BEMALEDANEK Telegram 2580
+ ሐሙሶች ሁሉ እግር ያጥባሉ +

   በሰሞነ ሕማማት ሳምንት በልዩ ታሪካዊ ሥርዓትና መንፈሳዊ ዳራ የሚከበረው በ'ሕጽበተ እግር' እና በሌሎች ተጨማሪ አምስት ስያሜዎች የሚጠራው ዕለተ ሐሙስ ካለፈ እነሆ ሰባት ቀናት ሆነ፡፡

   "አሁን የትንሣኤውን ክብረ በዓል አክብረን ወደ ዳግማዊ ትንሣኤው በምንሻገርበት ጊዜ ላይ ምን ነክቶህ ወደ ሕማማተ ሐሙስ ትመልሰናለህ?" የሚል ጥያቄ ታነሡልኝ ይሆናል፡፡ እኔም ጌታ በማንኛውም ጊዜ ያደረጋቸው እያንዳንዱ ሥራዎችና የተናገራቸው ቃላት በዓመት አንዴ ታስበው የሚውሉ የዝክር በዓላት ብቻ አለመሆናቸውን እነግራችኋለሁ፡፡

   ጊዜ በረጅም ቆጠራ ነጉዶ ከእውነት መነሻ ቦታ ሲርቅ፤ ክስተት መጀመሪያ ከተነሣበት አኳኋን በዘመናቶች መደራረብ ምክንያት ሲደበዝዝ፤ የድርጊት ስሜትና ዓለማ ከተፈጸመበት ቅጽበት ጀምሮ ወደፊት በተጓዘ መጠነ ልክ ሲረሣና ትዝታው በአሳብ አሊያ በቃል ብቻ ሲቀር፤ ከሁለት ሺህ ዓመታት በፊት በምድር የነበረው ክርስቶስና እና ዛሬ በስሙ የተጠራነው ክርስቶሳውያን መንገድ ተለያይተን በግራና በቀኝ ተነጣጠልን፡፡

   ለዚህም መነጣጠል ሁነኛ ማሳያ የሚሆነን ባለፈው ሳምንት ዐውደ በዓሉ የተከበረለት 'ጸሎተ ሐሙስ' ነው፡፡ በዚህም ዕለተ ቀን እንደምታውቁት ጌታና ሐዋሪያቱ የመጨረሻዋን ማዕድ እየተካፈሉ ሳለ ክርስቶስ ከመካከላቸው "ከእራት ተነሣ ልብሱንም አኖረ፥ ማበሻም ጨርቅ ወስዶ ታጠቀ፤ በኋላም በመታጠቢያው ውኃ ጨመረ፥ የደቀ መዛሙርቱንም እግር ሊያጥብና በታጠቀበትም ማበሻ ጨርቅ ሊያብስ ጀመረ።" (የዮሐንስ ወንጌል 13፥5)
   
   እንዲህ ያለውን መላእክትን ያስደነገጠ ታላቅ ትሕትና ወንጌል ሆኖ ትናንት የተጻፈው፤ ሁልጊዜ ትሕትናን በነባራዊነት እንኖረው ዘንድ ነው፡፡ ዘወትር በሰዎች ፊት ዝቅታን ጠባያችን እናደርገው ዘንድ ነው፡፡ በየዕለቱ ከታናናሾቻችንም ፊት አገልጋይ መሆንን እንመርጥ ዘንድ ነው፡፡

   ጌታ ነገ(ስቅለተ ዓርብ) በጎልጎታ ምድር እንደሚሞት አውቆ ዛሬን(የነጻነት ሐሙስን) ግን ከደቀመዛሙርቱ ሥር ተንበርክኮ እግር ሊያጥብ አጎነበሰ፡፡ እኛም ከመንፈስ ቅዱስ አብራክ በቤተክርስቲያን ማኅፀን የተወለድን አምሳያ ልጆቹ ስንሆን፤ ነገዎችን እየሞትን በምንኖርበት ዓለም ውስጥ ዛሬዎችን በርኅራኄና በገርነት እንድናሳልፋቸው 'የሚስጢር ቀን 'የተሰኘው ያ.. የክርስቶስ ሐሙስ ለዛሬዎቹ ክርስቲያን ሐሙሶች አጽንዖት ይሰጣል፡፡

   ነገር ግን እንደተገለጸው ከአምላካችን መንገድ በብዙ ኪሎሜትሮች ልዩነት የራቅን በስሙ ያመንን የድርጊት አረማውያን ነንና፤ በሰሞነ ሕማማት ሐሙስ በቀኑ ክፍለ ጊዜ ዝቅ ማለት ትልቅነት እንደሆነ የሚናገሩ ቃላትን፣ ትምህርቶችንና ምስሎችን በማሕበራዊ ሚዲያ ስናመላልስ ውለን፤ ከቀኑ የማታ ክፍለ ጊዜ ጀምሮ ትሕትናን ከባሕሪያችን መዝገበ ፍለጋ ፍቀን እናጠፋለን፡፡

   ክርስቶስ ሕማማትን እየጠበቅን በሁሉ ፊት ራስን አገልጋይ እንድናደርግ ቢፈልግ ኖሮ በቃሉ ላይ "ይህንን ሥራዬን በየዓመቱ መታሰቢያ አድርጉ" ብሉ ያዝዝ ነበረ፡፡ በደቀመዛሙርቱ በኩል የዕለት ጸሎትን 'አባታችን ሆይ በሉ' ሲል ያስተማረን ጌታ፤ በደቀመዛሙርቱ በኩል የዕለት ትሕትናንም እንዲህ በማለት አስተምሮናል፤ "እንግዲህ እኔ ጌታና መምህር ስሆን እግራችሁን ካጠብሁ፥ እናንተ ደግሞ እርስ በርሳችሁ እግራችሁን ትተጣጠቡ ዘንድ ይገባችኋል። እኔ ለእናንተ እንዳደረግሁ እናንተ ደግሞ ታደርጉ ዘንድ ምሳሌ ሰጥቻችኋለሁና። እውነት እውነት እላችኋለሁ፥ ባሪያ ከጌታው አይበልጥም። መልእክተኛም ከላከው አይበልጥም። ይህን ብታውቁ፥ ብታደርጉትም ብፁዓን ናችሁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 13፥14-17)

   ይህንንም የጌታችንን ትእዛዝ የተቀበልን እንደሆነ፤ ከትንሣኤ በፊትም፣ በሰሞነ ሕማማትም፣ ከትንሣኤ በኋላም ያሉት ሐሙሶቻችን ሁሉ እግር ያጥባሉ፡፡ በቻልንበት የቸርነት ቀናት ሁሉ ላይ ልብሳቸው የቆሸሸ፣ ሰውነታቸው ያደፈ፣ በመንገድ ዳር የወደቁ ወገኖቻችንን ለማጠብ ጎንበስ ማለትን ብናውቅበትና ብናደርገው ብፁዓን እንሆናለን፡፡

   ከውልደት በኋላ ተጠምቀን መስቀል በአንገታችን ማሰር ክርስቲያን አያስብለንም፡፡ ሲሆን ጥምቀታችንና ማኅተባችን በስማችን የተከፈተ የክርስትናን ሰነድ እንጂ ክርስትናን አይወክሉም፡፡ ክርስቲያን እንባል ዘንድ የሚገባው፤ እንደ ክርስትና አባታችን ክርስቶስ ባለን የሕይወት ዘመን ሁሉ ላይ የዋህነትን ጠመኔ፤ ሌሎችን በእውነተኛ አቅም ከልብ ማገልገል ፊደል አድርገን እርሱን በመከተል፤ የቃል ምግባርን ሃይማኖታዊ ሰነዳችን ላይ ስንጽፍ ነው፡፡

   ስለዚህ አሁን ጀምሩ፡፡ ከተቀመጣችሁበት ብድግ በሉና ከወገናዊነት ፍቅር የመነጨ ጽድቅን መኖር ጀምሩ፡፡ ቤታችሁ ውስጥ ያለ አልባስ ይዛችሁ በአቅራቢያችሁ ወዳለ ነዳይ ሄዳችሁ ስጡ፡፡ እግር ማጠብ ባዶ እግርን ማልበስ ጭምር ነው፡፡ ከምትቀያይሩት ጫማ አንዱን አንሡና ስጡ፡፡ እግር ማጠብ ባዶ እግር እሾህ እንዳይወጋው መከላከል ጭምር ነው፡፡ ሌላም ማድረግ የምትችሉትን ሁሉ ምንም ማድረግ ለማይችሉት ወገኖች አድርጉላቸው፡፡ ከዚህ ባሻገር ግን፤ በዓመት አንዴ የሚመጣውን ሐሙስ ለማሰብ ብቻ የጌታን ሕጽበተ እግር ስዕሎችና ተያያዥ ፎቶዎችን በማሕበራዊ ሚዲያ እየለጠፉ፥ በዕለተ ቀኑ ቤተክርስቲያን ሄዶ መምጣት ብቻውን የእምነት አቁማዳን አይሞላም፡፡ እንደውም እነዚህ ወቅት እየጠበቁ አንዴ የሚከናወኑ ልምዶች በማይቋረጥ የቅድስና ምግባር ካልተደገፉ እንደ ማስታወሻ ሐውልት በመልእክታቸው ክርስቶስ ሞቷልና አልተነሣም የሚሉ ናቸው፡፡ 'እንዴ ምን ማለትህ ነው? "እኔ ሕያው ነኝና እናንተ ደግሞ ሕያዋን ትሆናላችሁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 14፥19) የሚለውን ሕያው ቃል እኮ እናምናለን' ካላችሁኝ ዘንዳ፤ ሕያው ክርስቶስ መታሰቢያን ሳይሆን የጽድቅ ሥራን ይመርጣልና፤ እናንተ ውስጥ ሕያው ሆኖ እግር ማጠቡን በመቀጠል ከነፍስ-ባሕሪይ የሚፈልቅ ድንቅ ትሕትናን በሥጋ እንዲገልጥባችሁ፤ በሐሙሶች ሁሉ ላይ እግር ለማጠብ በዝቅታ ተመላለሱ፡፡

"ብትወዱኝ ትእዛዜን ጠብቁ።" (የዮሐንስ ወንጌል 14፥15)
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek

tgoop.com/bemaledanek/2580
Create:
Last Update:

BY በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪

Share with your friend now:
tgoop.com/bemaledanek/2580

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Ng, who had pleaded not guilty to all charges, had been detained for more than 20 months. His channel was said to have contained around 120 messages and photos that incited others to vandalise pro-government shops and commit criminal damage targeting police stations. The imprisonment came as Telegram said it was "surprised" by claims that privacy commissioner Ada Chung Lai-ling is seeking to block the messaging app due to doxxing content targeting police and politicians. While some crypto traders move toward screaming as a coping mechanism, many mental health experts have argued that “scream therapy” is pseudoscience. Scientific research or no, it obviously feels good. ‘Ban’ on Telegram How to Create a Private or Public Channel on Telegram?
from us

Telegram በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
FROM American