tgoop.com/agorethio/194
Last Update:
5. አጎር ባለ ወይን ጠጅ አበባ መዓዛ /ላቬንደር/ የእግር ማለስለሻ ማስክ (7 ጥንድ)
መግለጫ: በተቀነባበሩ የወተት ምርቶችና በተፈጥሮአዊ የተክል ውጤት የበለጸገው አጎር ላቬንደር የእግር ማለስለሻ ማስክ ከወተት በተወሰደ ግብዓት፣ ከወይን ጠጅ አበባ በተወሰደ ግብዓት፣ ከተፈጥሮ ተክል ቅመም እና ከቫይታሚን ኢ የተመረተ ሲሆን የማይፈለግ/ሙት ቆዳን ለማስወገድ፣ በእግር ላይ ሸካራን እና ስንጥቅን ለማለስለስና ለማከም የሚውል ነው፡፡ ምርቱ እግርን ልስልስ እና ያማረ ያደርጋል፤ በአጠቃቀም ላይም ለስለስ ያለና የማይለበልብ ሲሆን የእግርን ቆዳ ተገቢ የሆነ ርጥበትና ልስላሴ ያጎናጽፋል፡፡
ግብዓቶች፡ ውሃ፣ ግሊሲሪን፣ ኢታኖል፣ ማንዴሊክ አሲድ፣ 2-ሀይድሮዛይፕሮፓኖይክ አሲድ (ላክቲክ አሲድ)፣ ከወተት የተወሰደ ግብዓት፣ ሜላሉካ አልተርኒፎሊያ፣ ሀይድሮላይዚንክ ኮላገን፣ ሀይድሮጂኔት የተደረገ የጉሎ ዘይት፣ የሺአ ቅቤ፣ የሬት ጭማቂ፣ ጆጆባ ዘይት፣ ዛንታም ሙጫ፣ የወይን ጠጅ አበባ ግብዓት፣ የአሮማቴራፒ መሰረታዊ ዘይቶች
አጠቃቀም:
1. የእግር ማለስለሻ ማስኩን ከእሽግ ውስጥ በማውጣት በመቀስ መቁረጥ
2. እግርን ማጽዳትና ማድረቅ፣ የእግር መሸፈኛውን ማድረግ፣ ውጫዊውን የመሸፈኛውን ክፍል በቀስታ ጫን ማድረግና በማጣበቂያው አማካይነት መድፈን
3. እጆቻችንን በመጠቀም እግርን ከ2-3 ጊዜ ማሸት/ ማሳጅ ማድረግ
4. ከ45 ደቂቃ ቆይታ በኋላ ማጣበቂያውን ማላቀቅና በውሃ መታጠብ
5. ጥሩ ውጤት ወይም ለውጥ ለማግኘት ለ7 ሳምንታት ያህል በሳምንት አንድ ጊዜ መጠቀም፤ በድጋሚ ለ7 ሳምንታት ለመጠቀም ካሰቡ ደግሞ በመካከል ቢያንስ አንድ ወር መቆየት ያስፈልጋል
አቀማመጥ፡ ምርቱን ከቀጥታ የጸሐይ ብርሐን መጠበቅ እንዲሁም በጣም ከፍተኛ ወይም በጣም ዝቅተኛ በሆነ ሙቀት ከማስቀመጥ መቆጠብ ያስፈልጋል
ማስጠንቀቂያ:
1. በእግር ላይ ያልዳነ ቁስል ካለ ምርቱን ከመጠቀም ይቆጠቡ
2. በእግር ላይ በመጠኑ የመጠዝጠዝ ወይም የሙቀት ስሜት ቢኖር አያሳስብዎ፤ ነገር ግን በጣም ለመቋቋም የሚከብድ ማቃጠል ካጋጠመ ወዲያውኑ ማስኩን በማስወገድ እግርን መታጠብና ደግሞ ያለመጠቀም ይመከራል
3. ከአይን ጋር ንክኪ እንዳይኖር ይጠንቀቁ፤ ንክኪ ከተፈጠረም ወዲያውኑ በውሃ መታጠብ ያስፈልጋል
4. ህጻናት በማይደርሱበት ቦታ ይቀመጥ
5. የእግር ቆዳ መላጥ/ መነሳት ሲጀምር ቆዳውን በእጅ ከመላጥ ይቆጠቡ፤ የተሻለ ውጤት ለማግኘትና መነሳት የጀመረውን ቆዳ ለማስወገድ አጎር ሺአ የሰውነት፣ የእጅ እና የእግር ስክራብን ይጠቀሙ፡፡
ብዛት: 7 ጥንድ
BY Trésbien Cosmetic (Agor) 🇪🇹
Share with your friend now:
tgoop.com/agorethio/194