"ሁሉ፡መዳንን፡ይወርሱ፡ዘንድ፡ስላላቸው፡ለማገዝ፡የሚላኩ፡የሚያገለግሉም፡መናፍስት፡አይደሉምን ?"ዕብ 1፥14
† የዚህ መልዕክት ዋና ዓላማ ከዘለዓለም ሞትና እርግማን በደሙ ካዳናቸው ጌታ ይልቅ በአገልግሎት የተራዷቸውን መላዕክት በላቀ ክብር ይመለከቱ ለነበሩ የአይሁድ ክርስቲያኖች ማስተማሪያ ይሆን ዘንድ በቅዱስ ጳውሎስ የተጻፈ መልዕክት ነው።†
ሰላም ለሁላችሁ ይሁን ።በቅድሚያ ለቀረበው ጥያቄ ተሳትፎ ያደረጋችሁ ሁሉ እግዚአብሔር አምላክ የጥበብና የዕውቀትን ጸጋ ያብዛላችሁ።
በርዕሱ ላይ የተቀመጠውን ኃይለ ቃል ቅዱስ ጳውሎስ በዕብራውያን መልዕክቱ ላይ ጽፎታል።የዕብራውያን መልዕክት የተጻፈው ከአይሁድ እምነት ወደ ክርስትና ለመጡ የመጀመሪያው መቶ ክፍለ ዘመን ክርስቲያኖች ነው።
አይሁድ በኤቦር ዕብራውያን፣በእስራኤል(ያዕቆብ) እስራኤላውያን፣በይሁዳ አይሁድ፣በፋሬስ ፈሪሳውያን፣በሳዶቅ ሰዱቃውያን እየተባሉ በቀደሙ አባቶቻቸው ስም የመጠራት ባህል አላቸው።
በኤቦር ዕብራውያን የተባሉት ክርስቲያኖች ምንም እንኳ ክርስትናን እንደ አዲስ እምነት በቅዱሳን ሐዋርያት ስብከት ቢቀበሉም ቀድሞ የነበሩበት የይሁዲ እምነትና ባህል ቶሎ ከአዕምሯቸው ስላልወጣ ብዙ ነገር ይደበላለቅባቸው ነበር።በተለይ ነገረ -ድኅነት ቶሎ ሊገባቸውና ከውስጣቸው ጋር ሊዋሐድ አልቻለም ነበር።በክርስቶስ ደም እንዲሁ ያለዋጋ በጸጋ ያገኙትን ዘለዓለማዊ ድኅነት በእምነት መቀበል አቅቷቸው ጥለወት የመጡትን የይሁዲ እምነት ልማድ ይቀላቅሉ ነበር።
መስዋዕተ ኦሪት ከመስዋዕተ አዲስ ይልቃል ብለው ያስቡ ነበር ፤ ከክርስቶስ ይልቅ ዓበይት ነቢያት፣ሊቃነ ካህናት ና አባቶቻቸው ይከብራሉ ብለውም ይቀበሉ ነበር፣ቅዱሳን መላዕክት ከክርስቶስ ይልቅ የላቀ ክብርና አገልግሎት እንዳላቸውም ያስቡ ነበር።በዚህ የተደበላለቀ መረዳት ውስጥ ለነበሩ ጀማሪ አማኞች ቅዱስ ጳውሎስ የጠራ የእምነት አመለካከት እንዲኖራቸው የዕብራውያንን መልዕክት ጽፎላቸዋል።መልዕክቱን የጻፈላቸው በ64 ዓ.ም ሮም ጣሊያን ለአገልግሎት ሳለ እንደሆነ የመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ይመሰክራሉ።
ቅዱስ ጳውሎስ መልዕክቱን እንዲህ በማለት ነው የጀመረላቸው፦
" ከጥንት፡ጀምሮ፡እግዚአብሔር፡በብዙ፡ዐይነትና፡በብዙ፡ጎዳና፡ለአባቶቻችን፡በነቢያት፡ተናግሮ፥ዅሉን፡ወራሽ፡ባደረገው፡ደግሞም፡ዓለማትን፡በፈጠረበት፡በልጁ፡በዚህ፡ዘመን፡መጨረሻ፡ለእኛ፡ተናገረን፤እርሱም፡የክብሩ፡መንጸባረቅና፡የባሕርዩ፡ምሳሌ፡ኾኖ፥ዅሉን፡በሥልጣኑ፡ቃል፡እየደገፈ፥ኀጢአታችንን፡በራሱ፡ካነጻ፡በዃላ፥በሰማያት፡በግርማው፡ቀኝ፡ተቀመጠ።" ይላል ዕብ 1፥1
ልብ በሉ! አይሁድ ከክርስቶስ በላይ በክብር አግዝፈው ይመለከቷቸው የነበሩ አባቶችንና ነቢያትን ሁሉ ቅዱስ ጳውሎስ በአንድነት ጠቅልሎ እኒህ ክርስቶስ እስኪ መጣ ድረስ እግዚአብሔር በልጁ የሚፈጽመውን ማዳን በልዩ ልዩ ዓይነት ምሳሌና መንገድ ያናግራቸው የነበሩ መንገድ ጠራጊዎች እንጂ እነርሱ የጽድቅ መንገድ እንዳልነበሩ በአጽንዖት ከገለጸላቸው በኋላ፤ በእግዚአብሔር የዘለዓለም ሐሳብ ውስጥ ዓለምን ለማዳን የቀጠራት ቀን ስትደርስ ግን የተነገረው ትንቢትና የተመሰለው ምሳሌ ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ እንደተፈጸመ፣ ሕዝብና አሕዛብን ሁሉ በፍቅር በሚወርሰው በልጁ የዓለም የድኅነት ምሥራች እንደተናገረ ያስረዳቸዋል። ይህ የነቢያት ትንቢትና የካህናት መስዋዕት ምሳሌ የሆነው ጌታ ከሁሉ የላቀ ክብር ያለው ሊቀ ካህን፣ በመለኮት ከአብ ጋር የሚተካከል የባሕርይ አምላክ ፣ዓለማትን በቃልነት የፈጠረ ደግሞም ዛሬም ዓለማትን በመለኮታዊ ቃል ደግፎ ያቆመ ኤልሻዳይ፣ የሰው ልጆችን ኃጢአት በደሙ ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ የተቀመጠ የትንሳኤ በኲር ሕያው አምላክ መሆኑን ይነግራቸዋል።
ቀጥሎ ደግሞ ከክርስቶስ ይልቅ ለመላዕክት ያላቀ ክብር ይሰጡ ነበረና እንዲህ ይላቸዋል፦
"ከመላእክት፡ይልቅ፡እጅግ፡የሚበልጥ፡ስምን፡በወረሰ፡መጠን፥እንዲሁ፡ከነርሱ፡አብዝቶ፡ይበልጣል።" ዕብ 1፥4
ሐዋርያው ይህንን ካለ በኋላ ነው ስለ ቅዱሳን መላዕክት መንፈሳዊ ተልዕኮ ሲገልጽ ሰው ሁሉ በክርስቶስ ኢየሱስ የተፈጸመለትን መዳን ይወርስ ዘንድ ለማገዝ የሚራዱ ተራዳህያን፣በጸሎትና በልመናቸው የሚያግዙ መንፈሳዊ ኃይላት፣ ከእግዚአብሔር ወደ ሰው መልዕክት በማምጣት የሚያገለግሉ፤ የሰዎችን ልመናና ጸሎት ደግሞ እግዚአብሔር እንዲቀበል በፊቱ ለልመና የሚቆሙ ታማኝ አገልጋዮች መሆናቸውን ገልጿል።
ቅዱስ ጳውሎስ ይህንን የሚገልጽላቸው ቅዱስን መላዕክት በሰው ልጆች መዳን እጅግ የሚደሰቱ ፣የሚዘምሩ፣ አንድን ጌታ የሚያመሰግኑ አገልጋዮች ሲሆኑ አዳኙ፣አጽዳቂው ግን ክርስቶስ ኢየሱስ ብቻ መሆኑን አውቀው የዕብራውያን ክርስቲያኖች የላቀውን ክብርና አምልኮ ለክርስቶስ ይሰጡ ዘንድ በጥበብ ያስተማረበት አንቀጽ ነው።
መላዕክትን "መናፍስት" ያለበት ምክንያት ደግሞ እነርሱ ሥጋችንን ያልተዋሐዱ መንፈስ ሲሆኑ ክርስቶስ ግን የባሕርይ አምላክ ሳለ መለኮቱን ከሥጋችን ጋር አዋሕዶ በፍቅር የተዛመደን፣ባሕርያችንን ባሕርይው አድርጎ በምድራችን የተመላለሰ የፍቅር ጌታ መሆኑን ለመግለጽ ነው።
ወገኖቼ በጣም ልብ በሉ! ይህ መልዕክት ዛሬም ለእኛ ለኦርቶዶክሳውያን ብዙ ትምህርት ይሰጣል ። ኢየሱስን ከማክበር ይልቅ ቅዱሳን መላዕክትን በላቀ ሁኔታ ማክበር የተለየ በረከት ያሰጠናል ብለን ለምናምን ሰዎች አመለካከታችንን እንድናስተካክል ማስተማሪያ ነው።ቅዱሳን መላዕክትን ማክበር ተገቢና በጣምም አስፈላጊ ሥርዐት ነው። በአፋችን ክርስቶስ አምላክ ነው እያልን በተግባር ግን ከክርስቶስ በላይ ለመላዕክት የመንፈጽማቸው ሃይማኖታዊ ተግብራት እንደ አይሁድ ክርስቲያኖች እኛንም ያስወቅሱናል።ብዙዎቻችሁ ታዝባችሁ ይሆናል ዛሬ ኢየሱስ ነው ሲባል ቤተክርስቲያን የሚሄደው ሰው በጣት የሚቆጠር ነው፤ ስለ ኢየሱስ ክብር ሲዘምርና የክርስቶስን ክብር ከፍ አድርጎ ሲገልጽ የሚውለው በጣም ጥቂት ነው።ዛሬ ገብርኤል ነው ሲባል ግን በየቤተክርስቲያኑ የሚተመውን ሕዝብ ስንመለከት፣በአፍና በጽሑፍ ሲዘምር፣ሲሰብክ፣ሲመሰክር የሚውለውን ሕዝብ ግን ስንመለከት ለክርስቶስ በልባችን የሰጠነው ቦታ ምን ያህል እንደሆነ በግልጽ ማሳያ ነው።እንደ አይሁድ በደሙ ካገኘነው ጽድቅ ይልቅ በሥጋዊ ሕይወታችን ያገኘናቸው ስጦታዎች እጅግ እንደላቁብን ማሳያ ነውና ሁላችን መዳንን እንወርስ ዘንድ ሕይወቱን በመስቀል የሰጠንን ጌታ ከማንም በላይ አልቀን በልባችን ዙፋን ላይ እናንግሥ።
ክብርና ምሥጋና አምልኮና ጌትነት ለታረደው በግ ይሁን።
መ/ር ታሪኩ አበራ

እሾኹ ተነቅሏል፡፡
አዳም "እሾኽና አሜከላ ይብቀልብህ" ተብሎ ተረግሞ ነበር፡፡
በዚኽም ምክንያት ይህ እሾኽ የአዳምን እግሮች ሲወጋ ኖረ፡፡ ዛሬ ግን እሾኹ እግር እንዲወጋ ኾኖ አልተሠራም፤
አክሊል ኾኖ በመድኃኔዓለም ራስ ላይ ተደፋ እንጂ፡፡ በእሾኽ ምክንያት መቁሰል ከአዳም እግሮች ጀመረ፤ በመድኅን ክርስቶስ ራስ ላይ ተፈጸመ፡፡
አዳምን "ይብቀልብህ" ያለውን እሾኽ በራሱ ላይ 'እንዲበቅል' አደረገ፡፡
በዚህ እሾኽ አምሳል፥ ፍዳ መርገም፣ ኀጢኣት…ተነቅሏል:: ከኀሳር ወደክብር ተሸጋግረናል፡፡ መርገሙ ተሽሯል፡፡
Simur Alamrew

በፈተና ላሉት
ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.
✍🏽 ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ እንደጻፉት
ይሄ ፈተና ከምን መጣ? ፈተናው ከእኛ ጋር ካሉት ይልቅ በእኛ ላይ ለምን በዛ? ምንጭ የሌለው ፈተና ባይኖርም ምንጩን ሳናውቀው በመጣ ፈተና ነፍሳችን ደከመች። ሰውነታችን ኑሮን ሰለቸች። ፈተናው አስመርሮናል፤ መከራው ከብዶናል ነገር ግን የፈተናውን ምክንያት ሳናውቅና ሳንመረምር ከፈተና ወደ ፈተና ስንሸጋገር እንኖራለን። በመጀመሪያው ማስቆም ሲቻል የመጀመሪያው ፈተና ይኸው ለቀጣይ ፈተና አሳልፎ ሰጥቶን በፈተና እንናወጣለን። በዚህ መንገድ አልፈው ብዙዎቹ ለሚፈልጉት ስኬት ደርሰዋል እኛ ግን አቃተን። በኛ ዘንድ ምናኔም ፈተና ሆኖብናል፤ ትዳርም ፈተና ሆኖብናል። ለምን?
ትዳር በእኛ አልተጀመረም። ከሴት ጋር መኖር ለብዙዎች በረከት ነው። መጽሐፍም “መወደዷ ከወርቅ ይመረጣልና ብልህና ደግ የሆነች ሴትን አትጥላ” ሲራ 7፥19 ብሎ ከቀይ ወርቅ ይልቅ የተወደደ ጸጋ ያላት መሆኑን ይናገራል። ቢሆንም እኛ ዘንድ ሲመጣ ፈተና ያልሆነብን ምን ነገር አለ? ቅዱሳን ሐዋርያት “በጌታ ዘንድ ሴት ያለ ወንድ፤ ወንድም ያለ ሴት አይሆንም” 1ቆሮ 11፥11 ብለው እያስተማሩን እኛ ግን ከዚያ ውጭ በሆነ ሕይወት መኖር እንደነበረብን እያሰብን ነው ያለነው።
የፈተናዬ ምንጭ እሷ ናት ወይም እሱ ነው እየተባባሉ የሚኖሩ ብዙዎች ናቸው። ባል ሚስቱን፤ ሚስትም ባሏን፤ ወንድም ወንድሙን ወይም አንዱ በሌላው ምክንያት ይህ ፈተና እንደመጣበት ሊያስብ ይችል ይሆናል። ዳሩ ግን የፈተና ምክንያት ብዙ ጊዜ በክርስትና ወጣንያን በሆኑ ሰዎች ሕይወት ውስጥ የራሳችን ፍላጎት እንጅ ከሰው ወይም ከሰይጣን የሚመጣ ፈተና እምብዛም የለብንም።
ከዕለታት በአንድ ቀን ጴጥሮስና ዮሐንስ ክርስቶስን ተከትለው ወደ አንድ ስፍራ ተጓዙ። ደብረ ታቦር ወይም ደብረ ዘይት ተከትሎ እንደመሄድ ያለ ቀላል መንገድ ግን አልነበረም። የሰው ገጠመኙ ብዙ አይደል? መንገዶች ሁሉ ወስደው፣ ወስደው የሚያጋፍጡን የሕይወት ግጥሚያ የተለያየ ነው። የነዚህም ቅዱሳን ሰዎች ጉዞ ከዚህ በፊት ከእርሱ ጋር ሲያደርጉት እንደነበረው ያለ ቀና መንገድ አልሆነላቸውም። እስካሁን በተጓዙባቸው ቦታዎች ሁሉ መለያየት አልታየባቸውም ነበር፤ በሁሉም መንገዶቻቸው ዕኩል ተጉዘው አብረው በደስታ ይመለሱ ነበር። ለሌላው የማይነግሩት ድንቅ ምሥጢር ተገልፆላቸው ይመለሱ ነበር። የዛሬው ግን ይለያል። አንዱን ከአንዱ የለየ ታሪክ የተስተናገደበት፤ ወንድማማቾች አብሮ ጀምሮ አብሮ መጨረስ ያልቻሉበት ፈታኝ ጉዞ ነበር። የጸና ብቻ ካልሆነ የተጓዘ ሁሉ የማያሸንፍበት መንገድ።
ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተያዘባት ሌሊት ከደቀ መዛሙርቱ መበተን በኋላ ከመበተን ተርፈው ሁለቱ ጴጥሮስና ዮሐንስ ብቻ እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ ተከትለው መሄዳቸውን ቅዱስ ዮሐንስ በጻፈው ወንጌል ላይ ተጽፏል ዮሐ 18፥15 የጴጥሮስ መከተል በተናገረው ቃል መሠረት ነው ሉቃ 22፥33። የዮሐንስ ግን የሚደንቅ ነው። በአፉ ሳይናገር ሠርቶ የሚያሳይ ሰው እንዴት የታደለ ነው። ስላልነገሩን፣ ስላልጻፉልን፣ የጻፍነውን like share ስላላደረጉልን እንጅ በልባቸው የሚወዱን ስንት ሰዎች አሉ መሰላችሁ።
ከጴጥሮስ ቀድሞ በልቡ ከክርስቶስ ጋር ለመሞትም ሆነ ለእስራት ሊሄድ በልቡ ቃል የገባ ዮሐንስ ነው ነገር ግን በጉባኤ መካከል ከመናገር ተቆጥቦ ጉባኤው ከተፈታ በኋላ ሲያደርገው ታየ። ሕዝብ ሲሰበሰብ፣ ጉባኤው ሲሰፋ ማያደርጉትን ሚቀባጥሩ፤ እጃቸው ላይ የሌለውን ዘር ሊዘሩ የሚሞክሩ፤ በራበው ሕዝብ መሳለቅ ልምድ ሆኖባቸው ሊጎርስ አፉን ለከፈተ ሕዝብ እንጀራ ያልጠቀለሉበትን እጃቸውን የሚዘረጉ፤ የሕዝቡ መሰብሰብ ብቻ ገፋፍቶ የማያውቁትን የሚያናግራቸው፤ ከመናገራቸው በፊት ያላሰቡትን ተናግረው የሚያስቡ ሰዎች ይገርሙኛል። እንደ ዮሐንስ ያሉት ክርስቲያኖች ግን ሁሉን ነገር በጊዜውና በቦታው ካልሆነ አያደርጉትም። የቅዱስ ጴጥሮስ ፈተና የሚጀምረው ከዚህ ነው − የማያደርጉትን ከመናገር።
የማትፈጽሙትን ቃል ኪዳን አትግቡ። ከባድ ፈተና በሕይወታችሁ ይዞ ይመጣና ሕይወታችሁን ይበጠብጣል። ቃል ኪዳናችሁ ከመፈጸም ዐቅማችሁ በላይ ሊሆን አይገባም።
ለማንኛውም የጴጥሮስ ፈተና ቀጠለ። እስከ ሊቀ ካህናቱ ግቢ በር ድረስ አብሮ ቢመጣም ክርስቶስ በገባበት የመከራ በር አብሮ መግባት ከበደው። ለነፍሱ ሳስቶ ከበር ውጭ ቆሞ ቀረ። በሰዎቹ ዘንድ በመታወቅ ቢሆን ኖሮ ከዮሐንስ የሚበልጥ እሱን የሚያውቀው አልነበረም። “በሊቀ ካህናቱም ዘንድ የታወቀ ነበረ” ተብሎ የተጻፈው ለዮሐንስ ነውና። ግን ዮሐንስ በልቡ ጨክኖ ስለነበር ከክርስቶስ ፍቅር የሚለየው ምንም ነገር አልነበረም። ጴጥሮስ ገና ለዚህ መዐርግ አልደረሰም። የበረታው ዮሐንስ ያልበረታውን ወንድሙን ሊያበረታ ወደ ውጭ ወጥቶ ለበረኛይቱ እንድታስገባው ነገረለትና ገባ።
የበረታ ባልንጀራ ማለት ወንድሙን አንድ እርምጃ ወደ ክርስቶስ ማቅረብ የቻለ ነው። ግን አሁንም ሁኔታዎቹ ለጴጥሮስ ምቹ አልነበሩም። ቀኑ በጣም ውርጭ ነበርና የመጣበትን የክርስቶስን ነገር ረስቶ እሳት አንድደው ከሚሞቁ የሊቃነ ካህናቱ በለሟሎች ጋር ተሰልፎ ነፍሱን ለጊዜው ከሚደርስባት ጭንቅ ማዳን ፈለገ። የእሳቱ ወጋገን በገለጠላቸው ብርሃን ተመርተው ሂደው እየተመላለሱ መላልሰው ሃይማኖቱን አስካዱት። ያሳዝናል! በጥቂቱ የተጀመረ ፈተና አሁን ይኸው እዚህ ደረሰ። በትንሹ ያላጠፋነው ኃጢአት ለትልቅ ኀጢአት አሳልፎ ይሰጣል።
አሁን በሕይወታችን ለገጠመን ለዚህ ሁሉ ፈተና መነሻ የሆነውን ነገር እንዳትረሱ፤ ያ በመጀመሪያ ከልብ ጨክነን የማንፈጽመውን ቃል መግባታችን ነው። ብዙዎች ጥሩ ባለትዳር ሊሆኑ ሲችሉ ወደ ምንኩስና ገብተው ራሳቸውን ፈተኑ። አንዳንዶቹ ደግሞ ጥሩ መነኮሳት ሊሆኑ ሲችሉ ወደ ትዳር ገብተው ለራሳቸውም ለትዳር አጋራቸውም ፈተና ሆኑ። አንዳንዶቹ አለቅነት አልተሰጣቸውም። ለአለቅነት መሐላ ሲፈጽሙ ተዉ የሚላቸው ጠፍቶ ነው እንጅ ዛሬ እንዲህ የማይወጡት ፈተና ውስጥ ወድቀው አይቀሩም ነበር። ይሄን ሁሉ የትዕቢት፣ የፍቅረ ንዋይ፣ ድሆችን የመጥላት፣ ያለ ጊዜ መብላት መጠጣት እና ሌሎችም ፈተናዎች ከወዴት መጡ? ከምንችለው በላይ ማሰባችን፣ የማይገባ ንግግራችን የሚያመጣብን ፈተና ነው። ከቆንምለት ዐላማ መዛነፋችን፣ መንገዳችንን መሳታችን፣ ጅማሬአችንን ከፍጻሜችን የተለየ አድርጎታል።
ብዙዎቻችን አሁን በምንኖረው ሕይወት የጠበቅነውን ኑሮ ማግኘት አልቻልንም። ከዓለም ወጥተን ወደ ቤተ ክርስቲያን መጠጋታችን፤ ከመሸታ ቤቶች ይልቅ ቤተ ክርስቲያን አካባቢ ለማምሸት መምጣታችን፤ በችግራችን ሁሉ ካህናትን ለማማከር መወሰናችን፤ ለሕመማችን ቅዱስ ቊርባንን እንደ መፍትሔ ማሰባችን አሁን የደረሰብን ፈተና እንዳይደርስብን በመስጋት ነበር። ነገር ግን ካሰብነው በተቃራኒ ሆነ። ፈተናው መልኩን ቀይሮ መጣ። ለምን? አንዳንዶቻችን የፈተናው ምንጭ ራሳችሁ መሆናችሁን ላስረዳችሁ።
ከዓለማዊነት ወጥታችሁ ቤተ ክርስቲያን አዘውታሮች መሆናችሁ መልካም ነበር፤ ነገር ግን ትንሽ ከቆያችሁ በኋላ ለድኅነት ብላችሁ በተጠጋችኋት ቤተ ክርስቲያን ከድኅነቱ ድኽነቱ ይቅደም ብላችሁ BUSINESS መሥራት ጀመራችሁ። ዛሬ ለናንተ የታቦት መውጣት በጉጉት የምትጠብቁት የገቢ ምንጭ ሆኗል። ከመሸታ ቤት መውጣታችሁ መልካም ነበር፤ ነገር ግን አሁንም መጠጡ ነው እንጅ የቀረው የመሸታ ቤቱን ወሬ ይዛችሁት ቤተ ክርስቲያን ገብታችኋል። አዳራሽ ውስጥ በተቀመጣችሁ ጊዜ የምታወሩት ፌዝና

ቧልት ከመሸታ ቤት ሰዎች በምን ይለያል? ያኔ ወደ እግዚአብሔር ፊታችሁን እንድትመልሱ ወንጌል የሰበኩላችሁና የዘመሩላችሁ ሰዎች ዛሬ የጫወታ ማድመቂያዎቻችሁ ናቸው።
ለሕመማችሁ ቅዱስ ቊርባንን መድኃኒት ማድረጋችሁ መልካም ነበር፥ ነገር ግን እንደ ቆረበ ሰው የኖራችሁት ኑሮ ወዴት አለ? ያለ ልክ ትናገራላችሁ፤ ሰክራችሁ ትታያላችሁ፤ አድማ ትሠራላችሁ፤ ሰውን ትጠላላችሁ። ታዲያ እንዴት በቊርባኑ ትጠቀማላችሁ? አንድ ሐኪም ባዘዘው መሠረት ያልተወሰደ መድኃኒት በሽታ የመከላከል ዕድል ሊኖረው ይችላልን?
