አንድ አምላክ በሚሆን በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አሜን
ጥቅምት 27-ዓለምን በመዳፉ የያዘ አምላክ በአይሁድ እጅ እንደሌባ ተያዘ፡፡ ሠራዊተ መላእክት ለምሥጋና በፊቱ የሚቆሙለት መድኃኔዓለም እርሱ ሊፈረድበት በፍርድ አደባባይ ቆመ፡፡ በእስራት ያሉትን የሚፈታ እርሱ በብረት ችንካር ተቸነከረ፡፡ ሰማይን በከዋክብት ምድርም በአበባ ያስጌጠ እርሱ ግን የእሾህ አክሊል በራሱ ላይ ደፋ፡፡ ዓለሙን ሁሉ በቸርነቱ የሚመግብ እርሱ ተጠማሁ አለ፡፡ወዮ የመድኃኔዓለም የማዳኑ ምሥጢር ምንኛ ድንቅ ነው! ወዮ ለዚህ ለመድኃኒዓለም ፍጹም ትዕግስት አንክሮ ይገባል!
በመድኃኔዓለም ክርስቶስ ሞት በአንድነት እናለቅስ ዘንድ ቅዱሳን ሁላችሁ ኑ! መድኃኒታችን ሙቷልና ፍጥረታት ሁሉ ያለቅሳሉ፤ መያዝንና መታሠርን የተቀበለ መድኃኒታችን ሙቷልና፡፡ ጥፊንና ግርፋትን የተቀበለ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ መደብደብንና መመታትን የታገሰ መድኃኒታችን ሞተ፡፡ ሄኖክ እግዚአብሔር ‹‹በሴም ቤት ይደር›› ብሎ አብ ስለራሱ የተናገረለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አብርሃም ቃልኪዳን የገባልህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ይስሐቅ ከሰይፍ ቤዛ የሆነህን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ያዕቆብ በበረሃ የታገለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮብ በደመና የታየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሙሴ ስለ እርሱ ‹እንደእኔ ያለ ነቢይ ይነሣል› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳዊት ‹‹እነሆ በኤፍራታ ሰማነው፣ በበረሃ ዛፍም አገኘነው›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤርሚያስ ‹‹የክቡሩን ዋጋ ሠላሳ ብር ተቀበሉ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢሳይያስ ‹‹ወልድ ሰው ለመሆን ተገለጠልን፣ ሕፃን ተወለደልን፣ ድንቅ መካር ኃያል አምላክ›› ብለህ የተናገርኽለት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅኤል ‹‹አምላክ ወደ ተዘጋች ደጃፍ ገባ፣ ከተዘጋች በርም ወጣ›› ብለህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዳንኤል ነጭ ሐር ለብሶ ያየኸውን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኤልያስ ከሞት በፊት የሰወረህ በእሳት ፈረሶች ያሳረገህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ሕዝቅያስ የፀሐይ መግባቱን ያሳየህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ምናሴ ችንካሮችህን ከእግር ብረት የፈታ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ኢዮስያስ ፋሲካውን ያደረግህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ አናንያ፣ አዛርያና ሚሳኤል ከእሳት ምድጃ ያዳናች የመድኃኒታችንን ሞቱን ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ አብያና ሲላ ፌንቶስ ከመወለዱ አስቀድሞ ያመናችሁበት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ የቀድሞ አባቶች ነቢያት ሁላችሁ ከፋራን ተራራና ከቴማን ይመጣል ያላችሁት የመድኃኒታችንን ሞቱን ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ አሞፅ በአድማስ ቅጥር ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዘካርያስ በተራራዎች መካከል ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዕዝራ በአርፋድ በረሃ ያየኸው የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ስምዖን በክንድህ የታቀፍከውን ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ዮሴፍ እንደ አንተ የተሸጠ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ ጠራቢ ዮሴፍ በትከሻህ ያዘልከው በክንድህ የተሸከምከው ሕፃን የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡ መጥምቁ ዮሐንስ ከሕፃንነትህ ጀምሮ በበረሃ ያለ እናት ያለ አባት ያሳደገህ መንገዱንም እንድትጠርግለት ያዘጋጀህና መለኮትን እንድታጠምቅ የመረጠህ የመድኃኒታችንን ሞቱን ታይ ዘንድ ና፡፡
ኢያቄምና ሐና ሆይ የልጃችሁን ልቅሶዋን የልቧንም መዘንጋት ታዩ ዘንድ ኑ፡፡ ከሔዋን እስከ ፋኑኤል ልጅ እስከ ሐና ያላችሁ ሁላችሁ ቅዱሳት ሴቶች የድንግልን ልቅሶዋን ታዩ ዘንድ ኑ፣ አንድ ልጇ ሙቷልና፡፡
የለመለመ የሥጋ ሞት ሕንፃ የተጀመረበት የአቤል ተከታዩ፣ ከጎኑ የፈሰሰው ደም ሔዋንን ከጥፋት ያዳናት የተገደለ መድኃኒታችን ነው፡፡ የናቡቴ ጓደኛው የተገፋው መድኃኒታችን ነው፡፡ አቤል ስለሚስቱ ሞተ፡፡ ናቡቴም ስለ ወይኑ ቦታ ሞተ፡፡ መድኃኒታችን ግን በቀኙ ያነጻት ዘንድ ስለቤተክርስቲያን ሞተ፡፡ ነፍሳችሁን ይወስዷታልና መውረዱንም አላወቁምና ስለ ወገኖቹ ኃጢአት እስከ ሞት ደረሰ ብሎ ስለ እርሱ የተናገረ አባቱን እንስማው፡፡ ሙሴም እርሱን ያውቁት ዘንድ አላሰቡትም፣ በሚመጣበት ቀንም አላወቁትም አለ፡፡ ዕዝራ በባሕር ጥልቅ ያለውን ማወቅ እንዳይችሉ ወልድንም ማወቅ እንዲሁ ሆነባቸው አለ፡፡ ጳውሎስም ብታውቁትስ ኖሮ የክብርን ጌታ እግዚአብሔርን ባልሰቀላችሁት ነበር አለ፡፡
በመሰደድ፣ ያለምንም በደልም በፍርድ አደባባይ በመቆም መከራ መስቀልን በመሸከም አብነት የሆናችሁ ሰማዕታት ሁላችሁ ኑ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት አስባችሁ በጋራ አልቅሱለት፡፡ ሁሉ የእርሱ ከእርሱ ለእርሱ ተፈጥሮ ሳለ በምድር ላይ ምንም ሳይኖረው ራሱን እንኳን የሚያስጠጋበት ቤት ሳይኖረው አብነት የሆናችሁ ባሕታውያንና መነኮሳት ሁላችሁ ኑ በዛሬዋ ዕለት ስለሞተው አምላካችሁ መሪር ዕንባን አልቅሱለት፡፡ ሕግ ጠብቆ፣ ሥርዓት አክብሮ፣ ነዳያንን በመመገብና ያዘኑትን በማጽናናት 33 ዓመት በምድር ላይ ኖሮ አብነት የሆናችሁ እናንት በዓለም ሆናችሁ ሕግ ጠብቃችሁ፣ አሥራት በኩራቱን አውጥታችሁ፣ ድሆችን በመርዳት የምትኖሩ ክርስቲያኖች ሁላችሁ የመድኃኔዓለምን የሞቱን ዕለት ታስቡ ዘንድ ኑ፡፡
‹‹የተጠራችሁለት ለዚህ ነውና ክርስቶስ ደግሞ ፍለጋውን እንድትከተሉ ምሳሌ ትቶላችሁ ስለ እናንተ መከራን ተቀብሎአልና›› ብሎ ቅዱስ ጴጥሮስ እንደጻፈልን (1ኛ ጴጥ 2፡21) እርሱ ንጹሕ ባሕርይ ሲሆን ወደ መጥምቁ ቅዱስ ዮሐንስ ዘንድ ወደ ዮርዳኖስ በመሄድ ለተጠመቅን ለእኛ ለተነሣሕያን ለሁላችን አብነት የሆነን መድኃኒታችን ስለእኛ ሞቷልና ሞቱን እናስብ ዘንድ ኑ በቤቱ ተሰብስበን እናልቅስለት፡፡ መታሰቢያውንም እናድርግለት፡፡ ጌታችን ሞቶ ተቀብሮ ካረገ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያትና ለቅዱሳን አባቶቻችን ለእነ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ለእነ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ እንደነገራቸው የሞቱን መታሰቢያ የሚያደርግ ኃጠአተኛ እንኳ ቢሆን ሲኦልን አያያትም፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ሲኦል ራሷ አፍ አውጥታ ‹‹ይህችን ነፍስ ወደኔ አታምጡብኝ›› ብላ ትጮሃለች እንጂ ችላ አትቀበለውም፡፡
የጌታችን ወዳጆቹ ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በድርብ በፍታና በመቶ ወቄት ሽቱ ገንዘው በሐዲስ መቃብር ሊቀብሩት ቢሉ ጌታችን ያን ጊዜ ዐይኑን ክፍቶ ‹‹በሰውነቴ መዋቲ ብሆን በመለኮቴ ሕያው ነኝ እንጂ ምነው እንደ እሩቅ ብእሲ ዝም ብላችሁ ትገንዙኛላችሁን?›› አላቸው፡፡ ይህን ጊዜም ዮሴፍ ኒቆዲሞስ በታላቅ ድንጋጤ ሆነው ‹‹አቤቱ ጌታችን ሆይ! እንግዲያስ ምን እያልን እንገንዝህ?›› አሉት፡፡ መድኃኒታችንም እንዲህ እያላችሁ ገንዙኝ አላቸው፡- ‹‹ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተወልደ እማርያም እምቅድስት ድንግል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተጠምቀ በዮርዳኖስ ወተሰቅለ ዲበ ዕፀ መስቀል ተሣሃለነ እግዚኦ፡፡ ቅዱስ እግዚአብሔር ቅዱስ ኃያል ቅዱስ ሕያው ዘኢይመውት ዘተንሥአ እሙታን አመ ሣልስት ዕለት ዐርገ በስብሐት ውስተ ሰማያት ወነበረ በየማነ አቡሁ ዳግመ ይመጽእ በስብሐት ይኰንን ሕያዋነ ወሙታነ ተሣሃለነ እግዚኦ› እያላችሁ ገንዛችሁ ቅበሩኝ አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ መድኃኒታችን ለወዳጆቹ ለ12ቱ ሐዋርያት፣ ለ72ቱ

አርድእት፣ለ36ቱ ቅዱሳት አንስት ‹‹እስከ ሦስት ቀን እነሣላችኋለሁ እዘኑ አልቅሱ፣ እህል ውኃ አትቅመሱ በሏቸው›› ብሎ ለዮሴፍና ለኒቆዲሞስ አክፍሎት አስተማራቸው፡፡
ዳግመኛም መድኃኔዓለም ክርስቶስ ከዕርገቱ በኋላ ለቅዱሳን ሐዋርያት የሞቱን መታሰቢያ እንዲያደርጉ ነግሯቸዋልና፡፡ ሕማሙንና ሞቱንም እንዲዘክሩ አዟቸዋልና አሁንም ያንን ሁሉ የመድኃኔዓለምን ሞቱን ያላሰበና የሞቱን መታሰቢያ በዓል ያላከበረና እርሱንም የማይወደው ቢኖር ዕድል ፈንታው ጽዋ ተርታው ከአይሁድ ጋር ነው፡፡
የአምላካችንን የመድኃኔዓለምን ሞቱን በሚመስል ሞት ከእርሱ ጋር ተባብረን ትንሣኤውን በሚመስል ትንሣኤ ከእርሱ ለመተባበር ያብቃን፡፡
አባቶቻችን በሠሩልን ሥርዓት መሠረት የመጋቢት 27 የመድኃኔዓለም ክርስቶስ የስቅለቱን በዓል ወደ ጥቅምት 27 ቀን መጥቶ እንዲከበር አባቶቻችን ወስነዋል፡፡ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እመቤታችንን ያበሠራትና የጌታችንም ፅንሰት የተከናወነው በመጋቢት ወር በ29ኛው ቀን በዕለተ እሁድ በ3 ሰዓት ነው፣ ነገር ግን ብሥራቱና ፅንሰቱ ግን ታኅሣሥ 22 ቀን እንዲከበር ቅዱሳን አባቶች እነ ቅዱስ ደቅስዮስ ወሰኑ፡፡ እነርሱም በዓሉን በዚሁ ዕለት አክብረውታል፡፡ አንድም ነገረ ልደቱን ከማክበር አስቀድሞ ነገረ ፅንሰቱን ማዘከር ማክበር ተገቢ ስለሆነ ነው፡፡ በዓቢይ ጾም ወቅት ደግሞ ፍጹም ሐዘን ልቅሶ ጾም ጸሎት ይያዛል እንጂ ደስታ ፌሽታ እልልታ ጭብጨባ የለም፡፡ ዓቢይ ጾም ፍጹም የሐዘን ወራት ነው፡፡ ታቦት አውጥቶ በዓል ማክበር ስህተት ነው፤ የአባቶችንም ሥርዓት ማፍረስ ነው፡፡ ምስጋና ይድርሳቸውና ቅዱሳን አባቶቻችን ሁሉንም ነገር በሥርዓት በሥርዓቱ አድርገው ሰፍረው ቆጥረው አስቀምጠውልናል፡፡ ከዓቢይ ጾም በኋላ ያሉትን 50 ቀናት ረቡዕና ዓርብንም ጭምር ሥጋ እንኳን እንድንበላ ነው ሥርዓት የሠሩልን፡፡ አባቶቻችን የሠሯት ሕግ ፍጽምት ናት፡፡ በዚህም መሠረት አባቶቻችን ሥርዓትን ሠሩልንና የመጋቢት 27 የጌታችንን የስቅለቱን በዓል ወደ ጥቅምት 27 ቀን አምጥተው እንዲሁም የመጋቢት 5 የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስን የዕረፍት በዓል ወደ ጥቅምት 5 ቀን አዙረው እንዲከበር አድርገዋል፡፡
+++
+ ዳግመኛም በዚህች ዕለት ጥቅምት 27 ቀን ታላቁ አባት አቡነ መብዓ ጽዮን ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጥበው ጥሬ እየተመገቡ 9 ዓመት ከቆዩ በኋላ ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር ሆነው የእመቤታችንን ስደት በጥልቀት የሚተርከውን ‹ማኅሌተ ጽጌን› የደረሱት አቡነ ጽጌ ድንግል ዕረፍታቸው ነው፡፡
+ በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ የሚያስቀምጥበትን አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳምን የመሠረቱት ታላቅ ጻድቅ ግብፃዊው አቡነ ሐራ ድንግልም ዕረፍታቸው ነው።
+ + +
አባ መቃርስ ዘሀገረ ቃው፡- ቃው የምትባል ሀገር ኤጲስቆጶስ የሆኑት አባ መቃርስ ሁልጊዜ ወንጌልን በሚያስተምሩበት ወቅት ያለቅሱ ነበር፡፡ ከደቀ መዛሙርቶቻቸውም አንዱ በእግዚአብሔር ስም ካማላቸው በኋላ ለምን ሁልጊዜ እንደሚያለቅሱ በመሐላው አምሎ ጠየቃቸው፡፡ እርሳቸውም ስለመሐላቸው ፈርተው ነገሩት ‹‹ዘይት በብርሌ ውስጥ ጎልቶ እንደሚታይ የወገኖቼም ኃጢአት እንዲሁ በታየኝ ጊዜ አለቅሳለሁ›› አሉት፡፡ በሌላም ጊዜ ጌታችን በመሠዊያው ላይ ሆኖ ተገልጦላቸው የእያንዳንዱን ሰው ኃጢአት መላእክት ሲያቀርቡለት አሳያቸው፡፡ ቀጥሎም ‹‹ሕዝቡን አስተምረህ ከክፋታቸው መልሳቸው›› አላቸው፡፡ እሳቸውም ‹‹አይሰሙኝም›› ቢሉት ጌታችንም ‹‹አስተምረሃቸው ከክፋታቸው ባይመለሱ ደማቸው በራሳቸው ላይ ይሆናል›› አላቸው፡፡
መና*ፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስና ተከታዮቹ ክብር ይግባውና ጌታችንን ‹‹ሁለት ባሕርይ›› በማለታቸው ጉባዔ ሠርተው አባቶች ሲሰበሰቡ ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ዲዮስቆሮስ አባ መቃርስን አስከትሎ በጉባዔው ተገኘ፡፡ አባ ዲዮስቆሮስና አባ መቃርስም ሁለት ባሕርይ ባዮችን አስተምረዋቸው እምቢ ቢሏቸው አውግዘውና እረግመው ከቤተ ክርስቲያን ለዩአቸው፡፡ ለመከራም የተዘጋጁ ሆነው ራሳቸውን አሳልፈው ሰጧቸው፡፡ ከሃዲው ንጉሥም ወደ ጋግራ ደሴት አጋዛቸው፡፡ አባ ዲዮስቆሮስም ለአባ መቃርስ ‹‹አንተ በእስክንድርያ ሀገር ሰማዕትነት ትቀበላለህ›› በማለት ትንቢት ነግረዋቸው ከአንድ ነጋዴ ጋር ወደ እስክንድርያ ላኳቸው፡፡ እዚያም ሲደርሱ መና*ፍቁ ንጉሥ መርቅያኖስ አባ መቃርስን ይዞ ብዙ ካሠቃያቸው በኋላ ኩላሊታቸውን ብሎ ገደላቸውና የሰማዕትነታቸው ፍጻሜ ጥቅምት 27 ቀን ሆነ፡፡ ክርስቲያኖችም ሥጋቸውን ወስደው ከነቢዩ ኤልሳዕና ከመጥምቁ ዮሐንስ ሥጋ ጋር በአንድነት አኖሩት፡፡ ከሥጋቸውም ብዙ ተአምራት ተፈጽመው ታዩ፡፡ የአባ መቃርስ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ መብዓ ጽዮን፡- አባታቸው ንቡረ ዕድ እናታቸው ደግሞ ሀብተ ጽዮን ይባላሉ፡፡ በሌላኛው ስማቸው ተክለ ማርያም ይባላሉ፡፡ ይህንንም ስም ያወጣችላቸው እመቤታችን ናት፡፡ እመቤታችንን ከሕፃንነታቸው ጀምረው እጅግ ይወዷት ነበር፡፡ ትንሽ ልጅ ሳሉ አንድ ካህን ወደ ሀገራቸው በእግድነት መጣና አባታቸው ሀብተ ጽዮን አሳደሩት፡፡
እንግዳውም ካህን የእመቤታችንን ሥዕል ምስለ ፍቁር ወልዳን ይዞ ነበር፡፡ ሲተኛም በራስጌው ያኖራት ስለነበር በሀብተ ጽዮንም ቤት አድሮ ጠዋት ተነሥቶ ሲሄድ የእመቤታችንን ሥዕል በራስጌው እንዳኖራት እረስቶ ሄደ፡፡ ያንጊዜ ሕፃን የነበሩት አባ መብዓ ጽዮንም ሥዕሏን ወስደው ሳሟት፣ በእርሷም ደስ ተሰኙባት፡፡ ለሌላም ሰው አልሰጥም ብለው በአንገታቸው አሰሯት፡፡ ሀብተ ጽዮንም ‹‹ይህችን የእግዳው ካህን ንብረት የሆነች የእመቤታችንን ሥዕል ከቤት እንዳላስቀምጣት ኃጢአት ይሆንብኛል እንዳልሰጠውም ከየት አገኘዋለሁ›› እያለ ሲቀጨነቅ ከዕለታት በአንደኛው ቀን ያንን እንግዳ አገኘው፡፡ ባገኘውም ጊዜ ከቤት የተዋትን የእመቤታችንን ሥዕል እንዲወስድ ነገረው፡፡ መጀመሪያ ሕፃን መብዓ ጽዮን እንዳገኛትና በጣም እንደወደዳት ለሌላ ሰውም አልሰጥም ብሎ በግድ ቀምቶ እንዳስቀመጣት ነገረው፡፡ እንግዳውም ይህን ሲሰማ ‹‹የሥዕሊቱ ባለቤት እርሷ የሕፃኑ እንድትሆን ፈቅዳለታለች፤ ከእኔ ዘንድ መሆኗን ፈቅዳ ቢሆንማ ኖሮ ባልተረሳችኝ ነበር ለዚያ ላገኛት ልጅህ የተገባች ናት›› ካለው በኋላ እርስ በእርሳቸው ሰላምታ ተሰጣጥተው ተለያዩ፡፡
አቡነ መብዓ ጽዮን ዕድሜያቸው ከፍ ሲል ወላጆቻቸው ሚስት ሊድሩላቸው ሲሉ እርሳቸው ግን አላገባም ብለው የዚህን ዓለም ጣዕም ንቀው ነው የመነኑት፡፡ የምንኩስና ልብስ ከለበሱበት ጊዜ ጀምረው በበቅሎና በፈረስ ላይ ተቀምጠው አያውቁም፤ በአልጋም ሆነ በምንጣፍ ላይ አልተኙም ይልቁንም የአንድ ሰው ሸክም የሚያህል ትልቅ ድንጋይ በደረታቸው ተሸክመው ከአመድ ላይ ይተኙ ነበር እንጂ፡፡ ከሰንበት ቀናት ውጭ ሲቀመጡም ድንጋዩን በራሳቸው ላይ ይሸከሙታል፣ ሲሰግዱም በጀርባቸው ያዝሉት ነበር፡፡
አባታችን ለቅዱስ ሥጋ ወደሙ እጅግ ትልቅ ክብር ስለነበራቸው የቆረበ ሰው ከቤተክርስቲያን ወጥቶ ሲሄድ እንቅፋት እንኳን ሲመታው ስለሥጋ ወደሙ ክብር ብለው እግሩ የደማበትን ሰው ደሙን ይጠጡት ነበር፣ ደሙ የፈሰሰበትንም አፈር ይልሱታል፡፡ ይህም የመድኃኔዓለምን ሥጋና ደም ከማክበራቸው የተነሣ ነው፡፡ ጻድቁ ጌታችን በዕለተ ዓርብ መራራ ሐሞት መጠጣቱን አስታውሰው ሁልጊዜ ዐርብ ዐርብ ኮሶ ይጠጡ ነበር፡፡ መድኃኔዓለምም በየጊዜው በሕፃን አምሳል ይገለጥላቸዋል፡፡ በዕለተ ዓርብም

እንደተሰቀለ ሆኖ ይገለጥላቸው ነበር፡፡ ዳግመኛም ጌታችን ለአቡነ መባዓ ጽዮን በመሠዊያው ላይ በነጭ በግ አምሳል ይገለጥላቸው ነበር፡፡ መከራ ሞቱን እያስታወሱ ሰውነታቸውን ይጎዱ እንደነበር በቅዱስ ገድላቸው ላይ እንዲህ ተብሎ ተጽፏል፡-
‹‹በተቀደሰች በዓርባ ጾምም የመድኃኔዓለምን ግርፋት እያሰበ ሰውነቱን በእጅጉ ገረፈ፡፡ ደሙ ከመሬት እስኪወርድ ድረስ ልቡንም አጥቶ ከምድር ላይ ወደቀ፡፡ የመድኃኔዓለምን መከራውን አስቦ እንደሞተም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም ወደ እርሱ መጣና ‹ተነሥ እኔ ቁስልህን እፈውስሃለሁ› ብሎ የጀርባውን ቁስል ዳሰሰው፡፡ ምንም ሕማም እንዳላገኘውም ሆነ፡፡ መድኃኔዓለምም አባታችንን ‹በአንተው እጅ ትገደልን? እኔ እንኳ የተገደልኩት በአመፀኞች በአይሁድ እጅ ነው› አለው፡፡ በዚያችም ሰዓት ጌታ የመባዓ ጽዮንን ከንፈሮቹን ይዞ ሦስት ጊዜ እፍ አለበትና ‹የከበረ ትንፋሼም ከትንፋስህ ጋራ ይጨመር፣ ሥጋህም ከነፍስህ ጋራ የከበረ ይሁን› አለው፡፡ ‹አንተ በላዩ እፍ ያልህበትም የተቀደሰና የከበረ ይሁን› አለው፡፡››
ጌታችን ለአቡነ መብዓ ጽዮን የወርቅ በትር ሰጥቷቸው በእርሷ ነፍሳትን ከሲኦል ያወጡባት ነበር፡፡ መቋሚያዋም እሳቸው ካረፉ በኋላ የሚሞተውን ሰው እየለየች ትናገር ነበር፡፡ አባታችን እንደ አቡነ ተክለሃይማኖት ወደ ሰማያዊት ኢየሩሳሌም በመልአክ ተጥቀው ተወስደው የሥላሴን መንበር ከሃያ አራቱ ካህናተ ሰማይ ጋር አጥነዋል፡፡ ጌታችን ከተረገመችና ከተወገዘች ዕፅ ጋር በተገናኘ ለአቡነ ዘርዐ ቡሩክና ለአቡነ መብዓ ጽዮን ልዩ ምሥጢር እንደነገራቸው በሁለቱም ቅዱሳን ገድላት ላይ በሰፊው ተጽፏል፡፡
አቡነ መብዓ ጽዮን በይበልጥ የሚታወቁት ሁልጊዜ ወር በገባ በሃያ ሰባት መድኃኔዓለምን አብልጠው በመዘከራቸው ነው፡፡ በዚህም ምክንያት ‹‹እንደ አንተም በየወሩ በሃያ ሰባት የሞቴን መታሰቢያ ለሚያደርግ ነፍሳትን ከሲኦል አወጣለታለሁ›› የሚል ድንቅ ቃልኪዳን ከጌታችን ተቀብለውበታል፡፡ ይኸውም የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ የሚያድርግ ቢኖር ነፍሳትን ከሲኦል እንደሚያወጣ ሲነግራቸው ነው፡፡ ቅዱስ አባታችን ‹‹ጌታዬ ፈጣሪዬ ሆይ! በዓልህን አደርግ ዘንድ አንተ የምትወደውን ግለጥልኝ›› ብለው ጌታችንን ሲጠይቁት እርሱም ‹‹የሞቴን መታሰቢያ ያደረገ እንደ እኔ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ ‹በእኔ የሚያምን እኔ የምሠራውን ይሠራል፣ ከዚያም የበለጠ ይሠራል› ብዬ በወንጌሌ እንደተናገርሁ› አላቸው፡፡›› ከዚህም በኋላ አባታችን ለልጆቻቸው እንዲህ ብለው መከሯቸው፡- ‹‹ክርስቲያኖች ሁሉ የፈጣሪያችንን የመድኃኔዓለም ክርስቶስን የመታሰቢያ በዓሉን እናድርግ፡፡ የአባቶቻችን የሐዋርያት፣ የጻድቃን፣ የሰማዕታት፣ የመላእክት መታሰቢያቸው ባረፉበት በተሾሙበት ቀን ይከበራል፡፡ እነርሱን የፈጠራቸው እርሱ መድኃኔዓለም ነው፣ ያከበራቸው፣ ከፍ ከፍ ያደረጋቸው፣ ስማቸውን ለጠራ መታሰቢያቸውን ያደረገ እንደሚድን ቃልኪዳን የሰጣቸው እርሱ ነው፡፡ የመድኃኔዓለምን የሞቱን መታሰቢያ ያደረገ ግን የተኮነኑ ነፍሳትን ከደይን ያወጣል፣ በሞቱም ጊዜ ሥቃይን አያያትም፡፡››
የአቡነ መብዓ ጽዮን በዓለ ዕረፍታቸውም እጅግ አብዝተው በሚዘክሩበትና ዓመታዊ ክብረ በዓሉ ታስቦ በሚውለው በመድኃኔዓለም ቀን ጥቅምት ሃያ ሰባት ነው፡፡ ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
አቡነ ጽጌ ድንግል፡- ደራሲና ማኅሌታዊ ሲሆኑ የላመ የጣፈጠ ከመብላት ተቆጥበው ጥሬ ቆርጥመው 9 ዓመት ከቆዩ በኋላ የእመቤታችንን ስደት በጣም በጥልቀት የሚተርከውን ‹‹ማኅሌተ ጽጌን›› የደረሱ ታላቅ አባት ናቸው፡፡ ውኃም በሦስት ቀን አንድ ጊዜ ብቻ ነበር የሚጠጡት፡፡
አቡነ ጽጌ ድንግል ከደብረ ሐንታው ከአቡነ ገብረ ማርያም ጋር እንደ አንድ ልብ መካሪ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ ሆነው እመቤታችንንና ፈጣሪ ልጇን በጎ መዓዛ ባላቸው አበባዎችና ፍሬዎች እየመሰለ የሚያመሰግነውን ድርሰቱን በመዝሙረ ዳዊት መጠን 150 አድገው ደርሰዋል፡፡ አቡነ ገብረ ማርያምና አቡነ ጽጌ ድንግል ማኅሌተ ጽጌን በጥምረት ሊደርሱት የቻሉት አቡነ ገብረ ማርያም በወሎ ክፍለ ሀገር በወረኢሉ አውራጃ ልዩ ስሙ ደብረ ሐንታ በሚባለው ገዳም የሕግ መምሕር ሆነው በተሾሙበት ወቅት ነው፡፡ እነዚህም ሁለት ቅዱሳን የዘመነ ጽጌ የማኅሌት አገልግሎትን ሳይለያዩ በሰላምና በፍቅር በአንድነት አግልግለዋል፡፡ ይኸውም የሆነው እንዲህ ነው፡-
አንድ ዓመት አቡነ ገብረ ማርያም የክረምት መውጫና የዘመነ ጽጌ ዋዜማ በሆነው መስከረም 25 ቀን ከደብረ ሐንታ መጥተው ደብረ ብሥራት አቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ገብተው ከመስከረም 25 ቀን እስከ ኅዳር 5 ቀን ያለውን የዘመነ ጽጌ የ40 ቀን አገልግሎት ከአቡነ ጽጌ ድንግል ጋር ፈጽመው ኅዳር 8 ቀን ወደ ደብራቸው ደብረ ሐንታ ይመለሳሉ፡፡ በሚቀጥለው ዓመት ደግሞ አቡነ ጽጌ ድንግል ከገዳማቸው ከደብረ ብሥራት ተነሥተው ወደ ደብረ ሐንታ ሄደው እንዲሁ እንደ አቡነ ገብረ ማርያም 40ውን ቀን አግልግለው ይመለሳሉ፡፡ እነዚህ ሁለት ቅዱሳን እንደዚህ እያደረጉ በየተራ አንደኛው ወደ ሌላኛው ገዳም እየሄዱ እስከ ዕለተ ዕረፍታቸው ድረስ በፍጹም ፍቅርና በትሕትና አብረው እመቤታችንን ሲያገለግሉ ኖረዋል፡፡ ይኸውም በራሳቸው በአቡነ ገብረ ማርያም ገድል ላይ እና በአቡነ ዜና ማርቆስ ገድል ገጽ 72-73 ላይ በሰፊው ተጠቅሶ ይገኛል፡፡ የሁለቱ ድርሰታቸው የሆነው ‹‹ማኅሌተ ጽጌ›› ድርሰት የእመቤታችንንና የልጇን የጌታችንን ሥጋዊ ስደት የሚገልጽ ሲሆን በጨማሪም ስደት የማይገባው አምላካችን ወደ አህጉራችን አፍሪካ ተሰዶ የሠራቸውን ድንቅ ድንቅ ተአምራትና የእመቤታችንን ንጽሕናዋን ቅድስናዋን አማላጅነቷን የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ ነው፡፡
አባ ጽጌ ድንግል ከማኅሌተ ጽጌ በተጨማሪ ሌሎች በርካታ አስደናቂ ድርሰቶችን ደርሰዋል፡፡ የጻድቁ ቅዱስ ዐፅማቸው፣ ታቦታቸውና የደረሷቸው በርካታ ድርሰቶች በገዳማቸው ደብረ ጽጌ ውስጥ በክብር ተጠብቀው ይገኛሉ፡፡ አምሃራ ሳይንት ቦረና ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም የ5 ሰዓት የእግር መንገድ ከተሄደ በኋላ የሚገኘው ገዳማቸው ‹‹ደብረ ጽጌ›› ከአንድ ወጥ ዓለት ተፈልፍሎ የተሠራው ሲሆን አሠራሩም እጅግ ድንቅ ነው፡፡
የአቡነ ጽጌ ድንግል ገዳም ከአቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ ገዳም ጋር የሚያገናኘው ‹‹የእግዜር ድልድይ›› የተባለ አስገራሚ ታሪክ ያለው ድልድይ አለው፡፡ ሁለቱ ቅዱሳን በመንፈስ ተጠራርተው ለመገናኘት ቢያስቡም የወለቃ ወንዝ ሞልቶ በአካል ሳይገናኙ ቀሩ፡፡ በዚህም በጣም አዝነው ከወንዙ ወዲያና ወዲህ ሆነው ተላቅሰው አፈር ተራጭተው ወደየገዳማቸው ቢመለሱም ያ ተላቅሰው የተራጩት አፈር በተአምር ትልቅ ድልድይ ሆነ፡፡ ድልድዩን ሁለቱም በበዓታቸው ሆነው በመንፈስ አዩት፡፡ የበጎ ነገር ጠላት ሰይጣንም ይህንን ሲመለከት ድልድዩን በትልቅ ሹል ድንጋይ በስቶ ሊያፈርሰው ሲል አቡነ ጊዮርጊስ ዘጋስጫ በመንፈስ አዩትና ከጋስጫ ተነሥተው በደመና ተጭነው በመሄድ ሰይጣኑን በግዘፈ ሥጋ ገዝተው ያንን ድልድዩን አፈርስበታለሁ ያለውን ትልቅ ሹል ድንጋይ አሸክመውት በዓታቸው ጋስጫ ድረስ ወስደውታል፡፡ ያ ድንጋይ ዛሬ በጋስጫ አቡነ ጊዮርጊስ ገዳም ለመነኮሳቱ ደወል ሆኖ እያገለገለ ይኛል፡፡ ድልድዩም እስከ አሁን ድረስ ለአካባቢው ኢስላም ማኅበረሰብ ብቸኛው የወለቃ ወንዝ መሻገሪያቸው ሆኖ እያገለገላቸው ነው፡፡

የአቡነ ጽጌ ድንግል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
+ + +
ግብፃዊው አቡነ ሐራ ድንግል ብዙ ተአምራት የሚደረግበትንና በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ የሚያስቀምጥበትን አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳምን የመሠረቱት ታላቅ ጻድቅ ናቸው፡፡ በ9ኛ መ/ክ/ዘመን ዮዲት ጉዲት ነግሣ አብያተ ክርስቲያናትን ለ40 ዓመታት ያህል ስታጠፋ ግብፃዊው አቡነ ሐራ ድንግል በአክሱምና በታላላቅ ገዳማት የነበሩትን ቅርሶችና ቅዱሳት መጻሕፍት ሰብስበው በአርብ ሐራ መድኃኔዓለም ገዳም ዋሻ ውስጥ አስቀምጠውት ነበር፡፡ በተከታታይም ከግብፅ ሀገር ከገዳመ አስቄጥስ አርባ ቅዱሳን በእግዚአብሔር ትእዛዝ ወደ ሀገራችን መጥተው ከአቡነ ሐራ ድንግል ጋር ተቀምጠው በጾም ጸሎት ተወስነው ብዙ ትሩፋትን ፈጽመዋል፡፡ አቡነ ሐራ ድንግል አንድ ቀን ‹‹ወንድሞቼ ሆይ! ይህን ዋሻ ውስጥ ለውስጥ የምንፈለፍልበት መሣሪያ ፈልጉና አምጡ›› አሏቸው፡፡ አርባው ቅዱሳንም ወደ ሀገራቸው ግብፅ ተመልሰው ሄደው የዋሻ መፈልፈያ መሣሪያ አምጥተው ለጻድቁ ሰጧቸው፡፡ እርሳቸውም ቅዱሳኑ እየተራዷቸው ውስጥ ለውስጥ 4 ሰዓት የሚያስኬድ አስደናቂ ዋሻ ፈልፍለው በውስጡ ልዩ ልዩ ክፍሎች ሠሩ፡፡ ከዚያም አቡነ ሐራ ድንግል ቅዱሳኑን ወንጌልን እየተዘዋወሩ ይሰብኩ ዘንድ አሰማሯቸውና እርሳቸው በዋሻው አጠገብ በታላቅ ተጋድሎ በጾም ጸሎት ኖሩ፡፡ ብዙ መናንያንም ወደ እርሳቸው እየመጡ ቡራኬአቸውን ይቀበሉ ነበር፡፡ አቡነ ሐራ ድንግል በእንዲህ ያለ የተጋድሎ ኑሮ ሲኖሩ አንድ ቀን ሠርገኞች ሙሽሮችን አጅበው ሲሄዱ ጻድቁ በሚጸልዩበት አርብ ሐራ በተባለው ገዳም ሲደርሱ ሁለቱ ሙሽሮች ከበቅሎ ላይ ተንከባለው ከዋሻው በር ላይ ወድቀው ሞቱ፡፡ የሙሽሮቹ አጃቢዎችም ከፍተኛ ሀዘን ደረሰባቸው፡፡ አቡነ ሐራ ድንግልም ይህን ሁኔታ አይተው በጸሎታቸው ኃይል የሞቱትን ሙሽሮች አስነሥተው ለሠርገኞቹ አስረከቧቸው፡፡ ሠርገኞቹም ደስታቸው ዕጥፍ ድርብ ሆነ፡፡ ከጻድቁ እግር ሥር ወድቀው መንገዳቸውን ቀጠሉ፡፡
ከዚህም በኋላ የጻድቁ ዜና ይበልጥ በሁሉ ዘንድ ተሰማ፡፡ በላስታ የመራ ተክለ ሃይማኖት መንግሥት እንደተጀመረ ዋካ የሚባል ኃይለኛ ሽፍታ አቡነ ሐራ ድንግል ወዳሉበት ዋሻ መጥቶ ‹‹ይህን ዋሻ እፈልገዋለሁና ይልቀቁልኝ›› ብሎ ገና ቃሉ ከአፉ ሲወጣ መብረቅ በድንገት ከሰማይ ወርዶ ከነተከታዮቹ ገድሎ ፈጽሞ አጠፋቸው፡፡ ጻድቁም የእግዚአብሔርን ድንቅ ሥራ አይተው አደነቁ፡፡ አስከሬኑንም በወቅቱ የጣለው ጎርፍ ወሰደው፡፡ ሽፍታውም በመንዝ አውራጃ የታወቀና ኃይለኛ ስለነበር በመቅሰፍት መሞቱን ሰዎች ሲሰሙ ተደሰቱ፡፡
በአንድ ወቅትም የመንዙ ገዥ ልጁ ሞቶበት በታላቅ ሀዘን ውስጥ ሳለ ምእመናን ለገዥው ‹‹በግዛትህ ውስጥ የሚገኙት ጻድቁ አቡነ ሐራ ድንግል የልጅህን አስክሬን ብትወስድላቸው ከሙታን ለይተው ያስነሡልሃል›› ብለው መከሩት፡፡ እርሱም የልጁን አስክሬን አሸክሞ አምጥቶ ከአቡነ ሐራ ድንግል ፊት ጣለውና ‹‹ክቡር አባቴ ሆይ! በተሰጠዎት ሀብተ ጸጋ ልጄን ያድኑልኝ›› ብሎ በግንባሩ ወድቆ ለመናቸው፡፡ ጻድቁም ወደ እግዚአብሔር ጸልየው የሞተውን የገዥውን ልጅ አስነሡለት፡፡ ገዥውና ሕዝቡም ሁሉ በቅዱሳኑ ላይ ድንቅ ነገርን የሚያደርግ ልዑል እግዚአብሔርን አመሰገኑ፡፡ ጻድቁንም እጅግ አከበሯቸው፡፡ የሀገሩ ገዥና ምእመናንም ልብስና ገንዘብ እያመጡ ጻድቁ ለሚያስተምሯቸው ተማሪዎች እንዲሆን ሰጧቸው፡፡ ጻድቁም ለተማሪዎቻቸውና ለጦም አዳሪዎች አከፋፍለውታል፡፡አቡነ ሐራ ድንግል ለመንዝ ሕዝብ የቅዱሳት መጻሕፍትን ቃል በሚገባ አስተምረዋል፡፡ በተአምራታቸውም ብዙ ድውያንን ፈውሰዋል፡፡ ሙታንን አስነሥተዋል፡፡ ጻድቁ በተወለዱ በ220 ዓመታቸው ጥቅምት 27 ቀን በክብር ዐርፈዋል፡፡
አቡነ ሐራ ድንግል ከማረፋቸው በፊት በጸሎት ላይ ሳሉ ጌታችን ተገልጦ ብዙ ቃልኪዳን ገብቶላቸዋል፡፡ ዐፅማቸውንም አንድ ቅዱስ መነኩሴ በክብር ገንዞ በዋሻው ውስጥ አስቀምጦታል፡፡ ከግብፅ መጥተው እሳቸውን ሲያገለግሉ የነበሩት አርባው ቅዱሳንም ብዙ ካስተማሩና የትሩፋት ሥራ ሲሠሩ ከኖሩ በኋለ ዐርፈው በዚያው የጻድቁ ዐፅም ባረፈበት ዋሻ በክብር ተቀምጠዋል፡፡ መድኃኔዓለም ክርስቶስ ለአቡነ ሐራ ድንግል ከሰጣቸው አስደናቂ ቃልኪዳኖች አንዱ ‹‹…እስከ ዕለተ ምጽዓት ድረስ እኔን አምነው የሚነሡ ቅዱሳን የማረፊያቸው ቦታ ክቡር ዐፅምህ ባለቤት ቦታ ይሁንልህ›› የሚለው ነው፡፡ በዚህም ቃልኪዳን መሠረት እነሆ ከልዩ ልዩ ሥፍራ ነገር ግን ከየት እንደመጣ የማይታወቅ በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ ከአርብ ሐራ መድኃኔዓለም ገዳም ዋሻ ውስጥ ያስቀምጣል፡፡ ነጩ ንስር የቅዱሳንን ዐፅም ሲያመጣ በመጀመሪያ ከዋሻው ውስጥ የሚወጣው ጢስ መዓዛው ከከበረ ሽቱ ይበልጣል፡፡ የዕጣኑም ጢስ ከዋሻው ሲወጣ ይታያል፡፡ ቀጥሎም አስፈሪ የሆነ የነጎድጓድ ድምጽ ይሰማል፡፡ ወዲያው ነጭ ንስር ከዋሻው በር ላይ ባለው ዛፍ ላይ ሲያርፍ ይታያል፡፡ ወዲያው ዝናብ በሌለበት በፀሐይ ወቅትም ቢሆን የዋሻው በር በቀስተ ደመና ተከቦ ይታያል፡፡ ይህ በሚደረግበት ጊዜ እረኞችና ምሥጢሩ የሚገለጥላቸው ሰዎች ከዋሻው ራቅ ብለው ተአምራቱን ያያሉ፡፡ በማግሥቱ በዋሻው ሥር ያሉ እረኞችና ምእመናን ወደ ዋሻው ውስጥ ገብተው ሲመለከቱ ከወትሮው የተለየ ትኩስ የቅዱሳን ዐፅም በሰሌን ተጠቅሎ መቁጠሪያና መቋሚያ ይዞ ይገኛል፡፡ በዚህ ዋሻ ውስጥ የሚታዩትን እጅግ አስገራሚ የሆኑትን ተአምራት በቃላት ለመግለጽ ያስቸግራል፡፡ በቦታው ላይ አዲስ የመድኃኔዓለም ቤተ ክርስቲያን እየተሠራ ይገኛል፡፡
በአካባቢው ያለው የገጠሩ ምእመን በስዕለት ለዚህ ቅዱስ ቦታ የሚያስገባው መብዓ እና ከከተማ ለሚሄደው ተሳላሚ የሚሰጠው እምነት ለየት ያለ ነው፡፡
የአቡነ ሐራ ድንግል ረድኤት በረከታቸው ይደርብን፣ በጸሎታቸው ይማረን!
በንስር አሞራ የተመሰለ መልአክ ትኩስ የሆነ የቅዱሳንን አስክሬን እያመጣ የሚያስቀምጥበትን አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳምን በተመለከተ የዚህ ጽሑፍ አዘጋጅ አንድ የራሱ አተያይ አለው፡፡ ይኸውም፡- እንደ ታላቁ ሰማዕት ቅዱስ ገላውዴዎስ ካሉ አስደናቂ ገዳማት ውስጥ አዲስ የሚቀበር ትኩስ አስክሬን ከተቀበረበት ቦታ እየተሰወረ የት እንደሚሄድ አይታወቅም፡፡ ምናልባትም ወደ አርብ ሐራ መስካበ ቅዱሳን መድኃኔዓለም ገዳም በየጊዜው በተአምራት የሚመጣው ትኩስ አስክሬን እንደነገላውዴዎስ ካሉት ሌሎች ገዳማት ሊሆን ይችላል የሚል ግምት አለኝ፡፡ ጎንደር ውስጥ ከወሮታ ወደ እስቴ በሚወስደው መንገድ ላይ የሚገኘው የቅዱስ ገላውዲዮስ ቤተ ክርስቲያን በንብ ይጠበቃል፡፡ ምግብ በልቶ ወደዚህ ቤተ ክርስቲያን መግባት ፈጽሞ የተከለከለ ነው፡፡ በድፍረት በልቶ የሚገባም ካለ ጠባቂው የንብ መንጋ መጥቶ ይወረዋል፡፡ በዚህ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ሌላ ለየት ያለ አስገራሚ ተአምር ይፈጸማል፣ይኸውም በቤተ ክርስቲያኑ ውስጥ የካህናት፣ የወንዶችና የሴቶች መካነ መቃብር የተለያየ ሲሆን የሚቀበረው አስክሬን ከሳምንት በኋላ የት እንደሚሄድ ሳይታወቅ አስክሬኑ ይሰወራል፡፡ በመቃብሩም በሳምንቱ ሌላ የሞተ ሰው ይቀበርበታል፡፡ አዲስ የሚቀበረውም አስክሬን ከሣምንት በኋላ ይሰወራል፡፡
(ምንጭ፡- ድርሳነ መድኃኔዓለም፣ ሕመማተ መስቀል፣ ገድለ አቡነ ዘርዐ ቡሩክ፣ ገድለ አቡነ መባዓ ጽዮን፣ ስንክሳር ዘወርሃ ጥቅምት፣ ሐመር 6ኛ ዓመት ቁ.4 1990 ዓ.ም ከገድላት አንደበት)
✞ ✞ ✞

Forwarded from ✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️ (ዮሴፍ (ወልደ ሐዋርያት))
YouTube
የመሬት መንቀጥቀጡ ምልክት ነው መሪው ሱሰኛ ህዝቡ ዳንሰኛ እንዳትጠፉ እንደኖህ ዘመን ተጠንቀቁ ! #orthodox
ይህን ዶርቃ ሚድያ በተለያየ ነገር ለመደገፍ:-
1000115025008 ንግድ ባንክ አላዬ ወርቃገኘሁ
ዶርቃ ሚድያ subscribe share like በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
https://www.youtube.com/@Dorka_media
ስልክ:-0988121212
በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ አብረውን መጓዝ ይችላሉ እና ሀሳብ አስተያየትዎን በመስጠት የተለያየ የጉዞ መረጃዎችን በመጠየቅ አብረውን መጓዝ ይችላሉ።
1000115025008 ንግድ ባንክ አላዬ ወርቃገኘሁ
ዶርቃ ሚድያ subscribe share like በማረግ ቤተሰብ ይሁኑ።
https://www.youtube.com/@Dorka_media
ስልክ:-0988121212
በርሜል ቅዱስ ጊዮርጊስ አብረውን መጓዝ ይችላሉ እና ሀሳብ አስተያየትዎን በመስጠት የተለያየ የጉዞ መረጃዎችን በመጠየቅ አብረውን መጓዝ ይችላሉ።
Forwarded from ✝️ተግባራዊ ክርስትና ቻናል✝️ (ዮሴፍ (ወልደ ሐዋርያት))
YouTube
🛑 Bermel Georgis መኪና መንዳት አልወድም!! ከፈጣሪ በታች ባለቤቴ የስኬቴ ምስጢር ነች!!
👉 መኪና መንዳት አልወድም!! ከፈጣሪ በታች ባለቤቴ የስኬቴ ምስጢር ነች!!
☎️ ጉዞ ለመሄድ የምትፈልጉ 0910101073/0918181867 በዚህ ይደውሉልን።
#Orthodox #Terbinos_Media #Bermel_Georgis
👇Subscribe Now👇
https://youtube.com/@Terbinos_Media1?si=dBlvHgHMJq1TB8dw
👉 TikTok - https://www.tiktok.com/@…

🔔 "ጾመ ነቢያት [የገና ጾም] " 🔔
#ኅዳር 1⃣5⃣ ቀን 2017 ዓ/ም ይገባል።
በኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቀኖና መሠረት የዘንድሮ የገና ጾም ኅዳር 15 ቀን 2017 ዓ/ም በዕለተ እሑድ ይጀመራል።
ይህ ጾም ከ7ቱ አጽዋማት (ዐቢይ ጾም፣ ጾመ ፍልሠታ፣ ጾመ ሐዋርያት፣ ጾመ ነቢያት፣ ጾመ ድኅነት፣ ጾመ ነነዌ ና ጾመ ገሃድ) መካከል አንዱ ነው፡፡
#ጾም_ምንድን_ነው?
- በፊደላዊ (የቃሉ) ትርጉሙ፡-
ጾም ተወ፣ ታቀበ፣ ታረመ ካለው የግእዝ ግሥ የተገኘ ቃል ነው፡፡ የቃሉ ፍችም ምግብ መተው፣ መከልከል መጠበቅ ማለት ነው፡፡
#ምሥጢራዊ_ትርጉም፡-
ሰውነትን ከመብልና ከመጠጥ ከሌላውም ክፉ ነገር ሁሉ፤ መጠበቅ መግዛት፣ መቆጣጠር፣ በንስሐ ታጥቦ በጸሎት ወደ እግዚአብሔር መቅረብና እሱንም ደጅ መጥናት፣ ማረኝ ይቅር በለኝ በማለት ቅድመ እግዚአብሔር በመንበርከክ ምሕረትን ከአምላክ ለመቀበል መዘጋጀት ነው፡፡
🔔“ጾም” በታወቀ ዕለት፣ በታወቀው ሰዓት ሰው ከምግብ የሚከለከለው መከልከል ነው፡፡” /ፍትሐ ነገሥት አንቀጽ ፲፭/
#ስለ_ጾመ_ነቢያት_ፍትሐ_ነገሥታችን_እንዲህ_ይላል፦
ወይከውን ከመ ረቡዕ ወዓርብ፤ ወውእቱ ጾም ዘይቀድም እምልደት፤
ወጥንተ ዚኣሁ መንፈቀ ህዳር ወፋሲካሁ በዓለ ልደት።
የነቢያት ጾም እንደ ረቡዕና እንደ ዐርብ የሆነ፤ ይኸውም ከልደት አስቀድሞ የሚጾም መጀመሪያው የሕዳር እኩሌታ ፋሲካው የልደት በዓል የሆነ ጾም ነው። ፍትሐ ነገሥት (፲፭፥፭፻፷፰)
በቅዳሴ (በመንፈቀ ሌሉቱ የኪዳን ምስጋና) ክፍል እንዲህ የሚል ቃል ይገኛል ፦
ዘበመስቀልከ አቅረብከነ ኀበ አቡከ መልዕልተ ሰማያት
#በወንጌል_መራሕከነ
#ወበነቢያት_ናዘዝከነ
#ዘለሊከ_አቅረብከነ_አምላክ
"በመስቀልህ በጌትነት ወዳለ ወደባሕርይ አባትህ ያቀረብከን አምላክ በወንጌል መራኸን ፣ በነቢያት ያረጋጋኸን (በሥጋ ተገልጠህ በኩነት) ወደራስህ ያቀረብከን አምላክ ፈጣሪ … "
ነቢያት እግዚአብሔር በተስፋ ፍጥረትን ያረጋጋባቸው «የሕዝብ ዐይኖች» ፣ ከሰው ልጆች ጋር የተነጋገረባቸው «የእግዚአብሔር አፎች» ናቸው!
ይህንን ጾም በዘመነ ብሉይና በዘመነ ሐዲስ ብዙ ቅዱሳን ጾመውታል፤ በዚህም ምክንያት የሚከተሉት ስያሜዎች አሉት፡፡ እነርሱም፤
#ጾመ_አዳም
#ጾመ_ነቢያት
#ጾመ_ሐዋርያት
#ጾመ_ፊልጶስ
#ጾመ_ማርያም
#ጾመ_ስብከት
#ጾመ_ልደት
✅ #ጾመ_አዳም ይለዋል ፦ ለአዳም የተነገረው ትንቢት ስለ ተፈጸመለት፤
✅ #ጾመ_ነቢያት ይለዋል ፦ ነቢያት የተናገሩት ትንቢት ስለተፈጸመበት።
✅ #ጾመ_ሐዋርያት ይለዋል፦ ትንሣኤን ዐቢይ ጾምን ጹመን እናከብራለን ልደትን ምን ሥራ ሠርተን እናከብራለን ብለው ሐዋርያቱም ጹመውታልና።
✅ #ጾመ_ፊልጶስ ይለዋል ፦የአፍራቅያ ሰዎች ፊልጶስን በህዳር በ፲፯ ቀን ገደሉት ደቀመዛሙቱ እንቀብራለን ብለው ቢሔዱ ተሠወራቸው ሱባዔ ገቡ በለው ቢሔዱ ተሠወራቸው ሱባዔ ገቡ በሦስተኛው ቀን ትገለጸላቸው እሱን ቀብረው ጾሙን ጀምረን አንተውም ብለው ጹመውታል።
✅ #ጾመ_ማርያም ተብሏል፦ እመ ትሕትና እመቤታችን ሰማይና ምድር የማይወስኑትን አምላክ ፀንሼ ምን ሠርቼ እወልደዋለሁ ብላ ጹማለች።
✅ #ጾመ_ስብከት_፤ የወልደ እግዚአብሔርን ሰው መሆን ያስተማሩበት፥ የሰው ልጆች ተስፋ የተመሰከረበት፥ የምስራች የተነገረበት ስለሆነ ጾመሐዋርያት ይባላል።
✅ #ጾመ_ልደት_፤ የጾሙ መጨረሻ (መፍቻ) በዓለ ልደት ስለሆነ ‹‹ጾመ ልደት›› ይባላል፡፡
🔔“ጾም ቁስለ ነፍስን የምትፈውስ፤ ኃይለ ፍትወትን የምታደክም፤ የበጎ ምግባራት ሁሉ መጀመሪያ፤ ከእግዚአብሔ ጸጋን የምታሰጥ፤ የወንጌል ሥራ መጀመሪያ፤ የጽሙዳን ክብራቸው፤ የድንግልና የንጽሕና ጌጣቸው፤ የንጽሕና መገለጫ፣ የፀሎት ምክንያት ናት፤ የዕንባ መገኛ መፍለቂያ፤ አርምሞን የምታስተምር፤ ለበጎ ሥራ ሁሉ የምታነቃቃ፤ ሰውነትን በአግዚአብሔር ፊት ራስን በማዋረድ ትሕትናን ገንዘብ ለማድረግ የምትረዳ መድኃኒተ ነፍስ ናት” /ማር ይስሐቅ አንቀጽ ፬÷፮/
🔔“ጾም ተድላ ሥጋን የምታጠፋ የሥጋን ጾር የምታደክም ቁስለ ነፍስን የምታደርቅ፣ በጎልማሶች ጸጥታንና ዕርጋታን የምታስተምር ከግብረ እንስሳዊነት የምትከለክል ሰው መላእክትን መስሎ የሚኖርባትና ኃይል መንፈሳዊ የሚጎናጸፍባ ደገኛ መሣሪያ ናት” /ፆመ ድጓ/
🔔በጾመ ነቢያት ነቢያቱን በማዘከርና በስማቸው በመማጸን ደጅ እየጠናን እንድንቆይ አምላከ ቅዱሳን ሁላችንንም ያበርታን!
ካህኑ በቅዳሴው ፍፃሜ
«ያብእክሙ ኀበ ሀለዉ ማኅበረ ነቢያት ቅዱሳን» እንደሚል ቅዱሳን የሚሆኑ ነቢያቱ ወዳሉበት ማኅበር በቸርነቱ ሁላችንን ያግባን!
🔔 Share ይደረግ
አምላከ ነቢያት ፆሙ የበረከት የድኅነት ፆም ያድርግልን፤ ጾሙ በሰላም አስጀምሮ በሰላም ያስፈጽመን። አሜን
===================
መልካም ንባብ !!!
ህዳር 13/03/2017 ዓ/ም
ፍንጭ: መ/ር ሚኪያስ ዳንኤል Facebook page

Telegram
ቤተ ዮሴፍ-Bete Yosef
"መፍቀሬ ሰብእ"
🛑 የመፀሀፍ ቅዱስ ጥናት ወደተሰሎንቄ ሰዎች 1ኛ መልእክት
https://youtu.be/bNE3BwblY04
https://youtu.be/bNE3BwblY04
YouTube
🛑 የመፀሀፍ ቅዱስ ጥናት ወደተሰሎንቄ ሰዎች 1ኛ መልእክት