Telegram Web
መፍትሄ ሽተህ ህይወትን ስትኳትናት… ራስህን አትርሳ። ህይወት ማንንም አትጠብቅም። ሰውነትህን የሚወረው ሽበትና መጨማደድ…  ከረጅም እድሜ በኋላ ብቻ ይመጣል ብለህ አታስብ።
ከዛፏ አናት ላይ የተባረረችን ቅጠል አይተህ ታውቃለህ? … ከመድረቅ ውጪ ምን ተስፋ ነበራት?…ምንም!!… እንደሷ እንዳትሆን… ጭንቀትህን ግታው፣ ተስፋህን አለምልመው… ከመውደቅህና ከመረሳትህ በፊት ራስህን አትርሳ!!
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
የጅማሮዎች ሞቅታና ጉጉት ፍቅር አይደለም!
ታውቃለህ? የሰው ልጅ በሳምንት ወይም በወር ውስጥ አያፈቅርም። በዚህ ወቅት አንተ  ፍቅር ብለህ የምታስበው… ጊዜያዊ ጉጉትና መደነቅ ነው። ዳርቻው ላይ ሆነህ ባህሩን ስለማፍቀር ልታወራ አይቻልህም። … ውስጡ ዘልቀህ መግባት ይኖርብሃል፣ ማዕበሉ ሊመታህ ይገባል፣ ጨለማ ጎኑን መመርመር፣ ነውሩን መዳበስና የቁጣውን መልክ ማወቅ አለብህ። ከዚያ በኋላ ነው… ወይ ፍቅርህ ወይ ጥላቻህ የሚለየው… ፍቅር የሚጀምረው ጊዜያዊው ሞቅታ ሲያበቃ እንደሆነም አስተውል።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ተፈጥሮ ሆኖ
ብገረምብሽ ባደንቅ መልክሽን
አስተውላለሁ
"ምግባር" የሚሉት የሰው ልክሽን።

نَـحْـنُ أَبْـنَاءُ السَّلفِــيِّينْے
"ሰዎች ባንተ ከተገረሙ… የተገረሙት አላህ ነውርህን ስለሸፈነልህ መሆኑን እወቅ!" [ኢብኑል ጀውዚ]

አንድ ፀጋ ባይለገስህ ኖሮ ፀጋዎች ሁሉ ዋጋ እንደማይኖራቸው ታውቃለህ?…  የመሸፈን ፀጋ… አላህ ብዙ ነውሮችህን ሸፍኖልሃል… ይህንን መጋረጃ  ቢገልጥብህ…  አንገትህን ቀና አድርገህ ሰውን መመልከት ያሻፍርህ ነበር… ሰውም አንተን ማየት ይቀፈው ነበር።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
"ትዳርን የማትወርድበት የሀሴት ሰገነት አድርገህ አታስበው። ነፃነትን የሚገፍ እስርቤትም አይደለም። … ቀድመህ የምታውቀውና ገብተህ የምታየው ፍፁም ይለያያል። ገነትም ገሀነምም ውስጡ አለ። እዚያ ውስጥ ትፈተናለህ። ፈተናውን ለማለፍ ሁለቱ ሩሆች ፍቃደኛ መሆን አለባቸው… ፍቅር ብቻውን ዋጋ አይኖረውም… መረዳትና መተማመንም ከውስጡ ያስፈልጋል።"
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
በጣም ደስ የሚል ስሜት አለው… ነብይህ ላይ የምታወርደው ሰለዋት… በስምህ ሲደርሳቸው… እገሌ የእገሌ ልጅ ተብሎ … አላህም በአስር እጥፍ አንተ ላይ እዝነቱን ሲያሰፍን… ደስ የሚል ስሜት አለው… ነብይህ  በሰለዋት ብዛት ያውቁህ ይሆን?
ﷺﷺﷺﷺﷺﷺﷺ
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ነቢዩሏህ ያዕቁብን አልዘነጋውም … ግን የዩሱፍን ንግስና እየገነባ ነበር… ሰዓቱ ደረሰ… ቀሚሷ የያዕቁብን የአይን ብርሃን እንድትመልስ አደረጋት… ህፃን እያለ ያጣው የዓይን ማረፊያ ልጁን ትልቅ ሆኖ ከንግስናው ጋር ተመለከተው… ልቡ ተጠገነች… አህባቢ… እርሱ ልቦችን እንዴት እንደሚጠግን ብታውቁ  ተስፋ መቁረጥ አይጠጋችሁም ነበር።

« ዐለይሂማ ሰላም »
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
Audio
ሐበሻዊ ነው…ተጋበዙልኝ።
ሰያው አሏህ ይጨምርልህ
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ታውቃለህ? ነብይህ እጅግ በጣም አይናፋር እንደነበሩ… ከሃያኣቸው የተነሳ አይናቸውን አፍጥጠው ተመልክተው እንደማያውቁ…ታውቃለህ??…  ያሊላህ… ምን አይነት መሪ ነበሩ…
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
“አንድ ሰው በሚሰማው ስሜትና ለሌሎች ማብራራት በሚችለው አቅም መሀል ያለው ርቀት  ምን ያህል ትልቅ ነው!!”
[አህመድ ኻሊድ ተውፊቅ]

ሲናገር የሚያለቅስ ሰው… በደሉን ሲገልፅ የሚስቅ ሰው… ለመናገር በረጅሙ የሚተነፍስ ሰው አጋጥሞህ ያውቃል?… በስሜቱና በሚያስረዳው ነገር መሀል ያለው ርቀት ነው።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ከላይ የምትመለከቱት በወረባቦ "ደለይመሌ" መስጂድ የአዛን ማድረግያ ቦታ ነው። በወረባቦ ውስጥ…ታሪካዊ ቅርሶች ከሚባሉት አንዱ ነው።

ምን ትዝ አለኝ መሰላቹህ?…የአባቶቻችን ጥንካሬ፣ የሙያ ክህነታቸው፣ ለኢስላም የከፈሉት መስዋኣትነት፣…ዲንጋዩን አቅልጠው፣ ዋሻውን ቦርቡረው መስጂዶችን ሰርተዋል'ኮ…ያአሏህ
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ያጀማዓ! ይሄ መስጂድ የት እንዳለ ታውቃላቹህ?

በወረባቦ  012 ቀበሌ ውስጥ ነው። ከዋና ከተማችን ከቢስቲማ 27 ኪ.ሜ ርቀት ላይ ይገኛል፣ በዕድሜ አንጋፋ ከሚባሉ መሳጂዶች ውስጥ ነው፣ ከ'800 እስከ 900 ዕድሜ እንዳለው ይገመታል።

ክብር ለአባቶቻችን!።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ለመኖር… ጠንካራ መሆን ይጠበቅብሃል… የአካል ጥንካሬ ሳይሆን እያንዳንዱን መጥፎ ነገር የመቻል ጥንካሬ… መጥፎ ፊት ፣ ያልተገባ ባህሪ……
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ምንድነው መስፈርቷ???
....................................

ስላንቺ ሰምቼ ልቤ ተንጠልጥሏል፣
መጥቼ እንዳላይሽ ሩቅ ናት ብለዋል።
ቦታሽ ጋር ለመድረስ መስፈርት አላት አሉኝ፣
ውስጥሽ ያለው ነገር ግሩም ነው መሰለኝ።
መንገዴን ጀምሬ ወዳንቺ እየመጣሁ፣
ድንገት ጎዳናው ላይ አንድ ሰው አገኘሁ፣
  ፍርሃት እየያዘኝ ድፍረት እያጠረኝ     
ጠጋ አልኩኝና፣
  ጥያቄ አቀረብኩኝ እየተነፈስኩኝ
የውስጤን ገመና።
ውዴታዬ ፀና ፣ ናፍቆቴም በረታ፣
ወደርሷ ለመድረስ ምንድነው መስፈርቷ?
                            ምንድነው መስፈርቷ?
ትንሽ ዝም አለና "እኔም መንገድ ላይ ነኝ" አለኝ እያላበው፣
"ግን በነገርህ ላይ ልብህ እንደምን ነው?" አለኝ ሳልጠይቀው።
ልቡ ለጠቆረ ፣ ታማኝ ላልሆነ ሰው፣
ምላሱ ለማያርፍ፣ እውነት ላልተቸረው፣
ፆም ላይ ሳይዘወትር ዘንግቶ ለኖረ፣
አንደማትገባ በትልቅ መዝገብ ላይ አንብቤ ነበረ፣
በማለት አስታውሶኝ ንግግር አቁሞ በዝምታው ቀረ።
እናም ጎደኞቼ…
ከመካከላችሁ በደግነት በልጦኝ ቀድሞኝ የደረሰ ፣
ህይወት ያማረለት እሷን ተጎናፅፎ ጎጆ የቀለሰ፣
መልዕክት አለኝና ለርሷ አድርሱላት፣
በናፍቆት የናኘ አንድ ሰው ነበረ ብላቹ ንገሯት፣
አንድ የዋህ አፍቃሪ በፍቅሩ ሳይኮራ፣
ስላንቺ ሲገጥም ስምሽን ሲጠራ ፣
ሰምተነው ነበረ በሉልኝ አደራ።
አንቺ ማለት እኮ…
ምንዳ ሲከፋፈል በትንሳዔ እለት በፆሙ ለፀና፣
በደማቅ ውበትሽ መግቢያ እንድትሆኚ ተፈጥረሻልና።
እጅግ ጓጓሁልሽ ተነሳ ስሜቴ፣
የፆመኞች በር "ረያን" ጀነቴ።
.........
"ረያን" ማለት ፆመኞች ብቻ የሚገቡበት የገነት በር ናት።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
"ትዳር ከሥጋዊ ዝንባሌ መገላገያ ብቻ ሳይሆን የተለያዩ መመዘኛዎችን የሚፈልግ ቁሳዊ፣ሥነ ምግባራዊ እና ማኅበራዊ ኩባንያ ነው።"

