Telegram Web
ATC NEWS
መመሪያ.pdf
በ2016ዓ.ም የተማሪዎች ከክፍል ወደ ክፍል ዝውውር ፖሊሲ

አንደኛ፣መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች የተማሪዎች ከክፍል ወደ ክፍል ዝውውር ፖሊሲ በየአመቱ በከተማ ደረጃ በወጥነት በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ እንደሚዘጋጅ ይታወቃል ፡

በመሆኑም የ2016ዓ.ም ከክፍል ወደ ክፍል የዝውውር ፖሊሲ ስለተዘጋጀ በክፍለ ከተማችሁ ስር ለሚገኙ የአንደኛ፣ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ት/ቤቶች እንዲደርሳቸው እና በተቀመጠው መሰረት ተግባራዊ እንዲደረግ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ አሳስቧል፡፡

Read More 👉 Click

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
💥በ2016ዓ.ም የተማሪዎች ከክፍል ወደ ክፍል ዝውውር ፖሊሲ‼️

📌 ከ 1ኛ እስከ 3ኛ ክፍል በተከታታይ ምዘና ድጋፍ ተደርጎላቸው ለደረጃው የተቀመጠው አጥጋቢ የመማር ብቃት ማሟላታቸውን እየተረጋገጠ ወደ ሚቀጥለው የክፍል ደረጃ ይዛወራሉ ጅ፡፡

📌 የ4ኛ ክፍል የቀንና የማታ ተማሪዎችን በተመለከተ፡-

ሀ. በሁሉም የትምህርት አይነቶች 50 እና በላይ ያገኙ ወደ 5ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ለ. በ (1) የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 51 ካገኙ ወደ 5ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሐ. በ (2) የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 52 ካገኙ ወደ 5ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

መ. በ3 እና ከዛ በላይ የትምህርት አይነቶች ከወደቁ #ይደግማሉ ፡፡

📌 የ5ኛ ክፍል የቀንና የማታ ተማሪዎችን በተመለከተ፡-

ሀ.በሁሉም የትምህርት አይነቶች 50 እና በላይ ያገኙ ወደ 6ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ለ. በ1 የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 51 ካገኙ ወደ 6ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ሐ. በ2 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 52 ካገኙ ወደ 6ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

መ. በ3 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 53 ካገኙ ወደ 6ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ሠ. በ4 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 54 ካገኙ ወደ 6ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ረ. በ5 እና በላይ የትምህርት አይነቶች ከወደቁ #ይደግማሉ ፡፡

📌 የ7ኛ ክፍል የቀንና የማታ ተማሪዎችን በተመለከተ፡-

ሀ. በሁሉም የትምህርት አይነቶች 50 እና በላይ ያገኙ ወደ 8ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ለ. በ1 የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 51 ካገኙ ወደ 8ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

ሐ. በ2 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 52 ካገኙ ወደ 8ኛ ክፍል #ይዛወራሉ ፡፡

መ. በ3 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 53 ካገኙ ወደ 8ኛ ክፍል 8ኛ ክፍል #ይዛወራሉ

ሠ. በ4 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 54 ካገኙ ወደ 8ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ረ. በ5 እና ከዛ በላይ የትምህርት አይነቶች ከወደቁ #ይደግማሉ፡፡

📌 የ9ኛ ክፍል የቀንናየማታ ተማሪዎች በተመለከተ፡-

ሀ. በሁሉም የትምህርት አይነቶች 50 እና ባላይ ያገኙ ወደ 10ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ለ. በ1 የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 51 ካገኙ ወደ 10ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሐ. በ2 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ 52 ካገኙ ወደ 10ኛ ክፍል #ይዛወራሉ

መ. በ3 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 53 ካገኙ ወደ 10ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሠ. በ4 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 54 ካገኙ ወደ 10ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ረ. በ5 እና ከዛ በላይ የትምህርት አይነቶች ከወደቁ #ይደግማሉ፡፡

📌 የ10ኛ ክፍል የቀንና የማታ ተማሪዎች በተመለከተ፡-

ሀ. በሁሉም የትምህርት አይነቶች 50 እና ባላይ ያገኙ ወደ 11ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ለ. በ1 የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 51 ካገኙ ወደ 11ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሐ. በ2 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ 52 ካገኙ ወደ 11ኛ ክፍል #ይዛወራሉ

መ. በ3 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 53 ካገኙ ወደ 11ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሠ. በ4 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 54 ካገኙ ወደ 11ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ረ. በ5 እና ከዛ በላይ የትምህርት አይነቶች ከወደቁ #ይደግማሉ፡፡

📌 የ11ኛ ክፍል የቀንና የማታ ተማሪዎች በተመለከተ፡-

ሀ. በሁሉም የትምህርት አይነቶች 50 እና ባላይ ያገኙ ወደ 12ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ለ. በ1 የትምህርት አይነት ወድቀው አማካይ ውጤት 51 ካገኙ ወደ 12ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሐ. በ2 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ 52 ካገኙ ወደ 12ኛ ክፍል #ይዛወራሉ

መ. በ3 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 53 ካገኙ ወደ 12ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ሠ. በ4 የትምህርት አይነቶች ወድቀው አማካይ ውጤት 54 ካገኙ ወደ 12ኛ ክፍል #ይዛወራሉ፡፡

ረ. በ5 እና ከዛ በላይ የትምህርት አይነቶች ከወደቁ #ይደግማሉ፡፡

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#TVT

በፌዴራል ቴክኒክና ሙያ ስልጠና ኢንስቲትዩት ሞዴል የመውጫ ፈተና በ21/2016 ዓ.ም እና #ዋናው የመውጫ ፈተና በ24/2016 ዓ.ም የሚሰጥ ስለሆነ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ እናሳውቃለን፡፡ (ኢኒስቲትዩቱ)


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#ExitExam

ላለፉት ስድስት ቀናት ሲሰጥ የቆየው ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ዛሬ ይጠናቀቃል፡፡

ለሁሉም የቅድመ ምረቃ ዕጩ ተመራቂዎች በኦንላይን የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ለመውሰድ 178,000 ተማሪዎች መመዝገባቸውን ትምህርት ሚኒስቴር መግለፁ ይታወሳል፡፡

በዛሬው ዕለት የጤና ትምህርት መስክ ፈተናዎች ከ30 ሺህ ለሚበልጡ ተፈታኞች በመሰጠት ላይ ይገኛሉ፡፡

ምስል፡ ራያ ዩንቨርሲቲ
ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news/
#AMU

ለአርባምንጭ ዩንቨርሲቲ መደበኛ ተማሪዎች በሙሉ

በሀገር አቀፍ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና እንዲሁም ከዩንቨርሲቲያችን የ2016 የትምህርት ዘመን ምረቃ ጋር በተያያዘ ከተመራቂ ተማሪዎች ውጭ ያላቹህ ተማሪዎች በሙሉ እስከ ሰኔ 25/2016 ዓ.ም. ድረስ ባለው ጊዜ ክሊራንስ በማጠናቀቅ ወደ ቤተሰቦቻቹህ እንድትሄዱ እያሳሰብን የ2017 የትምህርት ዘመን መግቢያ ቀንን በተመለከተ በቅርብ ቀን በሚድያ የምናሳውቅ መሆኑን እናሳውቃለን።

[የአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ ሪጂስትራርና አልሙናይ ዳይሬክቶሬት]

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
የመውጫ ፈተና ውጤት መቼ ይፋ ይደረጋል?

ከአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ህብረት ያገኘነው መረጃ 👇

<The exit exam result will be released today after the health science COC exam end.

National Students Council>


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ለኢንትራንስ ፈተና Ethio Matric አፕሊኬሽንን በመጠቀም ይዘጋጁ፡፡

🔷 አፕሊኬሽኑ ከ2008 - 2015ዓም የኢንትራንስ ፈተና ከነመልሱ እና ከነማብራሪያው የያዘ ሲሆን ፤ እነዚህን ፈተናዎች በቀላሉ መለማመድ የምትችሉበት መንገድ አዘጋጅቷል፡፡

🔷 አፕሊኬሽኑን ዳውንሎድ ለማድረግ ታች ያለውን ሊንክ ይጫኑ
https://play.google.com/store/apps/details?id=com.addismatric.addismatric

Telegram channel: www.tgoop.com/ethiomatric
በሁለቱም ቅርንጫፎቻችን (ሜክሲኮና መገናኛ) እንዲሁም በኦንላይን በምንሰጣቸዉ  ስልጠናዎች ከሁሉም ላይ ታላቅ የዋጋ ቅናሽ አድርገናል! አሁኑኑ ይመዝገቡና ትልቅ ለዉጥ ወደሚያመጡበት ተቋም ይቀላቀሉ!

ከትምህርትና ስልጠና ጥራትና ቁጥጥር ባለስልጣን ሙሉ ዕዉቅና ካለዉ ሰርተፊኬት ጋር!

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

የብዙ አመት ልምድ እና ብቃት ባላቸዉ አሰልጣኞች!

