Telegram Web
Amen Electrical Technology Official®
Photo
#ማስታወቂያ
===
ነገ ሰኞ በ 02/03/2017 ሊጀምር የነበረውና  በሳምንት 5 ቀን ከሰኞ-አርብ ከቀኑ 8:00-11:00 የሚሰጠው 30ኛ ዙር #አድቫንስድ_የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርጋታና_ጥገና ስልጠና  ወደ #አርብ 06/03/2017 የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ቀን ከቀኑ 8:00 ላይ ቦሌ ሚካኤል በሚገኘው ማሰልጠኛችን በመገኘት ስልጠናችሁን እንድትከታተሉ እናሳስባለን።
👉በዚህ #ዙር_የመሰልጠን ፍላጎት ያላችሁ ውስን ቦታዎች ስላሉን ቀድማችሁ  በመመዝገብ  እጅግ ልዩ የሆነውን #በክፍል#በወርክሾፕና_በሳይት ልምምድ የሚሰጠውን ስልጠና መከታተል እንደምትችሉ እናሳስባለን።
  
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ  ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️
#አድራሻ
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)

#ለተጨማሪ_መረጃ
👇
0118644716
0991156969
👍163
☑️#የፍሪጅ_ጋዝ_እንዴት_እንሞላለን?
☑️#How_to_refilling_refrigerat_gas
=======
👉ሰላም ጤና ይስጥልኝ ውድ #የአሜን_ኤሌክትሪካል_ቴክኖሎጂ ቤተሰቦች ለናንተ ይጠቅማል ብየ ያሰብኩትን ይዠላችሁ መጥቻለሁ እናንተም ልክ እኔ ጊዜ ሰጥቸ እንደምፅፍላችሁ ሁሉ እናንተም ለሌሎች ለማድረስ ጊዜ ሰታችሁ #ሼር ስለምታደርጉት ከልብ አመሰግናለሁ።
👉ዛሬ የምናየው የፍሪጅ ጋዝ አሞላል ቅደም ተከተሎችን ሲሆን ከዚህ በፊት ግን ይበልጥ ግልፅ ለማድረግ የተወሰኑ ጥያቄዎችን በመጠየቅ እጀምራለሁ፦
1. ፍሪጅ መቸ/ለምንድን ነው ጋዝ የሚሞላው?
2. ፍሪጅ ምን አይነት ጋዝ ነው የሚሞላው?
3. የተሞላ የፍሪጅ ጋዝ ያገልግሎት ማብቂያ(expired date) ምን ያህል ነው?
4. የፍሪጅ ጋዝ ለመሙላት የሚያስፈልጉ ምሳሪያዎች ምን ምን ናቸው።
👉አሁን የፍሪጅ ጋዝ አሞላል ቅደም ተከተል ከማየታችን በፊት እነዚን ጥያቄዎች በመመለስ እንጀምር።
#መልሶች
👉 1. ፍሪጅ ጋዝ የሚሞላው የፍሪጁ ጋዝ ማስተላላፊያ ቱቦ ላይ ጋዝ የሚወጣ ከሆን(leakage) ወይም ቱቦው ተዘግቶ የፍሪጅ ጋዝ እንደፈለገ የማያልፍ ከሆነ(blockage) ጥገና ስለሚፈልግ ከጠገንን በኋላ ደሞ ጋዙ ስለወጣ መሞላት ይኖርበታል።
👉 2. በዙ አይነት ጋዝ ቢኖርም ለፍሪጅ የተለመዱት 2 አይነት ጋዞች ሲሆኑ እነርሱ፦
R-134a (Tetrafluoroethane)
R-600a(Iso Butane) ናቸው። ነገር ግን እነዚን ጋዞች ስንሞላ የፍሪጁ ኮምፕረሰር ወይም ሌላ ክፍል ላይ አምራች ድርጅቱ የለጠፈውን የጋዝ አይነት አይተን መሆን ይኖርበታል።
👉 3. የፍሪጅ ጋዝ ከላይ በተገለፀው መልኩ ካልወጣ ያገልግሎት ዘመኑ አያልፍም። ስለዚህ ፍሪጅ ጥገና ካልተደረገለት በስተቀር ጋዝ መሙላት አስፈላጊ አይደለም ማለት ነው።
👉4. የፍሪጅ ጋዝ ለመሙላት የሚያስፈልጉ መሳሪያዎች/ዕቃዎች የሚከተሉት ናቸው።
ሁሉም ለብየዳ የሚያስፈልጉ መሰሪያዎች የሚያፈስ ወይም የተዘጋ ቱቦ ካለ ቆርጠን ስለምን በይድ ለብየዳ የሚያስፈልጉ መሳሪያውች እንደ የኮፐር መረጫ፣ ኦክስጅን ሲሊንደር፣ ቡቴን ጋዝ ሲሊንደር ፣ መበየጃ ፣ ሆዝ፣ ፓውደር፣ ሲልቨር ወዘተ ያስፈልጉናል።
የፍሪጅ ጋዝ(Refrigerant gas) ፍሪጁ እንዲሰራ የሚሞላ ጋዝ ሲሆን እንደ ፍሪጁ አይነት R-134a ወይም R-600a ሊሆን ይችላል።
ማንፎልድ ጌጅ የፍሪጃችን ጋዝ ለመሙላትና የግፊት መጠኑን ለማወቅ የምንጠቀምበት መሳሪያ ነው።
ፊልትሮየኮንደንሰር ወደ ኢቫፖሬተር ጋዝ በሚዛዋወር ጊዜ ለማጣራት ይጠቅመናል።
ጋዝ መሙያ ቫልቭ(charging valve) ጋዝ ለመሙላትና የፍሪጁን የጋዝ መጠን ለማወቅ የማንፎልድ ጌጃችን ሰማያዊ ቀለም ያለውን ሆዝ ከኮምፕረሰር የጋዝ መሙያ ጫፍ (charging) ጋር ለማገናኘት ይጠቅመናል።
ናይትሮጅን ጋዝፍሪጃችን ለማፅዳት ይጠቅመናል።
ቫኪዩም ፓንፕ ማሽንጋዝ ከመሙላታችን በፊት ለማፅዳት የምንጠቀምበት ነው ከሌለ ግን በራሱ በፍሪጁ ሲስተም ማፅዳት ስለሚቻል ግዴታ አይደለም።
የተበላሸውን ክፍል(ኮንደንሰር ቱዩብ ፣ ኢቫፖሬተር ቱዩብ፣ ፊልትሮ ወዘተ ) የሚተካ ዕቃ
👉አሁን የሚያስፈልጉንን መሳሪያዎችና ዕቃዎች ካወቅን ወደ ጋዝ መሙላት ቅደም ተከተል እንሄዳለን።
1. በመጀመሪያ ከላይ የዘረዘርናቸውን መሳሪያዎች/ዕቃዎች ካዘጋጀን ባኋላ ፍሪጁ ጋዝ የሚያፈስበትን ወይም የተዘጋበትን ቦታ በጥንቃቄ ከፈለግን በኋላ ቆርጠን አውተን አስፈለጊውን የፓይፕ መጠንና እርዝመት እንበይዳለን።
2. ጋዝ መሙያ ቫልቩን (charging valve) ከኮምፕረሰሩ የጋዝ መሙያ ጫፍ ጋር መበየድ።
3. የበየድናቸውን ቦታዎች ጋዝ እንደማያፈስ ማረጋገጥ።
4. ፍሪጁ ጋዝ በሚያፈስበት ጊዜ እና ስንበየድ አላስፈላጊ ጋዝ ስለሚገባ የፍሪጁን የውስጥ ክፍል በራስ አገዝ(self Vacum) ወይም ቫኪዩም ፓንፕ ማሽን(Vacum pump machine) ተጠቅመው ማፅዳት።
ሀ. #በራስ_አገዝ(self Vacum) የማፅዳት ዘዴ
ከካፕላሪ ቱዩብ ትንሽ ክፍል ቆርጠን ከወሰድን በኋላ ፊልትሮውን በኮንደንሰር በኩል እንበሳለን።
ከዛ ከካፕላሪ ቱዩብ የቆረጥነውን አንደኛውን ጫፍ በተበሳው የፊልትሮ ቀዳዳ እንከተውና እንበይደዋለን።
በይደን ከጨረስን በኋላ ምን ያህል ግፊት እንዳለው የማንፈልድ ጌጃችን ሰማያዊ ሆዝ ከኮፕረሰሩ ጋዝ መሙያ ቱዩፕ ጋር አገናኛለን።
ማንፎልድ ጌጃችን እስከ -20 ድረስ እስከሚያነብልን ከጠበቅነው በኋላ ፊልትሮ ላይ በይደነው የነበረውንና ጋዝ ሲወጣበት የነበረውን ካፒላሪ ትዩብ ጫፍ አየር እንዳይገባብን መበየድ።
ለ. #ቫኪዩም_ፓንፕ ማሽን(Vacum pump machine) ተጠቅሞ የማፅዳት ዘዴ
በዚህ ጊዜ ቫኪዩም ፓንፕ ማሽን ያስፈልገናል።
የማንፎልድ ጌጃችን ሰማያዊ ሆዝ(ዝቅተኛ ግፊት) ከኮፕረሰሩ ጋዝ መሙያ ቱዩፕ ጋር አገናኛለን።
የማንፎልድ ጌጃችን ኮመን(ቢጫ ሆዝ) ከቫኪዩም ፓንፕ ማሽን ጋር እናገናኛለን።
ከዛ ቫኪዩም ፓንፕ ማሽኑን ኤሌክትሪክ ሀይል እንሰጠው እና ማንፈልድ ጌጃችን እስከ -20 ሲደርስ ማንፎልድ ጌጃችን እንዘጋው እና ጋዝ ወደ መሙላት እንሄዳለን።

5. ጋዘ መሙላት
👉ጋዝ ለመሙላት የማንፎልድ ጌጃችን ኮመን(ቢጫ ሆዝ) ከጋዙ ሲሊንደር ጋር አገናኝተን ፍሪጁን የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲያገኝ እናደርጋለን።
👉 የጋዙን ሲሊንደርና ማንፎልድ ጌጃችን ከፍተን ከ30-40 ሴኮንድ ከሞላን በኋላ ማንፎልድ ጌጃችን ዘግተን ለ10 ደቂቃ ያህል ኮምፕረሰሩ እየሰራ እንጠብቃለን። ከ10 ደቂቃ ባኋላ እንደገና ከ30-40 ሴኮንድ ያህል ማንፎልድ ጌጃችን ከፍተን ከሞላን በኋላ አሁንም መልሰን ለ10 ደቂቃ ገደማ ዘግተነው እንቆያለን።
👉ይህን ሂደት #ኮምፕረሰራችን እስኪሞቅና ኢቫፖሬተራችን እስኪቀዘቅዝ ድረስ(ማንፎልድ ጌጃችን 60psi እስከሚደርስ ድረስ) እንደጋግመዋለን።
👉 አሁን በትክክል ጋዝ መልተን ስራችንን ስላጠናቀቅን አረፍ ይበሉና ይን ፖስት ለግለሰቦችና ለተለያዩ ጉርፖች #ሼር በማድረግ ሌሎችንም ተጠቃሚ ያደርጉ❗️
#እናመሰግናለን❗️
👉#በግል_ወይም_በቡድን_የሙያ_ስልጠና_ለመሰልጠን_በሚከተሉትን_ስልክ_ቁጥሮች_ያገኙናል❗️
👇👇👇👇👇
0991156969
0118644716
" #ለሌሎች_ለውጥ_ምክንያት_እንሁን!"
🔹🔸🔹 #ለወዳጅዎም_ያጋሩ!🔸🔹
🔹🔸🔹🔹 #እናመሰግናለን!🔹🔸
👍357
#ማስታወቂያ
===
ነገ ሰኞ በ 02/03/2017 ሊጀምር የነበረውና  በሳምንት 5 ቀን ከሰኞ-አርብ ከቀኑ 8:00-11:00 የሚሰጠው 30ኛ ዙር #አድቫንስድ_የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርጋታና_ጥገና ስልጠና  ወደ #አርብ 06/03/2017 የተራዘመ መሆኑን አውቃችሁ በዚህ ቀን ከቀኑ 8:00 ላይ ቦሌ ሚካኤል በሚገኘው ማሰልጠኛችን በመገኘት ስልጠናችሁን እንድትከታተሉ እናሳስባለን።
👉በዚህ #ዙር_የመሰልጠን ፍላጎት ያላችሁ ውስን ቦታዎች ስላሉን ቀድማችሁ  በመመዝገብ  እጅግ ልዩ የሆነውን #በክፍል#በወርክሾፕና_በሳይት ልምምድ የሚሰጠውን ስልጠና መከታተል እንደምትችሉ እናሳስባለን።
  
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ  ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️
#አድራሻ
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)
#ለተጨማሪ_መረጃ
👇
0118644716
0991156969
👍10
#ክፍት_የስራ_ቦታ_ማስታውቂያ
===
👉 #የኢትዮጵያ_ኤሌክትሪካል_መሃንዲሶች _ማህበር ከዚህ በታች በተጠቀሰው ክፍት የስራ መደብ ላይ ተፈላጊ ችሎታ
አሟልተው ለሚመዘገቡ ስራ ፈላጊዎች መካከል አወዳድሮ በቋሚነት ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለሆነም ተፈላጊ
ችሎታ አሟልታችሁ ለመወዳደር የምትፈልጉ የስራ ፈላጊዎች ይህ የቀጥር ማስታወቂያ ለመጀመሪያ ጊዜ
ከወጣበት ቀን አንስቶ ባሉ ሰባት (7) የስራ ቀናት ውስጥ መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን፡፡
#የስራ_መደቡ_መጠሪያ:-  የቢሮ ጸሐፊ
ደረጃ፡ 1
#የቅጥር_ሁኔታ፤ በቋሚነት
ብዛት፡ 2
#ጾታ አይለይም (ቅድሚያ ለሴት)
ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ እና የት/ት ዓይነት፤ ዲፕሎማ በጸሐፊነት እና ቢሮ አስተዳደር
(የኤሌክትሪካል ፊልድ ትምህርት ያለው ቅድሚያ ያገኛል)
አግባብነት ያለው የስራ ልምድ፤ አንድ ዓመት እና ከዚያ በላይ
የስራ ቦታ፤ አዲስ አበባ (5ኪሎ ዩኒቨርስቲ ግቢ ውስጥ)
ለበለጠ መረጃ 0911410369/ 0911750005/
👉መረጃችሁን  ከዚህ በታች ባሉት የቴሌግራም ሊንኮች በመላክ  ያመልክቱ!
👇👇
https://www.tgoop.com/meseet1990
ወይም
https://www.tgoop.com/Samra2017
👍91
.#ስታር_ዴልታ_ሞተር_ማስጀመሪያ_ዘዴ/#Star_Delta_Motor_starting_Method
=========
👉ከዚህ ቀደም 4ቱን የተለያዩ የሞተር ማስጀመሪያ ዘዴዎችን አይተናል። ዛሬ ደግሞ ስለ ስታር- ዴልታ ሞተር ማስጀመሪያ ዘዴ እናያለን። ይህ የማስጀመሪያ ዘዴ የተለመደ እና በብዛት ስለምንጠቀምበት በጥልቀት ለማየት እንመክራለን።
👉ስለ ስታር-ዴልታ የሞተር ማስጀመሪያ ከማየታችን በፊት ግን ስታር ኮኔክሽን እና ዴልታ ኮኔክሽን ምንድን ናቸው? የሚሉትን እናያለን። መልካም ቆይታ🙏

🔸ስታር /Star & ዴልታ/Delta
👉ስታር እና ዴልታ ከስማቸው እንደምንረዳው ስማቸው ቅርፃቸው ያመለክታል።
👉ስታር / Star connection የምንለው 3 ፌዝ ያላቸውን ሰርኪዩቶች አንደኛውን ጫፍ አንድ ላይ በማሰር የጋራ ኒውትራል ነጥብ(Neutral point) በመፍጠር መብረቅን ለመከላከል ከመሬት ጋር ማሰር የሚያስችል ዘዴ ነው።
👉ይህ ዘዴ የ "Y" ቅርፅ ያለው ሲሆን "star" ወይም "wye" Connection ብለን ልንጠራው እንችላለን።
🔸ዴልታ/Delta Connection
👉ዴልታ ኮኔክሽን የምንለው ደግሞ የሦስት ማዕዘን ቅርፅ ያለው ሲሆን 3 ፌዝ ያላቸውን ሰርኪዩቶች የንዱን መጀመሪያ ከ ሌላኛው መጨርሻ (end-to- start) በማገናኘት የምንፈጥረው ዘዴ ነው።
👉በመቀጠል ስለሁለቱ ባህሪ ወይም ተመሳሳይነት እና ልዩነት እናያለን።
#Star Vs #Delta_Connection

🔸 #ስታር/ #Star
1. አራት የኤሌክትሪክ ዋየሮች ሲኖሩት 3ቱ ፌዞች ሲሆኑ አንዱ ኒው ትራል ነው።
2. የመስመር ከረንት(Line current) እና ፌዝ ከረንት(Phase current) እኩል ናቸው። IL=Ip
3. ፌዝ ቮልቴጁ(Phase Voltage/220V) በ√3 ሲባዛ የመስመር ቮልቴጁን(Line Voltage/380V) ይሰጠናል። VL= √3*Vp
4. ፌዝ ቮልቴጁ አነስተኛ ስለሆነ አነስተኛ የፕላስቲክ ሽፋን(Insulation cover) ይጠቀማል።
5. 3- ፌዝ 4-ኤሌክትሪክ ገመድ ያላቸውንም ሆነ 3-ፌዝ 3-ኤሌክትሪክ ገመድ ያላቸውን ሲስተሞች ይቀበላል።
6. ፍጥነቱ አነስተኛ ነው ምክንያቱ ደግሞ ፌዝ ቮልቴጁ(220v) አነስተኛ ስለሆነ ነው።
7. ብዙ ጊዘ ሲነሱ አነስተኛ ከረንት(low starting current) ለሚፈልጉ እና እረጅም እርቀት ላላቸው አገልግሎቶች እንጠቀመዋለን።
8. ሁለት የተለያዩ መጠን ያላቸውን ቮልቴጆች(220V & 380V) እንድንጠቀም ያስችለናል።
🔹#ዴልታ/ #Delta
1. ሶስት ኤሌክትሪክ ወየሮች ብቻ አሉት(ኒውትራል የለውም)።
2. ፌዝ ከረንት(Phase Current) በ√3 ሲባዛ የመስመር ከረንት(Line current) ይሰጠናል። IL= √3*Ip
3. የመስመር ቮልቴጅ(Line Voltage) እና ፌዝ ከረንት(Phase Voltage) እኩል ናቸው። VL=Vp
4. ፌዝ ቮልቴጁ ከፍተኛ ስለሆነ ከፍተኛ የፕላስቲክ ሽፋን(Insulation cover) ይጠቀማል።
5. 3-ፌዝ 3-ኤሌክትሪክ ገመድ ያላቸውን ሲስተሞች ብቻ ይቀበላል ምክንያቱም ኒውትራል የለውም።
6. ፍጥነቱ ከፍተኛ ነው ምክንያቱም ፌዝ ቮልቴጁ(380v) ከፍተኛ ስለሆነ ነው።
7. ብዙ ጊዘ ሲነሱ ከፍተኛ ቶርክ (high starting torque) ለሚፈልጉ እና አጭር እርቀት ላላቸው አገልግሎቶች እንጠቀመዋለን።
8. 380V ቮልቴጅ ብቻ ያስጠቅማል።
ወ.ዘ.ተ
#ሼር #ሼር #ሼር

#የአጭር_ጊዜ_ሙያ ስልጠና_ከፈለጉ ይደውሉ❗️
0991156969
0118644716

#አድራሻ
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)

👉#ስለምትከታተሉን_እናመሰግናለን🙏

👉#ለሌሎችም_ያጋሩ❗️

"ለሌሎች ለውጥ ምክንያት እንሁን!"
🔹🔸🔹ለወዳጅዎም ያጋሩ!🔸🔹🔸
🔹🔸🔹🔹እናመሰግናለን!🔹🔸🔹
👍355
#በቅርብ_የሚጀምሩ_የስልጠና_አይነቶች
=====

1️⃣.#አድቫንስድ_የህንፃ_ኤሌክትሪክ_መስመር_ዝርግታ-- #አርብ በ 06/03/2017 ከቀኑ 8:00 ይጀምራል❗️---#30ኛ_ዙር
2️⃣.#አድቫንስድ_የጀነሬተር_ዝርጋታ(With MTS & ATS) እና ጥገና  እንዲሁም #ሞተር_ኮንትሮል_ሲስተም --- #ሰኞ ህዳር 9/2017  ጥዋት 3:00 ላይዓይጀምራል❗️- #3ኛ_ዙር
3️⃣. #አድቫንስድ_የቤት_እቃዎች(ፍሪጅ፣ ልብስ ማጠቢያ ማሽን፣ ኦቨን፣ ማይክሮዌቭ ኦቭን፣ ስማርት ቲቪ  ወዘተ ) ጥገና ደግሞ #ረቡዕ ህዳር 18/2017 ዓ.ም ጥዋት 3:00  ይጀምራል❗️--- #4ኛ_ዙር
👉ክፍያው ለ 3ቱም የስልጠና አይነቶች 6200 ብር  ሲሆን ሰልጣኞች ስልጠናቸውን ሲያጠናቅቁ የተቋም ምዘና እና COC የሚመዘኑ ይሆናል❗️
↪️ ስልጠናው ገሚሰጥው እጅግ የረጅም አመት ልምድ ባለቸው #ኤሌክትሪካል_ኢንጅነሮች ሲሆን በሳይትና በኢንዱስትሪ ስልጠና የታገዙ በመሆኑ እጅግ ልዩ ያደርገዋል❗️
👉ይህን በአይነቱ ልዩ የሆነ ስልጠና ለሌሎችም #ሼር በማድረግ ውለታ ይዋሉላቸው❗️
👉ልዩነታችን ግልፅ ነው ይመዝገቡ❗️ይሰልጥኑ❗️ልዩነት ፈጣሪ ባለሙያ ይሁኑ❗️ከፍተኛ ተከፋይ ይሁኑ❗️
👉በአጭር ጊዜ ስልጠና የረዥም ጊዜ ህልምዎን ያሳኩ❗️
ልዩነታችን ብቁ ባለሙያ  ማድረጋችን ብቻ አይደለም የሥራ ባለቤት ማድረጋችንም ነው❗️
#አድራሻ
https://rb.gy/8pwr92 (ቦሌ ሚካኤል)
#ለተጨማሪ_መረጃ
👇
0118644716
0991156969
👍224
Reading Electrical drawing-part -2
https://vm.tiktok.com/ZMhG4WLNu/
👍9
2025/07/13 01:33:14
Back to Top
HTML Embed Code: