Telegram Web
Amen Electrical Technology Official®
Photo
#Done❗️
👉ከላይ ስማችሁ የተዘረዘራችሁ የተቋማችን ሰልጣኞች ቀድማችሁ ስማችሁን የላካችሁ ስትሆኑ ምናላባት በዚህ ዙር ያልተካተታችሁ ካላችሁ በቀጣይ ወደ ሌላ ድርጅት  የምንልካችሁ ይሆናል። ቁጥራችሁን ወደ 5 ዝቅ ያደረግነው ድርጅቱ የሰው ሀይል ቁጥር ላውጥ ስላደረገ ነው !
የተላካችሁ ስልካችሁን ክፍት አድርጋችሁ ጠብቁ ለድርጅቱ ልከናል❗️
መልካም የሥራ ዘመን❗️
አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ
👍83
Amen Electrical Technology Official®
Photo
#ማስታወቂያ
===
👉
#ሰኞ#ረቡዕና_አርብ ከጥዋቱ 3:00-6:00 የሚሰጠውን እጅግ ልዩ የሆነውን #በክፍል#በወርክሾፕና_በሳይት ላይ ልምምድ የሚሰጠውን 26ኛው ዙር #የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርግታ ስልጠና
ለመሰልጠን የተመዘገባችሁና
#የመሰልጠን_ፍላጎት ያላችሁ #ሰኞ መስከረም 13/2017 ዓ.ም   3:00 ላይ ቦሌ ሚካኤል በሚገኘው ማሰልጠኛችን በመገኘት ስልጠናችሁን እንድጀምሩ እናሳስባለን❗️
👉የዚህ ስልጠና ክፍያ ከመደበኛው በ25% ቅናሽ ያደረግንበት የአዲስ አመት ቅናሽ ሲሆን  ሙሉ ክፍያው የ 2 ወር  #5400 ብር ብቻ❗️

👉
#የቅዳሜና_እሁድ ስልጠና የሚጀምርበት ቀን የምሳውቅ ይሆናል❗️
አድራሻችን፦
👇
https://rb.gy/8pwr92
(
#ቦሌ_ሚካኤል)

#ለተጨማሪ_መረጃ
0118644716
0991156969

ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ  ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️

      በአጭር ጊዜ ስልጠና  ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️

አሜን  ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
👍183
#የኤሌክትሪክ_መኪና_ከመግዛትዎ_በፊት_ማወቅ_ያለብዎ_ወሳኝ_ነጥቦች
======================
👉በሐገራችን ኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ተሺከርካሪዎች በስፋት እየገቡ እንደሆነ ይታወቃል። ነገር ግን እነዚህን ተሽከርካሮዎች ከመግዛታችን በፊት ከሌላው አለም በተለየ መልኩ ልናስብባቻው የሚገቡን ነጥቦች እንዳሉ በተለያዩ ቤቶች ለሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ቻርጅ ለመዘርጋት ስንሄድ    አስተውለናል   እንደሚከተለው እናያቸዋለን❗️
1. የቤታችን ኤሌክትሪክ ቆጣሪ መኪና ቻርጅ የማድረግ አቅም አለው ወይ
👉እንደሚታወቀው በሀገራችን ኢትዮጵያ የሀይል እጥረት እንዳለ ይታወቃል። በዚህም የተነሳ ለመኖሪያ ቤት  የሚፈቀደው ነጠላ ፌዝ 25A ነው። በዚህም የተነሳ ብዙ ቤቶች ምጣድ ለኩሶ ተጨማሪ ስቶቭ፣ ውሃ ማሞቂያና የመሳሰሉትን በተመሳሳይ ሰዐት ከተጠቀሙ የቆጣሪው ብሬከር እየመለሰ እንደሚያስቸግር የታወቀ ነው። በዚህ ላይ የመኪና ቻርጀር ከተጨመረበት ቆጣሪው እየመለሰ መጠቀም አይቻልም። ለመኪና ቻርጀር ከ 20A ብሬከር እና ከዛ በላይ የምንጠቀም ሲሆን ቻርጅ ማረግ ከፈለግን ራሱን ችሎ አንድ ቆጠሪ ስለሚፈልግ ከላይ ያሉትን እቃዎች እጥፍተን ቻርጅ ማረግ እንዳለብን መረዳት ይኖርብናል።
👉ስለዚህ 25A ቆጣሪ ያለው መኖሪያ ቤት ላይ ከ20A በላይ የሆኑትን #ፋስት_ቻርጀሮች መጠቀም እንደማንችልና በመደበኛው ቻርጀር ብቻ እንደሚጠቀሙ መረዳት ይኖርብዎታል።
2. የቤታችን ኤሌክትሪክ Ground/Protective Earth ተሰርቶለታል ወይ
👉Ground/Protective Earth የሰውን ህይዎት ወይም ንብረቶቻችን ከኤሌክትሪክ አደጋ የሚከላከል ወሳኝ የደህንነት ጉዳይ ቢሆንም ከባለሙያ የግንዛቤ ችግር ወይም ችልተኝነት የተነሳ ብዙ ትላልቅ ህንፃዎች ሳይቀሩ ያለ  Ground/Protective Earth ተሰርተው ይገኛሉ። በውጪው አለም እነዚህንና መሰል የኤሌክትሪክ ደህንነት(Electrical Safety) ሳያካትቱ የተገነቡ ቤቶች አገልግሎት እንዳይጀምሩ፣ በለቤቱም እነዚህንና መሰል ጉዳዮችን ሳያሰራ መሸጥም ሆነ ማከራየት አይችልም።
👉የኛ አገር ግን ቁጥጥር ስለማይደረግ ስራውን በሚሰራው ባለሙያ ስለሚወሰን እንዲሁም ባለሙያ ሲመረጥም ቸልተኝነቱ ስላለ እጅግ በጣም ብዙ ቤቶች Ground/Protective Earth የላቸውም።
👉አብዛኞቹ ቻርጀሮች ደግሞ ለመኪናው ደህንነት ሲባል  Ground/Protective Earth ካላገኙ እንዳይሰሩ ተደርገው የተመረቱ ናቸው።
3. የኤሌክትሪክ መኪና ብግዛ የት ነው ቻርጅ የማደርገው
👉 በሀገራችን ኢትዮጵያ እንደሌሎች  ሀገሮች የኤሌክትሪክ ስቴሽኖች ገና አልተቋቋሙም። ስለዚህ ተከራይተው ለሚኖሩና የጋራ መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ለሚኖሩ ሰዎች መኪናቸውን ቻርጅ ለማድረግ የሚያስችል ምቺ ሁኔታ እንደሌለ መረዳት አስፈላጊ ነው።
4. ዝርጋታውን የሚሰራ ብቁ ባለሙያ እንዴት አገኛለሁ
👉የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀር መስመር መዝርጋቱ ቀላልና ማንኛውም ባለሙያ የሚዘረጋው ቢሆንም የብሬክር
መጠን፣ የገመድ መጠን፣የሶኬት ወዘተ በትክክል መምረጥ የሚችልና ከመኪናዎች ጋር ትውውቅ ያለው በቁ ባለሙያ ያስፈልጋል። ይህ ካልሆነ በሚሊዮን የተገዛ መኪና ላይ ጉዳት ሊደርስ ይችላል።

#የመኪና_ቻርጀርና ሌሎች #የኤሌክትሪክ ስራዎችን #በጥራትና_በተመጣጣኝ ዋጋ ማስራት ከፈለጉ ይደውሉ❗️

👇👇👇👇👇
 
0118644716
 
0991156969
         
"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን❗️"
🔹🔸🔹
#ለወዳጅዎም_ያጋሩ❗️🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹
#እናመሰግናለን❗️🔹🔸🔹
👍215👏1
📝#ስለ_አሜን_ቴክኖሎጂ_ኢንስቲትዩት አጭር ማብራሪያ
====
👉አሜን ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የተለያዩ ስራዎችን የሚሰራ ፣ አጫጭር የተግባር ስልጠናዎችን የሚያሰለጥንና የማማከር አገልግሎት የሚሰጥ እጅግ በብዙዎች ተወዳጅነትን እያገኘ ያለ ድርጅት ሲሆን የሚሰራቸው ስራዎችና የስልጠና አይነቶችም እንደሚከተለው ቀርበዋል፦
#የስልጠና_አይነቶች
1⃣. Advanced Building Electrical installation training
2⃣. Home and Office Equipment Maintenance (fridge, Washing Machine, Oven, Stove , Printer, Photocopy Machine  etc )
3⃣. Generator Installation ,Maintenance & Motor Control Systems
4⃣.Single and Three-Phase Motor Rewinding
5⃣. Digital Marketing
6⃣. Graphic Design
7⃣. BIM & AutoCAD Software Trainings
8⃣. Safety Management and Standards Training
9⃣. Job Readiness Course
. #የምንሰጣቸው_አገልግሎቶች/ስራዎች
1⃣. Building Electrical installation & Maintenance Work & consulting
2⃣. Security camera and fire alarm system installation and Maintenance work & Consulting
3⃣. Electric Car Charger Installation work & Consulting
➡️ከላይ የተዘረዘሩት አገልግሎቶች ከማሰልጠንና ከመስራት ባሻገር የረጅም ጊዜ ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች #ነፃ የማማከር አገልግሎት እንሰጣለን❗️
#ስልጠናው_የሚመለከታቸው
👉የተግባር/የሙያ ስልጠና ስለሆነ የተለየ የት/ት ደረጃ አይፈልግም ነገር ግን እንግልዥኛ ማንበብና መፃፍ ግዴታ ነው❗️
1️⃣. ለዩንቨርሲቲ ተማሪዎችና ተመራቂዎች
2️⃣. 12ኛ ክፍል ለጨረሱ
3️⃣. 10ኛ ክፍል ለጨረሱ
4️⃣. ከ10ኛ ክፍል በታች ሆነው እንግልዝኛ  ማንበብና መፃፍ ለሚችሉ
#የስልጠናው_ቀንና_ሰዓት
1⃣. #የጥዋት_ፈረቃ ከ3:00 -- 6:00
👉ከሰኞ-አርብ በሳምንት 3 ቀናት
👉ለ 2 ወራት
2⃣.
#የከሰዓት_ፈረቃ---ከ8:00--11:00
👉ከሰኞ-አርብ በሳምንት 3 ቀናት
👉ለ 2 ወራት
3⃣.
#የማታ_ፈረቃ ----ከ 12:00---1:30
👉በሳምንት 3ቀናት
👉ለ 3 ወራት
4⃣.
#የቅዳሜና_እሁድ
👉ቅዳሜ ከ8:00-11:00 እና  እሁድ ጥዋት ከ3:00-6:00
👉ለ 3 ወራት
5⃣. በግል ወይም በቡድን  ለሚመጡ ደግሞ  በተጨማሪ ክፍያ ደንበኞች 
#በሚመቻቸው_ቀንና_ሰዐት ስልጠናውን መውሰድ ይችላሉ❗️
#ማሰልጠኛችን_ከሌሎች_ማሰልጠኛ ተቋማት_በምን_ይለያል
1️⃣. እንደ ህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታና መሰል የስልጠና አይነቶች  በባህሪያቸው በወርክሾፕ ወይም በክፍል ስልጠና ብቻ በቁ ባለሙያ ማድረግ እንደማይቻል ስለምንረዳ  ስልጠናችን የሚሰጠው ከክፍል ባሻገር #በወርክሾፕና_በሳይት_ላይ_ልምምድ መሆኑ ልዩ ያደረገናል❗️
2️⃣. አስልጥነን ስራ የምናስቀጥር መሆኑ❗️
3️⃣. አሰልጣኞቻችን እጅግ በጣም በሙያው የላቁ መሆናቸውና ማሰልጠን ብቻ ሳይሆን ሳይት ላይ የሚሰሩና እውቅትን ከክህሎት ጋር ጥንቅቅ አድርገው የያዙ መሆናቸው❗️
4️⃣. ሰልጣኞቻችን ስልጠና ላይ እያሉም ሆነ ስልጠናቸውን አጠናቀው ወተው ስራ ላይ የሚያጋጥማቸውን ማንኛውንም ችግር ለመፍታት በነፃ የማማከር አገልግሎት መስጠታችን❗️
5️⃣. ከስልጠና ባሻገር  የተለያዩ ስራዎችን የሚሰራ ድርጅት በመሆኑ ሰልጣኞች የምር ምን እንደሚያስፈልጋቸው ጠንቅቀን ማወቃችንና የሳይት ላይ ልምምድ እንዲያደርጉ መልካም አጋጣሚ መፍጠሩ❗️
6️⃣. ከስልጠናው ባሻገር ሰልጣኞቻችን ስለግል ስብዕናቸውና ስለ ንግድ በቂ ግንዛቤ እንድኖራቸው ማድረጋችን❗️
7️⃣. ተቋሙ የተመሰረተው ከዚህ በፊት
#በቴሌግራምና_በፌስቡክ ገፃችን ሙያውን ለማሳደግና ሌሎችን ለመርዳት ካለን ፍላጎት የተነሳ በተጀመረ #ነፃ የመስመር ላይ ስልጠና  ከሚከታተሉን ቤተሰቦቻችን በተነሳ ጥያቄ አማካኝነት መሆኑ ሁሉንም የቻናላችን ተከታዮችና ሰልጣኞች እንደባለቤትና መስራች የምናይና ተቀብለን ብትህትናና በልዩ ሁኔታ የምናስተናግድ መሆኑ❗️
8️⃣. ከጅምሩ ጀምራችሁ ቻናላችን ላይ ስትከታተሉን  የነበራችሁና ከተቋማችን የሰለጠናችሁ ጨምሩበት...
#በተደጋጋሚ_የተጠየቁ_ጥያቄዎች
1⃣. ስልጠናውን ስንጨርስ ሰርተፍኬት አለው ወይ
#መልስ
👉ስልጠናውን ሲያጠናቅቁና COC ተመዝነው ብቁ ከሆኑ 2 የምስክር ወረቀቶችን ይወስዳሉ።
1. የስልጠና ምስክር ወረቀ ይሰጣል ከማሰልጠኛ ተቋማችን
2. የCOC ምዝና የምስክር ወረቀት  ከአዲስ አበባ ከተማ  COC ማዕከል 

2⃣. ስልጠናውን ለመሰልጠን መሰፈርቱ ምንድን ነው? የት/ት ደረጃ ይጠይቃል ወይ
#መልስ
👉ስልጠናው የሙያ/የተግባር ስልጠና እንደመሁኑ መጠን  ለመሰልጠን  የት/ት ደረጃ  አይጠይቅም ነገር ግን ስልጠናውን ለመሰልጠን እንግልዝኛ ማንበብና መፃፍ መቻል አለባቸው።
3⃣. ክፍለ ሀገር ቅርንጫፍ  አላችሁ ወይ
#መልስ:-
👉ክፍለ ሀገር ምንም አይነት ቅርንጫፍ የለንም። ነግር ግን የስልጠና ፍላጎት ያላችሁ  ኮመንት ላይ እንድንጀመር የምትፈልጉበትን አካባቢ ፃፉልን።
4⃣. አድራሻችሁ የት ነው
#መልስ:-
👉የወርክሾፕና የክፍል ስልጠናው ቦሌ ሚካኤል ከቅዱስ ሚካኤል ቤተክርስትያን ፊት ለፊት  የሚገኘው ህንፃ 2ኛ ፎቅ ሲሆን የሳይት ላይ ልምምዱን ድርጅታችን አሜን ኤሌክትሪካል ቴክኖሎጂ በተቋራጭነት በያዛቸው ሳይቶችና በአጋር ድርጅቶች  ለርስዎ የሚቀርብዎትን በመምረጥ መለማመድ ይችላሉ።
5⃣. የምሰጡት ስልጠና ደረጃ ስንት ነው
#መልስ:-
👉የምንሰጠው ስልጠና ከደረጃ 1 እስከ ደረጃ -4 ካሉት የብቃት አሃዶች አንድን ባለሙያ ብቁ ያደርጋሉ ተብለው የተመረጡትን የብቃት አሃዶች ሲሆን የአጭር ጊዜ የሙያ ስልጠና ነው።
6⃣. ስንጨርስ የስራ ቅጥር እድል አለው ወይ
#መልስ
👉አዎ በትክክል ሲጀመር የኛ ባለሙያዎች ገና ስልጠናቸውን እንኳን እስከሚያጠናቅቁ የማይቆዩበት ጊዜ አለ   3 ወይም 4 የስልጠና ቀናት ሲቀራቸው ቀድመው ተቀጥረው ከድርጅቶች ጋር በመነጋገር  ፈቃድ ተሰቷቸው ስልጠናቸውን ያጠናቀቁ ብዙዎች ናቸው።
እስካሁን በ21 ዙሮች በህንፃ ኤሌክትሪክ መስመር ዝርጋታ  ያሰለጠናቸውን ብቁ ባለሙያዎች ሁሉንም አስቀጥረናል። አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በብሮጀክት መጠናቀቅና በተለያዩ ምክንያቶች ከተቀጠሩበት ድርጅት ጋር ሲለያዩም ለ 2ኛ እና ለ3ኛ ጊዜ ያስቀጥርናቸው አሉ።
7⃣. በ online መሰልጠን ይቻላል ወይ
#መልስ
👉የለንም ነገር ግን ዩቱዩብ ላይና  ቲክቶክ ላይ የለጥፍናቸውን በስታንዳርድ ዙሪያና ሌሎች ቲወሪ ክፍሎችን ተከታትሎ ለተግባር ስልጠና  ወደ ማሰልጠኛችን ቢመጣ የስልጠና ጊዜውን ማሳጠር ይችላል። 
አመስግናለሁ🙏
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
#ለተጨማሪ_መረጃ
👇👇👇
0118644716
0991156969
👍397👏3
#ማስታወቂያ
===
1⃣. በመስቀል በዓል ምክንያት ይራዘምልን ብላችሁ በጠየቃችሁት መሰረት የተራዘመውና  
#ሰኞ#ረቡዕና_አርብ ከጥዋቱ 3:00-6:00 የሚሰጠው እጅግ ልዩ የሆነው #በክፍል#በወርክሾፕና_በሳይት ላይ ልምምድ የሚሰጠውን 26ኛው ዙር(ለ 2ወራት ቆይታ) #የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርግታ ስልጠና
ለመሰልጠን የተመዘገባችሁና
#የመሰልጠን_ፍላጎት ያላችሁ #ረቡዕ  መስከረም 22/2017 ዓ.ም   3:00 ላይ #ቦሌ_ሚካኤል በሚገኘው ማሰልጠኛችን በመገኘት ስልጠናችሁን እንድጀምሩ እናሳስባለን❗️
↪️ሙሉ ክፍያው( የ 2 ወር ) 7200 ብር ቢሆንም ለአዲስ አመት ባደረግነው የ25% ቅናሽና  ለ12ኛ ክፍሎች ባደረግነው የ50% ቅናሽ መሰረት 5400ብር እና 3600 ብር ብቻ ነው። 
2⃣. እንዲሁም
#ቅዳሜ ከ8-11 ሰዓትና #እሁድ ከጥዋቱ3-6 ሰዓት የሚሰጠው ስልጠና ቅዳሜ ጥቅምት 02/2017ዓ.ም የሚጀምር ይሆናል።
↪️ሙሉ ክፍያው(የ3 ወር) ደግሞ መደበኛው ክፍያ 7800ብር ቢሆንም አሁን ባለው ቅናሽ ለ12ኛ ክፍሎች 3900ብር ብቻ ሲሆን ከ12ኛ ክፍሎች ውጪ ለሆኑ ሰልጣኞች 5850 ብር ይሆናል❗️

#የቅናሹ_ጊዜ_የሚቆየው
እስከ
#መስከረም 30,2017 ዓ.ም  ይሆናል❗️
አድራሻችን፦
👇
https://rb.gy/8pwr92
(
#ቦሌ_ሚካኤል)

3⃣. እንዲሁም ሌሎች ስልጠናዎችንና ተጨማሪ መረጃዎችን የምትፈልጉ በእነዚህ ስልኮች ይደውሉ❗️
0118644716
0991156969

ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ  ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️

      በአጭር ጊዜ ስልጠና  ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️

አሜን  ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
👍202😢1🎉1
#የመብራት_አምፖሎች_ቶሎ_ቶሎ_እየተቃጠሉ_ተቸግረዋል
              ==🔹🔸🔹==
በየጥቂት ሳምንቶች ወይም ወራቶች አምፖሎች ለምን እንደሚቃጠሉ እና ምን  ማድረግ እንዳለብዎት ተቸግርዋል?
🔹 በአጠቃቀምዎ መሰረት አምፖሎች ከ4-6 ወር ያለምንም ችግር ይሠራሉ ፡፡ ነገር ግን አገልግሎት መስጠት ያለባቸዉን ያህል ሳይቆዩ ሊቃጠሉ ይቸላሉ ፡፡
🔹አምፖሎች በፍጥነት  የሚቀጥሉባቸው  ምክንያቶች ብዙ ሲሆኑ እንደሚከተለዉ እናያለን ፡፡
1. #ከፍተኛ_ቮልቴጅ
👉ኢትዮጵያ ውስጥ 220 ቮልት የኤሌክትሪክ ሀይል መደበኛ ነዉ ፡፡ ነገር ግን አንድ አምፖል ከመደበኛዉ በላይ የሆነ ከፍተኛ ሀይል ካገኘ ይሞቃል፤ ቶሎ ቶሎም ይቃጠላል  ፡፡
#መፍትሔው፡-
👉ፈቃድ ያለው የኤሌክትሪክ ባለሙያ የቤትዎን የኤሌክትሪክ አቅርቦት በመመርመር የችግሩ ምንጭ ምን እንደሆነ ከታወቀ መፍትሔ ማምጣት ይችላል ፡፡
👉ከፍ ያለ ቮልት የሚያነብ ከሆነ ታዲያ መጪውን ቮልት እንዲመረምር እና በዚህ መሠረት እንዲያስተካክለው ለኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ያመልክቱ ይህ ካልሆነ ውድ የኤሌክትሪክ መገልገያዎቾን ሊያጡ ይችላሉ ፡፡
2.#ጥራታቸዉን_ያልጠበቁ_አምፖሎች
👉አምፖሎችን በፍጥነት ለማቃጠል በጣም ከተለመዱ ምክንያቶች አንዱ ርካሽ ወይም ዝቅተኛ አምፖሎችን መጠቀም ነው ።
👉አምፖሎች በፍጥነት እየተቃጠሉ ከተቸገሩ  ጥራት ያላቸዉን ለመቀየር ይሞክሩ እና ችግሩ አሁንም እንደቀጠለ ይመልከቱ ፡፡
#መፍትሄው ፡-
👉ጥሩ ጥራት ባላቸው አምፖሎች ላይ ትንሽ ተጨማሪ ኢንቬስት ለማድረግ ይሞክሩ ይህም አምፖሎችን ለመተካትና ለኤሌክትሪክ ሙያተኛ የሚያወጧቸዉን ወጭዎች ያስቀራል፡፡
3.#ከመጠን_በላይ_መሞቅ
👉የአምፖሉ ዋት ከማቀፊያዉ ወይም ከሚመከረው ከፍ ያለ ከሆነ ከመጠን በላይ ሙቀት ሊፈጥር ይችላል ፡፡
👉ይህ የአምፖሉን ቆይታ የሚቀንስ እና ያለጊዜው እንዲቃጠል የሚያደርግ ነዉ ፡፡
#መፍትሄው፡-
👉አዲስ አምፖሎችን በሚገጥሙበት ጊዜ ሁል ጊዜም ከማቀፊያዉ ዋቶች ያነሱ ዋቶች መሆናቸዉን ያረጋግጡ ፡፡
4.#ከመጠን_በላይ_የሆነ_ንዝረት
👉ከጣሪያ አየር ማቀዝቀዣዎች እና ከመግቢያ በሮች አቅራቢያ ያሉ ኢንካንዲሰንት አምፖሎች በንዝረቶች(vibration) ምክንያት  ክር መሳዩ የአምፖሎችን ከፍል እንዲበጠስ በማድረግ በፍጥነት እንዲቃጠሉ ያደርጋሉ ፡፡
👉ለጥምዝ( CFL) አምፖሎችም  እንዲሁ የተለመደ ጉዳይ ነው ፡፡
#መፍትሔው፡-
👉ፌከሰቸሩ ደህንነቱ የተጠበቀ መሆኑን በማረጋገጥ ንዝረትን ይቀንሱ እንዲሁም  የLED አምፖሎች ይጠቀሙ።
5.#ቶሎ_ቶሎ_ማብራትና_ማጥፋት
👉ይህ ለጥምዝ(CFL) አምፖሎች ትልቅ ምክንያት ሊሆን ይችላል ፣ ምክንያቱም ኤሌክትሮዶች መብራቱ በሚበራበት ጊዜ ሁሉ ውጥረት ስለሚሰማቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ዝቅ እንዲሉ ያደርጋቸዋል ፡፡
👉ስለዚህ ለ10,000 ሰዓታት አገልግሎት የሚሰጠው የ ጥምዝ(CFL)  አምፖል በአንድ ጊዜ ለጥቂት ደቂቃዎች ብቻ ከበራ ለ 3,000 ሰዓታት ብቻ ሊቆይ ይችላል ፡፡
#መፍትሄው :-
👉እንደ መጸዳጃ ቤት ፣ እንቅስቃሴን የሚቆጣጠሩ ሴንሰሮች እና ቁምሳጥን በመሳሰሉ ለአጭር ጊዜ ብቻ በሚበሩ መብራቶች ውስጥ ጥምዝ(CFL) አምፖሎች በ LED አምፖሎች ይተኩ ፡፡
6.#የማይጣጣም_የዲመር_ማብሪያ_ማጥፊያ
👉የቆዩ የዲመር መቀየሪያዎች ከኢንካድሰንት አምፖሎች ጋር እንዲጠቀሙ ተደርገዋል ፡፡
👉እነዚህ  መቀየሪያዎች  ለCFL ወይም ለLED አምፖሎች መጠቀም አምፖሉን ወይም ሰርኪዩቱን ሊጎዳ ይችላል ፡፡
👉በተጨማሪም ፣ ሁሉም አዲስ አምፖሎች ከዲመር ማዞሪያዎች ጋር የሚጣጣሙ አይደሉም ፡፡
👉የእርስዎ ደብዛዛ ማብሪያ/ማጥፊያ እና አምፖል እርስ በርሳቸው የሚስማሙ መሆናቸውን ያረጋግጡ።
#መፍትሔው:-
👉ከLED አምፖሎች ጋር ለመስራት የተነደፉ የደብዛዛ ማብሪያዎችን መግዛት ይኖርብዎታል ፡፡
👉የድሮ ደብዛዛ ማብሪያ / ማጥፊያውን ከ LED አምፖሎች ጋር በሚስማማው ብቻ ይተኩ እና ችግሩ ይፈታል!
7.#በአግባቡ_ያልታሰረ_የኤሌክትሪክ_ሽቦ
👉የባለሙያን ልዕቀት ሊጠይቅ የሚችል አንድ ችግር ይህ ነው ፡፡
👉ማቀፊያዉ መገናኛው ሳጥን ውስጥ ከሽቦዉ ጋር በትክክል ካልታሰረ ወደ አምፖሉ የሚሄደውን ቮልቴጅ በፍጥነት እንዲለዋወጥ ሊያደርግ ይችላል ፡፡
#መፍትሄው:-
👉 በመገናኛው ሳጥኑ ውስጥ ያሉትን ሽቦዎች ከማቀፊያዉ ተርሚናል ጋር በጥብቅ መገናኘት አለባቸው ፡፡
8.#የተሳሳቱ_ዓይነት_አምፖሎች
👉ከማቀፊያዉ ጋር ንክኪ በሚያደርግበት አምፖል የታችኛው ክፍል ላይ አንድ አነስተኛ ብይድ ነጥብ አለ ::
👉ይህ ነጥብ ሁልጊዜ ተመሳሳይ መጠን ያለው መሆን አለበት ፣ነገር ግን አንዳንድ ርካሽ ብራንዶች በቂ ብየዳ የላቸውም ፣ ይህም የአምፖሉን ሕይወት ያሳጥረዋል።
#መፍትሄው፡-
👉አምፖሉን በተለየ ማቀፊያ ውስጥ ይሞክሩ እና ተመሳሳይ ችግር ካለ ትክክለኛዉን ምርት ይቀይሩ ፡፡

#ለሌሎችም_ያጋሩ❗️

#ማንኛውንም_የኤሌክትሪክ_ስራ_ለማሰራት_ወይም_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_የሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል
👇👇👇👇👇
0118644716
0991156969
👏15👍136
2025/07/14 05:22:06
Back to Top
HTML Embed Code: