Telegram Web
ከ20 ምናምን ዓመት  ቡኃላ እማዬ ወጥ ጭማሬ ማለት ተገቢ አይደለም። ትዳር እየያዛቹህ'ጂ!።
አሁን ላይ የቱንም ያክል ረሺ ብንሆንም
እያንዳንዷን ጥቃቅንና ዝርዝር ስራችንን የምናስታውስበትና ከዚያም እነሆ የስራ መዝገብህ ያውልህ። ራስህም አንብበው የምንባልበት ቀን ከፊታችን ይጠብቀናል።

              "يوم يتذكر الإنسان ما سعى
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
የሰው ልጅ ይለምዳል። ሙያ ብቻ ሳይሆን ስሜትንም በመልመድ ይኖራል። በህይወቱ እንዳይከሰቱ ይፈራላቸው የነበሩ ቀናት ተከስተው መመልከት ይጀምራል። የቅርብ ቅርብ ሰዎቹ መሞት፣ የእጅ ማጠር፣ ወዳጆቹን ማስታመምና ከብዙ አብሮነት በኋላ የሚመጣ ብቸኝነት… የሚፈራቸውን ያህል ተፈጥረው ያገኛቸዋል። መጀመሪያ ነገር… ያለቅሳል፣ ይጨነቃል፣ ልዩ የሀዘን ስሜት ያጋጥመዋል። ከዚያስ? አይለመድ ነገር የለምና መላመድ ይመጣል። በየትኛውም ክስተት ውስጥ የማይሰብርህ ግን የአላህ ፍቅር ነው። አላህን መልመድ ከቻልን ነገርዓለሙ ሁሉ ይግራራል። መጥፎ ሁኔታ ውስጥ እንኳን ብናልፍ!!
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የሸሪዓ ህግ "የገደለ ይገደል"  የሚለው ተፈፃሚ እስካልሆነ ድረስ…የሰው ሂዎት እንደቅጠል መርገፉ አይቀርም። በዚህ ልክ የሰውን ነፍስ መቅጠፍ ምን አይነት ጭካኔ ቢሆን ነው። አሏህማ! እዝነቱ ሰፊ ነው። ይህ ሁሉ ግፍ እያለ እሳትን አለማዝነቡ…ዕውነትም አዛኝ ነው።

በቃ ዱንያ እንዲህ ነች!። ደስታና ሀሰን፣ ሳቅና ለቅሶ፣ እዝነትና አረመኔነት የተቀላቀለባት ባለ ብዙ ቀለም…ሰባራ ሸክላ ናት። አያቹህ! ሞት መቼ እንደሚመጣ አይታወቅም።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
በፍቅር ውስጥ ከባድ ወይም ኃያል ተብሎ የሚጠራ ሰው የለም። የተጨበጨበለት ስኬት ላይ ብትደርስም በፍቅር ቤት "አንቱ" ተብሎ አይሰገድልህም። የቱንም ያህል የገነነ ስም ቢኖርህም ስታፈቅር ቅጣምባሩ ሌላ ነው። ነብይ ብትሆን እንኳን እንደነብይህ ባለቤትህ ጉልበትህን እንድትረግጥ አድርገህ ግመሉ ላይ እንድትወጣ ማድረግ ይኖርብሃል ፣ ሩጫ ውድድር በማጫወትና አጋርህ ውሃ የጠጣችበትን የእቃው ቦታ እየፈለግህ በመጠጣት ስለፍቅር ትሸነፋለህ፣ ዝቅም ትላለህ። ስትወድ እንደህፃን ልጅ ትከሻ ላይ ትንጠለጠላለህ፣ ተለምዶና ህግ ብዙም ቦታ አይኖራቸውም። እና የወንድነት ትርጉሙም እዚህ ቦታ ላይ ለየት ብሎ… በመሸነፍ ይተካል። መሸነፍ በቃ…
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
"ኡምሩቀይስ" የተባለ ጀግና ሰው ነበር ፣ በፍቅር ተሸንፎ…ከታች ያሉትን ግጥም ሰደራቸው ፦

رجُلٌ وما استسلمْتُ قَبْلُ لفارسٍ
‏ مالي أمام عيونها مُستسلِمُ !؟
‏⠀⠀⠀
‏أأعودُ منتصِرا بكل معاركي
‏وأمام عَيْنيها البريئة أُهْزَمُ !

ከዚህ በፊት ለፋርስ - እጅ ያልሰጠሁ
ምነው ከዓይኗቿ ፊት - እጄን  ሰጠሁ

በጦርነቴ ሁሉ በድል እመለሳለሁ
በፈካ ዓይኖቿ ፊት - እሸንፋለለሁ

አብደረህማን አማን
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ወዳጄ ምንም መልካም ሰሪ ብትሆን ባንተ ጉዳይ የሚጠመዱ ሰዎች አይጠፉም። ይህን ግሩም አንቀጽ ተመልከት

﴿وَقَالُوا مَا لَنَا لَا نَرَىٰ رِجَالًا كُنَّا نَعُدُّهُم مِّنَ الْأَشْرَارِ﴾

ዱንያ ላይ በመጥፎ የምናያቸው የእሳት እንደሆኑ የምንቆጥራቸው ሰዎች የት ጠፉ? ይላሉ።

እጅግ አቃጣይ በሆነው እሳት ውስጥ፣ በዛ ከባድ ህመም ውስጥ ሆነው እንኳን ስለ ሌሎቹ የህመም ደረጃ ለማወቅ የሚፈልጉ ሰዎች አሉ። የራሳቸው ህመም ስለሌሎቹ ለማወቅ ከመፈልግ አላገዳቸውም።

እሳት ውስጥ እንዲ ካሉ፣ በዱንያስ?
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
አንድ ሰውዬ የራሱን ጥላ ለመያዝ ያስባል አሉ። ወደ ጥላው በቀረበ ልክ ጥላው ከሱ ይሸሻል። ከጥላው በላይ መፍጠን አለብኝ ብሎ ያስብና መሮጥ ይጀምራል። በሮጠ ቁጥር ጥላውም ይሮጣል። ልይዘው አልቻለም፣ ደከመውና ተስፋ ቆርጦ ወደኋላ መመለስ ይጀምራል። ጥላው ይከተለዋል። ቅድም ሲያሳደው የነበረው ጥላ አሁን አሳዳጅ ሆኖ መጥቶበታል። ሰውዬው ሩጫውን ጀመረ ጥላውም ከኋላው ይሮጣል፣ ራሱን እስኪስት ድረስ ሮጠ፣  ጥላው አለቀቀውም። በመጨረሻም በቃ የምርም ሊበቀለኝ ነው ብሎ አሰበ ይባላል!

ይህ የዱንያ መገለጫ ነው። አንዳንዴ በህይወታችን አንዳንድ ነገሮችን እስካልተውናቸው ድረስ አናገኛቸውም።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
«فهل تستطيع أن تغيب وجهك عني؟! »

ይቅርታ የምታደርግላቸው ግን ደግሞ ስብራቱን የማትረሳላቸው ሰዎች አሉ። እነሱን ማየት የሚፈጥርብህ መጥፎ ስሜት ስላለ ይቅር ብያችኋላሁ ባይሆን ግን እንዳላያችሁ እሻለሁ የምትላቸውም አሉ። ይህን ማድረግህ ያደረግከውን ይቅርታ ደረጃውን ዝቅ የሚያደርግ፣ ዋጋውን የሚያሳጣ ሆኖ አይደለም። ግን በቃ ልታስወግደው የማትችለው ሰዎች ባንተ ላይ ጥለውት የሚያልፉት፣ ሰዎቹን ባየሃቸው ቁጥር ያ መጥፎ ትዝታቸውና ግፋቸው እየታወሰህ የሚያሳምምህ መጥፎ ጠባሳ ስለሆነ ነው።

