tgoop.com/bahruteka/5673
Last Update:
🚫 ከሀዲያንን በባአላቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት
በመለኮታዊ የሕይወት መመሪያ በሆነው የአላህ ቃል የሚመራው እንከን የለሹ ኢስላም ካስቀመጣቸው ግልፅና የማያሻሙ ህግጋቶች ውስጥ ከሃዲያንን በባአላቸው እንኳን አደረሳችሁ ማለት ክልክል መሆኑ ነው ።
ተህኒኣ ( እንኳን አደረሳችሁ ) ለከሀዲያን ማለት ሐራም መሆኑ አጠቃላይ የኢስላም ሊቃውንቶች በአንድ ድምፅ ያፀደቁት መሆኑ ኢብኑል ቀዪም አሕካሙ አህሊ ዚማህ በሚለው ኪታቡ የጠቀሰው ሲሆን በኩፍር መደሰትን ስለሚያሲዝ ወደ ኩፍር ሊያደርስ እንደሚችል በዚሁ ኪታቡ ላይ ያብራራል ። ቀድሞ እንኳን አደረሳችሁ ማለት ብቻ ሳይሆን እነርሱም ሲሉ እንኳን አብሮ አደረሰን ማለትም ተመሳሳይ ብይን እንዳለው የኢስላም ሊቃውንቶች ያስቀምጣሉ ።
በዚህ ጉዳይ ላይ አራቱም አኢማዎች ተመሳሳይ አቋም ያላቸው ሲሆን ከዘመናችን ዑለሞች እንደነ ሸይኽ ኢብኑ ባዝ, ሸይኽ ዑሰይሚንና ሸይኽ ፈውዛን የመሳሰሉት ሐራም መሆኑን አስቀምጠዋል ።
በመሆኑም ይህ ጉዳይ የቀደምቶች ስምምነት ያለበት ስለሆነ መወዛገብ አይፈቀድም ። የኻለፈ አካል ትንሹ ብይኑ የስሜት ተከታይ ( ሙብተዲዕ) ይሆናል ። ከፍ ሲል በኩፍር ላይ የደስታ መልእክት ማስተላለፍ ስለሆነ ያከፍራል ።
በጣም የሚገርመው እንዲህ አይነት ግልፅ የሆነ ሸሪዓዊ ብይን የተሰጠበትን ከባድ የመሰረታዊ የእምነት ነጥብ በሚቃረን መልኩ ለዛው በአላህ ቤት መስጂድ ላይ ይህን ወደ ኩፍር ሊያደርስ የሚችል መልእክት በአደባባይ የቅርብም የሩቅም በሚያየው መልኩ ተሰቅሎ መታየቱ ነው ። ይህ የሆነው ቄራ ሰላም መስጂድ ላይ ነው ። ይህን መልእክት በገፃችን ላይ መለጠፉ ስለሚቀፍ በሚቀጥለው ሊንቅ ገብታችሁ ተመልከቱት : –
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
https://drive.google.com/file/d/11ISLKe4SHvZ_5tf3MRxdCKK2sdcqi0yf/view?usp=drivesdk
የሚያሳምመውና የሚያሳዝነው በአላህ ቤት ላይ መሆኑ እንጂ የተጠቀሰው መስጂድ የሚያስተዳድረው ዲኑን ለስልጣንና ለግል ጥቅም የሚሸጠው የኢኽዋን አንጃ አካል ስለሆነ አይገርምም ። ምክንያቱም ፈለጋቸውን የሚከተሉት የግብፅ, የቱርክና ሱዳን ኢኽዋኖች ወደ ሀይማኖት አንድነት ነውና የሚጣሩት ። በመሆኑም ከሀገራችንም ኢኽዋኖች አላህ ይምራቸው እንጂ እንኳን አደረሳችሁ ብቻ ሳይሆን ወደ ሀይማኖት አንድነት ይጣራሉ ተብሎ ነው የሚጠበቀው ።
መሪዮቻቸው ከእንጀራ አባቶቻቸው ጋር የተለጠፉት የነሲሓ ቲፎዞዎች ምን ይሰማቸው ይሆን ? ነው ወይስ 30 ክኒኖቹ ይህም እንኳን እንዳይሰማቸው አደንዝዟቸው ይሆን ? ወይስ በሱፍይ ሙሪዶች ቀመር ስለሚጓዙ ሸይኾቻቸው የሰሩት ነገር ለምን አይባልም ? አላህ ሆይ ልባችንን ሐቅ ካሳወቅከው በኋላ አትቀይረው ።
https://www.tgoop.com/bahruteka
BY ባህሩ ተካ - Bahiru Teka
Share with your friend now:
tgoop.com/bahruteka/5673