ጾም ሙሽሪትን ትመስላለች፤ ሙሽሪትን በሠርግ አዳራሽ ኾነው የሚቀበሏት ሰዎች ቤቱን ያስጌጡታል፤ ይሸልሙታል፡፡ ወደ ሠርጉ አዳራሽ የሚገባውን ሰው የሠርግ ልብስ ለብሶ እንደኾነ፣ የቆሸሸ እንዳልኾነ አይተው ያስገቡታል፡፡ እኛም እንዲኽ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡
ልቡናችንን በማንጻት፣ ልል ዘሊል ከመኾን በመራቅ፣ የክፋት እርሾን በማስወገድ፣ ከጾም ጋር አብረው የሚመጡትን የሚያጅቧትን መልካም ምግባራትንም ለመቀበል የልቡናችንን ውሳጤ በመክፈት የምግባር እናት፣ የማስተዋል እንዲኹሉም ለሌሎች ምግባራት ኹሉ ንግሥት የምትኾን ጾምን ልንቀበላት ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ይኽን ያደረግን እንደኾነ ታላቅ ሐሴት እናደርጋለን፤ ርሷም ቁስለ ነፍሳችንን ትፈውስልናለች፡፡
በሌላ አገላለጽ ብነግራችኁ ሐኪሞች በአንድ ታማሚ ሰውነት ውስጥ ያለውን ቆሻሻ፣ መርዘኛ ፈሳሽን ማስገድ ሲፈልጉ መጀመሪያ የሚያደርጉት ነገር ቢኖር ታማሚው ምግብ ከመውሰድ እንዲቈጠብ ነው፡፡ ታማሚው ለጊዜው ምግብን ከመብላት ካልተከለከለ ሓኪሞቹ የሚሰጡት መድኃኒት እንደተፈለገው ውጤት አይሰጥም፡፡ እኛም ቁስለ ነፍስ ቁስለ ሥጋ የምትፈውሰውን ጾም ስንቀበላት ከዚኽ በላይ ልንኾን ይገባናል ብዬ እነግራችኋለኹ፡፡ ድኅነተ ሥጋ ድኅነተ ነፍስን የምንሻ ከኾነ ልቡናችንን ንጹሕና ንቁ በማድረግ ልንወስዳት ይገባናል፡፡ እንዲኽ ካልኾነ ግን ከጥቅሟ ይልቅ ጉዳቷ ያመዝናል፡፡
#ቅዱስ_ዮሐንስ_አፈወርቅ
ጾመ ነነዌ ጥር 29/2015 ዓ.ም
(feb, 6/2023 G.C) ይገባል፡፡

🏴 የቅዱስ ሲኖዶስ መልእክት
🖤 በሙሽራው በክርስቶስ የደረሰውን መከራ ዐይታ ፀሐይ ለ፫ ሠዓት በምድር ላይ እንደጨለመች የሙሽሪቷን የቤተክርስቲያንን መከራ ያዩ ምእመናን በምድራቸው ላይ ለሦስት ቀን ይጨልማሉ!
【https://www.youtube.com/live/hv_59sOTrmg?feature=share】
"ሰብአ ነነዌ ጸዊሞሙ ተማኅሊሎሙ ድኅኑ እሞቶሙ…
አድኅነነ እግዚኦ አምላክነ ዘአድኃንካ ለነነዌ ሀገር በትንብልና ሣህልከ"
ጾመ ነነዌንና በወቅቱ የደረሰብንን ታላቅ መከራ ምክንያት በማድረግ ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፩ ለ፫ ቀናት ( ፳፻፲፭ ዓ.ም.) በዓለም ያሉ ኢትዮጵያውያን ምእመናን ሁሉ ጥቁር ልብስ ብቻ በመልበስ ጾም ጸሎትና ምኅላ በመያዝ በዐውደ ምሕረት ተገኝተን ሁሉን ማድረግ ወደሚችል አምላክ ወደ እግዚአብሔር እንድናለቅስ ጥሪ ተላልፏል።
☞ ጥቁር የመከራ ምልክት ነው ⚫!
መከራ የወደቀባቸው ሰዎች ሐዘን ደርሶብናል ሲሉ ጥቁር ይለብሳሉ።
እኛም በደረሰብን መከራ በማዘናችን አምላካችን ከልባችን ሐዘን አርቆ ከፊታችንሸእንባ አድርቆ ወደእኛ የምሕረት ፊቱን እንዲመልስልን በንሰሐ ወደእርሱ ጥቁር ለብሰን እንማጸናለን።
☞ ጥቁር የእውቀት ምልክት ነው 🎓!
ከእውቀት ማዕድ የተሳተፉ ምሩቃን ‘አዋቆች’ ነን ሲሉ ጥቁር ይለብሳሉ።
እኛም የእውቀት ባለቤት እግዚአብሔርን የምንከተል መንፈሳውያን ሁላችን ሁሉን የምንመረምር በማንም የማንመረመር ነን ስንል ጥቁር ለብሰን የክርስትናውን ክብር እንገልጣለን።
☞ ጥቁር የእውነት ምልክት ⚖️ !
ዳኞች ፍትሕ አድራጊዎች ነን በእውነት እንፈርዳለን ሲሉ ጥቁር ይለብሳሉ።
እኛም በምድራውያኑ ዳኞች ሚዛን ሲዛባ ፍርድ ሲጎድል ደካማው ሲበደል እኛን ግን የሚመራን እውነተኛው ዳኛ እንዳለ በማመን እግዚአብሔር በሚመራን የእውነት መንገድ የምንኖር እውነተኞች ነን ስንል ጥቁር ለብሰን የእውነት ምስክሮች ለመሆን የምንተጋ መሆናችንን እናሳያለን።
▪️ "Those are called the likes of angels who, clothed in the black pallium, have cast away the world and all worldly things, live in celibacy and seek to be like Christ."【Blessed Jerome of Stridon】
↳ እነዚያ ጥቁር ሞጣሕት ለብሰው ዓለምንና በዓለም ያለውን ሁሉ ንቀው የጣሉ ክርስቶስን ለመምሰል የሚጋደሉ በመላእክት ሕይወት የተገለጡ ምድራውያን መላእክት ናቸው ! 【የተመሰገነ ይሩማሲስ】
የገዳማውያን ኅብረት በላኩልን መልእክት ደግሞ ይህ ሁሉ የመጣው በእኛው ጾም ጸሎትና ቅድስናን ችላ በማለታችን ስለሆነ እስከ ዓርብ (ከጥር ፳፱ እስከ የካቲት ፫) ድረስ
◾▪️በየዕለቱ ፵፩ ስግደት እንድንሰግድ
◾▪️እስከ ፱ ሠዓት እንድንጾም
◾▪️ዓርብን በአክፍሎት እንድናሳልፍ
◾▪️ጠዋት ለኪዳን ቀን ለቅዳሴ ሠርክ ለምሕላ ቤተክርስቲያን እንድንገኝ
◾ ▪️በ3:00 ፣በ6:00 ፣ በ9:00 ባለንበት ፩ ሰላም ለኪ እና አቡነ ዘበሰማያት በማድረስ አምላካችንን እንድንማጸነው ጥሪ ተላልፏል።
"ድንግል ሆይ ከዓይኖችሽ የፈሰሰውንና በተወደደ ልጅሽ ፊት ወረደውን መሪር እንባ አሳስቢ" 【ቅዳሴ ማርያም】

YouTube
ከቅዱስ ሲኖዶስ የተላለፈ መልእክት
Watch "MK TV || " ኑ! ለቅሶ እንድረስ "|| ገጣሚት ምሥራቅ ተረፈ" on YouTube
https://youtu.be/FEMGkYsesdQ
https://youtu.be/FEMGkYsesdQ
YouTube
MK TV || " ኑ! ለቅሶ እንድረስ "|| ገጣሚት ምሥራቅ ተረፈ
Subscribe and share https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......
https://www.youtube.com/user/EOTCMK?s......