ልክ ነብዩ ﷺ የአጎታቸውን ገዳይ ወህሽዪን رضي الله عنه ይቅርታ አድርገውለት "ምናለ ፊትህን ዞር ብታደርግልኝ" እንዳሉት። ይህንን የረሱልን ሃዘን ላለማስታወስ ሲል ረሱል ሲመጡ መንገድ ሁላ ይቀይር ነበር።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
"የነገ ሟች የዛሬን ሟች ይቀብራል።"

ሀሰን አል-በስሪይ
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
[وَلَا يَجْرِمَنَّكُمْ شَنَآنُ قَوْمٍ عَلَىٰ أَلَّا تَعْدِلُوا ] المائدة 8

ለሰዎች ያላችሁ ጥላቻ ፍትሃዊ እንዳትሆኑ አይገፋፋችሁ ብሎን አዞናል!። ብርቱ የሆነ ጥላቻም ይሁን ውዴታ ባለቤቱን አጥፊ ነው። ነቢዩሏህ ዩሱፍ عليه السلام ተፈትኖበታል።የወንድሞቹ ብርቱ የሆነ ጥላቻ ጉድጓድ ውስጥ እንዲጣል አድርጓል። ብርቱ የሆነ ውዴታም ለእስር  ዳርጎታል።

እኛ የልባችንን አቋም መቋቋም ሊያቅተን ይችላል።በየትኛውም ሁኔታ ወደድንም ጠላን ፍትሃዊ እንድንሆን ግን ታዘናል።

ስለምትወደው ብለህ የምትወደውን ሰው ወንጀል መልካም ስራ አታድርግ። ስለምትጠላው ብለህ የምትጠላውን ሰው መልካም ስራ ደግሞ ወንጀል አታድርግ።

በየትኛውም ሁኔታ ፍታሃዊ ሁን!።

رسائل من القرآن
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ለምን ይሁን ግን ብዙ ኪታቦች ላይ ብዙ ግዜ ስለ ንጽህና የሚያወራው ክፍል ቀድሞ እየመጣ ስለ ጂሃድ የሚያወራው ግን መጨረሻ የሚመጣው ተብለው ተጠየቁ።

"ስለ ንፅህና የማያውቅ ስለ ጂሃድ እንዳያወራ ነው።" ብለው መልሰዋል ቀደምት ሰለፎች
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
የሶሀቦች ቅሬታ
ባለሀብቶቹ አጅሩን ሁሉ ጠቀለሉብንኮ ስለዚህ ለደሃዎች ብቻ የተገደበ ስራ ይጠቆመን የሚል ነበር።

የኛ ቅሬታ ደግሞ እነሱ ሀብታም ሆነው
ለምን እኔ ደሃ ሆንኩ የሚል ይመስላል።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ልጁን "አብዱ'ሰታር" ብሎ የሰየመ  "አብዱ'ሰቲር" በሚል ይቀይረው። ሰታር የሚባል ለአሏህ ስም የለውም። ያሰታር ሳይሆን ያሰቲር ነው ሊባል የሚገባው!። አንዳድ ዑለሞች "ሰታር" የሚለውን ስም ከአሏህ ስሞች ውስጥ አድርገው ቢጠቅሱትም፣ መረጃ ግን የላቸውም። የአሏህ ሲፋዎች ሁሉ "ፈዒል በሚል ወዝን ነው የመጡት!" ልክ ፦ ሐሊሙን፣ ሰቲሩን፣ ከሪሙን፣ ቀዲሩን እንደሚባለው።

ሸይኽ ሙ/ድ አሊ አደም አል-ኢቲዮጲይ
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
2025/01/12 12:06:41
Back to Top
HTML Embed Code: