tgoop.com/atc_news/24739
Create:
Last Update:
Last Update:
የ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ተጠናቀቀ
******************
የከፍተኛ ትምህርት የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተጠናቅቋል፡፡
በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሐመድ፤ በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐ ግብሮች ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን ገልጸዋል።
57 የመንግስትና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ያስፈተኑ ሲሆን ፈተናውም በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።
ለፈተናው ከተመዘገቡት 169ሺህ 790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ 117ሺህ 192 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡
እንዲሁም 52ሺህ 598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
BY ATC NEWS
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/Tv2944azC9tqaNFbSKXmuMySLCi7jYWxxbe7itxeI5LKMOaOq-qoqpA1UbCa19REazC2sIBmLDcE5WZjSvmYBOwTqFyf25cD3Zp-qtrg9TZ198tpE8aKbUHEngeX19qgfKqY_pcCDH8deDxC4v5iufwSNPyzqVkEpZ3Rs0-BF4M2VLTV77a8IYEg5t1f9OQyC3J-14dRiRjtNLr7AHh3aVo7ykKrzmOu9NteNNia_eRSvQuSu-TnlWE4pgweWqDBFyEp_WtXlSBYF94lSjSRohB31icFEDjalbUNTSYMn7Za3v9qDAtwW7sC69BWP9Qdh3ZdW9jixy5OhAYdthXzbA.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/atc_news/24739