tgoop.com/agorethio/185
Create:
Last Update:
Last Update:
3. አጎር ተፈጥሮአዊ የጸጉር ማለስለሻ/ ኮንዲሽነር (500ml)
አጎር ተፈጥሮአዊ የጸጉር ማለስለሻ/ ኮንዲሽነር ቀለል ያለ የአጥላስ (ቬልቬት) ቀለም ያለው እጅግ ምቹና ተመራጭ ምርት ነው፡፡ ጸጉርን በማለስለስና ለአያያዝ ምቹ በማድረግ እጅግ ተመራጭ የሆነው ይህ ምርታችን ጸጉርን ከማለስለስና የተጣበቀ ጸጉርን ከማፍታታት አልፎ ለጸጉር መፋፋት ወሳኝ የሆኑትን ተፈጥሮአዊ የሺያ ቅቤ፣ የሱፍ ዘይት፣ የወይራ ዘይት እና ሌሎች የተፈጥሮ ንጥረ ነገሮችን ይዟል፡፡ በተጨማሪም አጎር የጸጉር ኮንዲሽነር ደረቅ ቆዳን በማከም ረገድ ለሁሉም የጸጉር አይነቶች ተስማሚ ነው፡፡
• የራስ ቅል ቆዳ መቅላትና ማሳከክን ይቀንሳል
• ጸጉርን ለስላሳ፣ አብረቅራቂ እና ለአያያዝ ይበልጥ አመቺ ያደርጋል
• የጸጉር መሳሳትን በመከላከል የጸጉር ውፍረትን ይጠብቃል
• የጸጉር እድገትን ያግዛል
• ደረቅ የራስ ቅል ቆዳን ያክማል
ግብዓቶች:
የሺያ ነት ቅቤ፣ ጆጆባ ዘይት፣ ሱፍ፣ ውሃ፣ የወይራ ዘይት፣ የሾላ ፍሬ፣ ጅንጅብል፣ የአቮካዶ ዘይት፣ የጉሎ ፍሬ ዘይት፣ ሬት፣ የመዓዛና ሽታ ዘይት ቅመሞች እንዲሁም የስኳር ድንች ቢቴይን
BY Trésbien Cosmetic (Agor) 🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/agorethio/185