#MKTV #MahibereKidusan #EOTCMK

🖤🖤🖤 ኑ ለቅሶ እንድረስ 🖤🖤🖤
በገጣሚት ምሥራቅ ተፈራ
ያሳደግችኝ ደብር ተቀመጠች አሉኝ ለቅሶ
ውለታዋ ተዘንግቶ ክብር ማዕረጓ ተድሶ
በትዕቢት ተረማመደ ቅጥር ግቢዋን ጥሶ
ማር ይዘንባል ማር (×3) ነበር ዜማ ቅኝቷ
ስጋጃው በደም ራሰ ጥይት ዘነበ ከቤቷ
ሰንደቅ አላማ ነበር የዘለ ዕለት ውበቷ
ኑ እንድረሳት ለቅሶ ማቅ ለብሷል ጉልላቷ
እንዳትካስ ለብድሯ ወርቀዘቦ ተንቆጥቁጣ
በምን ቃል ይገለፃል በምን ቃል ይገለፃል
በውን ቆሞ እንደማየት ባዳፋ ጫማ ተረግጣ
ቅጥሯን ለተዳፈረ ለናቃት ይስጠው መጥኔ
የአለምን ሀይል ተመክቶ የታበየ ለኩነኔ
አለም በቃኝ ብለው ምለው ያፀኗት በምናኔ
ኑ እንላቀስ ምዕመን ያልሰማ ይስማ መርዶ
ደብራችን አንብታለች መጋረጃዋ ተቀዶ
ደብረ ሀይል ቅዱስ ራጉኤል የልጅነቴ
በመልዐክ ሀይል ምልጃ የፀናችልኝ ህይወቴ
የአባ መሸ ኪላራይሶ የገብረ ኪዳን ሰንበቴ
የአዝኖና መጠጊያ የነብስ ስጋ ቋቴ
የሀይማኖት መሰረቴ
አፍ መፍቻ ትምህርት ቤቴ
እስኪ ተጠየቁ እስኪ ልጠይቃችሁ
እስኪ ተጠየቁ
መስቀልና እስኬማ ካባ ደርባችሁ
በቀን በአደባባይ ነብስ የቀጠፋችሁ
እንደምን ይቀደሳል የምዕመን ደም ተራምዶ
እንዴትስ ይታረቃል መንፈስ በግፍ ላይ ወርዶ
በምድር የፈታችሁት በሰማይ እንዲፈታ
ግብራችሁን ስታችሁ በማስተስረይ ፈንታ
ባረካችሁን በወኔ ተሳለምን በቃታ
ፊደል ቀራጭ ስንዱዬ እኔን ልጅሽ ፊደል ጠፋኝ
ሀ ብለሽ ያስቆጠርሽው ሆ ብሎ ፊትሽ ደፋኝ
በፀአዳ ግምጃሽ ፈንታ ክልሽን ሳየው ከፋኝ
ህዝቤ በገዛ ሀገሩ ቢገፋ ቢያጎብጠው የኑሮ ቀንበር
የፀለየላት ኢትዮጵያ እንዳትፈርስበት ሀገር
ወዝ የራቀው ገፁን በውሀ እየወለወለ
ረሀብ ጥማቱን ችሎ በደጇ የተጠለለ
መስዋዕቱን ሊሰዋ በገናውን የደረደረ
ከጌታው ጋር ተቃጥሮ ተመስገን ሊለው ነበረ
ደረቱን ተቀረደደ በድኑ ተሽቀነጠረ
ይፅናናበት ማልቀሻችን ምናለን ከደብሩ ሌላ
እንፅናናበት ማልቀሻችን ምን አለ ከደብሩ ሌላ
ድርሳን አላቃጠ መንገድ አልዘጋ ኬላ
ጥበብ እየመገበች ኮትኩታው ነበር ከልላ
ለምጣዱ ሲባል ትለፍ ብለናል አይጧ
ሰስተንላት ነገር ፈርተን ይሄ ቀን እንዳይመጣ
ይልቅ ይልቅ ግፍህን ታጠብ በደልህን ተለቃለቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
ምህረት ደጇ ሳይዘጋ የፈሰሰው ደም ሳይደርቅ
የተማመንከው ቢደድር አስተምሮትህ ብረቅም
ከሺህ አመታት ዶሴ ከአባቶቻችን አይልቅም
ብንጠፋ ብናጠፋ ከደጀ ሰላሟ ብንርቅም
የተስፋ ርስታችን ናት ደብራችንን አንለቅም
እኔም አንድ ፓትርያርክ አንድ ሲኖዶስ
ከአንዲት ቤተስኪያን ወድያ
አቻ ክብር አላውቅም ልጄም በካህን እንጂ በአቶ አይጠመቅም ይኸው ነው !!!

የጵጵስና ሢመት የሚጠይቀው ቅድመ ሁኔታ
ክፍል ፩
በዲ/ን አሻግሬ አምጤ
++++++++++++++++++++++++++++++++++++++++
ጵጵስና መንፈሳዊ አባትነት በመሆኑ ለዚህ ሢመት የሚታጩ መነኰሳት የሚመረጡት በጥንቃቄ ነው። በጥንቃቄ መመረጥ የሚያስፈልገውም ኃላፊነቱ ሰማያዊ፣ ሹመቱ አምላካዊ በመሆኑ ነው። መነኰሳትን ለመንፈሳዊው ሾመት የሚያጩዋቸው አባቶች ቢሆኑም ሢመቱ አምላካዊ በመሆኑ የሚመረጡት ሰዎች አምላክን የሚያስደስቱ፣ ሰዎችን ወደ አምላክ ለማቅረብ የማይታክቱ መሆን አለመሆናቸው ከግንዛቤ ውስጥ መግባት ይኖርበታል። ጥንቃቄ የሚጠይቀውም ኃላፊነቱ የሰውን ሕይወት ለመጠበቅ የሚሰጥ ሹመት በመሆኑ ነው። በኒቂያ የተሰበሰቡ ቅዱሳን አባቶቻችን የእስክንድርያ ቤተ ክርስቲያን ፓትርያርክ ተፍጻሜተ ሰማዕት ቅዱስ ጴጥሮስ በሕይወት እያለ እና መንበሩን ምንም አይነት ችግር ሳይገጥመው መላጥያኖስ የተባለው ግለሰብ በራሱ ፍላጎት ተነሣሥቶ ጳጳሳትን በመሾሙ በአገር አቀፍ ጉባኤ ተወግዞ የነበረ ቢሆንም ውግዘቱን በመተላለፍ በማን አለብኝነት የቤተ ክርስቲያንን ሥርዓት እየጣሰ በአፈንጋጭነቱ ቀጥሎ ስለነበር የኒቅያ ጎባኤ ለጉዳዩ ትኩረት በመስጠት ውሳኔ አስተላልፏል።
ጉባኤው ያስተላለፈው ውሳኔ “መላጥያኖስና በእርሱ የተሾሙ ጳጳሳትና ካህናት ቤተ ክርስቲያንን የማወክና ሥርዓትን የመጣስ ተግባራቸው ምሕረት የማይገባው ቢሆንም ጉባኤው ቅጣቱን በማቅለል መላጥዮስ የጵጵስና ስምና ክብር ብቻ እንዲኖረው፣ በሀገረ ስብከቱ ከተማ ብቻ ተወስኖ እንዲኖር እንጂ በሌሎች ሰበካዎች እንዳይገኝ፣ ጳጳሳትንም መርጦ እንዳይሾም ወስኗል። በእስክንድርያው ሊቀ ጳጳሳት የተሾሙት ኤጲስ ቆጶሳት በየሀገረ ስብከታቸው እያሉ በመላጥዮስ ተሹመናል የሚሉት ተደርበው ማወካቸው ከሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን ያፈነገጠ ነው። በመላጥዮስ የተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳትን በተመለከተ ደግሞ ትሕትናቸውና ግብረ ገብነታቸው ታይቶ በሕጋዊ ሢመት አንዲሾሙ አገልግሎታቸውም በቅዱስ እለ እስክንድሮስ ሥር እንዲሆን” (NPNF,second serious, vol. 3, 2012, P,46)።
አስቀድሜ በጠቀስኩት የኒቅያ ውሳኔ ብዙ ቁም ነገሮች የተካተቱበት መሆኑን አንባብያን የሚረዱት ነው። የመጀመሪያው ጉዳይ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ትዕግሥትና ሆደ ሰፊነት በጉልህ የሚያሳይ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑ ነው። የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን ሆደ ሰፊነት የሚገልጠውም “መላጥዮስ ምሕረት የማይገባው ቢሆንም ቅጣቱን በማቅለል የጵጵስና ስምና ክብር ብቻ እንዲኖረው” መፍቀዱኑ ነው። አንባብያን ልብ ልንለው የሚገባው መላጥዮስ ምሕረት የማይገባው ቢሆንም ቅድስት ቤተ ክርስቲያን የአንድ ሰው ነፍስ ስለሚገዳትና በውግዘት ቆርጦ ከመጣል ይልቅ ምሕረት በማድረግ ዕድል መስጠት ተገቢ መሆኑን ስለምትገንዘብ አባቶች ያሳዩት ርኅራኄ የሚያስገርም ነው። ምድራዊ ነገሥታትም እንዲህ ያለውን ሆደ ሰፊነት የሚያሳዩ ቢሆኑ ኖሮ ጦርነትና መገዳደል ተወግዶ በዓለም ላይ ሰላም በሰፈነ ነበር።
አባቶች ብዙ ነገሮችን ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት ለመላጥዮስ ምሕረት ቢያደርጉለትም መላጥዮስ ወደ ጥፋት ተመልሶ ቤተ ክርስቲያንን እንዳያውክ እግድ አስቀምጠውበታል። ለጥፋት ያላት ከተማ ነጋሪት ቢጎሰምባት አትሰማ እንደተባለው እርሱ ግን በጥፋቱ ቀጥሎ ከአርዮሳውያን ጋር የጥፋት ኅብረት እየፈጠረ ቤተ ክርስቲያንን ሲወጋ ቅዱስ አትናቴዎስንም ሲያሳድድ ኖሯል። አባቶቻችን ያስቀመጡት እግድም መላጥዮስ በሀገረ ስብከቱ ከተማ ብቻ ተወስኖ እንዲኖርና በሌሎች ሰበካዎች እንዳይገኝ፣ ኤጲስ ቆጶሳትንም እንዳይመርጥ እና እንዳይሾም ማድረጋቸው ነው። ከዚህ ውሳኔ መረዳት የሚቻለው መላጥዮስ ይዞ የቀረው የጵጵስናውን ስም ብቻ መሆኑን ነው። እንዲህ ያለው ውሳኔ ልብ ላለውና ራሱ የፈጸመውን ስሕተት ለመመርመር ለሚጣጣር ክርስቲያን የንስሓ ጊዜ የሚሰጥ፣ ወደ አሳዘነው አምላኩ የመመለሻ ዕድል የሚያጎናጽፍ፣ የበደላትን ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን የመታረቂያ ጊዜ ማግኛ ነው።
በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ትውፊት የሚታወቀው አባቶች በሌላቸው ሥልጣን በአባቶች መንበር ጣልቃ በመግባት መነኰሳትን መርጠው ኤጲስ ቆጶስነት መሾም ሳይሆን ኃላፊነት መቀበል ይቻላቸዋል ተብለው ሲመለሡ እንኳ አይቻለንም ሲሉ ነው። ንጽሕናቸው ታይቶ መንጋውን ለመምራት ይችላሉ ተብሎ ለጵጵስና መዓርግ ሲታጩ በትሕትና የማይቻላቸው መሆናቸውን በመናገር እንዲተዋቸው ይማጸናሉ። አባቶች ከሹመት የሚሸሹት አንድም በትሕትና፣ ሁለትም ኃላፊነቱ በሌሎች ኃጢአት የሚያስጠይቅ በመሆኑ በራሳችን ኃጢአት ብቻ እንጠየቅ እንጂ ለምን በጥፋት ላይ ጥፋት በመፈጸም አምላካችንን እናሳዝናለን በማለት ነው።
ሌላው ከዚህ ጥቅስ የምንረዳው ነጥብ በመላጥዮስ የተሾሙትን ጳጳሳት በተመለከተ ትሕትናቸውና ግብረ ገብነታቸው ታይቶ በሕጋዊው ሊቀ ጳጳስ ኤጲስ ቆጶስነት ይሾሙ ዘንድ፣ አገልግሎታቸውም በእለ እስክንድሮስ ሥር ይከናወን ዘንድ መወሰኑ ነው። እንዲህ ያለውን ቤተ ክርስቲያን የምትሰጠውን መልካም ዕድል አጣመው በመተርጎም ሥጋዊ ፍላጎት ያላቸው ግለሰቦች ደም ለመፍሰስ ምክንያት የሆኑት አካላት መካተት እንደማይገባቸው የሚያሳውቀው ትሕትናቸውና ግብረ ገብነታቸው ታይቶ የሚለው ቅድመ ሁኔታ ነው። አንድ ሊቀ ጳጳስ በሚመደብበት ሀገረ ስብከት ለሚገኘው ለጠቅላላው ቤተ ክርስቲያን መንፈሳዊ አባት በመሆኑ (፳፻፱ ዓ.ም የተሻሻለው ቃለ ዐዋዲ፣፹፪ ) ለአባትነት ሲታጭ በመልካም አርአያነቱ የሚታወቅ እንጂ እጁ በደም የተነከረ፣ መጣልን የሚባል እንጂ መጣብን የማይባል ሊሆን ስለሚገባው ነው። ነቀፋ ያለበት ግለሰብ አባት ተብሎ በአንድ ሀገረ ስብከት ቢመደብ የሀገረ ስብከቱ ምእመናን እንደ አባት ሊቀበሉት ቀርቶ በዓይናቸው ማየትና እርሱ በሚገኝበት ቤተ ክርስቲያን ተገኝተው መንፈሳዊ አገልግሎት ማግኘት እንደማፈልጉ መረዳት ይገባል። ሰው ለማስደሰት ወይም ቍጥር ለመሙላት መንፈሳዊነት የሌላቸውንና የሰው ልጅ ድኅነት ግድ የማይሰጣቸውን ግለሰቦች መርጦ መመደብ ከጥቅሙ ጉዳቱ እንደሚያመዝን መታወቅ ይኖርበታል።
አባቶች እንዲህ ያለውን ቅድመ ሁኔታ ያካተቱት ምንም እንኳ ኢቀኖናዊ በሆነ ሢመት ተካትተው የነበረ ቢሆን ከሰው ልጅ ስሕተት አይጠፋምና ምግባር ትሩፋታቸው ለሌሎች የሚተርፍ፣ መንጋውን ለመበተን ሳይሆን ለመጠበቅ ትጋት ያላቸው አባቶች ካሉ ዕድሉ እንዳያልፋቸው የተከሠተውን ችግር ምክንያት አድርጎ በሕጋዊው ሢመት ቢታለፉ ምእመናን ሊያገኙት ከሚገባው መንፈሳዊ አገልግሎት እንዳይቀርባቸው ነው። ልብ ሊባል የሚገባው የኒቅያ ጉባኤ እንዲህ ያለውን ውሳኔ ያስተላለፈው ቤተ ክርስቲያንን እና ምእመኖቿን የሚጠቅሙ ሰዎች ቀርተው መንጋውን ለማገልገል ዳተኛ የሆኑት ግለሰቦች ተሾመው ቤተ ክርስቲያን እንዳትታወክ እንጂ ተሿሚዎችን ለማስደሰት አይደለም።
ይቆየን
ምንጭ:ማህበረ ቅዱሳን

🟢👉[ድራማ_ለመስራት_አንመጣም]🟢🟢👉_ምክረ_አበው_ለተጠየቁት_ጥያቄዎች_መልስ_ሙሉ_ክፍል(128k)
<unknown>
♦ምክረ አበው
®በዲ/ን ቴዎድሮስ በለጠ
&እና
@መጋቢ ሃዲስ ነቃወጥበብ
https://www.tgoop.com/atronss
#ለመምህሮቻችን ቃለ ህይወት ያሰማልን
✍የሰዓቱ መርዘም አትፍሩት ከልባችሁ አድምጡ እንኳን 2:00 ሰዓት 2ዓመት ተከታታይ ፊልም አይተናል! ምንፈልገውን ቆርጠን ሳይሆን ሚያስፈልገንን ለሕይወት ለድህነት ስንቅ ብለን እናዳምጥ

Forwarded from 📚👳♂🌼ኦርቶዶክሳዊ ሕይወት🌼👳♂📚 (ማኔ ቴቄል ፋሪስ)
YouTube
"እርሷ ብቻናት" ተሰምቶ የማይጠገብ ዝማሬ በዘማሪ ግዛቸው ሹካ Subscrbers🤏🔔 Like👍 sher⤵️ በማድረግ ናታኒም ቲዩብ ቤተሰብ ይሁኑ!!
#ethiopian_orthodox_tewahedo
#ethiopian_orthodox_tewahedo#henok_haile #ቴቄል #henok_haile ቅድስት ቤተ #ክርስቲያናችን,Ethiopian Orthodox
tewahedo,eotc tv,zehabesha news,ethiopian orthodox sibket,orthodox mezmur,ethiopian news,mehreteab asefa,ebstv worldwide…

አትሮንስ ዘተዋህዶ-atronss zethewahdo
Photo
መስፈርት አብጁ
በህይወት ዘመናችሁ በየጊዜው ብዙ ነገሮች ተራቸውን ጠብቀው ወደ ህይወታችሁ ይመጣሉ ፤ እነዚ ነገሮች ግን እናንተ ጋር መጥተው ለመኖር አንድ መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፤ መስፈርቱም የመጡት ነገሮች እናንተ ጋር ለመቆየት በእናንተና በክርስቶስ መካከል ያለውን ህብረት የማይረብሹና የማያቀዘቅዙ መሆን አለባቸው፤ ካለዚያ ግን ወደ ህይወታችሁ የመጡት ነገሮች ምንም ያህል መልካም ቢሆኑም ከእናንተ ጋር ግን እንዲቆዩ አትፍቀዱላቸው።
ወዳጆቼ በየጊዜው ወደናንተ የሚመጡ ብዙ ነገሮች ይኖራሉ፤ ለምሳሌ ጓደኛ፣ ገንዘብ፣ ዝና ፣ክብር፣ ሀብት ፣ማግኘት ፣ማጣት ፣ጭንቀት ፣ሀዘን ብቸኝነት ፣ተስፍ መቁረጥ ፣ብቻ ብዙ ነገሮች ጊዜያቸውን ጠብቀው ይመጣሉ፤ የሚመጡት ነገሮች ግን በእናንተና በክርስቶስ መካከል ያለውን ህብረት የሚረብሹ ከሆኑ ፈጥናቹ ከህይወታቹ አርቋቸው፤ ካልሆነ ግን በጊዜ ብዛት የምቶዱትን አምላክ ከልባቹ ውስጥ የማውጣት አቅም ያገኛሉ።