BEMALEDANEK Telegram 1924
1• ፍቅር

1.1• ፍቅር ምንድነው?

ክፍል - ፩

  ✞ የሰው መልኩ ፍቅር ነው

"እግዚአብሔር አምላክም ሰውን ከምድር አፈር አበጀው፤ በአፍንጫውም የሕይወት እስትንፋስን እፍ አለበት፤ ሰውም ሕያው ነፍስ ያለው ሆነ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 2፥7)

    አምላክ ፍጥረታትን ሁሉ በስድስት ቀን ተከታታይነት ፈጥሮ ሥራውን ካበቃ በኋላ፤ በመጨረሻው ላይ ከፈጠራቸው ፍጡራን ሁሉ ለየት ያለ አንድ ፍጡርን በረቂቃን እጆቹ ሠራ፡፡ የመሬትንም ጭቃ አንስቶ ከመለኮቱ ኃይል የወጣ እስትንፋስን አሳረፈበት፡፡ በዚህ ጊዜ ሸክላው መንቀሳቀስ ጀመረና ሕይወት ያለው ልዩ አካል ሆነ፡፡  (እግዚአብሔር ከሁሉ የተሰወረ ሕላዌ ያለው መንፈስ ነውና፤ ጭቃ አንስቶ ሠራን ሲባል፥ ይሄ ክንውን መንፈሳዊ አንድምታ እንዳለው መረዳት ይገባናል፡፡ በሥጋ ምናብ እንደምንስለው አፈር የማድቦልቦል አይነት ሥራ ሠራ ማለት አይደለም፡፡ )

   በተገለጸው የአፈጣጠራችን ሂደትም መሠረት የሰው ልጆች ከፍጥረታት ሁሉ በሦስት ነገሮች እንለያለን፡፡ አንደኛ ከሁሉ በስተመጨረሻ የተገኘን የአምላክ አሳብ መጥቅለያና ማረፊያ በመሆናችን እንለያለን፡፡ ሁለተኛ እግዚአብሔር ፍጥረታትን ያስገኛቸው በቃሉና በአርምሞ ሲሆን፤ እኛን ሁላችን ግን የእጁ ሥራ ነን፡፡ (ኢሳይያስ 64፥8) ሦስተኛ ምድራዊ አካል አፈር እና ሰማያዊ አካል የመለኮት እስትንፋስ ተዋሕደው ባሕሪያችንን ገንብተዋል፡፡ እነዚህ ሦስቱ ልዩነቶችም የሰው ልጅ ከሁሉ ፍጥረታት ይልቅ በእጅጉ የከበረ ፍጡር ስለመሆኑ ያሳያሉ፡፡

    በሦስተኛነት የተጠቀሰው የልዩነታችን እውነት ግን የከበረን ፍጡራን ብቻ ሳንሆን የእግዚአብሔር መልክ የተሳለብን የንጉሥ ልጅ ንጉሦች እንደሆንን ያስረግጣል፡፡ "እግዚአብሔርም አለ። ሰውን በመልካችን እንደ ምሳሌአችን እንፍጠር፤" (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)

    እግዚአብሔር በራሱ መልክ አምሳል አድርጎ ሰዎችን የፈጠረው በእስትንፋሱ በኩል ነው፡፡ ሁሉንም ፍጡራን ሲያስገኝ ከክሂሎቱ እውቀት ወይንም ከሌላ ተፈጥሮ በመውሰድ በሥልጣኑ ጥበብ ሲፈጥር፤ አዳምን ግን ያስገኘው ከራሱ ውስጥ ካለ መለኮት አካፍሎ፥ እስትንፋሱን ነፍስ አድርጎ በመለገስ ነበረ፡፡

    የሰው ልጅ አርአያ አምላክ ነው ሲባል፤ በተክለ ቁመናው፣ በአካላዊ ገጽታውና በተፈጥሮ ቅርጹ አይደለም፡፡ ይልቅስ በነፍሱ ነው፡፡ ነፍስ ከእግዚአብሔር አካል እስትንፋስ በመውጣት ሳትጎድል፥ በኛ ሥጋ ውስጥ በማደሯ፤ የርሱን ረቂቅ ባሕሪያት ማንነቷ አድርጋ በመያዝ ፈጣሪን የሚመስል ሕልውና ይዛ ትገኛለች፡፡

    ነፍስ የእግዚአብሔር ክፍል እንደመሆኗ መጠን፤ እርሱ የሆነውን ነች፡፡ አምላክ መለኮታዊ ባሕሪይ እንዳለው እርሷም ከዚህ ባሕሪይ ተካፋይ ነች፡፡ አምላክ ረቂቅ ኃይል እንደሆነ እርሷም መንፈሳዊ አካል ነች፡፡ አምላክ በልዩ ሦስትነትና አንድነት ማንነቱ ሲገለጥ፤ እርሷም ሦስት ባሕሪያትን በአንድ አካል ላይ ሳትቀላቅልና ሳትነጣጥል ይዛለች፡፡ አምላክ የማይለወጥ አንድ ፈጣሪ እንደሆነው፤ ነፍስም መሞት፣ መጥፋትና መቀየር የማያገኛት ጽኑዕ ነች፡፡ አምላክ የሁሉ አስተዳዳሪ ንጉሥ እንደሆነ፤ የንጉሥ አካል ንጉሥ የሆነቺው ነፍስም በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትን ሁሉ አዳም እንዲገዛ ምክንያት ነበረች፡፡ "...የባሕር ዓሦችንና የሰማይ ወፎችን፥ እንስሳትንና ምድርን ሁሉ፥ በምድር ላይ የሚንቀሳቀሱትንም ሁሉ ይግዙ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 1፥26)

    አሁን ይህንን ግንዛቤ እንደ መሠረታዊ ብያኔ ወስደን፤ ወደተነሣንበት ርዕስ ስንመጣ "ፍቅር ማለት ምን ማለት ነው?" የሚለውን ጥያቄ ለመመለስ የሚያስችል ቃል፤ መጽሐፍ ቅዱስ በ1ኛ የዮሐንስ መልእክት 4፥8 ላይ "እግዚአብሔር ፍቅር ነው" በማለት ያስቀምጣል፡፡ እግዚአብሔር ፍቅር ከሆነ ዘንዳ፥ ነፍስም ደግሞ ፍቅር ናት፡፡ በሌላ አገላለጽ፤ ፍቅር ማለት የነፍስ ጠባይ ነው፡፡ ፍቅር ማለት የሰው መለኮታዊ መልክ ነው፡፡

    ፍቅር የተሰኘውን የእግዚአብሔርነት አካል፤ የምንማረው፣ የምንሰለጥነውና እንደ መረጃ የምንቀበለው ግኝት ወይንም እውቀት አይደለም፡፡ (ከሰው ልጆች መካከል የገዛ መልኩን ከሌላ ሁለተኛ አካል የሚቀበል ማነው?)

    ፍቅር ስንወለድ አብሮን የሚወለድ ማንነት ነው፡፡ ፍቅር ስናድግ አብሮን የሚያድግ አካላችን ነው፡፡ ፍቅር ባለ የሕይወት ዘመናችን ሁሉ ላይ የማይጠፋ፣ የማይቆረጥ፣ የማይለይና የማይጣል ውሳጣዊ ክፍለ ባሕሪይ ነው፡፡

    አንዳንዴ ሰዎች "እኔ ፍቅር የለኝም" ብለው በደፈናው ሲናገሩ ይደመጣል፡፡ አላወቁትም እንጂ እያሉ ያሉት "እኔ መልክ የሌለኝ ሕይወት አልባ ፍጡር ነኝ" ነው፡፡ ያለ ነፍስ የተፈጠረ አንድም የሰው ዘር እንደሌለ ሁሉ፤ ያለ ፍቅርም የተገኘ ነፍስ ሊኖር አይችልም፡፡

    ፍቅርን ከሕልውናው መዝገብ አውጥቶ የጣለ ብቸኛው ፍጡር ዲያቢሎስ ነው፡፡ (አሁን ያለንበት ዓለም የፍቅርና የጥላቻ ፍትጊያ መነሻ ሰበዙ የሚመዘዘው ከዚህ ፍጡር የዓመፃ ታሪክ ላይ ነውና እስቲ ነገሩን በዝርዝር እንየው)

    ከሁሉ አስቀድሞ በራሱ ዓለም ይኖር የነበረው ቅዱስ እግዚአብሔር፤ በአርምሞ ኃይል "ሰማይንና ምድርን በመጀመሪያ ከፈጠረ" በኋላ፤ በቃል በመናገር ደግሞ እግዚአብሔር በፈጠረው ዓለም ላይ "ብርሃን ይሁን አለ፡፡" ኦሪት ዘፍጥረት 1፥3)

    የእግዚአብሔር ቃል ብርሃንን ወደ ዓለም ከማስገባቱ በፊት፤ ሰማይና ምድር በተፈጠሩበት የመጀመሪያው ቀን አብረው ስለተፈጠሩት መቶ የመላእክት ነገድ በመጽሐፍ ቅዱስና በሌሎች በርካታ መንፈሳዊ መጽሐፍት ላይ ተመዝግቦ እናገኛለን፡፡ ከእሳትና ከነፋስ በልዩ ጥበብ የተፈጠሩት መላእክት፤ ሁሉ ጨለማ በነበረበት የዓለም ገጽታ ውስጥ ፈጣሪያቸውን ለማግኘት በተሰጣቸው የእውቀት ፈቃድ መመራመር ያዙ፡፡ መላእክቱን ሁሉ መርቶ ወደ አምላካቸው እንዲያደርስ አለቃ ሆኖ የተመረጠው ሳጥናኤል ነበረ፡፡

    ይህ መልአክም የእግዚአብሔር ሕልውናና ኃይል በብርሃን ባልተገለጠበት ሁኔታ ከእርሱ ማዕረግ ከፍ ያለ ሕይወት ያለው ፍጥረት አለመኖሩን ከተረዳ በኋላ በልቡ የመታበይን አሳብ አፈለቀ፡፡ (ዲያቢሎስ ክፉ ማንነቱን ከባሕሪዩ ወይንም ከልቦናው ነው ያነቃት፡፡ በእግዚአብሔር ፈቃድ በጭራሽ የማይታውቅ ጠባይን ከእውቀቱ ውስጥ በራሱ ፈቃድ አፍልቆታል፡፡ (ትንቢተ ኢሳይያስ 14፥8-20 ፤ የዮሐንስ ወንጌል 8፥44) በእርግጥም በባሕሪይው ፍጹም ቅድስና ያለው እግዚአብሔር፤ ሃያ ሁለቱን ሥነ ፍጥረታት ሲፈጥር አንድም ቅዱስ ያልሆነ ፍጥረት አላስገኘም፡፡ ኦሪት ዘልደትም በመነሻው ላይ ከፍጥረታት መገኘት በኋላ "መልካም እንደሆነ አየ" በማለት ስድስት ጊዜ በተደጋጋሚ ያስቀመጠው የእግዚአብሔር እይታ፤ በስድስት ቀን ውስጥ የተፈጠሩት ሁሉም ፍጡራን በፈጣሪያቸው ቅድመ አሳብ መልካም እንደሆኑ ያስረዳል፡፡)

    ከዚህ ጊዜ በኋላ የእግዚአብሔር ቃል በዓለም "ብርሃን ይሁን" የሚለውን አምላካዊ ሥልጣን ገለጠ፡፡ በተፈጠሩበት የቅድስና አሳብ ጸንተው የቆዩት መላእክት ይህንን ኃይለ ጸዳል ለብሰው ብርሃናውያን ሲሆኑ፤ ክሕደትን ያስገኘው ሳጥናኤልና ያመኑበት መላእክት ደግሞ ጽልመትን ማንነት ጨለማን መገለጫ አድርገው ቀሩ፡፡ (ወደ ኤፌሶን ሰዎች 6፥12)

tgoop.com/bemaledanek/1924
Create:
Last Update:

BY በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪

Share with your friend now:
tgoop.com/bemaledanek/1924

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

To upload a logo, click the Menu icon and select “Manage Channel.” In a new window, hit the Camera icon. Members can post their voice notes of themselves screaming. Interestingly, the group doesn’t allow to post anything else which might lead to an instant ban. As of now, there are more than 330 members in the group. Polls Among the requests, the Brazilian electoral Court wanted to know if they could obtain data on the origins of malicious content posted on the platform. According to the TSE, this would enable the authorities to track false content and identify the user responsible for publishing it in the first place. So far, more than a dozen different members have contributed to the group, posting voice notes of themselves screaming, yelling, groaning, and wailing in various pitches and rhythms.
from us

Telegram በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
FROM American