ሙሀመድ አልጘዛሊ
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
በጊዚያዊ ስሜቶች ለሚያስተናግዱህ ሰዎች ክፍት ሁን ብዬ አልመክርህም። ሲፈልጉህ እላፊ ተጠግተው የነፍስ ዓለም የሚያደርጉህና ስትፈልጋቸው ደግሞ ሽታቸው የሚርቅህ ዓይነት ሰዎች ማለቴ ነው። እና እዚህ ዓይነት ብቻህን የምትፋለምበት ግንኙነት ውስጥ ሰላምም ህይወትም የለም። መራራቅ የማያደበዝዘው፣ መከራና ደስታን የሚጋራና መከታ የሚሆን ግንኙነት ውስጥ ራስህን ኢንቨስት አድርግ። ጓደኞችህንም  በመመርጥ ላይ እያልኩህ ነው።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
ሁሌም ብቻህን ሆነህ ከአላህ ጋር አውራ። እንደዘከሪያ «ዐለይሂ'ሰላም» ድካምህን ስትገልፅ ድምፅህን ዝቅ አድርገህ "አንተን በመለመኔ እድለቢስ ሆኜ አላውቅም" በለው።  "መሻትህን ወድጃለው ፣ ውሳኔህን በፀጋ እቀበላለሁ" ብለህ ስትነግረው…  እርግጠኛ ሁን ፍላጎትህን ይወድልሃል፣ ያስደስትሃልም።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
"አላህ አዳዲስ ጅማሮዎችን ሲሰጥህ… የበፊት ስህተቶችን አትድገም።"
[ነጂብ መህፉዝ ]

ምናልባት ትናንትህ  በብዙ ስህተቶች ተሞልቷል። ትናንት ላይ ያባከንካቸው በርካታ እድሎች ይኖራሉ። ግን አስተውል ዛሬ አዲስ ጀንበር ወጥታለች… ጨለማውን የገረሰሰች ጀንበር… ስለዚህ አዲስ ጅማሮን አላህ ሲሰጥህ የትናንቱን ብኩንነትና ስህተት አትድገም።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
መርየም በዚያ አስቸጋሪ የጭንቀት ዓለም ውስጥ ሆና… "ባልተፈጠርኩ" የሚያስብል  ስቃይን እያስተናገደች፣   ሁሉም ነገር ዳገት ሆኖባት…  “ብዪ ፣ ጠጪም፣ ተደሰችም”[ሱራ መርየም 26] ተብላለች።  አላህ ምን እያለህ ይመስልሃል?  ነፍስን የሚፍቅ ሰቀቀን ቢያጋጥምህም ፣ ዓይንህ አላስችል ብሎት የእንባ ቋንጣውን ቢወረውርም … እላፊ በማብሰልሰል ከሰዋዊ ፍላጎትህ አትራቅ… ነፍስህንም አትቅጣ። ህይወትህን እንደሚገባህ ኑር። እያለህ አይመስልህም?
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
በውስጥህ ያለውን የዩሱፍ «ዐለይሂ'ሰላም» "ይቅርታ" ያወቁ ሰዎች ፣ ከጉድጓዱ ስር አንተን ለመወርወር አያመነቱም።
www.tgoop.com/abdu_rheman_aman
2025/02/22 03:58:57
Back to Top
HTML Embed Code: