tgoop.com/adinunnesiha/10537
Last Update:
ሶለዋት ➝ የአላህን እዝነት ያስገኛል‼️
▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬ ▬
✍ለአለማት እዝነት ተደርገው በተላኩት በውዱ ነብያችን ሙሐመድ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረድ በጁሙዓ ዕለት ከሚወደዱ ዒባዳዎች መካከል አንዱ ነው። ሶለዋት ሱና ብቻ ሳይሆን የአላህን ትእዛዝ መታዘዝ ብሎም፤ የቂያም ቀን የርሳቸውን አማልጅነት ማገኛም መንገድ ነው።
-
በርሳቸው ላይ ሶለዋት ማውረድ የአላህን እዝነት ያስገኛል። አላህ ኸይር ነገር በርሳቸው ላይ አወረደ፤ እኛንም ከዚህ ኸይር ተጋሪዎች አደረገን። ኣንድ ሶለዋት ስናወርድ፤ አላህ በእኛ ላይ ዓስር ሶለዋት ያወርዳል። ከአላህ ዘንድ ለፍጥረታት የሚወ'ረድ ሶለዋት ደግሞ ከጨለማ ያወጣል። ብርሓንን ያስገኛል። የኣላህን እዝነትና ውዴታን ያጎናጽፋል።
*
በጁሙዓ ዕለት፣ ተሽሑድ ላይ፣ የርሳቸው ስም ሲነሳ፣ ኣዛን ሲባልና መስጅድ በምንገባበት ጊዜ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማውረዱ ይበልጥ ሙስተሓብ ከሚሆኑባቸው ወቅቶች ናቸው።
√ ሶለዋት አጭር ድካም ትልቅ ትርፍና የተነባበረ ፀጋ!
«በእኔ ላይ ኣንድ ጊዜ ሶላዋት ያወረደ፤ አላህ በርሱ ላይ ዓስር ጊዜ ሶለዋት ያወርድለታል።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ:-📒ሙስሊም (384)
«مَنْ صَلَّى عَلَيَّ صَلاَةً صَلَّى اللهُ عَلَيْهِ بِهَا عَشْرًا.»
√ ሶለዋት ከነብዩ ጋር በቀጥታ ሰላምታን ያስገኛል።
«ማንም ሰው ለእኔ ሰላምታ (ሶለዋት) ካደረገ፤ አላህ ሩሔን ይመልስና ሰላምታውን እመልስለታለሁ።»
ረሱል (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም)
ምንጭ፦📒ሶሒህ አቡ ዳውድ (2041)
«ما من أحدٍ يسلِّمُ عليَّ إلَّا ردَّ اللَّهُ عليَّ روحي حتَّى أردَّ عليْهِ السَّلامَ.»
√ በተቃራኒው ደግሞ በነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ላይ ሶለዋት ማድረግን የሰሰተ፤ በራሱ ላይ ኸይር ነገርን ከማግኘት ሰስቷል። በነፍሱ ላይ ነፍጓል።
ነቢዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዲህ ይላሉ፦
«ስስታም ማለት ከርሱ ዘንድ እኔ እየተወሳሁ፤ በኔ ላይ ሶለዋት ያላወረደ ነው።»
ምንጭ፦📒ሶሒሁ ቲርሚዚ (3546)
«البخيلُ الذي من ذُكِرْتُ عندَه فلم يُصَلِّ عليَّ.»
✔️ የሶለዋት ነገር ከባድ ከመሆኑ የተነሳ አላህ ራሱ እኔ አወርዳለሁ፤ እናንተም ኣማኞች ሁሉ በነቢዩ ላይ ሶለዋት አውርዱ የሚል ትዕዛዛዊ–መልክትን በቁርኣን ነግሯል።
إِنَّ اللَّهَ وَمَلَائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ ۚ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا
አላህና መላእክቱ በነቢዩ ላይ የአክብሮት እዝነትን ያወርዳሉ፡፡ እናንተ ያመናችሁ ሆይ! በእርሱ ላይ የአክብሮት እዝነትን አውርዱ፡፡ የማክበርንም ሰላምታ ሰላም በሉ፡፡
📒አል-ኣሕዛብ (56)
*
✔️ሶለዋት የምናወርደው እንዴት ነው⁉️
———
ከዕብ ቢን ዑጅረህ (ረድየል'ሏሁ ዓንሁ) እንዲህ ይላል፦
إنَّ النبيَّ صَلَّى اللهُ عليه وسلَّمَ خَرَجَ عَلَيْنَا،
فَقُلْنَا: يا رَسولَ اللَّهِ، قدْ عَلِمْنَا كيفَ نُسَلِّمُ عَلَيْكَ،
ነብዩ (ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) ወደኛ መጡ። የአላህ መልክተኛ ሆይ! በአንተ ላይ ሰላምታ እንዴት ማድረግ እንዳለብን አወቕን።
فَكيفَ نُصَلِّي عَلَيْكَ؟
“ሶለዋት የምናወርደው'ስ እንዴት ነው?” ብለን ጠየቕናቸው።
قالَ: فَقُولوا
እንዲህ በማለትም አስተማሩን፦
«اللَّهُمَّ صَلِّ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آلِ مُحَمَّدٍ كَمَا صَلَّيْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد،
اللَّهُمَّ بَارِكْ عَلَى مُحَمَّدٍ وَعَلَى آل مُحَمَّدٍ كَمَا بَارَكْتَ عَلَى إِبْرَاهِيمَ وَعَلَى آلِ إِبْرَاهِيمَ إِنَّكَ حَمِيدٌ مَجِيد.»
ምንጭ፦📒ሶሒሁል ቡኻሪ (6357)
“አሏሁመ ሶሊ ወሰሊም ወባሪክ ዓላ ነቢይና ሙሐመድ”
||
የቴሌግራም ቻናል፦
https://www.tgoop.com/adinunnesiha
BY አዲኑን ነሲሀ ESLAMIC KNOWLEDGE FOR ALL MUSLIM🎙

Share with your friend now:
tgoop.com/adinunnesiha/10537