የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ጥናትና ምርምር መጽሔት ስራዎች pinned «" ጾምን እንጹም ጓደኞቻችንን #እናፍቅር እርስ በርሳችንም #እንፋቀር " ቅዱስ ያሬድ»
++++++#ከሰኞ_ወዳሴ_አምላክ#++++++
"የተባረኩ ደቀ መዛሙርትህን ዐይኖች እንደ ከፈትህ፣ የተቀደሱ መጻሕፍትንም እንዳወቁ፣ አምላካዊ የኾነ የቃሉን ትርጒምም እንደ ተረዱ ወደምታስደንቅና አምላካዊ ወደ ኾነ ዕውቀትም እንደ ተመለሱ። አቤቱ የተቀደሱ መጻሕፍትን ትርጓሜያቸውንም እረዳ ዘንድ፣ ትእዛዝህንና ፍቃድህን አደርግ ዘንድ የዕውሩን ዐይን እንዳበራህ ሥጋዊና መንፈሳዊ ብርሃንንም እንደ ሰጠኸው ለእኔም እንዲህ ዓይነት ጸጋን ስጠኝ፤ አቤቱ እውነተኛ ብርሃንን አይ ዘንድ የሚያስደስትህንም አደርግ ዘንድ የልቤን ዐይኖች ክፈትልኝ።"
(ተስፋ ሚካኤል ታከለ (መ/ር ወተርጓሚ)፣ ውዳሴ አምላክ ዘሰኑይ ቍጥር 22)

Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ታላቅ የምሥራች እነሆ። በቀሲስ ዶክተር መብራቱ መጽሐፍ ተዘጋጅቶልናል። አኰቴተ ቍርባንን ያነበበ ይህን ለማንበብ ምን ያህል እንደሚቸኩል አልጠራጠርም።
+ ካልእ መጽሐፍ በእንተ ቅዳሴ
በልዑል እግዚአብሔር ቸርነት "ቅዳሴ፡ ወደ ጌታ ደስታ የመግባት ምሥጢር" በሚል ርእስ በቅዳሴአችን ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ ጽፌአለሁ፡፡ በያዝነው ዐቢይ ጾም ለንባብ ይበቃል፡፡ መጽሐፉ በዋነኝነት ለማን እንደተጻፈና የተጻፈበትን ምክንያት ለማወቅ ለቅምሻ ያህል ከሥር ያለውን መቅድም ይመልከቱ፡፡
ምስጋና
አኰቴተ ቊርባን በሚል ርእስ የታተመው መጽሐፌ አራተኛ እትም አንድ ኮፒ ሲደርሳቸው መጽሐፉን በሚገባ አንብበው፣ “ይህ መጽሐፍ ለቤተ ክርስቲያናችን ካህናት በተገቢው መልኩ መዳረስ አለበት” በሚል መንፈሳዊ ቅንዐት (ተነሳሽነት) አምስተኛው እትም (1000 ኮፒዎች) በራሳቸው ወጪ San Diego, California ውስጥ እንዲታተም ላደረጉትና እርሳቸው በሚያገለግሉበት ሀገረ ስብከት ለሚገኙ ካህናት በሙሉ መጽሐፉን በነጻ በማደል እውነተኛና ወንድማዊ ፍቅራቸውን ያሳዩኝን መልአከ ብርሃን ቀሲስ ማንችሎት ገበየሁን (በአትላንታ የደብረ ብርሃን ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን አስተዳዳሪ) በምን አይነት ቃላት እንደማመሰግን አላውቅም፡፡ መንፈሳዊ ፍቅርን ለደቀ መዛሙርቱ “አዲስ ትእዛዝ” አድርጎ የሰጠ ጌታ (ዮሐ. 13፡ 34-35) ለቀሲስ ማንችሎት ፍቅረ ቢጽን አብዝቶ እንዲያድላቸውና ባለቤታቸውን ከነልጆቻቸው እንዲባርክላቸው ከመመኘት በስተቀር ከዚህ የተሻሉ ቃላት ማግኘት አልቻልኩም፡፡
ከአኰቴተ ቊርባን መጽሐፍ ሳንወጣ፣ የመጽሐፉን አንድ ኮፒ ስሰጠው “ተጨማሪ መጽሐፎችን መጻፍ አለብህ” ከሚል መልእክት ጋር ለዚሁ ሥራ የሚሆን laptop ገዝቶ ያበረከተልኝን፣ የቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ትጉህና ቅን አገልጋይ የሆነውን ቴዎድሮስ መብራቱን አመሰግናለሁ፤ የበጎ ሥጦታዎች ሁሉ ባለቤት የሆነው ልዑል እግዚአብሔር ቤተሰቡን በሰማያውያንና ምድራውያን በረከቶቹ ይባርክለት ለማለት እወዳለሁ፡፡
በዚህ መጽሐፍ መቅድም በዝርዝር እንደተገለጸው ለዚህ መጽሐፍ መዘጋጀት ምክንያት የሆኑት ሲሳይ ደምሴ (የበገና መምህር) እና ብሌን ታከለ (ዘቶሮንቶ መንበረ ብርሃን) በያሉበት ምስጋናዬ ይድረሳቸው፡፡ በተጨማሪ፣ ብሌን በምእመናን ቦታ ሆና የመጽሐፉን ረቂቅ በደስታ በማንበብና ገንቢ አስተያየቶችን በፍጥነት በመስጠት ታላቅ አስተዋጽኦ አበርክታለች፡፡ “በጎ ስጦታ ሀሉ፣ ፍጹምም በረከት ሁሉ ከላይ ናቸው . . . ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ” ተብሎ እንደተጻፈ (ያዕ. 1፡17) ካሰብነው በላይ በመስጠት ሁሌም የሚያስደንቀን አምላካችን የልቧን መሻት ይፈጽምላት፡፡
የአርጋኖን መጻሕፍት መደብር ባለቤት የሆነው አብርሃም (ክፍሎም) ኃይሉ በቅዳሴ ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ የመጻፍ እቅድ እንዳለኝ፣ ነገር ግን የኅትመቱ ውጣ ውረድና የሥርጭቱ ጉዳይ ልቤን እንደሚያዝለው ስነግረው፣ “አንተ ጻፍ እንጂ ለኅትመቱና ለሥርጭቱ እኛ አለን” በማለት ብርታትና ጉልበት ስለሆነኝ በጣም አመሰግናለሁ፤ እንደ አብርሃም ያሉ በጎ እና ቅን አገልጋዮችን ያብዛልን፡፡
በመጨረሻም፣ ለቅዳሴ ልዩ ፍቅር ያላት ውዷ ባለቤቴ ሔለን (ወስመ ጥምቀታ “ፍቅርተ ኢየሱስ”) በቅዳሴ ላይ ሁለተኛ መጽሐፍ እንደምጽፍ ካወቀችበት ጊዜ ጀምሮ፣ ለዚህ መጽሐፍ ዝግጅትና ለተለያዩ የአገልግሎት ጉዳዮች በቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ቤተ ክርስቲያን ቢሮ ውስጥ ረጅም ሰዓታትን በማሳለፍበት ወቅት የልጆቻችንን (ዮሐና እና ሳሙኤል) የትምህርት ሂደት በትጋት በመከታተልና የቤታችንን ሸክም በመሸከም አገልግሎቴን ትደግፍ ስለነበር ልትመሰገን ይገባታል፡፡ እነዚህን ሁሉ በረከቶች ላበዛልኝ፣ በምሕሩቱ ባለጸጋ ለሆነው ሕያው አምላካችን ክብር፣ ምስጋና፣ አምልኮና ውዳሴ ይሁን፡፡
ማውጫ
• መታሰቢያ
• ምስጋና
• መቅድም፡ ምክንያተ ጽሒፍ
• መግቢያ፡ በደስታ የተሰበሰቡ አእላፍ ቅዱሳን
ክፍል ፩፡ ወደ ቅድስናው ምስጋና የመግባት ዝግጅት
† ቡራኬ 1፡ የሰማያዊ ሠርግ ጥሪ
† ቡራኬ 2፡ ግብአተ መንጦላዕት: የዝግጅት ጸሎት
† ቡራኬ 3፡ ቤተ ልሔም
† ቡራኬ 4፡ ሚ መጠን ግርምት ዛቲ ዕለት
† ቡራኬ 5፡ አግብኦተ ግብር
† ቡራኬ 6፡ አሐዱ አብ ቅዱስ . . .
† ቡራኬ 7፡ በእንተ ቅድሳት
ክፍል ፪፡ የቃሉ ትምህርት
† ቡራኬ 8፡ የሐዋርያት መልእክታት ምንባብ
† ቡራኬ 9፡ ዝ ውእቱ ጊዜ ባርኮት
† ቡራኬ 10፡ ሠለስቱ ቅዳስያት
† ቡራኬ 11፡ ነዋ ወንጌለ መንግሥተ ሰማያት
† ቡራኬ 12፡ ፃኡ ንኡሰ ክርስቲያን
† ቡራኬ 13፡ ጸሎተ ሃይማኖት
† ቡራኬ 14፡ ተሐፅቦተ እድ እና አምኃ ቅድሳት
ክፍል ፫፡ አኰቴተ ቊርባን፡ የአማንያን ቅዳሴ
† ቡራኬ 15፡ አልዕሉ አልባቢክሙ
† ቡራኬ 16: ጸሎተ አኰቴት፡ መቅድመ አኰቴተ ቊርባን
† ቡራኬ 17፡ ከዝማሬ ሱራፌል እስከ ጸሎተ ፈትቶ
† ቡራኬ 18፡ ቅድሳት ለቅዱሳን
† ቡራኬ 19: ነአኵቶ ለእግዚአብሔር ቅድሳቶ ነሢአነ
† ቡራኬ 20: አስተናጽሖ
† ቡራኬ 21: እትዉ በሰላም
• ማጠቃለያ
• መፍትሔ ቃላት (የቃላት መፍቻ)
መቅድም
ምክንያተ ጽሒፍ
አኰቴተ ቊርባን፡ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሥርዓተ ቅዳሴ መሠረት፣ ታሪካዊ እድገት እና ይዘት የተሰኘው መጽሐፌ የመጀመሪያ እትም ለንባብ ከበቃበት ኅዳር 2012 ዓ.ም. ጀምሮ ስድስተኛው እትም እስከታተመበት ነሐሴ 2016 ዓ.ም. ድረስ በቃልም ሆነ በጽሑፍ የተለያዩ አስተያየቶች ደርሰውኛል፡፡ በቤተ ክርስቲያናችን ሥርዓተ ቅዳሴ ላይ ሰፊ ጥናቶች ያደረጉ ሊቃውንት መጽሐፉ በተለይ ለካህናት፣ ለዲያቆናትና ለነገረ መለኮት (theology) ምሁራን ያለውን ጠቀሜታ አውስተውና ጠንካራ ጎኖቹን አድንቀው፣ በተሻለ መልኩ ሊቀርቡ ይገባቸዋል ያሏቸውን ነጥቦች ደግሞ በጽሑፍ እንዲደርሰኝ አድርገዋል፡፡ በርካታ ምእመናን አኰቴተ ቊርባን በቅዳሴ ውስጥ ያለውን የአምልኮ ውበት በማሳየት በአማርኛ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰፋ ባለ መልኩ የተዘጋጀ መጽሐፍ በመሆኑ ደስታቸውን የገለጹ ሲሆን፣ በጥንቷ ቤተ ክርስቲያን ቅዳሴያትና በአገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ በየዘመናቱ የታዩትን የሥርዓተ አምልኮ ሂደቶች የሚያትቱት የመጽሐፉ ሁለተኛና ሦስተኛ ምዕራፎቸ ለካህናት ካልሆነ በስተቀር በቂ የቤተ ክርስቲያን ትምህርት የሌላቸውን ሰዎች ትኩረት እንዳልሳቡ ሳይሸሽጉ ነግረውኛል፡፡ እንዲያውም መጽሐፉ ውስጥ በየገጹ የሚታዩትን የኅዳግ ማስታወሻዎች (footnotes) እንደ ትርፍ ነገር የቆጠራቸውና - ምንም እንኳን ማብራሪያ የሚያስፈልጋቸው የተወሰኑ ቦታዎች ላይ ሲደርስ ማስታወሻዎቹን ለማየት ቢገደድም - እነርሱን በማንበብ ጊዜ እንዳላጠፋ በግልጽ የነገረኝም ምእመን አጋጥሞኛል፡፡
መጠነኛ የንባብ ልምድ ያላቸው ሰዎች ዳጎስ ያሉ መጻሕፍትን ለማንበብ የሚያስችል ትዕግሥት እንደሌላቸው ይታወቃል፡፡ ለቅዳሴ ካላቸው ፍቅር የተነሣ ከላይ የተጠቀሰውን መጽሐፍ ገዝተው ለማንበብ የሞከሩና “ቅዳሴ ምንድን ነው?” የሚል ርእስ የሰጠሁትን የመጽሐፉን የመጀመሪያ ምዕራፍና የቅዳሴን ሦስት ዋና ዋና ክፍሎች ከመጠነኛ ገላጻ ጋር የሚያስቃኘውን አራተኛውን ምዕራፍ ብቻ ያነበቡ ወገኖች እንዳሉም ሰምቻለሁ፡፡ በተለይ ሲሳይ በገና የተባለ የቤተ ክርስቲያናችን አባል መጽሐፉ በቅዳሴ

ላይ ጥናት ማድረግ ለሚፈልጉ ሰዎች ያለውን ግብዐት አምኖበት፣ ነገር ግን በይዘቱ ትልቅ በመሆኑ (ከመግቢያውና መቅድሙ ውጪ 367 ገጾች አሉት) የንባብ ልምድ የሌላቸውን ምእመናን ትኩረት መሳብ ስላልቻለ፣ ምእመናን በቅዳሴ ውስጥ ያላቸውን ተሳትፎ የሚያሳይና ቀለል ባለ መልኩ የተጻፈ ሁለተኛ መጽሐፍ እንዳዘጋጅ በfacebook የላከልኝ መልእክት ይህን መጽሐፍ እንድጽፍ ዋነኛ ምክንያት ሆኗል፡፡ ወንድማችን ሲሳይ የጻፈልኝ የfacebook ምክረ ሐሳብ ይህን ይመስላል፡-
ይህ መጽሐፍ የቅድስት ቤተ ክርስቲያንን አገልግሎት ለማያውቁት ለማስረዳት በቀሲስ ዶ/ር መብራቱ ኪሮስ ለዓመታት በታመቀ እውቀት፣ በእምነትና በቁጭት የተጻፈ መጽሐፍ ሆኖ አገኘሁትና በፍቅር አነበብኩት። መጽሐፉ የጥናትና ምርምር መጽሐፍ በመሆኑ የንባቤ ትኩረት ቅዳሴው ላይ ብቻ ነበር፤ ከአቅሜ በላይ የሆኑትን መንፈሳዊና የታሪክ ጭብጦችን ጠልቄ ልመረምር አልሞከርኩም። መጽሐፉ በአብነትም በዘመናዊ ትምህርትም ተምረናል፣ አውቀናል ብለው ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንንና ቅዳሴን ለሚያቃልሉ አላዋቂዎች ትዕቢታቸውን የሚያስተነፍስ ፍቱን መድኃኒት እንደሚሆን አስተውያለሁ። ቅዳሴን በዚህ ልክ ሰማያዊና ዓለም አቀፋዊ አገልግሎቱን፤ አስፈላጊነቱን፣ ጥቅሙን፣ ክብሩን፣ የቅዳሴ ዓላማና ግቡን አስረድቶ የጻፈ መጽሐፍ ከዚህ በፊት አላነበብኩም። ስለ ቅዳሴ ለማወቅ ይኽን መጽሐፍ ሁሉም ሕዝበ ክርስቲያን ሊያነበው የሚገባ መጽሐፍ ሆኖ ሳለ፣ መጠኑ ትልቅ ስለሆነ በቤት ቁጭ ተብሎ እንጂ ለኪዳንም [ሆነ] ለቅዳሴ ሲሄዱ ይዘውት ሊንቀሳቀሱ ባለመቻሉ ቀዳሹም አስቀዳሹም በቀላሉ [ሊጠቀሙበት አልቻሉም]። ስለዚህ “አኰቴተ ቊርባን” መጠኑ ትልቅ ስለሆነ፣ የታተመው እንዳለ ባለው ይዘት ኅትመቱ ቀጥሎ፣ ዘወትር በቅዳሴ የሚሳተፉ ምእመናን በቀላሉ ከጸሎት መጽሐፋቸው ጋር ሊይዙት በሚችሉት መጠን ቀዳሹና አስቀዳሹ ሊያውቁት የሚገባውን ክፍል ስለቅዳሴ ለብቻ አውጥቶ በትንሹ መታተም ቢችል እጅግ በጣም ጥሩ ነው ብዬ ይህን የአደራ መልእክት አስተላልፋለሁ። (ትልቁ የቅዳሴው መጽሐፍ እያለ፤ ለምዕመናን [ለተሰጥዎ] መማሪያ ተብሎ በትንሹ በጸሎት መጽሐፍ መልክ እንደተዘጋጀው ዓይነት ማለት ነው)።
ብሌን ታከለ የቶሮንቶ መንበረ ብርሃን ቅድስት ማርያም ካቴድራል አባል ናት፡፡ የቅዳሴን ጣዕም ከልጅነቷ ጀምሮ የቀመሰችና ባደገችበት የሐዋሳ ገብርኤል ሰንበት ትምህርት ቤት ውስጥ ታላቅ የአገልግሎት ተሳትፎ የነበራት ልጅ ስለሆነች፣ አኰቴተ ቊርባን እጇ ውስጥ እንደገባ በደስታ አነበበችው፡፡ አቀራረቡን አስመልክቶ ግን ለየት ያለ አስተያየት ሰጠችኝ፡፡ “ቅዳሴን በትረካ መልኩ ያቀረበ መጽሐፍ መስሎኝ ነበር” አለች ብሌን፡፡ ይህን አስተያየት በርካታ ምእመናን ሊጋሩት እንደሚችሉ ተረዳሁ፡፡ ስለዚህ ይህ መጽሐፍ “ፍቅርተ ኢየሱስ” የተባለች፣ በጌታ የተወደደች፣ በደሙ እንደተዋጀች የምታውቅና የቅዳሴን ውበት እንድታይ በቅዱስ ቃሉ ትምህርት ዐይነ ልቡናዋ የበራላት ምእመን፣ ቅዳሴው ተጀምሮ እስኪያልቅ ድረስ በጣዕመ ዜማው፣ ከአዲስ ኪዳን መጻሕፍት በሚነበቡ ምንባባት፣ በቅዳሴው ጸሎትና ዑደት ሐሴት እያደረገች የቅዳሴው ተሳታፊ የምትሆንበትን ሂደት በዝርዝር ለማስረዳት ይሞክራል፡፡ ፍቅርተ ኢየሱስ ለቅዳሴ ካላት ፍቅር የተነሣ ዘወትር እሑድና በዐበይት በዓላት የቅዳሴ ተሳታፊ ስለምትሆን፣ ምእመናን ለዲያቆናቱና ለካህናቱ የሚሰጡትን የዜማ መልስ (ተሰጥዎ) በሚገባ ታውቃለች፤ መቅደሱ ላይ ያለውን የጌታ ስቅለት ሥዕል እያየች ዐይነ ልቡናዋን ወደ ቀራንዮ አቅንታ፣ ድምጽዋን ከፍ አድርጋ ታዜማለች፡፡ በሥርዓተ አምልኮው ከሚከናወኑ ድርጊቶች መካከል ምሳሌያዊ ትርጉሙ ያልገባት ነገር ካለ ወይም በአብዛኛው ከሚቀደሱት ቅዳሴያት ለየት ያለ ቅዳሴ (ለምሳሌ ቅዳሴ ሠለስቱ ምእት፣ ቅዳሴ ዮሐንስ ወልደ ነጐድጓድ፣ ቅዳሴ ኤጲፋንዮስ ወዘተ.) ከተቀደሰ፣ የንስሐ አባትዋን ቀሲስ ፍቅረ መለኮትን ትጠይቃለች፡፡ እርሳቸውም መጽሐፈ ቅዳሴውን ይዘው የአማርኛውን ትርጉም እያስነበቡ ጥያቄዎቿን በሙሉ በዕርጋታና በዝርዝር ይመልሱላታል፡፡
ይህ መጽሐፍ ማንኛውም የቤተ ክርስቲያናችን አባል ስለ ቅዳሴ ሊያውቃቸው የሚገባቸውን መሠረታዊ ትምርህቶች ለማቅረብ ሙከራ አድርጓል፡፡ ትምህርተ ቅዳሴው የቀረበበትም መንገድ፣ የቅዳሴውን ሦስት ዋና ዋና ክፍልች በመከተልና ከየክፍሉ በተመረጡ አርእስት ላይ መጠነኛ ሐተታ (ገለጻ) በመስጠት ሲሆን፣ ፍቅርተ ኢየሱስ የተባለች ገጸ-ባሕርይ የቤተ ክርስቲያናችንን ምእመናን እንድትወክል ተደርጓል፡፡ በሦስቱ የቅዳሴ ክፍሎች ሥር የቀረቡ ትምህርቶችን በምዕራፍ ከመከፋፈል ይልቅ፣ “ቡራኬ 1፣ ቡራኬ 2 . . .” የሚል ስያሜን መርጫለሁ፡፡ ባጠቃላይ መጽሐፉ በሦስት ዐበይት ክፍሎችና በሃያ አንድ (21) ቡራኬያት የተከፈል ሲሆን፣ ትምህርታዊ ገላጻ የተሰጠባቸው ሃያ አንዱ ቡራኬያት፣ ሠራዒው ካህን በቅዳሴ ሰዓት የሚያከናውናቸውን ሃያ አንድ የአፍኣ (የውጭ) እና የውስጥ ቡራኬያትን ያስታውሱናል፡፡
በመጽሐፉ ውስጥ ለተጠቀሱ የግእዝ ቃላትና የሥርዓተ አምልኮ ስያሜያት (liturgical terminologies) መፍትሔ ቃላት (glossary) ተዘጋጅቷል፡፡ ምእመናንን ወክላ በዚህ መጽሐፍ የቅዳሴውን ሂደት በተመስጦ፣ አንዳንዴም በዕንባ፣ የምትከታተለው ፍቅርተ ኢየሱስ የቅዳሴ ጸበል ብቻ ጠጥታ ወደ ቤቷ የምትመለስ ሳትሆን፣ ጌታችን ኢየሱስ በቅዱስ ወንጌል “ስለ ዓለም ሕይወት የምሰጠው እንጀራ ሥጋዬ ነው” (ዮሐ. 6፡51) እንዳለ፣ ከኃጢአት በሽታ የምትፈወስበትን ኅብስተ ሕይወትና ጽዋዐ አኰቴት (ሥጋውና ደሙን) የምትቀበል ኦርቶዶክሳዊት ክርስቲያን ናት፡፡ ፍቅርተ ኢየሱስን በምናባቸው እየሳሉ ይህን መጽሐፍ የሚያነብቡ፣ ነገር ግን ከቅዱስ ቊርባን የራቁ ወይም ከተቀበሉ ዓመታትን ያስቆጠሩ የቤተ ክርስቲያናችን አባላት በእውነተኛ ንስሐና በምክረ ካህን ተዘጋጅተው “ጸጋ ሆኖ የተሰጠንን ሥጋውንና ደሙን በእግዚአብሔር ጥበብ” እንደሚቀበሉ ተስፋ አደርጋለሁ - መልካም ንባብ፡፡
ቀሲስ መብራቱ ኪሮስ (Ph.D.)
ቶሮንቶ፣ ካናዳ

🌱 “እንዲህ #በሕይወቴ ዘመን አመሰግንሃለሁ፥ በአንተም ስም እጆቼን አነሣለሁ።”
መዝ 63፥4
መዝ 63፥4
በቤተክርስቲያን የአገልግሎት ሰዓት አገልጋዮች የእጅ ስልካቸውን ይዘው እንዳይገቡ ተከለከለ፡፡
(MK TV የካቲት 19/2017 ዓ.ም)
የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት እንዳስታወቀው በቤተክርስቲያን የአገልግሎት ሰዓት አገልጋዮች የእጅ ስልካቸውን ይዘው እንዳይገቡ ተከልክሏል ብሏል፡፡
የዐቢይ ጾምን አስመልክቶ አገልግሎቱ መከናነው በሚቻልባቸው መንገዶች ዙሪያ ከሁሉም ገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች፣ጸሐፍትና ሰባክያነ ወንጌልና ቄሰ ገበዞች ጋር ውይይት በተካሄደበት ወቅት የተለያዩ መመሪያዎች ተላልፈዋል።
በቤተ ክርስቲያን ውስጥ በሚከናወኑ የጸሎተ ቅዳሴና ሌሎች መንፈሳዊ አገልግሎቶች ጊዜ የእጅ ሞባይል ስልክ ይዞ መግባት በጥብቅ የተከለከለ መሆኑ ከተላለፈው መመሪያዎች ውስጥ አንድ ነው፡፡
በዚህም አላስፈላጊ የእጅ ስልክ አጠቃቀም በረከትን ከሚያሳጡ እንዲሁም ጸጋን ከሚያስወስዱ ድርጊቶች መካከል አንዱ በመሆኑ ተከልክሏል ተብሏል፡፡
መመሪያው ለየገዳማትና አድባራት አስተዳዳሪዎች እና ሰበካ ጉባኤያት ጥብቅ ክትትል በማድረግ እንዲያስፈጽሙ ተእዛዝ ተላልፏል፡፡
መረጃው፡- የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት ሚዲያ ነው፡፡
የማኅበረ ቅዱሳን ሚዲያ ማኅበራዊ የሚዲያ አማራጮችን ይወዳጁ
ፌስቡክ:- https://www.facebook.com/eotcmkidusan
ዩትዩብ:- https://www.youtube.com/@EOTCMK
ቴሌ ግራም:- https://www.tgoop.com/+1fuTLjgAW882MjI8
ቲክቶክ:-https://www.tiktok.com/@eotcmktv?_t=8shN97IVQlp

Facebook
Log in or sign up to view
See posts, photos and more on Facebook.