ችግራችሁን ለመፍታት ካህናትን ማማከራችሁ መልካም ነበር “የማይፈታውን እንፈታ ዘንድ ሥልጣንን የሰጠኸን....” ብለው በመጽሐፈ ኪዳን ሲጸልዩ የሰማናቸው ካህናት ካልፈቱት ችግራችንን ማን ሊፈታው ይችላል። ነገር ግን ስህተታችሁ ምን እንደሆነ ታውቃላችሁ? ከእውነተኞች መምህራን ትምህርት ይልቅ እንደ ሥነ ልቡና ባለሙያ ትችላለህ፤ ሕልም አለህ፤ የጌታ ልጅ ስለሆንህ ሁሉ ያንተ ነው፤ ጠላትህ የተወጋ ይሁን፤ ዐይነ ጥላ ተደርጎብሀል፤ ድግምት ተደግሞብሀል ወዘተ የሚሏችሁን ትከተላላችሁ። እውነተኛ ትምህርት ከመስማት ፈቀቅ ብላችኋል። የአጥማቂ፣ የነገር አዋቂ፣ የጎሳ፣ የጎጥ የምናምን አምላኪ ትሆናላችሁ። ክህነት በዘር ይወርድ ይመስል ከብሔሩ ውጭ በሆነ ካህን መባረክ የማይፈልግ ምዕመን እንዴት ብሎ ነው ከፈተና መውጣት የሚችለው? ምን ቢሆን ነው እግዚአብሔር ምሕረቱን ለሰው ሊሰጥ የሚችለው?
ለማንኛውም የፈተናው ምንጭ ራሳችን ከሆንን ራሳችንን እናስተካክል። ክርስቶስን ብለን የጀመርነውን ክርስትና በተለያየ ምክንያት የምንፈተንበት እንዳይሆን ከዐላማችን ፈቀቅ ልንል አይገባንም። ዐላማችን ክርስቶስን ተከትለን ወደ ቀራንዮ መድረስ ነው። ዮሐንስ ይህንን ሁሉ ፈተና መልስ ሳይሰጥ ስላለፈው ነው እንጅ ሌሊቱ ነግቶ በቀራንዮ ያየነው ዝም ብሎ እንዳይመስላችሁ። ድካም ካዩባችሁ ፈታኞቻችሁ ብዙ ናቸው። እንደ ዮሐንስ እያለፋችሁ መሄድን ልመዱ። ቀራንዮ ላይ በረከት ይጠብቃችኋል። ክርስቶስ ከምድር ከፍ ብሎ ታገኙታላችሁ። ማርያምን በእናትነት ትቀበላላችሁ። በገነት ለመኖር ዕድል ታገኛላችሁ። ለፈተና አሳልፈው የሰጡንን ድክመቶቻችንን ካወቅን ፈተናውን ማለፍ እንችላለን።
አቤቱ ወደ ፈተና ከሚወስዱ ክፉ ሀሳቦች አድነን!
ማስታወሻ :- ሊቀ ሊቃውንት ስምዐ ኮነ መልአክ የአራቱ ጉባኤያት መምህርና የባሕር ዳር ሀገረ ስብከት የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ ሲሆን የመጻሕፍት ደራሲም ናቸው::
#ወደዚህ_ሠረገላ_ቅረብ
#የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው
#እንዳልጽፍ_የሚከለክለኝ_ምንድን_ነው

አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
የአብያተ ክርስቲያናት አርማ
| ጃንደረባው ሚድያ | ኅዳር 2016 ዓ.ም.|
የቅድስት ቤተ ክርስቲያን አርማዋ መስቀል ነው:: "ከቀስት ፊት ያመልጡ ዘንድ ምልክትን ሠጠሃቸው" የሚለው ቃልም የሚፈጸመው በዚሁ መንፈሳዊ አርማ ነው:: ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለአስተዳደር እንዲመች ደግሞ በአህጉረ ስብከት ተከፍላ እንደምታገለግል ይታወቃል:: ለዚህ መንፈሳዊ አስተዳደርዋ ደግሞ ለእያንዳንዱ ቤተክርስቲያን የራሱ መታወቂያ የሆነ አርማ (logo) እና ዓላማ (emblem) አለው:: ኦርየንታል ኦርቶዶክስ አብያተ ክርስቲያናት የየራሳቸው አርማ አላቸው:: አርማዎቹም ትርጉም ያላቸውና አብያተ ክርስቲያናቱን የሚገልጹ ናቸው::
የጥቂቶቹን እንመልከት :-
⛪️ የግብፅ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ
በአራቱም በኩል እኩል የሆነ መስቀል ሲሆን እያንዳንዱ ሦስት ቀስት ያለው መሆኑ ቅድስት ሥላሴን ይወክላል:: ሙሉው ሲቆጠር ዐሥራ ሁለት ቀስቶች መሆናቸው ደግሞ ቅዱሳን ሐዋርያት በሰበኩት ወንጌል ላይ ቤተ ክርስቲያን መመሥረትዋን ያስረዳል:: በመስቀሉ ዙሪያ ያለው ቃል ደግሞ በኮፕቲክ ቋንቋ የተጻፈ ሲሆን "ኢየሱስ ክርስቶስ ወልደ እግዚአብሔር" ማለት ነው::
⛪️ የኤርትራ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ
ከላይ የሚታየው መስቀልና ከሥሩ ያለው አርዌ ብርት በሞቱና በትንሣኤው ለቤተ ክርስቲያንን ድል ነሺነትን የሠጠ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሲሆን አርዌ ብርቱ ደግሞ በፓትርያርኮች እጅ የሚያዘው "ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" የሚለውን ቃል የሚያስረዳ ያለ በደል ስለ እኛ ተሰቅሎ ያዳነንን ክርስቶስን የሚያሳይ ነው:: ከመስቀሉ ሥር ያለው ብርሃን በመስቀሉ ጨለማን ያራቀ የመድኃኔ ዓለም ክርስቶስ የማዳኑን ሥራ የሚያስረዳ ነው:: በመካከል ያለችው ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ስትሆን ከሥር ባለው መጽሐፍ ቅዱስ ላይም የተጻፈው "ቃል ሥጋ ሆነ" የሚለውን የተዋሕዶ መሠረት የሆነ ቃል ነው::
በዙሪያ ያለው የስንዴና ወይን ዘለላ ደግሞ ምሥጢረ ቁርባንን የሚያሳይ ነው::
⛪️ የሕንድ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ
ከላይ የሚታየው የጳጳሳት አስኬማ ከሐዋርያት ጀምሮ በቅብብል የመጣውን የፓትርያርኩንና የሊቃነ ጳጳሳትን ሥልጣነ ክህነት የሚገልጽ ነው::
መስቀሉ በሞቱና በትንሣኤው ለቤተ ክርስቲያንን ድል ነሺነትን የሠጠ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሲሆን አርዌ ብርቱ ደግሞ በፓትርያርኮች እጅ የሚያዘው "ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" የሚለውን ቃል የሚያስረዳ ያለ በደል ስለ እኛ ተሰቅሎ ያዳነንን ክርስቶስን የሚያሳይ ነው:: ከታች ያለው "አምላኬ ጌታዬም" የሚለው የሕንድ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያ የሆነው የቅዱስ ቶማስ ምስክርነት ቃል ነው:: (ዮሐ. 20:28
⛪️ የሶርያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አርማ

መስቀሉ በሞቱና በትንሣኤው ለቤተ ክርስቲያንን ድል ነሺነትን የሠጠ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል ሲሆን አርዌ ብርቱ ደግሞ በፓትርያርኮች እጅ የሚያዘው "ሙሴ በምድረ በዳ ዕባብን እንደሰቀለ ክርስቶስ ይሰቀል ዘንድ ይገባዋል" የሚለውን ቃል የሚያስረዳ ያለ በደል ስለ እኛ ተሰቅሎ ያዳነንን ክርስቶስን የሚያሳይ ነው::
ቁልፉ የአንጾኪያው የመጀመሪያ ፓትርያርክ ለሆነው ለቅዱስ ጴጥሮስ የተሠጠውን ሥልጣነ ክህነት የሚያሳይ ሲሆን ቁልፎቹ ሁለት መሆናቸው በጴጥሮስ ብቻ ያልተወሰነ መሆኑን ያስረዳል:: ሚዛኑ ፓትርያርኩ በፍትሕ ቤተ ክርስቲያንን እንዲያስተዳድሩ የተሾሙ እንደሆኑ የሚያሳይ ሲሆን ከሥር በዓረቢኛ የተጻፈው ደግሞ "የአንጾኪያና የመላው ምሥራቅ ፓትርያርክ" የሚል ነው::
⛪️ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አርማ እና ትርጉም
፩ የአርማ ቅርፅ እና ይዘት
፩ . መደቡ ነጭ
፪ . ዙሪያው የስንዴ ዛላ እና የወይን ዘለላ
፫ . ከላይ ከአናቱ ከአክሊሉ ፣ ከታች ከግርጌው መሃል ለመሃል ወጥቶ አናቱ ከአክሊሉ ስር የደረሰና መስቀል ያለበት አርዌ ብርት
፬ . በግራ ሆኖ በቀኝ እጁ አርዌ ብረት በግራ እጁ ዘንባባ የያዘ መልዐክ ፣ በቀኝ ሆኖ በግራ እጁ አርዌ ብረት በቀኝ እጁ ዘንባባ የያዘ መልአክ
፭ ከአርዌ ብርት ሥር "ነዋ ወንጌለ መንግሥት " ተብሎ የተጻፈበት መጽሐፍ ቅዱስ
፮ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሥር የ "ጸ" ፊደል ቅርጽ የሚመስል ሁለት ጫፎች ከመደቡ ወደ ውጭ የወጣ ሰበን
፯ የስንዴ ዘለላ እና የወይን ዘለላ በሚገናኙበት የዓለም ምስል ያለበት ይሆናል
፪ የአርማው ትርጉም
☞☞☞☞☞☞☞
ሀ / መደቡ ነጭ መሆኑ
ዘመነ ስጋዌ የምሕረት የደስታ የነፃነት ዘመን መሆኑን ያመላክታል
ለ / የአርማው ዙሪያ በስንዴ ዘለላ እና የወይን ዘለላ መሆኑ ምእመናን በቅዱስ ቁርባን አማካኝነት ከእግዚአብሔር ጋር አንድነት ፣ ስርየተ ኃጢአት የዘላለም ሕይወት የሚያገኙ መሆኑን
(ዮሐ ፮ ፥፶፫-፶፰ ማቴ ፳፮፥፳፮- ፳፱ መዝ ፬፥፯)
ሐ / በአርማው መሃል ቀጥ ብሎ የቆመ የአርዌ ብርት ምስል ከበላዩ ላይ መስቀል ከዚያም ከፍ ብሎ አክሊለ ክህነት መኖሩ ሕዝበ እስራኤል አርዌ ብርቱን ባዩ ጊዜ ከእባብ መርዝ እንደዳኑ ሁሉ መስቀል ላይ በተሰቀለው ጌታችን በአምላካችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ያመኑ ሁሉ ከዲያቢሎስ ምክንያት የመጣባቸው ፍዳ ኃጢአት የሚድኑ መሆናቸውን መስቀሉም የቤተ ክርስቲያን የድኅነት አርማ መሆኑን ያሳያል
( ዘኁ ፳፮፥፰ ዮሐ ፫ ፥፲፬ )
መ / አክሊሉ
ቅዱሳን በሰማያዊ መንግስት የሚቀዳጁት አክሊል ክብር እና ማኅተመ ጽድቅን ያመላክታል
(ዘፀ ፴፱፥፱ ፩ተሰ ፪ ፥፲፱ ፪ጢሞ ፬ ፥፲ ፩ ጴጥ ፭፥ ፲፬ ራዕይ ፪፥፲ : ፲፥፲፬ )
ሠ / ሁለት መላዕክት የአርዌ ብረት እና የዘንባባ ዝንጣፊ መያዛቸው
ዘንባባ በመንፈስ ቅዱስ የሚገኝ ደስታ ድኅነተ ነፍስን ያመላክታል:: ቅዱሳን መላዕክት የቤተ ክርስቲያን ጠባቂዎች እና የመልካም ዜና አብሣሪዎች መሆናቸውን ያሳያል የአርዌ ብርቱን ይዘው መቆማቸው ነገረ መስቀሉን አምኖና እምነቱን አጽንቶ ይዞ የሚኖር የዘላለም ድኅነት የሚያገኝ መሆኑን ያሳያል:: (መዝ ፺፥ ፲፩ ሉቃ ፲፫፥ ፮-፱ ዕብ ፩፥፲፬ )
ረ / በአርማ መሃል መጽሐፍ ቅዱስ ሆኖ በላዩ ላይ "ነዋ ወንጌለ መንግሥት" የሚል ጽሑፍ መኖሩ
የቤተ ክርስቲያን ሀይማኖት ቅኖና እና ትውፊት በመፅሐፍ ቅዱስ ትምህርት ላይ የተመሠረተ መሆኑን ያመላክታል ( ማቴ ፳፬ ፥ ፲፬ )
ሰ / የስንዴ ዛላና ዘለላ በተገናኙበት ቦታ የሚታይ ክብ ነገር ዓለምን የሚወክል ሲሆን ዓለም በክርስቶስ መዳኑን ያሳያል:: ( ዮሐ ፫፥ ፲፯ )
ማስታወሻ :- የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያንን አርማ ጃንደረባው ሚድያ ደረጃውን በጠበቀ ሁኔታ ሠርቶታል:: ዛሬ ምሽት ከሰርክ ጸሎት በኋላ ይፋ ይሆናል::

የቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናት ፍሬ
በትውልድ እንግሊዛዊው እና ለብዙ ዘመናት የፕሮቴስታንቲዝም አንዱ ቅርንጫፍ በሆነው የአንግሊካን እምነት ውስጥ የቆየው ዕውቁ ሊቅ ሰባስትያን ብሮክ ቅዳሜ ግንቦት 18 (May 25) በሶርያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጥምቀተ ክርስትና ተፈጽሞለት በቅብዓ ሜሮን ከብሮ ዋለ።
ሰባስትያን በኦርቶዶክሱ ዓለም በሶርያ የሚገኙ ጥንታዊ የሆኑ የነ ቅዱስ ኤፍሬም ድርሳናትን ከጥልቅ ሐተታዎች ጋር በመተርጎም እና የሶርያን ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ ሕይወት በማጥናት በሰፊው ይታወቃል። በዚህ ዙሪያ የሠራቸው እና ያሳተማቸው የጥናት እንዲሁም ትርጉም መጻሕፍት ዝርዝር ብቻ ወደ ሠላሳ ገጽ ይሆናሉ። የሶርያም ቤተ ክርስቲያንም ለዚህ ድካሙ የቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ሜዳልያ (Medal of St. Ephrem the Syrian) የተባለውን በክብር አበርክታለታለች።
እነዚያን ወርቅ የሆኑ አጥንት ድረስ ዘልቀው የሚወጉ የማር ኤፍሬምን ድርሳናት ከውጭ (በሃይማኖት) ሆኖ መተርጎሙ ሁሌ ያሳዝነኝ ነበር። ታምሞ ግን የሚድንበትን መድኃኒት ተሸክሞ እንደሚቸገር ምስኪን ሰው አድርጌም አስበው ነበር። ድርሳናቱ መቼ ነው ወደሚድንበት መርከብ እየመሩ የሚያስገቡት ብዬ ብዙ ጊዜ እጠይቅ ነበር።
ያለፈው ቅዳሜ ግን ይህን ኀዘን የሚሽር የምሥራች ሰማሁ። ለካስ ቅዱሱ የቀጠረለት ቀን ነበር?! ይኸው የኤፍሬም ቀለም የበላውን (ያቃጠለውን) ምሁር ከኦርቶዶክሳዊው ካህን ስር በትሕትና በርከክ ብሎ አየሁት።
ይህ መመለስ የቅዱሱ ምልጃ እና በቅዱስ ኤፍሬም ድርሳን ያለቀሱ የብዙ የዋሃን ምእመናን እንባ ውጤት ነው።
የአበው ድርሳን አሁንም በሥራ ላይ ነው!!!
ዲያቆን አቤል ካሣሁን

"የክርስቶስ ቤዛነት ይህ ነው፦ እርሱ ስለተሸከማቸው ዘግናኝ ሕማሞች እና ኃጢኣቶች እስካሁን ድረስ ያለማቋረጥ ይናገራል። ኃጢኣት የማያውቀውን እርሱን እግዚአብሔር አብ ስለእኛ ሲል 'ኃጢኣት እንዲሆን' አደረገው። አመንዝራው፣ ስድ ሆኖ የሚበድለው፣ ቆሻሻ በሆኑ ተግባራት አረንቋ ውስጥ የሚዛቅጠው እና ኃፍረት አልባ በሆኑ ተግባራት የሚበላሸው ሁሉ ከክርስቶስ ሲሸሽ ድምጹ በኋላው ይከተለዋል። ይኸውም 'የተወደድህ ልጅ ሆይ፥ ና! ኃጢኣቶችህ ከእኔ ጋር
