tgoop.com/bahruteka/5668
Last Update:
👉 ከላይ ሆኖ መጮህ
" ሐቅና ባጢል ተጣልተው ባጢል ሐቅን ጥሎት ከላይ ሆኖ ኡኡ ኡኡ እያለ ይጮሃል ። የአካባቢው ማህበረሰብ ምን ተፈጠረ ብሎ እየተጣደፈ ሲመጣ ባጢል ከላይ ሆኖ እየጨኸ ነው ። በጣም በመገረም ምን ሆነህ ነው ከላይ ሆነህ የምትጮኸው ይሉታል ። ባጢልም አዪዪ የምጮኸውማ እንደ ሚገለብጠኝ ስለማውቅ ቀድማችሁ እንድትደርሱልኝ ብዬ ነው ። !!!!! አለ ይባላል ።
የኢኽዋንና የሙመዪዓ ጥምሮችና ቲፎዞዎቻቸው ሰለፍዮች በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች በሚያደርጉት የተውሒድ ችግኝ ተከላ ዘመቻ ላይ ከላይ ሆነው እየጮኹ ነው ።
ሶሞኑን ከሓራና ሀሮ ፕሮግራም በኋላ በስልጤ ዞን አሊቾ ወረዳ ጮል ቀበሌ ሰለፍዮች በጣም አስደንጋጭ በሆነ መልኩ ባደረጉት የተውሒድ ችግኝ ተከላ የዳዕዋ ፕሮግራም እንዚሁ አካላት ድንብርብራቸው ወጥቷል ። ከላይ ሆነው ለተለያዩ ከበታቾቻቸው ላሉ አካላት አስቁሙ የሚል ትእዛዝ አስተላልፈው የነበረ ቢሆንም ምኞታቸው ሳይሳካ መና ሆኖ ቀርቷል ። የወረዳው አስተዳዳሪ ሴት ከበላይ የመጣውን ትእዛዝ ለማስፈፀም በፀጥታ ሀይል ታጅበው ቦታው ሲደርሱ ከየአካባቢው የመጣው ማህበረሰብ መስጂዱ አልበቃው ብሎ ዳስ ውስጥ ሞልቶ ቁርኣንና ሐዲስ በሰለፍይ መሻኢኾች ሲማር በማየታቸው ሀሳባቸውን ቀይረው ተመልሰዋል ። ቁርኣንና ሐዲስን እንዲሁም የህገመንግስቱን መርህ ጥሶ ስልጣንን ለግል አመለካከት ለመጠቀም ትእዛዝ ያስተላለፈውን የበላይ አካል ፍላጎት ወደ ጎን በመተው የተጣለባቸውን የህዝብ አደራና የህገመንግስቱን መርህ መሰረት በማድረግ ፕሮግራሙ እንዲቀጥል የፀጥታ ሀይል በመመደብ ያለ ምንም ስጋት ፕሮግራሙ እንዲካሄድ አድርገዋል ። በዚህም እነዚህ አካላት የመንግስት ሴክትር መ/ቤት አመራሮች ከኛ ፍላጎት ውጪ አይወጡም ስለዚህ በእጅ አዙር ዞኑን እኛ እንመራዋለን የሚለውን ከንቱ ምኞት አድርገው አሳይተዋል ። ሌሎቹም የዞኑ የመንግስት አመራሮች ፈለጋቸውን እንዲከተሉና የዞኑን ገፅታ ወደ ነበረ ታሪኩ እንዲመልሱ አደራ ለማለት እውዳለሁ ።
አመራርዋ ለዚህ ፍትሀዊነታቸው ምንዳቸውን አላህ ይክፈላቸው የሚለው ዱዓኤ ነው ። የሚያሳዝኑት ከላይ ሆነው ጯሂዮች የፈሩት በመድረሱ ጩኸታቸውን ያቆሙ ይሆን ወይስ ይብስ ይሆን ? ለማንኛውም የምናየው ይሆናል ።
በአላህ ፈቃድ ሰለፍዮች የተውሒድን ችግኝ መትከላቸውንና ችግኙን የሚያቀጭጩና የሚያጠወልጉ አረሞችን ምንነት ግልፅ ማድረጋቸውን ይቀጥላሉ ። ችግኙም መፅደቁና ፍሬ መስጠቱም ይቀጥላል ። ለጩኸታሞቹ የምንለው ሂዳያ የሚገባችሁ ከሆነ አላህ ይምራችሁ ካልሆነ በቁጭታችሁ ሙቱ ነው ።
https://www.tgoop.com/bahruteka
BY ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
Share with your friend now:
tgoop.com/bahruteka/5668