። ስብሰባውን መሳተፍ የምትችለው የግዮን ልጆች በሚል ኮድ ነበር። ስብሰባውን የሰበሰበውና ያደራጀው ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ ሲሆን፣ የሰኔ 15ቱ አክተር አማኑኤል አብነት፣ ይኼነው የሸበሉ፣ ዳዊት ብዙነህ፣ ምስጋናው ዘግዮን፣ እነ ሄኖክ እና እኔ የዲማው ዘመዴ ነበርን። መጨረሻ ላይ ማን ቢመጣ ጥሩ ነው? አስረስ መዓረይ…? ሁሉንም ቀድቼአቸዋለሁ።
"…አስረስ ሲያወራ ዘሜን ተመልከቱት። ቢረፍድም ግን በሰዓቱ ደርሼአለሁ። መርጦለ ማርያም ዘግናኝ ጉድ እየሰማሁ ነው። ለጊዜው ተስፋዬ ወልደ ሥላሴ በኮሚቴነት ላለበት የገንዘብ ስብሰባ ተጠንቀቁ እላለሁ።
"…አሄሄ ወዴት ወዴት አባዬ? ወዴት ወዴት? የዘንዶውን ራስ ረግጬዋለሁ። እኔ ዘመዴ እንደሁ አንደዜ ከነከስኩ ነከስኩ ነው። ጎጃም እቆያለሁ። የነገ ሰው ይበለን። ተስፍሽም ተዘጋጅተህ ጠብቀኝ።
BY Zemedkun Bekele (ዘመዴ)
Share with your friend now:
tgoop.com/ZemedkunBekeleZ/29764