ናቸው፤' እያለ የሚጣራ የእግዚአብሔር ልጅ ደም ነው! ገና የሠራሃቸው ዕለት ነው በምልዓት የተሸከምኳቸው። ካሣውን ከፍያለሁ፦ ሐፍረት ተጭኖብኛል፤ ተገርፌያለሁ፤ ደቅቄያለሁ፤ ተሰቅያለሁ፤ እንዲሁም መርገምን ተሸክሜያለሁ። ለአንተ የይቅርታ እና የንጽሕና ተግባራትን እንዲሁም ይገባኛል የምትልበትን ጸጋ አዘጋጅቼልሃለሁ። ና! ለአንተ መከራ የተቀበልኩትን ያህል በአንተ ደስ ይለኝ ዘንድ ና! የመዳንን ዘውድ እደፋልህ ዘንድ፣ ፍቅሬን እና መንፈስ ቅዱስን
በአንተ ላይ አፈስስ ዘንድ፣ እንዲህ አድርጌ ወደ አባቴ አቀርብህ ዘንድ ና! አንተ ከበጎቼ ሁሉ እጅግ ውዱ ነህ፤ እኔ ደሜን እስከመክፈል ደርሼ ከፍ ያለ ዋጋ ሰጥቼሃለሁና።"
***
የክርስቶስ ስሞች፣ ገጽ 135-36።

----------------- ምእመናን ግን !!! አንድ ነገር ልብ -------- አድርጉ ።
ምእመናን ኾይ!! እኛ ዲያቆናቶቻችሁ እና እኛ ካህናቶቻችሁ እኛ መምህሮቻችሁ ቁራሽ ሰጥታችሁ ፣ ድግስ አካፍላችሁ አሥራት በኲራት ሰጥታችሁ እንዳስታማራችሁን እናውቅላችኋለን። አኹንም ሕልውናችን ከፈጣሪ በታች በእናንተ ድጋፍ ነው። ነገር ግን ይህንን የእኛን ንትር ክ አይታችሁ ከቤታችሁ ስንዝርም ኾነ ሴንቲ ሜትር ወደ ኋላ አትበሉ ።ቤታችሁ እማ ቅድስት ናት ክብርት ናት ንጽሕት ናት ብጽፅት ናት ። የጸጋ ግምጃ ቤት የክብር ሙዳይ ናት ፣ ኹልጊዜም ይህንን ታሪክ አስታውሱ
በዐለመ መላእክት በቅዱሳኑ መሀከል ዲያብሎስና ሠራዊቱ ፣ በዕብራውያን ሕብረት መካከል ሰለጵአድና አካን፣ በጌታ ጉባኤ መሀከል ይሁዳ፣በሐዋርያት ጉባኤ ግኖስቲኮች፣ በኤልሳእ ጉባኤ ግያዝ፥ በጳውሎስ ጉባኤ ዴማስ ።፤ በ፫፻ጉባኤ መሀከል አርዮስና ግብር አበሮቹ በ፪፻ ሊቃውንት መሀከል ንስጥሮስና ግብር አበሮቹ ፣ በ፩፻፶ ሊቃውንት መሀከል መቅዶንዮስ ግብር አበሮቹ ፤ እስከ ዕለተ ምጽአት በሚነሱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሀከል እስከ ዕለተ ምጽአት የሚነሱ እኩያን መምህራን ሰባክያን ኤጲስቆጶሳት ጳጳሳት እንደሚነሱ መረዳት አለባችሁ። ይሁዳን ብቻ አይታችሁ ተስፋ አትቁረጡ ከይሁዳ አጠገብ ተስፋ የምታደርጉት ክርስቶስና ቅዱሳን ሐዋርያት አሉና ። አርዮስን ብቻ አይታችሁ የርሱን ዜና ሰምታችሁ ተስፋ አትቁረጡ ።
ተስፋ የማንቆርጥባቸው አትናቴዎስና እለ እስክንድሮስ አሉንና ። መቅዶንዮስን ብቻ አይታችሁ ተስፋ አትቁረጡ ተስፋችሁን የሚያጸና ጢሞቴዎስ ዘአልቦ ጥሪትም አለላችሁና። አይዟችሁ ምእመናን እናንተን ያለ አንድ ቄርሎስ፣ ያለ አንድ አትናቴዎስ ፣ ያለ አንድ እለ እስንድሮስማ ያለ አንድ ተክለ ሃይማኖት አይተዋችሁም ። በእውነቱ አይታዋችሁም እናት ልጇን ሙሽራ ጌጧን ትረሳለችን????
ምእመናን ኾይ! ታድያ የኛ ጌታስ እናንተን ይረሳልን?? ልጁ ዳቦ የሚለምነው ፣ አባቱ ድንጋይ የሚያጎርሰው ማን ነው? ይልቁንስ የዳቦውን ልብ ልቡን አውጥቶ ያበላው የለምን? ልጁ እንቁላል የሚለምነው አባቱ እምቧይ የሚሰጠው ማን ነው? አስኳል አስኳሉን አውጥቶ ይሰጠው የለምን???
ታድያ የእናንተ የሥጋው አባት እንደዚህ የሚራራ ከኾነ አባታችሁ እግዚአብሔርማ እንደምን አይራራልችሁ ???
ምእመናን ኾይ!! ይህ የነበረ ያለ የሚኖር ነው። ይህንን ሰምታችሁ በካህኑ እጅ ከመቀበል በመ/ሩ አንደበት ከመሰበክ ፣ በጳጳሱ እጅ ከመባረክ ወደ ኋላ አትበሉ ።
ገንዳ ለራሱ እየደረቀ በጎችን ግን ያጠጣል።ሻማም ለራሱ እየቀለጠ ለሌላው ግን ያበራል። ካህናትም እንደደዚሁ ናቸው ነን ። ሻማውን ትታችሁ ብርሃኑን ተጠቀሙ ።ገንዳውን ሳይኾን ውሃውን ገንዘብ አድርጉ። ጌታ በወንጌል እንዲህ ብሏል ። ጸሐፍትና ፈሪሳውያን በጌታ ወንበር ተቀምጠዋል።ስለዚህ ያዘዟችሁን ኹሉ አድርጉ ጠብቁትም።ነገር ግን እየተናገሩ አያደርጉትምና እንደ ሥራቸው አታድርጉ። ከባድና አስቸጋሪ ሸክም ተብትበው በሰው ትከሻ ይጭናሉ። እነርሱ ግን በጣታቸው ስንኳን ሊነኩት አይወዱም ማቴ ፳፫ ፥ ፪ ከላይ የተቀሰውን ጥቅስ ኹላችሁ መለስ ጊዜ አስቡት። ቤ/ክርስቲያንን በግለሰቦች መለካት መመጠን ታላቁ ስህተት ነው። ቤ/ክርስያናችሁ ዐለቷ ክርስቶስ ነው፤ የትምህርት የሃይማኖት ዐለቷ ቅ/ጴጥሮስና ሐዋርያት ናቸው። እና ነፋሳት በነፈሱ ቁጥ ማዕበላት በወረዱ ቁጥር ጎርፎች በጎረፉ ቁጠር አትነቃነቁ ። እኛ እናሻግራለን እንጅ እኛ እናሻግራለን እንጅ አንሻገርም የተባለውን ምሳሌ አልሰማችሁምን?? ። ።።።።።።።።።።።።።።።።።።