🎯 Graphics Design
🎯 Interior Design
🎯 Digital Marketing
🎯 Adobe photoshop
🎯 Website Design
🎯 Programming Language
🎯 Video Editing
🎯 Database
🎯 Basic Computer
🎯 Accounting Softwares (Peachtree/ Queeck books)
🎯 Engineering Softwares (Autocad,Etabs, Civil 3d,Reviet, solid work, bill of quantity, software engineering courses)
🎯 SPSS & STATA
🎯 MS-Project
🎯  Foreign (English, Arebic, German, Chinese, French, Italy, swedish, Norway, Spanish, Turkish..) & Local (Amharic, Oromiffa, Tigrigna, Geez..) Languages

እኛጋ ለመሰልጠን ኮምፕዩተር መግዛት አያስፈልግዎትም!

አድራሻ:-1. መገናኛ መተባበር ህንፃ 4ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 419 (ሊፍት ይጠቀሙ)
            2. ሜክሲኮ ኬኬር ህንፃ 6ኛ ፎቅ ቢሮ ቁጥር 639 (ሊፍት ይጠቀሙ ሁለተኛዉን ሊፍት(ትንሹ ኬኬር)

☎️ 0910317675/0991929303/0991929304
@Top_trainings

Join our telegram channel
https://www.tgoop.com/topinstitutes
የ2016 ዓ.ም የከፍተኛ ትምህርት ተማሪዎች የዩኒቨርስቲ መውጫ ፈተና ተጠናቀቀ
******************

የከፍተኛ ትምህርት የ2016 ዓ.ም የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች የመውጫ ፈተና ተጠናቅቋል፡፡

በትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት የጥራትና ብቃት ማሻሻል ዴስክ ኃላፊ አቶ ሰይድ መሐመድ፤ በ244 የቅድመ ምረቃ መርሐ ግብሮች ከሰኔ 14 እስከ 19 ቀን 2016 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የመውጫ ፈተና መጠናቀቁን ገልጸዋል።

57 የመንግስትና 124 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎቻቸውን ያስፈተኑ ሲሆን ፈተናውም በ51 የፈተና ማዕከላት ተሰጥቷል።

ለፈተናው ከተመዘገቡት 169ሺህ 790 ተማሪዎች መካከል ለመጀመሪያ ጊዜ 117ሺህ 192 ተማሪዎች የመውጫ ፈተናውን መውሰዳቸው ተጠቅሷል፡፡

እንዲሁም 52ሺህ 598 ተማሪዎች ደግሞ ፈተናውን በድጋሚ ለመውሰድ የተመዘገቡ መሆናቸውን ከትምህርት ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።


ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
#Result #Remedial #Exit_Exam

የ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና እና የሪሚዲያል ማጠቃለያ ፈተና ውጤቶች መቼ ይፋ ይደረጋሉ?

ቲክቫህ ዩንቨርሲቲ ከትምህርት ሚኒስቴር አመራር አገኘሁት ብሎ ያጋራው መረጃ👇

📌 የሪሚዲያል ተማሪዎቹ ውጤት ከሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና መጠናቀቅ በኋላ ባሉት ቀናት በጣም ከዘገየ እስከ #ሰኞ ሰኔ 24/2016 ዓ.ም ይፋ ይሆናል።

📌 የመውጫ ፈተና ውጤት በቀጣይ ቀናት ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን ማስመረቅ ከመጀመራቸው #በፊት ይፋ ይደረጋል።

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
ከመውጫ ፈተናው ጋር በተያያዘ በርካታ ቅሬታዎች እየቀረቡ ይገኛል።

እንድንዘጋጅበት ከተነገርን ይዘት እና በትምህርት ሚኒስቴር ከቀረበው ብሉ ፕሪንት ጋር የሚገናኝ አይደለም ብለው ቅሬታ ካቀረቡት መካከል፦

👉 የማኔጅመንት
👉 የማርኬቲንግ ማኔጅመንት
👉 የሀይድሮሊክና ውሃ ሃብት
👉 የቬተርነሪ ሜድስን
👉 የኸልዝ ኢንፎርማቲክስ ይጠቀሳሉ።

ከዚህም ባለፈ ፥ " የተሰጠን ሰዓት በቂ አልነበረም ፣ፈተና ዘግይቶ የመጀመር፣ ለፈተናው በቂ ሰዓት አለመመደብ ችግር ነበር " የሚል ቅሬታ ያቀረቡም አሉ።

ምንም እንኳን በርካታ ተማሪዎች ቅሬታቸውን በተለያዩ መንገዶች ያሰሙ ቢሆንም ትምህርት ሚኒስቴር ግን አንድም ቅሬታ አልደረሰኝም ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

የተማሪዎቹ ቅሬታ ውጤት ይፋ ከመደረጉ በፊት ምላሽ ሊያገኝ ይገባል‼️

ለጥቆማ 👉 @atc_newsbot
➡️ https://www.tgoop.com/atc_news
2024/06/27 00:16:58
Back to Top
HTML Embed Code: