tgoop.com/alemameninerdawe/11932
Last Update:
*የሐዲስ ኪዳን የመጀመሪያዋ ቃል "የዳዊት ልጅ . . . " የምትል ናት:: (ማቴ. 1:1) ጌታችን "ወልደ ዳዊት" መባልን ወዷልና:: እንዲያውም ራሱ "እኔ የእሴይ ሥርና የዳዊት ዘር ነኝ" ሲል ተናግሯል:: (ራዕ. 22:16)
+"+🌷 ዕረፍት 🌷+"+
=>ነቢየ ጽድቅ: ልበ አምላክ ቅዱስ ዳዊት እሥራኤልን ለ40 ዓመታት መርቶ አረጀ:: 'ምነው ያ ኃያል የእግዚአብሔር ሰው ቶሎ አረጀ?' ቢሉ ከገድሉ ጽናት ሰውነቱ ተቀጥቅጦ ነበርና::
*በዚያውም ላይ አንድ ቀን ስለ ሕዝበ አሥራኤል ቤዛ ይሆናቸው ዘንድ በቀሳፊ መልአክ ፊት ቆሞ ነበርና (ዜና. 21:16) ሰውነቱ ደከመ:: በዚህ ጊዜም ልጁን ሰሎሞንን አንግሦ በ70 ዓመቱ ከክርስቶስ ልደት ሺህ ዓመት በፊት በዚህች ቀን ዐርፏል::
+"+ 🌷ዳዊት በሰማይ🌷 +"+
=>በራዕየ ጐርጐርዮስ እንደ ተጻፈው ቅዱስ ዳዊትን በሰማይ 99ኙ ነገደ መላእክት ከበውት ያመሰግናል:: ከርሱ ዝማሬ ግርማ የተነሳ የሰማያት ግዘፋቸው ይናወጻል:: በገድለ አቡነ ኪሮስ እንደ ተጻፈው ደግሞ ቅዱሳን ነፍሳቸው ከሥጋቸው የምትለየው በዳዊት በገና ጣዕመ ዝማሬ ነው::
*በነገረ ማርያም ትምሕርት ደግሞ የቅዱስ ዳዊት ቤቱ ከልዑል አምላክ መንበር ሥር ነው::
*እንግዲህ ምን እላለሁ! ስለ ቅዱስ ዳዊት ከዚህም በላይ መጻሕፍት ብዙ ይላሉ:: ክብሩ ታላቅ ነውና::
<< በእውነት . . . በእውነት . . . በእውነት . . . ያለ ሐሰት ለዳዊት ክብርና ምስጋና ይገባል >>
=>አምላከ ዳዊት ስለ ከበረው ቃል ኪዳኑ ይማረን:: ከንጹሕ አምልኮው ይክፈለን:: በዝቶ ከተረፈ በረከቱም አይለየን::
✞✞✞ ታሕሳስ 23 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት=
1.ቅዱስ ዳዊት ልበ አምላክ
2.አባ ጢሞቴዎስ ገዳማዊ
3.አባ ሳሙኤል ጻድቅ
4.አባ ስምዖን ጻድቅ
5.አባ ገብርኤል ጻድቅ
6.አባ ይስሐቅ ጻድቅ
=>ወርኀዊ በዓላት
1.ቅዱስ ጊዮርጊስ ሊቀ ሰማዕታት
2.ነቢየ ጽድቅ ቅዱስ ሰሎሞን (ንጉሠ እሥራኤል)
3.ቅዱስ ዳንኤል ነቢይ
=>+"+ ከሕዝቤም የተመረጠውን ከፍ ከፍ አደረግሁ::
ባሪያየን ዳዊትን አገኘሁት::
ቅዱስ ዘይትም ቀባሁት::
እጄም ትረዳዋለች::
ክንዴም ታጸናዋለች::
ጠላት በእርሱ ላይ አይጠቀምም::
የዓመጻ ልጅም መከራ አይጨምርበትም::
ጠላቶቹን ከፊቱ አጠፋለሁ::
የሚጠሉትንም አዋርዳቸዋለሁ:: +"+ (መዝ. 88:20)
✞✞✞ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✞✞✞
https://www.tgoop.com/zikirekdusn
BY አለማመኔን እርዳው ጌታዬ #ማር 9፥24
Share with your friend now:
tgoop.com/alemameninerdawe/11932