Telegram Web
፬. ዮሴፍና ዮሃንስ

ዮሴፍ ለማርያም በእጮኝነት ስም የተመደበ ባለአደራ ነው። ይህ ሰው በማያውቀው ሁኔታ የማርያምን መፀነስ ሲያውቅ ሊተዋት ሲፈልግ ‘እርሷን ለመውሰድ አትፍራ፣ የፀነሰችው በመንፈስ ቅዱስ ነውና ውሰዳት” ተብሎ ወስዷታል። ዮሓንስ በቀራንዮ “እነሆ እናትህ“ ተብሎ ወስዷታል። ሁለቱ ሰዎች ማርያምን ውሰዱ በመባል አንድ ናቸው፤ አንዱ በጽንስ ሌላው በመስቀል። ዮሴፍ ተወዳጁ በህጻንነቱ እንዳይገደል ከእናቱጋ ይዞት ሸሽቷል። ሄሮድስ አላገኘውም። በመከራው ብዙ ተፈትኗል። ቤተሰብ ይዞ መሰደድን የሚያውቅ ያውቀዋል። ፈተናው “ውሰድ” ከተባለ በኋለ የተከተለው ነው። ዮሓንስ ማርያምን ተወዳጁ በመከራ ሳለ ነው የወሰዳት። እነሆ እናትህ ተባለ። በማርያም እናትነት በኩል የጥምቀትን እናትነት ተመልክቶበታል። በጌታ ሞት እኛ ተወልደንበታል። ስለዚህ በማርያም ውስጥ የዮሓንስ ልጅነት ሲኖር በዮሓንስ ውስጥ የማርያም እናትነት ታውቋል። በዚህ ውስጥ የአብን ወላዲነት የወልድን ልጅነትንም አውቋል። “አባት ሆይ አንተ በእኔ እኔም ባንተ እንዳለሁ እነርሱም በእኛ አንድ ይሆኑ ዘንድ እለምናለሁ” ያለውን ቃል ያስቧል። ዳግም ከተወለድን በኋላ ሰውን በክርስቶስ እንጂ በሥጋው አናውቀውም። ለምሳሌም ማርያምን የምናውቃት ኢየሱስ በእርሷ በሰራው ታላቅ ስራና ጥበብ እንጂ በመልኳ ወይ በዜግነቷ አይደለም። የተነሳው ክርስቶስ በመልክ እንደማንረዳው ሁሉ በትንሳኤው ያሉትንም በመልክ አናውቃቸውም። በቃል፣ በድምጽ ይታወቃሉ። ቃሉም መንፈስና ህይወት ስለሆነ ስንሰማና ስንኖራቸው እናውቃቸዋለን። ዮኃንስ ይህን የመንፈስ ቅዱስ ስርዓት አግኝቶታል። ቃሉን ሰምቶ የሚያደርገው ለጌታ እናቱም ወንድሙም ዘመዱም ነው። ተወዳጇ እመቤትም “እንደቃልህ ይደረግልኝ” በማለቷ ቃል በእርሷ ሥጋ ሆኗል። እናቱ ሆናለች። በዚህ በኩር ናት።

በዮሴፍ ጊዜ ተወዳጁ አልተገደለም። በዮሓንስ ጊዜ ግን ተወዳጁ በፈቃዱ ሞቷል። ዮሴፍ የግርዘቱን ደም ሲያይ ዮኃንስ የመከራውን ደም ተመልክቷል። ማርያም ሁለቱንም ጊዜ ተመልክታለች። ዮሓንስ በራእዩ ሴቲቱ 1260 ቀን እንደተስደደች ጽፏል። ይህ ሶስት ዓመት ከመንፈቅ በዮሴፍ ጊዜ ሆኗል።
ኢትዮጵያ ዮሴፍ ህፃኑና እናቱን ይዞ ከሄሮድስ ተሸሽጎባታል። ግብጽና ኢትዮጵያ መሸሸጊያ ናቸው(መንበረ ማርቆስ)። ይህን ያወቅነው በዮሃንስ የመቅደስ መለኪያነት ነው።መለኪያው ያለው ዮሓንስን ሆኗል (ማርያምን “ፀጋን የሞላብሽ” የሚያስብለን መንፈስ ለእኛም የተሰጠ እንደሆነ ያመለከተን ዮሓንስ ነው።”ቃል ስጋ ሆነ።ጸጋና እውነትን ተሞልቶ በእኛ አደረ” በማለት...በዓለም ያሉ አብያተ ክርስቲያናት ክፍፍል መነሻዎች ይህ የቃል ሥጋ ሆነ ነገር ነው)።

1260 ቀን በሰሜኑ በር 1985 ዓመታት ናቸው። ዓለምም እውነቱን ሲያሳድድና ሲገል እስከዛሬ አለ። ለዚህን ያህል ዘመን ይህ የወንጌል እውነት ተሸሽጎ ነበር። አሁን ከስደት ተመልሷል። እንደ ዮሴፍ በዚህ ተሸሽጓል። እንደዮኃንስ ከዚህ ይነገራል። 1985 ዓመታቱ ተጠናቀዋል። ዮሴፍ ስራውን ፈጽሟል። ዮሓንስ ይቀጥላል። በትንሣኤው “ና ተከተለኝ” ተብሎ በድጋሚ የተጠራ እሱ ነው።ወደ አብ የሚያርገው ተወዳጅ ስለጠራው ሙሉውን መለኪያ አግኝቷል። ‘በመጀመሪያ ቃል ነበር’ ብሎ ከአብ መወለዱን መስክሯል። የማርያምን የአብ ምሳሌነት አውቋል። አግኝቶታልም። ኖሮታልም።

ቅዳሴያችን በቤተልሄም ጀምሮ በቀራንዮ ያልቃል። እንደ ማርያም ስናየው በዮሴፍ ጀምረን በዮሃንስ እንፈጽማለን። ይህ እውነት በህይወታችን ከተፈጸመልን በእውነት ፍልሰታው ለእኛም ሰርቷል። በእምነቱ በዮሴፍነት ላይ ያለም በበአለ ሃምሳ ያለም ይጸልይ። ፍጻሜው ጌታ ነው፤ ይገለጻል። አበው ዮሴፍና ዮሃንስ አብረው ሲቀድሱ የዓለም ፍጻሜ ይሆናል ይላሉ። ሁለቱን በአንድ ሰብእናና ዘመን አግኝተን እየኖርነው አይደል? ኢትዮጵያ የዮኃንስ ራእይ ማእከል ናት። በመቅደሱ ፍጻሜ በቅድስተ ቅዱሳን ነን። በሃያው ክንድ ወይም በአስሯ ቀን ነን። እርሷም መቶሃያው ቤተሰብ የተጉባትና በመንፈስ ቅዱስ የተጠመቁባት ናት። አህዛብን ሁሉ በብረት በትር የሚገዛው ወንዱ ልጅ በዚያ ይኖራል። ለሁሉም እንደየቋንቋው ሊሰማው የሚችል ከነገድ ከቋንቋ የሚዋጅ የፅዮን ድምጽ ይነገርባታል።

፻፳ን በ፲ ስናበዛው ፲፪፻(1200) ቀናትን ይሆናል። ከዋናው የበዓለ ሀምሳ ፶ ቀናት'ጋ ሲደመር ሶስት ዓመት ከስድስት ወር ይሆናል (እራሳቸው መቶሃያው ቤተሰብ ሶስት ዓመት ከመንፈቅ ተሰደዋል። አሁን ይህ እየሆነ ነው። በምስራቁ በር መንፈስ ቅዱስ የወረደው በማርቆስ እናት ቤት ነው። በሰሜኑም እንደዚያው ይሆናል (ኢትዮጵያ በማርቆስ መንበር ናት፤ እዚያ ነን)፡፡ ዛሬ በዓለምና በተለይ በሃገራችን ዘንዶው እያሳደደ ያለው ይህን እውነት ነው። ምእመኗን ካላጠፋሁ ብሎ የከበበው ለዚህ ነው። ለ1260ቀን ውሸቱን እየለቀቀ ያሳድዳል። "ምድር ግን ሴቲቱን ረዳቻት" ይላል ዮኃንስ። ዘንዶው የተፋውን ውኃ ውጣዋለች። እኛ ከተማይቱን ገልጾልን አይተናታል። ከሃያው ክንድ ኅይል ይወጣል። እንደሄደብን ይመጣል። ደግሞም መጥተናል። እስቲ እንደሀዋርያት እንዲገለጽልን የምንፈልገውን ነገር እንንገረው። ፍጻሜው ላይ ነን፤ ሚካኤል ስራ ላይ ነው (ለዛሬ በጸሎት ያላችሁ የዮኀንስ ወንጌልን እያነበብችሁ አስቡን)።

ተጻፈ: በደመወዝ ጎሽሜ (ጋሼ)
ማስታወሻ :- ፲፮ የሚለውን መጽሐፉን ካላነበባችሁ የቁጥር ስሌቱን ጨምሮ ሙሉ መረዳት አይኖራችሁም:: ለአሁን፣ የሆነ ነገር ካገኛችሁበት በቂ ነው:: ዞሮ ዞሮ፣ እስቲ መልካም ቆዩ!

@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.2•  ንስሐ ለምን እንግባ? ክፍል - ፪                 ✞ የኃጢአትን ምሽግ ለማፍረስ ✞    ኃጢአት የሚለውን ቃል በቀጥተኛ ፍቺ ስንተነትን፤ ከእግዚአብሔር ንጹሕ ፈቃድ መለየት፣ የእግዚአብሔርን ፍጹም አሳብና ባሕሪይ መሳት፣ እግዚአብሔር አስቀድሞ መልካም አድርጎ ባየው ነገር ላይ ማመፅ፣ የጽድቅን በጎ ሥርዓትና ትእዛዝ መተላለፍ፣ የቅድስና አነዋወርን መቃወም አሊያ…
2•  ንስሐ

   2.2•  ንስሐ ለምን እንግባ?

ክፍል - ፫

                     ✞ ብርሃንን ለማየት

   ጨለማ በሥነ ፍጥረት መዝገብ የመጀመሪያው ቀን ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ከሰባቱ ቀዳማይ ፍጥረታት መካከል አምስተኛው እርሱ ነው፡፡ ብርሃንን ቀድሞ መጥቷል፡፡ "አክሲማሮስ" የተሰኘ የሥነ ፍጥረት መጽሐፍ ስለ ጨለማ ተፈጥሮ ሲያብራራ፤ "ጨለማ በዓይን እንደማይታይ በእጅ እንደማይዳሰስ ሁሉ፤ አምላክም የኔ ባሕሪየ መለኮት አይመረመርም አይታወቅም ሲል ፈጥሮታል" ይላል፡፡

   ጨለማ አለመታወቅን ምልክት እንዲያደርግ ተፈጥሯል እንደ ማለት ነው፡፡ ጨለማ ያለመታወቅና ያለመገለጥ ባሕሪይ ምሳሌ ሆኗል፡፡ ስለዚህ ጨለማ ውስጥ እውቀት የለም፡፡ እውቀት የሌለው ደሞ መንገድ ሊኖረው አይችልም፡፡ መሪ አቅጣጫ ስሌለው መነሻና መድረሻውን አይለይም፡፡ በመሆኑም አይንቀሳቀስም፡፡ ወደፊትም ወደኋላም ሳይሄድ አንድ ቦታ ላይ ይወሰናል፡፡ የሳሙኤል ቀዳማዊ መጽሐፍ፤ "እርሱ የቅዱሳኑን እግር ይጠብቃል ኃጥኣን ግን ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ" ያለው ለዚህ ሳይሆን ይቀራል?

   መላእክት በመጀመሪያ የሥነ ተፈጥሮአቸው መነሻ ታሪክ ላይ የገጠማቸው ድቅድቅ ጨለማ ነበር፡፡ ከየት እንደመጡ፣ ለምን እንደመጡ፣ በምን እንደመጡ፣ በማን እንደመጡ መርምረው ሊደርሱበት አልቻሉም፡፡ ከነርሱ አስቀድሞ የተፈጠሩት ፍጥረታት እስትንፋስ ያላቸው ባለመሆኑ ዋቢ ምስክር አድርገው የሚያገኙትን ግዙፍ ሕልውና አጡ፡፡ በዚህ መካከል ኢዮር ከተሰኘው ከላይኛው ከተማ "እነሆ ፈጣሪያችሁ" የሚል አንድ ድምፅ ተሰማ፡፡ ይሄ ድምፅ የወጣው ከዚሁ ከጨለማ ውስጥ ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ ድምፁ እውቀትን (ብርሃንን) ላጡት መላእክት ምንም አልፈየደላቸውም፡፡ የገለጠላቸው ምንም አዲስ ነገር የለም፡፡ እዛው ባሉበት ሁኔታ ውስጥ ናቸው፡፡ ግር እያላቸው የድምፁን ባለቤት ለማግኘት ወደላይ ቢያማትሩ ከነርሱ በአንዳች ያልተለየ አካልና ባሕሪይ ያለው ፍጡር አዩ፡፡ "እንዴ አንተማ ከኛው ወገን አይደለህ? እንደምን ፈጠርኳችሁ ትለናለህ?" አሉት፡፡

   ከፍ ብሎ ያለው መልአክ ተቆጣ፡፡ "ምቀኞች" አላቸው፡፡ "የምነግራችሁን ዝም ብላችሁ አትቀበሉም? በቃ እኔ ነኝ አልኩ እኔ ነኝ፤ በሉ አመስግኑኝ" ሲል አመረረባቸው፡፡ በጨለማ ውስጥ የሚነገር እውቀት እንዲህ ያለ ነው፡፡  "ዝምብሉ! ጥያቄ ሳታብዙ አርፋችሁ ተቀመጡ!" የሚል ነው፡፡ ከላይ ያነሣነው ጥቅስ ልክ ነው መሰል፡፡ "ዝም ብለው በጨለማ ይቀመጣሉ" ..

   "እሺ ጥሩ! አንተ ፈጥረኸን እንደሆነ እንግዲያው የመፍጠር ክሒሎት ያለህ ነህና በል ሌላ እንግዳ ፍጥረት አስገኝና አሳየን፥ መስገዱ ኋላ ይደርሳል" አሉ፡፡ ተከራከሩት (የዋዛ አይደሉም)፡፡ በድጋሚ "ምቀኞች" አላቸውና እፈጥራለሁ ብሎ እጁን ከእሳት ቢሰድ ፈጀው፡፡ እሰይ! .. ተነቃበት!

    በዚህ ጊዜ እግዚአብሔር የአርምሞ ዝምታውን ሰበረ፡፡ "ብርሃን ይሁን" የሚል መለኮታዊ ቃሉ በእሑድ ጠዋት የመጀመሪያው ሰዓት ላይ ተደመጠ፡፡ ቃሉ አምላካዊ ባሕሪይ ያለው ነውና፤ መላእክት የሥልጣኑን ኃይል የሰሙት እስከ ባሕሪያቸው ድረስ ነው፡፡ አበው ይህን ጉዳይ ሲያስረዱ፤ "ዓይን ከመጨፈኑ ሲገለጥ በቀጥታ ብርሃን ላይ እንዲያርፍ ሁሉ፤ መላእክትም ብርሃን ይሁን ያለውን ቃል በሰሙ ጊዜ የፈጣሪነቱ ሚስጢር ተገልጦላቸው ምስጋና ጀመሩ" ይላሉ፡፡ ስለዚህ የእግዚአብሔር ድምፅ እውቀትን ገለጠላቸው ማለት ነው፡፡ ጥበብ ተጨበጠችላቸው፡፡ የተከደነው ተከፈተላቸው፡፡ ራሳን መግዛት ተከናወነችላቸው፡፡ አሁን ከዚህ በኋላ ወዲያም ወዲህም ቢንቀሳቀሱ ይችላሉ፡፡

   ሐሰተኛው ድምፅ ግን ይህቺ አምላካዊ ግብር አልተፈጸመችለትም፡፡ በቀደመው ጨለማ ውስጥ ነው፡፡ በፊት ያውቀው ከነበረው ተጨማሪ ሊገለጥለት የሚችል አዲስ እውቀት የለውም፡፡ ምስጋና፣ ክብር፣ ፍቅር፣ ጸጋ፣ .. የሚባሉት የብርሃን ጉዳዮች ከባሕሪዩ ሸሽተዋል፡፡ በሌላ አገላለጽ በመጀመሪያ ሲያወጠነጥነው ከነበረው ዓመፅ፣ ውሸት፣ ትምክህት፣ ክፋትና እልህ ውጪ ሌላ ሊያስብ፣ ሊናገርና ሊሠራ አይችልም፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ብርሃን ለእርሱ አልደረሰችም፡፡ ዲያቢሎስ የሚለው ስያሜም የተሰጠው ይህን መሠረት አድርጎ ነው፡፡

   በመጀመሪያ ከዲያቢሎስ አሳብ መንጭቶ የወጣ ዓመፅ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ፤ ኃጢአት በመገለጫ መልኩ አስገኚ ባለቤቱ የነበረበትን የጽልመት ድባብ ይወክላል፡፡ ጨለማን!

   ጨለማ የኃጢአት ባልንጀራ ነው፡፡ እግር እግሩን ይከተላል፡፡ በሄደበት ይሄዳል፤ በወጣበት ይወጣል፡፡ ገብቶ በተቀመጠበትም ቤት ውስጥ ገብቶ ይቀመጣል፡፡ ሰው ኃጢአትን ፈጽሞ ካጠናቀቃት በኋላ ወዲያው ጨለማ ይወርሰዋል፡፡ ጭንቅ ጭንቅ ይለዋል፡፡ ውድቀት ይሰማዋል፡፡ ባዶነት ያገኘዋል፡፡ ብቸኝነትን ይፈልጋታል፡፡ ከራሱም ከአምላኩም ይሸሻል፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥10)

   "የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነው" የሚያሰኘውም ይሄ ነው፡፡ ኃጢአትን በሠራነው ቁጥር ትናንሽ ሞቶች ይከቡናል፡፡ በእያንዳንዱ የዓመፃ ጊዜዎች ላይ ከውስጣችን እየሞትን .. እየሞትን እንሄዳለን፡፡ ከጸጋ፣ ከበረከት፣ ከጽድቅ፣ ከበጎ ነገር ሁሉ እንሞታለን፡፡ የሞት አገሩ ደግሞ ጨለማ ነው፡፡

   በጨለማ ውስጥ ያለ ባሕሪይ ሩቅ አያይም፡፡ ኸረ ለነገሩ ከቅርብስ ምን ብርሃን ኖሮት ያያል? .. በአንድ የወንጌል ወቅት ላይ እንደዚህ ሆነ ..

"ወደ ቤተ ሳይዳም መጡ። ዕውርም አመጡለት፥ እንዲዳስሰውም ለመኑት። ዕውሩንም እጁን ይዞ ከመንደር ውጭ አወጣው፥ በዓይኑም ተፍቶበት እጁንም ጭኖበት። አንዳች ታያለህን ብሎ ጠየቀው። አሻቅቦም። ሰዎች እንደ ዛፍ ሲመላለሱ አያለሁ አለ። ከዚህም በኋላ ደግሞ እጁን በዓይኑ ላይ ጫነበት አጥርቶም አየና ዳነም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን ተመለከተ።" (የማርቆስ ወንጌል 8፥22-25)

   የሰው ልጅ በኃጢአት አኗኗር እየተመላለሰ ውስጡን ከእግዚአብሔር ብርሃን አርቆት የሆነ እንደሆነ፤ የጽድቅን እውነትና የቅድስናን ኃይል የሚያይበት ዓይኑ ይታወራል፡፡ ነፍሰ-ስውር ስንሆን ደግሞ ምኞቱና ፍላጎቱ የማያልቁለት ዓይማናው ሥጋ ኑሮአችንን ካልመራው፥ ካልተቆጣጠርኩ ይለናል፡፡ የሥጋ እይታ በጠባዩ በቃኝ ብሎ የሚያርፍበት መደላደያ ስሌለው፤ ይዞን ብዙ ቦታ ይዞራል፡፡

   ሥጋ ወደደም ጠላም ከሥጋ የሆነውን ያያል፡፡ መንፈሳዊውን ልየው እንኳ ቢል ተፈጥሮአዊው ባሕሪዩም አይፈቅድለትም፡፡ ስለሆነ ሊደርስበት የሚችለውን አፍአዊ (ግዙፍ አካላዊ) የሆነውን ብቻ ያያል፡፡

   ይህ የሥጋ ነገር በጣሙን የተመቸው ክፉው መንፈስ፤ ረቂቅ ተክለ ቁመናውን ተጠቅሞ ወደ ሕይወታችን በስውር ከተጠጋ በኋላ፤ ልክ እንደርሱ የጨለመ እይታ እንዲኖረን በእግዚአብሔር ላይ ማመፅን ያጨዋውተናል፡፡ ውሸት እንዲለምደን፣ ሐሜት እንዲግባባን፣ ስድብ እንዲጣባን፣ ቁጣ እንዲቀድመን፣ ተንኮል እንዲስማማን፣ ምቀኝነት እንዲሰማን፣ ጥላቻ እንዲያድርብን፣ ክሕደት እንዲቀለን፣ ግፍ እንዲዛመደን፣ ዝሙት እንዲያምረን፣ ስካር እንዲያዝናናን፣ ምቾት እንዲያጓጓን፣ ስስት እንዲይይዘን፣ ስርቆት እንዲቀለን፣ እብሪት እንዲወደን፣ ግለኝነት እንዲወረን፣ ደግነት እንዲርቀን፣ ቸርነት እንዲከብደን፣ ትዕግስት እንዲያጥረን፣ እውነት እንዲጨንቀን፣ ማስተዋል እንዲጠፋን፣ እምነት እንዲያንሰን፤ የመሻት ድንበሩ ወሰን በማይገኝለት የሥጋ ፍላጎታችን ውስጥ ተሸጉሮ ወደ ዓላማው መስመር እያንደረደረ ይመራናል፡፡
   ማየት የተሣነው ሰው መንገዱን በራሱ እርምጃ ሊጓዘው እንደማይችል፤ እንዲሁ የአምላክን ቃልና ፈቃድ ከማየት እምቢ ያልነው እኛም፤ የኑሮ እጃችን መዳፉን ለዲያቢሎስ አሳልፎ በመስጠቱ፤ ሕይወታችን በጊዜ መንገድ ላይ ሲሄድ የሚገኘው ከእግዚአብሔር እየሸሸ ነው፡፡

   "ሰው" ሆኖ የመኖር ልክን በሥጋዊ ሚዛኖች ብቻ ለክቶ የሚሰፍር አመለካከት እንደ ጣዖት ሁለንተናችንን ስለገዛው፤ በኃጢኢት ቀናቶች ተሞልተው ያለፉት ዓመታቶቻችን እግዚአብሔርን ከማየት የተከለከለ ታሪክ በዕድሜያችን ላይ ስለማስቀመጣቸው ገና በደንብ አልተረዳንም፡፡

   እያንዳንዷ በኃጢአት ቆይታ ውስጥ ያለፈችው ደቂቃ የነፍስ ዓይናችንን በበደል ስለት እየደነቆለች መንፈሳዊ እይታችንን በመጉዳቷ፤ ዓለም ላይ በገሐድ ተጨብጦ ከሚታየው ጉዳይ ውጪ ሌላ አተያየት በፍጹም ሊኖረን አልቻለም፡፡ የዲያቢሎስ ሠራዊት ወደ ሰዎች ሕይወት ሲመጣ "ባላጋራ" ይሆን ዘንድ አለውና፤ እነርሱ ከሰማይ (ከእግዚአብሔር ከሆነው) የተለዩበትን ባሕሪይ ለኛ ሰብአዊ ባሕሪይ ከውስጥ በኩል በማጋራት፤ እነርሱ ብቻ ወደሚታያቸው የጥልቁ አድራሻ በዝግታ ይወስዱናል፡፡

   ይህንን ወደ ዘላለማዊ ጽልመት የሚገፋ የመናፍስት ኮሽታ አልባ አካሄድ በራሱ የግንዛቤ ችሎታ በመደገፍ መርምሮ ሊረዳ የማይችለው ሥጋችንም፤ የሕይወትን (ሰማያዊና ምድራዊ) ሙሉ ትርጉም ሲኖር በገበየው የእውቀት ልክ እየጠቀለለ፤ ረቂቁን መንፈሳዊ ጎን ሳያገኘው፥ የመኖር ዘመኑ እስኪያልቅ በአንድ ጎኑ ተንጋድዶ ይኖራል፡፡

   የሥጋው ዓለም ትውልድ ሃይማኖታዊ ሥነ ሕይወትን ከነአካቴው ትቶ የሚገኝበት በተለይ ይሄ ዘመን፤ ኃጢአት ምድርን በመላ የሸፈነ የሰዎች የጋራ ገጽታ እስኪሆን ድረስ በመናፍስት ጥልፍልፍ አሠራር እንደተቀደመ ለማረጋገጥ የዚህ ዘመን ሰው መሆን ብቻ በቂ ነው፡፡ ስለዚህ ከኃጢአት ኋላ ረድፉን ጠብቆ ብቅ የሚለው ጨለማ ሁላችንን በሚያስብል የቁጥር ብዛት የውስጥ ዕውሮች አድርጎናል፡፡ ከዚህም በላይ አስቸጋሪና የመፍትሔ ውስብስነቱን በእጅጉ የሚጨምረው ጉዳይ ደግሞ፤ መድኃኒታችን "ዕውር ዕውርን ቢመራው ሁለቱም ከጉድጓድ ይወድቃሉ" ሲል ያስጠንቀቀበትን ቃል በውል ሳናጤነው፤ አንዳችን አንዳችንን እየመራን እጅ ለእጅ በመያያዝ በረጅም ሰልፍ ተቀጣጥለን የመጋመዳችን ጉዳይ ነው፡፡ (ወላጅ ልጆቹን፣ ወዳጅ ወዳጆቹን፣ አስኳላ ተማሪዎቹን፣ ከተማ ኗሪዎቹን፣ መንግሥት ዜጎቹን፣ .. የሚመራበት ሕግ፣ መመሪያ፣ ጽንሰ አሳብና ፍልስፍና መንፈሳዊ አዕማዶችንና የነፍስ መሥፈርቶችን መጠበቅ የማይችለው፥ ሥጋዊው አእምሮ የወለዳቸው ዕውር ሥርአቶች ናቸው)

   ማየት የማይችልን ሰው ሊመራ የሚችለው ግለሰብ ዓይናማ መሆን እንዲገባው ምንም አያወላዳም፡፡ ወደ ርዕሳችን ጨዋታ ዓረፍተ ነገሩን ስንቀላቅለው፤ የነፍስ ዕውርነትን ሊፈውስልን የሚችለው ብቸኛው መድኃኒት የእግዚአብሔር ብርሃን ነው እንላለን፡፡ ነፍስን የሚያሳውራት ጨለማ ደግሞ ኃጢአትን ተከትሎ ይመጣል ተባብለናል፡፡ በዚህ መሠረት ስንቀጥል የእግዚአብሔር ብርሃን ብለን የተጠራነው ኃይል ኃጢአትን ከሥሩ ነቅሎ በመገርስስ ጥቁር መጋረጃውን ሊቀድበት ይገባል ማለት ነው፡፡

   ይሄን የውስጥ ዕውርነትን በመዳሰስ የሚፈውስ መለኮታዊ መዳፍ ክርስትናችን ንስሐ ስትል ትጠራዋለች፡፡

   የእግዚአብሔርን ፍጹም ቸርነት ተስፋ አድርገው ንስሐ የሚገቡ ምዕመናን፤ ጌታ ከመንደሩ ለይቶ አውጥቶ የዳበሰውን ዕውር ሰው ይመስላሉ፡፡ ምክንያቱም "ለሰው ሁሉ የሚያበራው እውነተኛው ብርሃን" ኢየሱስ ክርስቶስ በምሕረት እጁ ዳስሷቸው፤ አጥርቶ ከማየት የጋረዳቸውን የዓለም፣ የሥጋና የክፉ መንፈስ ጨለማ ይገፍፉታልና፡፡ (የዮሐንስ ወንጌል 1፥9)

   ንስሐ ስንገባ፤ ለዓመፅ ሥራችን ክፍያ ሊሆን ተጠቅራሞ የነበረው የሞት ገንዘብ በመንፈስ ቅዱስ እሳት አመድ እስኪሆን ይቃጠላል፡፡ በዚህ ጊዜ ዙሪያችንን ከብቦ የዘጋው የዲያቢሎስ ጨለማ በእግዚአብሔር የይቅርታ ጸዳል ስለሚሸነፍ፤ ከቅርብም ከሩቅም ሳይቀር ሁሉን መመልከት ይቻለናል፡፡ ዳዊትም የሚመክረን ይሄንኑ ነው፦ "ወደ እርሱ ቅረቡ (ንስሐ ግቡ) [ከዛ] ያበራላችሁማል (ጨለማው ይገለጥላችኋል)፥ ፊታችሁም አያፍርም።" (መዝሙረ ዳዊት 34፥5)

   ስለ ንስሐ የተለያየ ትምህርት የተማሩ አማኞች፤ በቃል ጥሪ የተቀበሉትን የንስሐ ድምፅ ወደ ተግባር ሥጋ መግለጥ ሲቸገሩ ይስተዋላል፡፡ በእርግጠኝነት ክርስቲያኖች በብዛት ካደመጧቸው ስብከቶች መካከል የአንደኝነቱን ደረጃ የሚይይዘው "ንስሐ ግቡ" የሚለው ስብከት ነው፡፡ ሆኖም የትምህርቱ ተደጋጋሚነት ከመለመድ ርቆ የተሻገረ አመርቂ ውጤት አላመጣም፡፡ ስለዚህ ጉዳይ አያሌ አመንክዮቶችን በየዘርፍ በየዘርፉ በመደርደር ጥልቅ ትንታኔ ሊሰጥበት እንዲገባ ቢታወቅም፤ በጽሑፋችን ማዕከላዊ አሳብነት አንድን መሠረታዊና መነሻ ምክንያት ለማስቀመጥ እንሞክር፡፡ ዮሐንስም ይረዳናል፦

"ክፉ የሚያደርግ ሁሉ ብርሃንን ይጠላልና፥ ሥራውም እንዳይገለጥ ወደ ብርሃን አይመጣም" (የዮሐንስ ወንጌል 3፥20)

   በመግቢያችን እንዳወጋነው የእግዚአብሔር ብርሃን ወደ መላእክት ባሕሪይ በደረሰ ጊዜ፤ ዓመፀኛው መንፈስና ሠራዊቱ ከክሕደትና ከትምክህታቸው ባለመመለሳቸው በመረጡት ጽልመት ውስጥ ተውጠው ቀርተዋል፡፡ በሌላ አባባል የጨለማ ግብር የሚሰኘው ክፋት፣ ምቀኝነት፣ ሁከትና ጥላቻው ጥሟቸዋል፡፡ ታማኙ መልአክ "በያለንበት ጸንተን እንጠብቅ" ሲል ያስተላለፈውን የብርታት መልእክት እነርሱም ሳይሰሙት አልቀረም፡፡ ልቦናቸው ኃጢአትን ከማጠንጠንና ከማፈለቅ በጭራሽ የሚታጎል አይነት አይደለም፡፡ እንደው ተሳስተው ጽድቅና እውነትን አያስቡም፡፡

    ይሄ የመናፍስቱ ወደ ግራ ዘሞ የመጥመም ባሕሪይ በሰዎች ሕልውና ውስጥ ደባል ሆኖ ሲገባ፤ በሰዎቹ እንደ ሰዎቹ ሆኖ ይገለጣል፡፡ መንፈሱን "ባላጋራ" ብለን እንደጠራነው እንዳትረሳ! ዲያቢሎስ በመጀመሪያ ወደ ሰዎች ራሱን አጋርቶ፤ በመቀጠል እርሱን ወደ ሰዎች እንደሚያጋራ ልብ በል፡፡ ጉዳዩ መንፈሳዊ ነው፡፡ ማለት እርሱ ወደ ሰው፥ ሰው ወደ እርሱ የሚያያዝበት ሰንሰለት ረቂቅ በሆኑት በጠባይ፣ በአሳብ፣ በፍላጎት፣ በስሜት፣ በእውቀት፣ በእንዲህ .. እንዲህ መልኩ የሚገለጽ እንደሆነ ማስተዋል ይኖርብሃል፡፡

   ስለዚህ .. ሰዎች ለንስሐ ከሚሰጡት ሰብአዊ አረዳድ ጀርባ ሰፊ ጥናት ያልተደረገበት የመናፍስት ሽሽት እንደሚኖር ከተጨዋወትናቸው አሳቦች አንጻር መጠቅለል እንችላለን፡፡ ወንጌላዊው እንደተናገረው፤ ንስሐ የኃጢአትን ጨለማ የሚገልጥ የእግዚአብሔር ብርሃን በመሆኑ፤ ጨለማን ጎሬያቸው አድርገው ለክፋት ተልዕኮአቸው የሚያደፍጡት ክፉ መናፍስት መኖሪያቸው በቀላሉ ላለማስፈረስ ወጥረው መታገላቸው የሚጠበቅ ነው፡፡ ይህንን የመናፍስቱን ድብቅ ትግል ለመረዳት፤ ከራሳችን ጀምሮ በእምነት ታዛ ሥር እንኖራለን የሚሉ ሰዎችን ሁሉ "በኃጢአት ተይዞ እንደመሞት ያለ ከባድ ዕዳ ከፊታችሁ ሳለ፥ ንስሐ ስለምን አትገቡም?" ተብለው ሲጠየቁ በሚሰጡት ምላሽ ተንተርሰን፤ የክፉዎቹን ስልታዊ ሴራና በባሕሪይ ያለ ግፊት ልናስተውለው እንችል ይሆናል፡፡

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
🌼 ወትባርክ አክሊለ ዓመተ ምሕረት🌼
         🌸መዝ ፷፬ ፥ ፲፩
🌼 ዓመታትን በቸርነትህ ታቀዳጃለህ 🌼


🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸🌸
እንቋዕ አብጽሐክሙ አብጽሐክን እም ዘመነ ማቴዎስ ኀበ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በፍቅር ወበጥዒና ሠናይ በዓል ይኩን ለኲልክሙ

እንኳን ከዘመነ ማቴዎስ ወደ ዘመነ ማርቆስ በሰላም በፍቅር እና በጤና አደረሳችሁ አደረሰን።


       🌸🌸 መልካም በዓል 🌸🌸


🌼🌼🌼 ሠናይ ሐዲስ ዓመት 🌼🌼🌼

🕊🌻🌻🌻🌻🌻🕊
🌻🌻 መልካም 🌻🌻️
🌻🌻  አዲስ    🌻🌻
🌻🌻  ዓመት   🌻🌻️
🌻️🌹🌾🌻💐🌷🌻
🕊🌻🌻🌻🌻🌻️🕊
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌺 መልካም 🌺🌻
🌻🌻    በዓል!  🌻🌻
🌻🌻🌻🌻🌻🌻🌻
🌻🌻💐💐💐🌻🌻
🌻🌺   እንኳን   🌺🌻
🌻🌹አደረሳችሁ🌹🌻
🌻🌻🌾🌾🌾🌻🌻
##ልጄ_ሆይ_እንደ_ዘመኑ_አንተም_ተለወጥ
~~~

#ልጄ_ሆይ....... ወጣትነት ፈትኖህ፤ለስጋህ አድልተህ፤ነፍስህን አቀጭጨኻት ከአለም የኖርክበትን ዓመትህን ጥለኸው በንሰሐ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

#ልጄ_ሆይ ..... በአዲስ አመት ለአምላክህ የሚገባህን ግብር ትፈፅም ዘንድ በፍቅሩ አፀድ እንድትገኝ ካለመታዘዘ ተለወጥ

#ልጄ_ሆይ ....... በአፈር ከሚሸነፈው ስጋዊ ዘርህ ወጥተህ ሰማያዊነትን ከሚያለብስህ ከማይጠፋው ሰማያዊ ዘር ክብረት ታደርግ ዘንድ ሰውን ካለመውደድ ጥላቻ ተለወጥ

#ልጄ_ሆይ ...... በምክንያቶች ተደልለህ አፅዋማትን ዘለህ፤ምስጋናን ነፍገህ፥አገልግሎትን ንቀህ ከአለም ጫጫታ ውስጥ የዘፈቀውን ማንነትህ እንዳያጠፋህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ �

#ልጄ_ሆይ ...... ዲያቢሎስ በቃል እንዳያስትህ፤በማማለል እንዳይጠልፍህ የመንጋውን ጠባቂ ቃልን ስማ፤ የመታዘዝን በረከት ታገኝ ዘንድ ከትምህክትህ እንደ ዘመኑ አንተም ተለወጥ

#ልጄ_ሆይ .....ቀናት ሳይሆን መንፈስህ ይለወጥ፤ፀሐይ ሳትሆን የህይወት ጀንበርህ ይለወጥ።

#ልጄ_ሆይ ......ዕለታት አይሰልጥኑብህ፤ ዘመናት  እስከ ሞትህ ጥግ ድረስ እስኪገፉህ ሳትጠብቅ አንተም እንደ ዘመንህ ተለወጥ

#ልጄ_ሆይ .....የእግዚአብሔር ፍቅር ለተከፈተ ልብ ቸር ነው ። ርህራሄው ጥልቅ ነው ። በአምሳሉ ፈጥሮሃል እና እንዳትጠፋ አንድያ ልጁን ለሞት አሳልፎ እስከመስጠት የደረስ ጥልቅ ፍቅር አሳይቷል ። ስለዚህ ከዘመንህ ቀድመህ ተለወጥ።

#ልጄ_ሆይ ...አዛኝቷን ተለማመን፤መላአኩን ተማለደው ፤ቀደምት ቅዱሳን አባቶችህን ጥራ፤ ፃድቃንን ዘክር እንጅ ላለመለወጥ ተማምለው ቀናት ብቻ ከሚለወጥባቸው ሰልፈኞች ተርታ አትገኝ ።

|በንሰሀ ወደ በረቱ የምንመለስበት ዘመን ይሁንልን|


የቅዱሳን አምላክ ልዑል እግዚአብሔር  ዘመነ ማርቆስ ዓመቱን ይባርክልን፡፡ አሜን!!!+++

       የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼  ​​💚 @bemaledanek 💚
       💛 @bemaledanek 💛
     ❤️ @bemaledanek ❤️                       
🌼                                     🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የዘንድሮ ሰው ይበለን፡፡

        "ትጋትን ሁሉ እያሳያችሁ በእምነታችሁ በጎነትን ጨምሩ፥ በበጎነትም እውቀትን፥ በእውቀትም ራስን መግዛት፥ ራስንም በመግዛት መጽናትን፥ በመጽናትም እግዚአብሔርን መምሰል፥ እግዚአብሔርንም በመምሰል የወንድማማችን መዋደድ፥ በወንድማማችም መዋደድ ፍቅርን ጨምሩ።" (1ኛ ጴጥ. 1፥5-7)

@bemaledanek
"እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላም አደረሳችሁ !

"የመስቀል በዓል ታሪክ።

"የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ቅድስት እሌኒ በሮም እና በግሪክ አገሮች ላይ ንጉሰ ነገስት ሆኖ የተሾመው በሃይማኖት አህዛባዊ የነበረው ንጉስ ቁንስጣ የተባለ ታዋቂ ሰው አግብታ የነበረች አይሁዳዊ ሴት ናት። አይሁድ ክርስቶስን የተሰቀለበትን መስቀል ህሙማንን እየፈወሰ፣ አይን እያበራ፣ ለምፅ እያነፃ ፣ ጎባጣ እያቃና ፣ አጋንንትን እያስወጣ በአጠቃላይ ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ይሰራቸው የነበሩትን የተአምራት ስራ በመስቀሉ ሃይል ይሰራ ስለነበር በዚ የመስቀሉ አስደናቂ ተአምራት ብዙ ክርስቲያኖች ከአህዛብም ወገን ከአይሁድም ዘንድ እያመኑ በመስቀሉ ሃይል ምህረት እያገኙ በቁጥራቸው እየበዙ በመምጣታቸው ጌታን ሰቅለው የገደሉት አይሁድ በምቀኝነት ተነሳስተው መስቀሉን ለምልክት ግራ በሚያጋባ ቦታ እና ሰዎች ሁሉ መረጃ እንዳይሰጡ በማድረግ፤ ሁለቱ ወንበዴዎች በግራ እና በቀኝ የተሰቀሉባቸው ሁለቱን መስቀሎች አንዱን ከአንድ ተራራ፣ አንዱን ከሌላ ተራራ አድርገው በመካከል ጌታ የተሰቀለበትን መስቀል ለማሳሳት እና ግራ ለማጋባት በሚያመች ሁኔታ የጌታ መስቀል የተቀበረበትን ቦታ በከፍተኛ ደረጃ እያስተባበሩ በየቀኑ በአካባቢ ያሉ ሰዎች ሁሉ ቆሻሻ እንዲጥሉበት ወይም እንዲደፉበት ይደረግ ስለነበር ከጊዜ በኋላ ቦታው ቀደም ሲል የነበረበትን ቅርፅ አጥቶ ከፍተኛ ተራራ መሆን ችሏል።

ምንም እንኳን መስቀል ለማውጣት የሚያስችል መብትና አቅም ያለው አካል ባይገኝም በትክክል መስቀሉ የተቀበረበትን ቦታ የሚያውቁ በአካባቢው ብዙ ክርስተያኖች እና ተቆርቋሪዎች ይኖሩ ነበር። ከጌታ ልደት በኋላም በ 70 ዘመን በንጉሱ ጥጦስ የወረራ ምክንያት ቅድስት አገር እየሩሳሌምና አካባቢዋ ስለፈራረሰችና በህዝቡ ላይ ከፍተኛ እልቂት በመድረሱ ከጊዜ በኋላ መስቀሉ የተደፈነበት ቦታ የት እንደሆነ ለማወቅ አልተቻለም።

በዚህ ምክንያት የተለያዩ የእግዚአብሔር ሰዎች የመስቀሉ መቀበር ቢያሳዝናቸውም ምንም ማድረግ ባለመቻላቸው ከ300 አመት በላይ በመሬት ተዳፍኖ ቆይቷል። ከዚህ በኋላ ግን በ400 ክፍለ ዘመን (327) ከላይ እንደገለፅነው የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒ ባለችበት አገር ሆና ይህን ታሪክ ትሰማ ስለነበር መስቀሉን አስቆፍራ ለማስወጣት ከልጇ ከንጉስ ቆስጠንጢኖስ ፈቃድ ተቀብላ ወደ እየሩሳሌም ጉዞዋን አቅንታለች። ምክንያቱም አህዛባዊ ከሆነው ከቁንስጣ የወለደችውን ልጇን ቆስጠንጢኖስን ክርስቲያን እንዲሆንላትና የእግዚአብሔር አገልጋይ እንዲሆንላት እግዚአብሔርን ትለምነውና መስቀሉን ከተቀበረበት ለማውጣትም ሁሌ ፈጣሪዋን ትለምነው እንደነበረ የቤተክርስቲያን ታሪክ ይናገራል። ንግስት እሌኒ እየሩሳሌም ከደረሰች በኋላ አስቀድማ ባጠናችው ታሪክ መሰረት መስቀሉ ይገኝበታል ብላ የምትገምተውን ጉብታ ቦታ ወይም ተራራማውን ቦታ ሁሉ ለማስቆፈር ብትሞክርም ልታገኘው ባለመቻልዋ፤ በአካባቢው የሚኖሩትን አይሁዳውያንም ጠይቃ ለመረዳት ብትሞክርም ስለ ጉዳዩ እውነቱን የሚያውቅ ባለማግኘትዋ በልዩ ፀሎት እግዚአብሄርን መጠየቅ ቀጠለች በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሔር ፈቃድ ሆኖ ስለነበረ በዋሻ ውስጥ ተሰውሮ የሚኖር ኪራኮስ የሚባል አንድ አረጋዊ (ሽማግሌ) የንግስቲቱን ድካም ተመልክቶ ስለመስቀሉ ምስጢራዊ ታሪክ ይሰማ ስለነበረ የሚከተለውን ምስጢር ነገራት  “አንቺም አትድከሚ ሰውም በከንቱ አታድክሚ ፤ ብዙ እንጨት ሰብስበሽ እንጨቱን በአንድ ቦታ ከምረሽ (ደምረሽ) ብዙ እጣንም ጨምረሽ በእሳት ደመራውን ብታቃጥይው የእጣኑ ጭስ ወደሰማይ ወጥቶ ወደታች ሲመለስ መስቀሉ ባለበት በማረፍ መስቀሉ ያለበትን አቅጣጫ የት ቦታ ላይ እንዳለ ትረጂያለሽ” አላት። እሷም ያላትን ሁሉ አደረገች።

የደመረችውንም ደመራ በከፍተኛ ፀሎትና ምህላ እሳቱ ሲቃጠል ከደመራው የወጣው የእጣኑ ጭስ ወደላይ ወደ ሰማይ ወጣና ቅድመ እግዚአብሔር መሄዱን አመላክቶ ተመልሶ መስቀሉ ባለበት ቦታ ላይ እንደ ከዘራ ተቆልምሞ መስቀሉ ያለበትን ቦታ በእጅ ጠቁሞ የማሳየት ያህል ለንግስት እሌኒ ቦታውን አረጋግጦላታል። ስለዘህ ጉዳይ ታላቁ ኢትዮጲያዊ ሊቅ ቅዱስ ያሬድ ሲናገር “እጣኑ ወደላይ አመላከተ፤ የእጣኑ ጭስ ደግሞ ወደመሬት ሰገደ ፤ አይሁድ በጎለጎታ የቀበሩት እፀ መስቀል ዛሬ ተገኘ” በሏል።

ንግስት እሌኒ ማስቆፈር የጀመረችው መጋቢት 10 ቀን ነው፤ መስቀሉ የወጣበት ደግሞ መስከረም 17 ቀን ነው ተብሎ በቤተክርሰቲያን ታሪክ ይነገራል። በዚህም ምክንያት መስከረም 16 ቀን በዋዜማው በየአመቱ የደመራ በአል በአደባባይ በከተማም በገጠር አካባቢዎችም ችቦ እየተበራ ይከበራል፣ እዮሃ አበባዬ መስከረም ጠባዬ እየተባለ በባህላዊ ዜማ ይከበራል። ዘመኑ የፅጌ ዘመን ወይም የአደይ በመሆኑ ይሄንን ወቅቱን እና ግዜውን የሚገልፅ ባህላዊ እና መንፈሳዊ ዝማሬ እንደየአካባቢው ሁኔታ  ለደመራ በአል በተጋጀው ቦታ ላይ የአካባቢው ምእመናን በሃይማኖት መሪነት መስቀሉን ይለኩሳሉ። ለመስቀሉ ክብር በየአካባቢው ባህላዊ ሁኔታ በዚሁ ስርዓት ይከናወናል። አንዳንዶች ከሃይማኖታዊ ስርዓት ወጣ ባለ ሁኔታና አላማውን እየለቀቁ የመምጣታቸው ሁኔታ በስፋት ይታያል። ያም ሆነ ይህ የደመራ በአል ወይም የመስቀል በአል በተለይ በአገራችን ዋና መዲና በአዲስ አበባ በመስቀል አደባባይ እጅግ አለምን የሚያስደምም ደረጃ በከፍተኛ መንፈሳዊ ተመስጦ በየአመቱ ሲከበር እናያለን። ይህንን በአል ለማክበር ከአለም ዙርያ የሚመጡ ቱሪስቶችም ስፍር ቁጥር የላቸውም። ምንም እንኳን ዛሬም የመስቀሉ ጠላቶች ብዙ ሰዎች ቢኖሩም በዚሁ የበአሉ ተካፋዮች በመሆን  ያሳልፋሉ።

(ይቀጥላል)👇
ስለ #መስቀል እና  የመስቀል #ደመራ በአል

(ክፍል 2)

ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ስለተሰቀለበት ቅዱስ መስቀል ሲነሳ፤ በተዋህዶ ቤተክርስቲያን አማኞች ዘንድ ትዝ የሚለን እና የማይረሳን ታላቅ ሚስጢር አለ፤ ይህም በቀራኒዮ አደባባይ ስለኛ በደል የሞት  ካሳ ሊከፍል ወይም ስለኛ ቤዛ ሊሆን በመስቀል ላይ የዋለው እና ታላቅ ፍቅሩን የገለፀልን ጌታችን መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው። ይህን ታላቅ ምስጢር ዘወትር የሚያስታውሱ ክርስቲያኖች ሁሉ የመስቀሉ ምስጢር ከልባቸው አይጠፋም። ፈጣሪ እግዚአብሔር ለነብዩ ሙሴ ህገ ኦሪትን ሲያስተምረው “ማንም ሰው ለሞት የሚበቃውን ኅጢአት ቢሰራ እንዲሞትም ቢፈረድበት በእንጨትም ላይ ብትሰቅለው በእንጨት ላይ የተሰቀለ በእግዚአብሔር ዘንድ የተረገመ ነውና ሬሳው በእንጨት ላይ አይደር ነገር ግን አምላክህ እግዚአብሔር ርስት አድርጎ የሰጠህን ምድር እንዳታረክስ በርግጥ በዚያው ቀን ቅበረው።” (ዘዳ 21፥22- 23 )

ነገር ግን በብሉይ ኪዳን ለሞት በሚያበቃ ወንጀል በእንጨት ተሰቅለው የሞቱ ሰዎች እንደ እርኩስ ነገር ይቆጠሩና ምድርንም ያረክሷታል ተብሎ ይቆጠር እንደነበረ የአለም መድኅኒት ኢየሱስ ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል ለቤዛነትና ለካሳ እራሱ ቅዱስና ብሩክ አድርጎ በሕግ ከእኛ እርግማንን አርቆ ነፃ እንድንወጣ አድርጎናል። ለዚህም ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ በገላትያ ለሚኖሩ ክርስቲያኖች “በእንጨት የሚሰቀል ሁሉ የተረገመ ነው ተብሎ ተፅፏልና፤ ክርስቶስ ስለ እኛ እርግማን ሆኖ ከሕግ እርግማን ዋጀን።” (ገላ 3፥13)

ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የአለምን ኅጢአት በመስቀሉ ከማስወገዱም በላይ የተጣሉትን 7ቱን መስፃርራን አስታርቆበታል። ለአህዛብም ሰላሙንና ታላቅ ፍቅሩን ገልፆበታል። ስለዚህ ቅዱስ ጳውሎስ በመልእክቱ “በሥጋውም በመካከል የነበረውን የጥል ግድግዳ አፍርሶ ጥልን ሻረ ሁለቱንም አድሶ አንድ ያደርጋቸው ዘንድ በስርዓቱ የትእዛዝን ሕግ አጠፋ፤ ዕርቅንም አደረገ “ ኤፌ 2፤14 -17
እግዚአብሔር ሁሉንም ይቅር ይለው ዘንድ በመስቀሉ ባፈሰሰው ደም በምድርና በሰማያት ላሉ ሁሉ ሰላምን አደረገ” ቆላ 1፤20

እንግዲህ በ21ኛ መቶ ክፍለ ዘመን ብዙዎቹ የመስቀሉ ጠላት ሆነው እናያለን፤ እነዚህ የመስቀሉ ጠላቶች ይመጡ ዘንድ የግድ እንደሆነ ሲናገር ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስ “ ወንድሞች ሆይ እኔን የምትመስሉ ሁኑ  ብዙወች የክርስቶስ ጠላት ሆነው ይመላለሳሉና፤ ብዙ ግዜ ስለነሱ እንደምነግራችሁ ልዩ አካሄድ የሚሄዱ ብዙዎች አሉና አሁንም እነርሱ የክርስቶስ የመስቀሉ ጠላቶች እንደሆኑ በግልፅ እያለቀስሁ እነግራችኋለሁ” (ፊልጰ 3፤17)

እንግዲህ ክርስቲያኖች ሁላችሁም ስለ ክርስቶስ መስቀል መመስከርና መናገር ክብር ስንጂ ውርደት ስላለሆነ ጌታችን መድኅኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወደኝ ቢኖር መስቀሌን ተሸክሞ ይከተለኝ እንዳለ መስቀሉን የመሸከም ሃላፊነት የሁሉም ክርስቲያኖች አላማ መሆን ይገባዋል። በእርግጥ ግዜ እና ዘመን በሚያመጣቸው ፈተናወች የመስቀሉ ወዳጆች ሆነን በመገኘታችን እንደየአካባቢው ብዙ መከራ ሊመጣብን ይችላል። ይህንን ደግሞ እኛ ክርስቲያኖች በጠላቶች ዘንድ ስንሞት እየበዛን እንደሆነ፣ ስናዝንም እየተደሰትን እንደሆነ፣ ስንሸነፍም እያሸነፍን እንደሆነ ልናምን ይገባል። ክርስቶስም ሞትን ለሚመስል ሞት ሞቶ ነው የሁላችንንም ሞት የደመሰሰልን። ከዚህ የተነሳ የ 2015 ዓም የደመራ በአልን እስካሁን እንደተለመደው በታላቅ ድምቀት ለማክበር በዘመናችን የአገራችንና የአለማችን ፈተና ሆኖ የተከሰተው የዘመኑ ወረርሽኝ ወይም ጦረነት ይህን ለማድረግ  ክርስቲያን ፈተናን እና ሞትን እንዳይፈራ የእግዚአብሔር ቃል ይናገራልና ለሌሎቹ ፈተና ምክንያት እንዳንሆን ስርዓቱን በጠበቀ መልኩ ሆነን ከመስቀሉ በረከት ለመካፈል የልጅነት ድርሻችንን ልንወጣ ይገባናል።

በአጭሩ ዛሬ መጋቢት 10 ቀን የምናከብረውን የመስቀል በዓል ንግስት እሌኒ መስቀሉን ለማግኘት ማስቆፈር የጀመረችበት ቀን በማሰብ ለበረከት ያህል ስለ መስቀል ደመራ በአል አከባበር እና መሰረታዊ ታሪኩን በተነሳንበት የትምህርት ርዕስ ይህንን ያህል ካልን ወደፊት ስለ መስቀሉ ክብር በስፋት ልንማማር ስለምንችል ለግዜው መልእክቱን እዚህ ላይ እንፈፅማለን።

የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የመስቀሉ በረከት በሁላችን ይደርብን፤ ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቀን።



  የተለያዩ ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
      •➢ 👇  ለማግኘት // 👇
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
🌼🌼  ​​💚 @bemaledanek 💚
       💛 @bemaledanek 💛
     ❤️ @bemaledanek ❤️                       
🌼                                     🌼
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.2•  ንስሐ ለምን እንግባ? ክፍል - ፫                      ✞ ብርሃንን ለማየት ✞    ጨለማ በሥነ ፍጥረት መዝገብ የመጀመሪያው ቀን ላይ ሰፍሮ ይገኛል፡፡ ከሰባቱ ቀዳማይ ፍጥረታት መካከል አምስተኛው እርሱ ነው፡፡ ብርሃንን ቀድሞ መጥቷል፡፡ "አክሲማሮስ" የተሰኘ የሥነ ፍጥረት መጽሐፍ ስለ ጨለማ ተፈጥሮ ሲያብራራ፤ "ጨለማ በዓይን እንደማይታይ በእጅ እንደማይዳሰስ…
2•  ንስሐ

   2.2•  ንስሐ ለምን እንግባ?

ክፍል - ፬

                   ✞ አዲሱ ወይን እንዲሞላ

"በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።" (የማቴዎስ ወንጌል 9፥17)

አንድምታ ጸሐፊዎች ጥቅሱን እንዲህ ሲሉ ይተረጉሙታል፦
   /ወአልቦ ዘይውዲ ወይነ ውስተ ዝቅ ብሉይ/
        ባረጀ ራዋት ጉሽ ጠጅ የሚሾም የለም፡፡
   /ወእመ እነሰ ዝቁሂ ይነቅዕ ወወይኑሂ ይትከዓው/
        ቢሾሙ ግን ራዋቱም ይቀደዳል ወይኑም ይፈሳል፡፡
   /ወባሕቱ ለወይንሰ ሐዲስ ውስተ ዝቅ ሐዲስ ይወድይዎ/
         ጉሹን ጠጅ ግን በአዲስ ራዋት ይሾሙታል፡፡
    /ወይትዓቀቡ ፪ሆሙ በበይናቲሆሙ/
          እስበሳቸው በአንድነት ይጠባበቃሉ፤ አዲሱ ራዋት የጠጁን ፍላት ይችለዋል፤ የጠጁም ፍላት አዲሱን ራዋት ያለፋዋልና፤ አንድም ሐዋሪያትን በልጅነት ባልታደሰ ሰውነታቸው ሕግ ጠብቁ የሚላቸው የለም፡፡ /ወእመ አኮሰ/ ጠብቁ ቢሏቸውም ሕጉም ይፈርሳል ሰውነታቸውም ይጎዳልና፡፡ /ወባሕቱ/ በልጅነት በታደሰ ሰውነታቸው ግን ወንጌልን ጠብቁ ይሏቸዋል፡፡ /ወይትዓቀቡ/ እስበሳቸው ይጠባበቃሉ፤ እሳቸውም ሕጉን ይጠብቁታል ሕጉም እሳቸውሞ ይጠብቃቸዋል፡፡

   የዮሐንስ ደቀመዛሙርት ናቸው አሉ .. በአንዱ ጊዜ ላይ ወደ ክርስቶስ ጠጋ ብለው ይጠይቁታል፡፡ "እኛና ፈሪሳውያን፥ ብዙ ጊዜ [ነው] የምንጦመው፥ ደቀመዛሙርትህ ግን የማይጥሙት ስለምንድር ነው?" ይሉታል፡፡ የግብዝነት ድምጸት የቃኛት ጥያቄ፡፡ እነ እገሌ እንደኛ የማይሆኑት ምን ቢቆርጣቸው ነው? አይነት ግብዝነት፡፡ ጌታም "ሚዜዎች ሙሽራው አብሯቸው እስካለ ድረስ ለምን ብለው ይዘኑ?" ሲል መለሰላቸው፡፡ ቀጠለናም .. "በአረጀ አቁማዳ አዲሱን የወይን ጠጅ አያስቀምጡም.." የሚል ጥሩ ምሳሌ ጨመረላቸው፡፡

   የአዲሲቱ አቁማዳ ምሥጢር በሕይወት ግብር የተገለጠለት ሐዋሪያ በኋላ፤ "ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል" በማለት ጽፎአል፡፡ (2ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 5:17)

    በቀደመ ምዕራፍ ትምህርታችን ንስሐ ማለት "ፊትን ወደ እግዚአብሔር ጀርባን ለዓለም" ሰጥተን የምንጓዝበት መንፈሳዊ ጎዳና ነው ተባብለናል፡፡ በዚህ አባባል መሠረት ኃጢአት ደግሞ ማለት ፊታችን ወደ ዓለም እንዲዞር የሚያስገድድ በሥጋ ፈቃድ ላይ የሚሠለጥን የዲያብሎስ ኃይል ነው፡፡ "ወደ መጣህበት ተመለስ" የተባለው አዳም ከእግዚአብሔር ተለይቶ ከገነት ሲወጣ ፊቱን የሰጠው ከፀሐይ በታች ላለቺው ዓለም ነው፡፡ ስለዚህ ከአምላክ ፈቃድና ትእዛዝ መውጣት (ኃጢአት መፈጸም) አቅጣጫችንን ወደ ዓለም ያዞረዋል መባሉ ትክክል ነው፡፡

   የመጀመሪያው ሰው (አዳም) ፊቱን ከእግዚአብሔር አዙሮ ከወጣ በኋላ ነው ልጆችን የወለደው፡፡ በመሆኑም የአዳም ልጆች በሙሉ ከመለኮታዊው ፈቃድ በተለየ ቤተሰብ የተወለዱ ስለሚሆኑ ከጽድቅ ይልቅ ለኃጢአት ቅርብ ናቸው (ቃየንን ያስቧል)፡፡ በሌላ አነጋገር የአዳም ዘር እየተዋለደ በጊዜ ወደፊት ውስጥ መኖርን በቀጠለ ልክ፤ የሰው ልጅም ባሕሪይ የእግዚአብሔርን እውነትና ሥራ ከማወቅ እየሸሸ .. እየሸሸ፤ በሚመላለስባት ሥጋዊ ዓለም ውስጥ በሁለንተናዊ አኗኗሩ እየተወሰነ .. እየተወሰነ ይሄዳል፡፡

   ዳግማዊው አዳም መድኃኒታችን ፊቱን አዙሮ የጠፋ ማንነታችን ፍለጋ ተከትሎን ወደ ምድር ሲመጣ፤ የሰው ልጅ መንገድ የሳተ ባሕሪይ ገጹን ወደ እግዚአብሔር መንግሥት እንዲመልስ የእርሱን ሕይወት አርአያ (ወንጌል) አድርጎ አስቀመጠልን፡፡ በመዋለድ ሕግ እያለፈ ከአምላክ ፈቃድ እየወጣ በኃጢአት የሚጠፋውን አሮጌውን ሥርዓት ለወጠናም ከማይጠፋው ዘር የምትወልደንን አዲሲቱን እናት (ቤተክርስቲያን) ሰጠን፡፡ ይህ ማለት አንድ ማንኛውም ምዕመን በመሲሑ ሰው መሆን አምኖ በስሙ የተጠመቀ ሲሆን፤ "ከውኃና ከመንፈስ" የተወለደ አዲስ ስብእና (የእግዚአብሔርን ልጅነት) ይዞ በምድር የጽድቅ ጉዞ በኩል ወደ መንግሥተ ሰማያት (ወደ አባቱ ርስት) የሚራመድ ሰው ይሆናል፡፡

   ይህንን ሰማያዊ እርምጃ የሚቃወመው ክፉው መንፈስ፤ አሁን እዚህ ጋር ዕንቅፋት ሆኖ ይመጣል፡፡ ዳግም የተወለደው መንፈሳዊው ስብእና ጉዞውን ወደ ነፍሱ ፈቃድ አድርጎ እስከመጨረሻው በጽድቅ እንዳይቀጥል፤ ኃጢአትን ፈጽሞ ልክ እንደ አዳም ቤተሰብ ከእግዚአብሔር ፈቃድ አፈንግጦ በመውጣት ፊቱን ወደርሱ እንዲያዞርለት ዘወትር ፈተና እያመጣ ይዋጋዋል፡፡

   በዚህ ጊዜ፥ ንስሐ የሚባለው አንዱ የእምነት ጦር ዕቃ፥ ለሚገጥመን መንፈሳዊ ውጊያ በአገልግሎት ጥቅም ላይ ይውላል፡፡ ማለት ከዳግማዊው ክርስቶስ ተወልደን የማይጠፋው አዲሱ ዘራችንን በኃጢአት ለማጥፋት የሚፋለመውን ኃይል የምንታገለው በንስሐ ሕይወት ታግዘን ነው፡፡ ከላይ ባየነው የጥቅሱ አንቀጽ ስናወራ፤ ንስሐ በጥምቀት ያገኘውን አዲሱን ልጅነት (አዲሱን አቁማዳ) የሚያስጠብቅልን መንፈሳዊ እድሳት ነው፡፡

   አሮጌው አቁማዳ ጥገና አግኝቶ ካልታደሰ፥ ወይን ባኖሩበት ጊዜ መሸከም አቅቶት እንዲያፈስ፤ የንስሐ ሕይወት የሌለው ክርስቲያንም መንፈሳዊ ሕይወትን አጽንቶ ለመኖር የሚያስችለው የነፍስ ጉልበቱ በኃጢአት ሸክም ምክንያት ተዳክሞ ይዝልበታል፡፡ በደነደነ አማርኛ ያለ ንስሐ ኃይል የእግዚአብሔርን ሥራዎችና ሕግጋት በርትቶ ለመፈጸም አይቻለንም፡፡

   በኃጢአት ድምፆች የሰነበተ ጆሮ ቃለ እግዚአብሔርን ጸንቶ መስማት አይሆንለትም፡፡ በኃጢአት ቃላት የከረመ አንደበት ጽድቅን በርትቶ ማውራት አይሳካለትም፡፡ በኃጢአት ትዕይንቶች የተከበበ ዓይን ሃይማኖታዊ ምልከታው ሊዘልቅለት አይችልም፡፡ በኃጢአት አሳቦች የተዳከመ አእምሮ በመንፈሳዊ ቦታ ላይ ንቁ ሆኖ አይቆይም፡፡ ምክንያቱም በአረጃው አቁማዳ አዲሱ ወይን አይሞላም፡፡

   ያልተሠረዩ የኃጢአት ጊዜዎች ከሕይወት መዝገቡ ላይ ያልተፋቁለት ግለሰብ፤ ሕገ እግዚአብሔርን ጠብቆ መኖር ይሳነዋል፡፡ "እኔ ቅዱስ እንደሆንኩ እናንተም ቅዱሳን ሁኑ" የሚለውን ዐረፍተ እውነት ገልብጠን ብናነበው፤ "እኔ ርኩስ እንደሆንኩ እናንተም ርኩሳን ሁኑ" የሚል ይሆናል፡፡ የዲያቢሎስ ጥሪ ሆነ ማለት ነው፡፡ በዚህ ጥሪ መሠረት ደግሞ፤ በኃጢአት የወደቀ የኑሮ አጋጣሚያችን፥ በሌላ የኃጢአት ውድቀት ላይ ተሰናክሎ እንዲገኝ፥ ተጨማሪ የጥፋት አጋጣሚዎችን ክፉው ከኛ ውስጥ ሆኖ ይስባል፡፡

   ስለዚህ፥ ንስሐ በመግባት በኃጢአት የተሸነቆረ ሕይወታችንን በቶሎ ካልጠገንነው፤ ተጨማሪ የኃጢአት ሰዓቶች በዕለቶቻችን መካከል ሥጋዊ ምክያትን ሸፋን አድርገው እንዲገለጡ ጠላት ስለሚተጋ (ሌሎች ኃጢአቶችን ያለማቋረጥ ወደኛ ስለሚጎትት)፤ ጥቂት ሆና የጀመረቺው የኃጢአት ቀዳዳ ቀናት በተተኩ ቁጥር በቀስታ እየሰፋች .. እየሰፋች በመሄድ፤ የጸሎት ወይንን፣ የስግደት ወይንን፣ የቁርባንን ወይንን፣ .. ቋጥረን የማንይዝ የጽድቅ ሰባራዎች ሆነን እንቀራለን፡፡
  ስለ ወይን ስናወጋ፤ የቃናው ሠርግ ቤት ሳይነሳ ቢዘለል መቼም ያስተዛዝበናል፡፡ ወላጂቱ ማርያምና ከልጇ ጋር የታደሙበት የገሊላው ሠርግ፤ "በወይን ጠጅ ማለቅ" ምክንያት ወደ ውጥረት እየገሰገሰ ነበር፡፡ ታዳሚዎች የሚስተናገዱበት መጠጥ በመጥፋቱ አሳላፊዎች ጭንቀት ላይ ወድቀዋል፡፡ ቀላል ጉዳይ አይደለም! ገበታ ያልተሟላለት ድግስ ለጠሪዎቹ ታላቅ ሐፍረት ያስከትላል፡፡

   የጓዳውን ችግር አስተውላ ያየች እናቲቱ፤ ጉዳዩን ለመድኃኒቱ አሳወቀች፡፡ ወደ አገልጋዮቹም ተመልሳ "የሚላችሁን ሁሉ አድርጉ" አለቻቸው፡፡ እርሱም "ጋኖቹን እስከ አፋቸው ውኃ ሙሉአቸው" ሲል አዘዛቸው፡፡ ጸሐፊው ሉቃስ እንደሚለው እነዚያ ጋኖች በአይሁድ የማንጻት ልማድ መሠረት ታጥበው ከሁለት እስከ ሦስት ያህል የሚደርስ የእንስራ ውኃን ይይዙ ነበር፡፡

   ጉዳያችን ከጋኖቹ ነው፡፡ ከጋኖቹም የመታጠባቸው ጉዳይ፡፡ አንባቢ አስተውልልኝማ! ከወይን ጠጅ የተሟጠጡት ጋኖች ከውስጣቸው የቀረው እንጥፍጣፊ አተላ ተደፍቶና በውኃ ታጥቦ ካልጸዱ፤ በተአምራቱ ኃይል ወይን ይሆን ዘንድ ያለው ንጹሕ ውኃ ሊሞላባቸው አይችልም፡፡ ምክንያቱም የአተላው ዝቃጭ የአዲሱን ወይን ጣዕም ያበላሸዋል፡፡

   ታዲያ አንተስ እንዴት ነው ምን ትጠብቃለህ? .. የዓመፃ ታሪኮችህን በንስሐ ውኃ መቼ ነው አለቅልቀህ የምትደፋቸው? በልብስ ከሸፈንከው ከሥጋህ ሥር የተደፈደፈው የኃጢአት ዝቃጭ ተጠራርጎ ካልተደፋ፤ "የሕይወት ውኃ" ክርስቶስ ባንተ ውስጥ አይሞላም፡፡

   የሕይወት ውኃ ከሌለህ ደግሞ ትጠማለህ፡፡ ዐሥሬ ትጠማለህ፡፡ አሁንም .. በኋላም ይጠማሃል፡፡ ድርቀቱን ለማስታገሥ ብዙ ምንጮች ዙሪያ ትንጎማላለህ፡፡ ከሳይንሱም፣ ከፍልስፍናውም፣ ከሥነ ልቦናውም፣ ከቴክሎኖጂውም፣ ከመዝናኛውም ዓለም ቀድተህ ትጠጣለህ፡፡ ግን ጥምህ አይረካም፡፡ የዛሬው መጠጥ ለነገ አይሆንህም፡፡ ነገም ጠጣኝ ይልሃል፡፡  ከነገ ወዲያም..! አንዳንዴማ እየጠጣኸው ሳለም ሊጠማህ ይችላል፡፡ እርካታ የለህም፡፡ እፎይ አትልም፡፡ ስክን ብለህ አትቀመጥም፡፡ ብርጭቆዎችን በተደጋጋሚ እያነሡ ማስቀመጥ በራሱ ይሰለችሃል፡፡ የማይረሰረሱ ድርቀቶችን ማጠጣት ሥራ ይሆንብሃል፡፡ .. ምን ይሻላል? የጋኑን አተላ መቼ ልትደፋው ወሰንክ?

   ዝቃጭ ላይ የቀረው የወይን ጠጅ መራራ ነው፡፡ ቢቀምሱት ይጎመዝዛል፡፡ የአብዛኞቻችንም ሕይወት እንዲሁ መራራ ነው፡፡ ሳቃችን መራራ፣ ሐዘናችን መራራ፣ ጨዋታችን መራራ፣ አመለካከታችን መራራ፣ እውቀታችን መራራ፣ ገንዘባችን መራራ፣ ሰላማችን መራራ፣ ክብራችን መራራ፣ ታሪካችን መራራ፣ ቤታችን መራራ፣ ዕድላችን መራራ፣ .. መራራ ብቻ!

   እንደ አገርም ስንታይ መራራ ሕዝቦች ከሆንን ከ40 ዓመታት በላይ አሳለፍን፡፡ ለሕይወት እሴቶቻንን በሙሉ ጣዕም የሚሰጥ፥ የእግዚአብሔርን ቸርነትና እውነት "አንፈልግም!" ብለን በአንድ የትውልድ ድሞፅ ከጮኽን በኋላ፤ ብዙ መራራ መለያየቶችን፣ ጥላቻዎችን፣ ስደቶችን፣ ስቃዮችን፣ ኪሣራዎችን፣ ሞቶችን ለማስተናገድ ግድ ሆኖብናል፡፡

   ባልታጠቡ ጋኖች ላይ ወይኑ አይሞላም፡፡ ከክፋት ባልጸዳ ልብ ላይ ሰማያዊ ጥበብ አይኖርም፡፡ ከምቀኝት ባልወጣ አስተሳሰብ ላይ ብልጽግና አይመጣም፡፡ ከተንኮል ባልተለየ እቅድ ላይ ስኬት አይኖርም፡፡ ንስሐ ባልገባ ክርስትና ላይ የአምላክ ንጹሕ ሥራዎች አይጸኑም፥ ኃጢአት እያጎመዘዘ ያናውጣቸዋልና፡፡

   የአዲሱ አቁማዳ ባሕሪይ አዲሱን የወይን ጠጅ ይቀበላል፡፡  አዲሱም የወይን ጠጅ አዲሱ አቁማዳ ይስማማዋል፡፡ ሁለቱ እርስ በእርስ ይጠባበቃሉ፡፡ ንስሐ የገባ ሕይወትና የእግዚአብሔር ድንቅ ሥራ በእርግጥም እርስ በእርሳቸው ይጠባበቃሉ፡፡ ሕግ በሰው ትከበራለች፥ ሰውየውም በሕጊቱ ይከብራል፡፡ ወንጌል በምዕመን ትገለጻለች፥ ምዕመንም በወንጌል ይገለጻል፡፡

   እኛ አላወቅን እንደሆነ እንጂ፤ እርስ በእርስ የምንጠባበቀው ከዲያቢሎስ ሥራዎች ጋር ነው፡፡ ውሸት ተነግራ ለመደመጥ እኛን ትጠብቃለች፥ እኛም ውሸታችን እንዳትገለጥ ሸፍነን እንጠብቃታለን፡፡ ንፉግነት በኛ ለመታየት ተርታዋን ትጠብቃለች፥ እኛም ሐብታችን እንዳይሳሳ ንፉግነትን እንጠብቃታለን፡፡ ስድብ ከኛ ለመውጣት ስትቁነጠነጥ ትውላለች፥ እኛም በአስፈላጊ ቦታ የምንመዠርጣቸው ብዙ ስድቦች አሉን፡፡ ቅናት በምናየው ነገር ላይ ለመገኘት ወረፋ ስትይዝ፥ በቅርብ ወዳጆቻችን ከፍታ እየተበሳጨን እንደምናገለግላት አስቀድማ አውቃ ነው፡፡

   አዎ .. እርስ በእርስ የምንጠባበቀው ከክፉ መናፍስት ጋር ነው፡፡ እውነትን ሸሽተን፣ ትዕግስትን ንቀን፣ ጸጋን አዋርደን፣ ፍቅርን ጠልተን፣ እርጋታን አጥተን፣ ድሎትን ናፍቀን፣ ዝሙትን መርጠን፤ ከሕልውናችን ሥር አገዛዙን እየሰደደ አዙሪቱን እንዲያጠብቅብን ጠበቃ የቆምነው ለዲያቢሎስ መንፈስ ነው፡፡

   ስለዚህ ጠላት ልክ ነዋ! ለምን ታሰቃየኛለህ ትለው ዘንድ አትችልም፡፡ ፈቃዱን፣ ስሜቱን፣ ጠባዩንና ሥርዓቱን እስከጠበክለት ድረስ፤ እርሱ ደግሞ አንተን በክፋት ይጠብቅብህ ዘንድ መብት አለው፡፡ በጎነትን ሳታስቀድም፣ ርኅራኄን ሳትወደው፣ ምቀኝነትን ሳትተወው፣ ጉቦን ሳትጠየፈው  .. በጠቅላላው ኃጢአትን ሳትናዘዘው፤ "ከክፉ ሁሉ አድነኝ" እንጂ ብለህ መጸለይ መንፈሳዊ ስላቅ ይሆንብሃል፡፡ ከተኩላው በረት ሰተት ብለህ ገብተህ ከተኩላ አስጥለኝ እንደምን ትላለህ?

   እደግመዋለሁበአሮጌው ልብስ ላይ አዲስ እራፊ አይጣፍም፡፡ በአረጀው ራዋት ላይ አዲስ ወይን ጠጅ አያገቡም፡፡ ባልጸዱት ጋኖች ላይ ውኃው አይሞላም፡፡ ከኃጢአት ባልተለየ ኑሮም ላይ መንፈስ ቅዱስ አይገለጥም! የዲያብሎስን ኃይል ባልበሰረ ፈቃድ ላይ መንፈሰ ክፉ አይደክምም! ንስሐ ባልገባ ምዕመን ላይ የእምነት ሥራዎች አይጠነክሩም!

   እነዚያ ዐሥሩ ባለዘይቶች ያጨዋውቱናል፡፡ ሙሽራውን ሊቀበሉ የተዘጋጁ ቆነጃጅት ናቸው፡፡ አምስቱ ማሰሮአቸውን በዘይት ሞልተው ጠበቁ፤ ገሚሶቹ ሰዓቱ ሲደርስ እንደርሳለን ብለው ተኙ፡፡ እኩለ ለሊት ላይ ሙሽራው ስለመምጣቱ ተነገረ፡፡ ባለዘይቶቹ ማሰሮአቸውን በመብራት አድምቀው ወደ ሠርጉ መንገድ ሄዱ፡፡ ሰነፎቹ ዘይት ፍለጋ ተሯሩጠው ቢመጡ ደጁ ተዘግቶ አገኙት፡፡ ከውጪ በጨለማ ሆነው ጩኸትም ጀመሩ፡፡

   ዘይትን አዘጋጅተው የጠበቁት፤ ክፍት የሠርግ ደጅ ነው የጠበቃቸው፡፡ ሁለቱ እርስ በእርስ ይጠባበቃሉ ይሉሃል እንዲህ ነው፡፡ ዘይት ብዙ የአንድምታ ትርጉሞችን ቢይዝም፤ አንድም የንስሐ ሕይወትን ያስተረጉማል፡፡ የማያውቁት ነገን ሳይተማመኑ ዛሬን ንስሐ የሚገቡ ሁሉ ልባሞች ናቸው፡፡ እነርሱ ከኃጢአት ሲለዩ፤ ከዓለም ክፋት ሲርቁ፤ ከርኩሰት ጊዜ ሲሸሹ፤ ሙሽራው ደግሞ የተዘጉ በሮችን እየከፈተ ይጠብቃቸዋል፡፡ በእርግጥም ንስሐ ገብተው ያሉ ሰዎች፤ የሰላም፣ የእፎይታ፣ የመረጋጋትና የመቀደስ በሮችን ከከፈቱ ሰነባብተዋል፡፡ ማሰሮአቸው በዘይት ሙላት እስካለ ድረስ መንገዳቸው በጽልመት አይወረስም፡፡ ልብ እንበል! ጨለማ አይኖርም አይደለ ያለነው .. እነርሱ በሄዱበት ቦታ ሁሉ ጨለማው ይገፋል ነው የተባለው፡፡ ዓለም በበኩሏ የሙሽራውን ድምፅ ለመዋጥ፤ የማይነጉ የመሰሉ ለሊቶችን ለማርዘም፤ የማይሸነፉ የሚመስሉ ክፋቶችን ለማሳየት ድርሻዋን በመወጣቱ ረገድ ጎበዝ ናት፡፡ ቢሆንም .. በንስሐ ብርሃን ሕይወታቸውን ሞልተው ያሉ ሰዎችን በኃጢአት ጨለማ አጥቁራ ማስቀረት እንደማይሆንላት ግን [ባትናገረውም] ታውቀዋለች፡፡

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.2•  ንስሐ ለምን እንግባ? ክፍል - ፬                    ✞ አዲሱ ወይን እንዲሞላ ✞ "በአረጀ አቁማዳ አዲስ የወይን ጠጅ የሚያኖር የለም፤ ቢደረግ ግን፥ አቁማዳው ይፈነዳል፥ የወይን ጠጁም ይፈሳል አቁማዳውም ይጠፋል፤ ነገር ግን አዲሱን የወይን ጠጅ በአዲስ አቁማዳ ያኖረዋል፥ ሁለቱም ይጠባበቃሉ።" (የማቴዎስ ወንጌል 9፥17) አንድምታ ጸሐፊዎች ጥቅሱን እንዲህ…
2•  ንስሐ

   2.3•  ንስሐ እንዴት ብለን እንግባ?

ክፍል - ፭

             ✞ ኃጢአትን መጠየፍ

"እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።" (ኦሪት ዘዳግም 7፥26)

   ከእውቀት ዛፍ በልተናል፡፡ ስለዚህ መልካሙንና ክፉውን በማወቅ መለየት ችለናል፡፡ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የፈቃድ እቅፍ (ገነት) ሳለን ባሕሪያችን የክፉውን ቃል አላደመጠም ነበር፡፡  በኋላ ግን የእባቡን ምክር ተቀብለን ያለቀኑ አትንኩት የተባልነውን ፍሬ በልተን ከአምላክ ትእዛዝ በመውጣት ዓምፀናል፤ ኃጢአት ሠርተናል፡፡

   ከዚህ በኋላ አዳማዊ ባሕሪያችን ኃጢአትን መፈጸም የሚችል ባሕሪይ ሆኗል፡፡ ምክንያቱም ክፉውን እውቀት እንዲለይ ዓይኖቻችን ተከፍተዋል፡፡ ነገሩን ግልጽ ለማድረግ የሕፃናትን ሁኔታ እንመልከት፡፡ ልጆች እንደተወለዱ እውቀት የላቸውም፡፡ ስለ እዚህ ዓለም ሥርዓት፣ ስለ ራሳቸው ማንነት፣ ስለ ወላጆቻቸው፣ .. አያውቁም፡፡ በመሆኑም ኃጢአትን አይፈጽሙም፡፡ አይዋሹም፣ አይታልሉም፣ አይሰሩቅም፡፡ ለመዋሸት እንዲቻል መጀመሪያ እውነት የሆነውን በግርድፉ እንኳ ማወቅ ይገባልና፤ በአእምሮ ስሌት የማይመሩት ሕፃናት ልባቸው ወደሚስባቸው እየተጓዙ ያድጋሉ፡፡ ልብ ደግሞ የአባት ምሳሌ ነው፡፡ ከእርሱም የእውነት ቃል ይወለድበታል፥ ቅዱስ መንፈስ ይሠርጽበታል፡፡

   ማደግ ሲመጣ ግን እውቀት አብሮ ይመጣል፡፡ በሌላ አነጋገር ከእውቀት ዛፍ እንቀምሳለን፡፡ "ይሄ እሳት ነው እፉ ነው ያቃጥላል፣ ይሄ ቆሻሻ ነው ጣለው፣ ይሄ ብር ነው የምትፈልገውን ይገዛልሃል፣ .." እየተባልን ደጉንም ክፉውንም እንድንለይ እንማራለን፡፡ በተለምዶ ነፍስ ለማወቅ ደረስን እስከሚያሰኝበት ጊዜ ድረስ ወላጆቻችንና ታላላቆቻችን ያግዙናል፡፡ በአዳም ታሪክ ስናወራው የሰው ልጅ የእውቀትን ዛፍ ከበላ በኋላ መንፈስ ቅዱስም መንፈስ ርኩስም የየራሳቸውን እውቀት ይነግሩናል፤ ያሳዩናል፡፡

   አዳም ከፈጣሪው ሕያው ፈቃድ ሲያፈነግጥ፤ ለባሕሪይው የተሰሙት መራቆት፣ መገፈፍ፣ መፍራትና ብቸኛ መሆን ከስሕተት ላይ እንደወደቀ አረጋግጠውለታል፡፡ የእግዚአብሔርንም ቃል በገነት ሲመላለስ በሰማ ጊዜ በዱሩ መካከል ለመመሸግ ጣረ፡፡ ግን የቀደመው ሰላም አልተገኘም፡፡ ከራሱም ከፈጣሪውም ማምለጥ አልተቻለም፡፡ የማንነቱ ቀውስ አልተረጋጋለትም፡፡

    ይባስ ብሎ ፍርድን ተቀበለ፡፡ ምርጫው ተከበረለት፡፡ "ሥጋህን ማድመጥ ፈቅደሃልና ሂድ ወደ ሥጋህ" ተባለ፡፡ የነፍሱን ኃይል አጣት፡፡ ሕያውነት ከእርሱ ሸሸች፡፡

   አዳም ይሄን ጊዜ ዛፉን የበላበትን ቅጽበት አዘነበት፤ ጠላውም፡፡ ለዚህ ያበቃው ኃጢአቱን ተጸየፈው፡፡ ዓመፃን የፈጸመበት ታሪክ ናቀው፡፡ ከአምላኩ መስመር ተሻግሮ ለተራመደበት ፈቃዱ ተጸጸተ፡፡ ስለዚህ .. ንስሐ ገባ! "አጥፍቻለሁና ምሕረትህ ይደረግልኝ" አለ፡፡

   በዚህ መሠረት፤ አንድ ሰው ንስሐ ለመግባት ወድዶ እርምጃ አንድ ሲል፤ ኃጢአቱን ሁሉ ከመጸየፍ፤ ክፉውን ሁሉ ከመቃወም፤ ዓመፃን ሁሉ ከመሸሽ ይጀምራል፡፡

   ታስታውሱ እንደሆነ በምዕራፍ አንድ ቆይታችን ስለ ፍቅር ስንጨዋወት፤ "ፍቅር አልፋ ነው፥ ፍቅር ዖሜጋ ነው" ብለን አውግተናል፡፡ ፍቅር በእግዚአብሔር ባሕሪይነቱ አልፋ ሲሆን ከሁሉ የቀደመ ፊተኛና መነሻ ነውና፤ ንሰሐንም ፍቅር ይቀድመዋል (በነገራችን፥ ፍቅር ዖሜጋ ሲሆን ደግሞ የሁሉ ነገር ኋላኛ መደምደሚያ በመሆኑ የንሰሐ መንገድ ማብቂያ ፍቅር ነው)፡፡

   በፍቅር በኩል አገላለጻችንን ሰንደግመው፤ መነሻ እርምጃ ብለን ኃጢአትን ለመጸየፍ የምንችለው እውነተኛ የእግዚአብሔር ፍቅር ሲኖረን ብቻ ነው፡፡ እንደ ሕፃናቱ በልብ ምሪት ስንሄድ!

   እግዚአብሔርን ያላፈቀረ ሰውነት ኃጢአትን መጥላት አይሆንለትም፡፡ ምክንያቱም ዓመፃ በመልኳ ውብ ናት፤ በጣም ቆንጆ! ይህንን ጉዳይ ከመጀመሪያቱ ሴት በበለጠ በሚገባ የሚያውቀው ያለ አይመስለኝም፡፡ እንዴት?

"ሴቲቱም ዛፉ ለመብላት ያማረ እንደ ሆነለዓይንም እንደሚያስጎመጅለጥበብም መልካም እንደ ሆነ አየች፤ ከፍሬውም ወሰደችና በላች፤ ለባልዋም ደግሞ ሰጠችው እርሱም ከእርስዋ ጋር በላ።" (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥6)

   ሔዋኒቱ የዛፉን ፍሬ ከመቀንጠሷ በፊት ዛፉን አይታዋለች፡፡ ስታየው ደግሞ ያማረ፣ የሚያስጎመጅና ጥበብ ሰጪ ሆኖ ነው የታያት፡፡ በቀመደው ጊዜ ውስጥ በዔድን ጫካ መካከል ወዲህና ወዲያ ስትል ይህ እይታ አልነበራትም፡፡ "አማካሪው" መንፈስ ጠጋ ብሎ ካወያያት በኋላ ግን ቅርጫፎቹ ወዝተው፣ ፍሬዎቹ ተሽሞንሙነው፣ ቅጠሎቹ ቆንጅተው ታዯት፡፡ አበቃቀሉ ሳይቀር ሳባት፡፡ በዛ ላይ እንደሰማቺው ደግሞ እንደ አምላክ የሚያደርግ፤ ጥበብ ሰጪ ሆነባት፡፡ የምታየውና የምትሰማው ፍጹም እውነት መሰላት (ዛሬ እኛ እንደሚመስለን)፡፡ መቋቋም ተሳናት፤ ከሚያብለጨልጨው ፍሬ ወስዳ ቀጠፈች! (በኋላ ተቀጠፈቺበት እንጂ!)

   ኃጢአትን እንዳንጠላ፤ ዲያቢሎስ ኃጢአትን አስውቦ ያሳየናል (ኋላሳ፥ ቆንጆን ማን ይጠላል?)፡፡ በተጨባጭ ላለው የስሜት ሕዋሳችን የሚስማማ አድርጎ ዓመፃን ያለማምደናል፡፡ ቀላል ምሳሌ ልጥቀስ፡፡

   ከኑሮ ጉያችን ዘወትር የማትጠፋው ውሸት ኃጢአት እንደሆነች ሰምተንም ይሁን አንብበን እናውቃለን፡፡ "በሐሰት አትመስክር!" የሚል ሕግ እንዳለ ተምረናል፡፡ በገነቱ አነጋገር ዛፉን "አትንኩ!" ተብለናል (የጽድቅ ሕጎች ሁሉ ከዛፉ ክልከላ የወጡ ናቸው)፡፡ ነገር ግን ሐሰትን በባሕሪዩ የሚናገራት መንፈስ ዛፉን አስጊጦ ያሳየናል፡፡ ለመዋሸት የሚመቹ በቂ ምክንያቶችንና አጋጣሚዎችን ከፊታችን ያስቀምጥልናል፡፡ በዚህም ሳያበቃ ባሕሪያችንን ተጠግቶ ባሕሪዩን ያካፍልናል፡፡ አመለካከቱን ያጋራናል፡፡ የእርሱ እይታ ደግሞ ሁልጊዜ እንደርሱ "ከሰማይ ስፍራ የተለየ ነው"፡፡

    ውሸት ከዛፉ ፍሬዎች መካከል አንዷ ናት፡፡ ስለሆነ "አትናገራት!" ተብለናል፡፡ ግን አንችልም፤ ውሸት ውብ ነችና አንጠላትም፡፡ "ከእርሷ በተናገራችሁ ጊዜ ሥራው ይቃናል፤ ሐብት ይካብታል፤ ወዳጅ ይበረክታል፤ ዕድል ይከፈታል፤ ጨዋታ ይደራል፤ ስኬት ይቀላል" የሚል ስብከትን ዓለምና ሥርዓቷ በእጅ አዙር (አንዳንዴም በቀጥታ) ይሰብኩናል፡፡ ውሸት አንዴ ተገምጣ አታጠግብም፡፡ በየቀኑ ትርባለች፡፡ አልፎ ተርፎ ባልንጀሮቿ ግብዝነትን፣ ጉቦን፣ ሙስናን እና ሌሎቹንም ተራ በተራ ታስጎበኛለች፡፡ አንጠላት ነገር በውበቷ ታስደምማለች፡፡ ስትደመጥ ትጣፍጣለች፤ እንደ እውነት አትመርም፡፡

   የእባቡ ዓይን ያፈዛል፡፡ ዓመፃውን ያሳምራል፤ ውድቀቱን ለጊዜው ይሸፍናል፡፡ ዝሙትን የሚጠላት ማግኘት ይከብዳል፡፡ እስኪፈጽሟት ድረስ ታጓጓለች፡፡ ሐሴትን የምትለግስ ትመስላለች፡፡ በሥጋ ሲያዯት እንከን አያወጡላትም፡፡ መልክአ ኤዶምን የጻፉ ደራሲ ያሉት ትዝ አለኝ፦

"ዓለም እኮ የወደዳትን መልሳ ታጠፋዋለች፡፡  በወጥመዷም አስገብታ ብዙውን ሕዝብ በመርዟ እንደገደለች ይህን ሥራዋን የሚያውቅባት ከቶ እንደምን ያለ ብልህና አዋቂ ይሁን?"

   ዓለም ከሕይወት ብሌናችን ፊት ውበቷ የደመቀ ነው፡፡ ለጆሮም አትከብድም፡፡ መዝናኛዎቿና አኳኋኗ ሁሉ ቄንጠኛ ናቸው፡፡ ውደዱኝ በሚል ማባብያ ትቅለሰለሳለች፡፡ ፍቅር መሳይ ጥላቻ ግን ውስጧን ሞልቶታል፡፡
   ሥጋዊውን አኗኗር የሚቆጣጠረው ክፉ መንፈስ፤ የእርሱ ፈቃድና ምሪት ያለባቸውን ነገሮች ሁሉ ሲያቀርብልን ከጉድለታችን ትይዩ በመቆም ነው፡፡ ስለዚህ ኃጢአትን በመጠየፍ ንስሐ እንዳንገባ ከመኖር ሕልውናችን ውስጥ ያልተመለሱ ጥያቄዎችን፤ የተከለከልናቸው ትእዛዛትን፤ ያልደረስንባቸው ከፍታዎችን እንደ ውበት ማሳመሪያ ተጠቅሞ ኃጢአትን በማቆንጀት ያሳየናል፡፡ ኃጢአት መልከ መልካም ሆና ከታየች ደግሞ የእግዚአብሔርን ፍቅር ታኮስሰዋለች፡፡ ይህንን ጉዳይ መድኃኒቱ በአንድ ወቅት ሲናገር፦

"ከዓመፃም (ከኃጢአት) ብዛት የተነሣ የብዙ ሰዎች ፍቅር ትቀዘቅዛለች።" (የማቴዎስ ወንጌል 24፥12)

   ፍቅር የቀዘቀዘች እንደሆነ መንፈሳዊ ኑሮን እንድንመሠርት፤ ጉልበት፣ ጸጋ፣ ንቃትና ጽናት የምትሰጠን ንስሐ ጋር ለመድረስ የመነሳሳት አቅም እንኳ ያጥረናል፡፡ ምክንያቱም .. ፍቅር አልፋ (መነሻ)፥ ፍቅር ዖሜጋ (መጨረሻ) ስለሆነች!

   ንስሐ በአጭር ቋንቋ ከኃጢአት ወደ ጽድቅ አድራሻ የመለወጥ መንፈሳዊ ጉዞ ነው፡፡ ወይንም በሮሜ መልእክት (12፥9) አጻጻፍ "ክፉውን ሁሉ በመጸየፍ ከበጎው ጋር መተባበር" ነው፡፡

   አንድ ሰው ንስሐ እንዴት ብዬ ልግባ ብሎ ሲጠይቅ፤ አስቀድመህ በኃጢአቶችህ ላይ ሁሉ ዓምፅ የሚል ቀጭን መልስ ሊያገኝ ይገባዋል፤ ዓመፃ ላይ ያላመፀ ሰው እግዚአብሔር ላይ ለማመፅ ቅርብ ነውና፡፡

   ሁሉም በሚል መጠቅለያ ለመደምደም በሚያስደፍር ገሐድ፤ ቆሻሻ የነካውን ልብስ ለብሶ ሠርግ መታደም አይፈልግም፡፡ ይቅርና ሠርግ ሰው የማያየንም ስፍራ ላይም ቢሆን ጸያፍ ነገር የነካው ልብስ መልበስ አንመርጥም፡፡ ግን በእግዚአብሔር ፊት አስቀያሚ የሆነውን የኃጢአት ድሪቶ ተሸክመን ስንመላለስ አንዳች አይከብደንም፡፡ ለምን? ተወዳጁን አባት ስለማንወደው!

   እግዚአብሔርን ያፈቀረ ልብ ኃጢአቶቹ ሁሉ ያጸይፉታል፡፡ እንደ መጥፎ ጠረን ይከረፉታል፡፡ እንደ ሰቅጣጫ ድምፅ ይሰቀጥጡታል፡፡ የዓመፃ ሰዓቶቹን ሲያስባቸው ይሰገጥጠዋል፡፡ እንዲህ ያለ ሥራ በአምላኩ ፊት መሥራቱን ባስተዋለ ጊዜ የሚያቃጥል እንባ ከጉንጮቹ ኮለል እያለ ይወርዳል፡፡ በልቡም ዘወትር ሳያቋርጥ ይዘምራል "ዓመፃን ጠላሁ ተጸየፍሁም፤ ሕግን ግን ወደድሁ" (መዝሙረ ዳዊት 119፥163) .. በቃ ንስሐ ማለት ይኸው ነው!

   ፍቅርን ባልቋጠረ ሕይወት ንስሐ እንግባ ብንል ኃጢአትን መጥላት አንችልም፡፡ ኃጢአትን ካልጠላነው፤ በዓመፃችን አንጸጸትም፤ ካልተጸጸትን አንናዘዝም! (እውነትም ፍቅር አልፋ.. )

   ያዕቆብ በመልእክቱ "እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ፤ ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ ከእናንተም ይሸሻል" ሲል የጻፈልን ይህንኑ ነው፡፡ በመለኮታዊ መውደድ ተንበርክከን ሳለ ዲያቢሎስን በመቃወም ልናሸሸው ይቻለናል፡፡ ማለትም ኃጢአትን በመጸየፍ ዓመፃን ከኛ ማራቁ ይሳካልናል፡፡

   ከዚህ ባሻገር ግን የኃጢአትን እስራት በጥሰን የጽድቅ ነጻነትን ልንቀዳጅ አንችልም፡፡ ዓመፃን ካልጠላናት ተውባ መታየቷን ትቀጥላለች፡፡ እኛም እየቀነጠስን መቋደሳችን እንዲሁ ይቀጥላል፡፡

"ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ ወደ እናንተም ይቀርባል። እናንተ ኃጢአተኞች፥ እጆቻችሁን አንጹ፤ ሁለት አሳብም ያላችሁ እናንተ፥ ልባችሁን አጥሩ።" (ዝኒ ከማሁ)

   ንስሐን የሚጋርድ የኃጢአትን ውበት ለመግፈፍ የእግዚአብሔርን ፍቅር መነጽር ማድረግ ታላቅ መፍትሔ ነው፡፡ እኛ ወደርሱ በፍቅር ስንቀርብ እርሱ ደግሞ ወደኛ ከኛ ሁለት እጥፍ ተራምዶ ይቀርበናል፡፡ "ማንም ሰው አንድ ምዕራፍ ትሄድ ዘንድ ቢያስገድድህ ሁለተኛውን ከእርሱ ጋር ሂድ" ሲል የመከረ ጌታ፤ በአንድ የንስሐ ምዕራፍ ወደርሱ ስንጠጋ፥ ሁለት ምዕራፍ ከኛ ደርቦ መጥቶ አይጠጋንም ማለት ዘበት ነው፡፡ እርሱ ባያደርገው ኖሮ አድርጉት አይልም ነበርና፡፡ (የማቴዎስ ወንጌል 5፥41)

   ንስሐ መግባት እግዚአብሔርን የማፍቀር አንድ መገለጫ ነው፡፡ የምንወደውን ሰው አይደለም ስናሰቀይም ያስከፋነው ሲመስለን እንኳ እንጨነቃለን፡፡ በቶሎ አግኝተን ይቅርታ እስክንጠይቅ እንቸኩላለን፡፡ ከተፈቃሪውም የይሁንታ መልስ መቀበል ብቻውን ያስደስተናል፡፡ ይሄ ግን ለእግዚአብሔር አይሰጠውም፡፡ የፈጠረንን አምላክ ፍቅር ነፈግነው!

    በመሆኑም ፍቅር ባጣው እኛነታችን በኩል የጥላቻው መንፈስ የፍቅርን ካባ ደርቦ እየታየ፤ እንወድቅበት ዘንድ ሳር ወደከለለው ጉድጎድ አቅጣጫችንን ለመቀየስ ከፊታችን ቀድሞ በመሄድ መራን .. መራንና፤ በመጨረሻው ጊዜያችንን፣ አስተሳሰባችንን፣ ፍላጎታችንን፣ እውቀታችንን፣ ሥራችንን፣ ኑሮአችንን፣ ትውልዳችንን .. ሁሉ እንደርሱ የወደቀ አደረገው፡፡

    ኃጢአትን ያለ ቅድመ ሁኔታና ድርድር ለመፈጸም ሳንቸገር፤ ንስሐ ገብተን የቅድስና ፍሬን ለመስጠት ግን አያሌ ሰበቦችን እንደረድራለን፡፡ የመረጥነውን ድርጊትና ውሳኔ መከተላችንን በሚገባ እያወቅነው፤ ስለ ንስሐ በተወሳ ቁጥር "ልብ ይሰጠኝ" እያልን ሁለተኛ ልብ ፍለጋ ከራሳችን ዘወር እንላለን፡፡ አፈር የሚረግጥ ጫማችንን ሳንንቅ ወልውለን ነፍሳችንን ግን ከኃጢአት እድፍ ለመጥረግ በጣም ከበደን፡፡ አዎ .. በእርግጥም ከዓመፃ ብዛት የተነሣ የእግዚአብሔር ፍቅር ከውስጣችን ቀዝቅዛብናለች፡፡

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.3•  ንስሐ እንዴት ብለን እንግባ? ክፍል - ፭              ✞ ኃጢአትን መጠየፍ ✞ "እንደ እርሱም ርጉም እንዳትሆን ርኩስን ነገር ወደ ቤትህ አታግባ፤ ርጉም ነውና ተጸየፈው፥ ጥላውም።" (ኦሪት ዘዳግም 7፥26)    ከእውቀት ዛፍ በልተናል፡፡ ስለዚህ መልካሙንና ክፉውን በማወቅ መለየት ችለናል፡፡ አስቀድሞ በእግዚአብሔር የፈቃድ እቅፍ (ገነት) ሳለን ባሕሪያችን የክፉውን…
2•  ንስሐ

   2.3•  ንስሐ እንዴት ብለን እንግባ?

ክፍል - ፮

                ✞ ንስሐ መጸጸት ነው

  ንስሐ የሚለው ቃል ራሱ በአንድምታ ፍቺው ጸጸት ማለት ነው፡፡ እንግዲያስ፥ ንስሐ እንዴት እንግባ ስንባል፤ ከስሙ ቀጥተኛ ትርጓሜ ተነሥተን ስለ ኃጢአት በመጸጸት ብለን እንመልሳለን፡፡

  የጥፋተኝነት ስሜት፣ በራስ ላይ ማዘን፣ ባለፈው ጉዳይ መቆጨት፣ በፈጸሙት ስሕተት ማፈር፣ ክስተትን ወደኋላ ተመልሶ የማረም ፍላጎት "ጸጸት" በተባለ የግስ ቃል ውስጥ መሠረታዊ ብያኔዎች ሆነው የሚካተቱ ማስተንተኛዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ አንድ ምዕመን ንስሐን ባሰበ ጊዜ እነዚህን የጸጸት ክፍለ አካሎች ማወቁንና ከሕይወቱ ውስጥ ማግኘቱን ሊያረጋግጥ ያስፈልገዋል፡፡

   ኃጢአትን ከሠራን በኋላ እንዳጠፋን፣ ትክክል እንዳልሆንን፣ መንፈሳዊ ውደቀት እንደገጠመን፣ በጽድቅ ላይ እንዳመፅን፣ በጎውን መንፈስ እንደተቃወምን፣ ፍጹሙን ሕግ እንደተላለፍን ካላወቅን ብሎም ካልተሰማን ንስሐ ልንገባ አንችልም፡፡ ምክንያቱም ያለ ጸጸት ንስሐ የሚባል ነገር ከነአካቴው የለም!

   ክፍል አምስት ላይ እንዳየነው ንስሐ የመግባት የመጀመሪያ እርምጃ ኃጢአትን መጸየፍ ሲሆን፤ ቀጣዩ ሂደት የሚከተለው የተጸየፍነውን ኃጢአት በመፈጸማችን ራስን መውቀስ ከጀመርን በኋላ ነው፡፡ ንስሐ ከልብ እውነት ጋር ጥብቅ ቁርኝት አለው፡፡

   በክርስትናው ዓለም 'እግዚአብሔር አብ ልብ ነው፣ እግዚአብሔር ወልድ ቃል ነው፣ እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ እስትንፋስ ነው' ሲሉ አበው ሚስጥረ ሥላሴን አስተምረውናል፡፡ የሰው ልጆችም በዚህ የሦስትነት አርአያ የተፈጠርን ምሳሌዎች በመሆናችን በነፍስ ሕላዌ ውስጥ ባለች ልቦና እናስባለን፣ ከእርሷ በተወለደ ቃል እንናገራለን፣ ከእርሷ በሠረጸ እስትንፋስም ሕያው ሆነን እንቀሳቀሳለን፡፡

   በመሆኑ፥ አንድ ግለሰብ "አማኝ" ነው ተብሎ በግብር ሲገለጥ፤ በልቡ፣ በቃሉና በአኗኗሩ በኩል በሚያሳየው የእግዚአብሔር እውነት አማኝነቱ ይረጋገጣል፡፡ በንስሐው አገላለጽ፤ ንስሐ ከነፍስ በታሰበች የልቦና ኃይል ተጀምራ በሕይወት ስትፈጸም መንፈሳዊ ክብሯና ምንነቷ ሙሉ ይሆናል፡፡

   ንስሐ ለመግባት ኃጢአታችንን ስንጸየፍም ሆነ በኃጢአትችንን ስንጸጸት፤ ነገሩን በተጨባጭ ከነፍሳችን ልናስበውና ልንኖረው ያስፈልጋል፡፡ በተለመደ የአማርኛ ዘይቤ አነጋገር "ከአንጀታችን" በንስሐ ልንመላለስ ተገቢ ነው፡፡

   ንስሐ የኃጢአት ዘገባ አይደለም፡፡ ንስሐ የበደል ሪፖርት አይደለም፡፡ ንስሐ ካህን ፊት ሆኖ ጥፋትን መዘርዘር አይደለም፡፡ ይልቅስ፥ ንስሐ እግዚአብሔርን ካሳዘነ ልቦና የነቃ የጸጸት ጥዝጣዜ ነው፡፡ ንስሐ ፍቅር ላይ ማመፅን ተከትሎ የሚመጣ የቁጭት ቁስል ነው፡፡ ንስሐ በነፍስ አባት ጆሮ የሚደመጥ የእንባ ድምፅ ነው፡፡ ንስሐ ንጉሥ ዳዊትን በሐዘን ማቅ ያስለበሰ ስሕተትን የመንቀፍ ልባምነት ነው (ዳዊት "እንደ ልቤ" የተባለው [አንድም] ለዚህስ  አይደል?)፡፡

   ብዙዎች ከጉሮሮ አውጥተው እንደሚናገሩት ንስሐ "እኔ ኃጢአተኛ ነኝ" ብሎ በደፈናው ማወጅ አይደለም፡፡ በመጽሐፍ ቃል "ሁሉ ተሳስተዋል፥ አንድስ እንኳ ጻድቅ የለም" የሚለውን ንባብ ተገን በማድረግ፤ የዓመፅኝነትን የጋራ ተለምዶ አጽድቆ በመቀበል "ምን ይገርማል እኔም ሰው ነኝ" የምንልበት የምላስ ቋንቋ አይደለም ንስሐ፡፡ ንስሐ ከልብ የመጸጸት፥ መልካምነትን የመውደድ ሰብአዊነት ነው፡፡ አባትየው እንዲህ ይለናል፦

"በልብ ሞልቶ ከተረፈው አፍ ይናገራልና። መልካም ሰው ከልቡ መልካም መዝገብ መልካም ነገርን ያወጣል፥ ክፉ ሰውም ከክፉ መዝገብ ክፉ ነገርን ያወጣል።" (የማቴዎስ ወንጌል 12፥34-35)

ሐዋሪያው ደግሞ፦

"የትእዛዝ ፍጻሜ ግን ከንጹሕ ልብና ከበጎ ሕሊና ግብዝነትም ከሌለበት እምነት የሚወጣ ፍቅር ነው" (1ኛ ወደ ጢሞቴዎስ 1፥5)

   በልብ ሞልቶ ያለውን ጸጸት አፍ ይናዘዘዋል፡፡ የሰው መዝገቡ ልቡ ነው፡፡ መዝገቡ ሲገለጥ ቃላት ይነበባሉ፡፡ ቃላቱ ደግሞ በሕይወት ይተነተናሉ፡፡ እንኪያስ፥ መንፈሳዊ ንስሐ ከልባችን ይጸነሳል፡፡ በአሳባችን ማኅፀን ኃጢአትን መጸየፍ፣ ዓመፃን መሸሽ፣ ክፋትን መተው፣ ጽድቅን መመኘት፣ እውነትን መውደድ፣ ቅድስናን መጠጋት እየሆነ ያድጋል፡፡ የእርግዝና ወሩም በገፋ ጊዜ ጸጸትን ያወጣል፡፡ የሚነዘንዝ ቁጭትን ያመላልሳል፡፡ ንጹሑን ባሕሪይ ማሳዘን እረፍት ይነሳል፡፡ የእንባ ዘለላዎችን በዓይን እየቋጠረ ያስቸግራል፡፡ ብቸኝነትን አጥብቆ የሚወተውት ይሆናል፡፡ ቅዱሱን የመካስ ቁርጠኝነት ያወጠነጥናል፡፡ ጊዜውም ሲደርስ ቃል ይወለዳል፡፡ "አቤቱ፥ እንደ ቸርነትህ መጠን ማረኝ፤ እንደ ምሕረትህም ብዛት መተላለፌን ደምስስ። ከበደሌ ፈጽሞ እጠበኝ፥ ከኃጢአቴም አንጻኝ፤ እኔ መተላለፌን አውቃለሁና፥ ኃጢአቴም ሁልጊዜ በፊቴ ነውና። አንተን ብቻ በደልሁ፥ በፊትህም ክፋትን አደረግሁ" ሲል ከሲቃ ፊደላት ጋር ይናዘዛል፡፡ (መዝሙረ ዳዊት 51፥4) ኑዛዜውም በመኖር ሕልውና ውስጥ ይታያል፡፡ ለሰሞን አልቅሶ ራሱን የሚያባብል አይደለም፡፡ ዳዊት እንዳለው ኃጢአቱ ሁልጊዜ ከፊቱ ድቅን እያለበት ውድቀቱን ያስታውሳል፡፡ ከዚህ ውድቀት ላይም ይነሣ ዘንድ ሕይወቱን በአራቱም ማዕዘን በየቀኑ ያድሳል፡፡ በሁለንተናውም ተለውጦ ይገኛል፡፡ አሁን በዚህ አይነት ንስሐ ላይ ማን ከበሩ? .. ሥላሴ ከበሩ! ሥላሴ ደግሞ በባሕሪይ ፍጹም እውነት ናቸውና እንዲህ ከልብ እስከ ሕይወት የተናበበው ንስሐም ፍጹም እውነት ስለመሆኑ የታመነ ይሆናል፡፡ ወይንም በሌላ አነጋገር ለአርያም ካህናት ቅዳሴ መባዕ ሆኖ የክርስቲያኑ ስም በሰማይ መቅደስ ይጠራል፡፡  (የሉቃስ ወንጌል 15፥10)

   ለጢሞቴዎስ ሰዎች እንደተጻፈላቸው፤ "ንስሐ ግቡ" የሚለው ሰማያዊ ትእዛዝ ወደ ፍጻሜ የሚያደርሰው ከልብ ሲጀምር ነው፡፡ ጸጸትን ከይስሙላ ሳይሆን ከነፍስ የሚያፈልቅ ግለሰብ፤ ልቡ እና ሕሊናውን ለማንጻት የወደደ ነው፡፡ ጸጸት ያለ ግብዝነት ሙሉ እውነትን ሆኖ ካልተገለጠ ግን፤ ንስሐችን አይጸናም፡፡ ዞረን ዞረን፥ ከተናዘዝነው ኃጢአት እንመለሳለን፡፡ ምናልባትም ቀኖናውን እንኳ ሳንጨርስ በፍጥነት ኃጢአት ልንደርብ እንችላለን፡፡

   ከሥሩ ያልተነቀለ ተክል መልሶ እንዲያቆጠቁጥ፤ በልብ ጸጸት ያልተገረሰሰ ኃጢአትም ከሕይወታችን ሊርቅ አይችልም፡፡ ለምሳሌ ሐሰትን በመናገር ዓመፃ የተጠመደች አንደበት፤ ስላዳወረቻቸው የውሸት ሸማዎች ሁሉ ከልቧ ካላዘነች፤ ንሰሐዋን ለካህኑ ተናዝዛ ቤቷ ስትመለስ ሌላ ሐሰትን ከመናገር ወደኋላ አትልም (ድመት መንኩሳ..)፡፡

   ሰዎች ንስሐ እንዳይገቡ መሰናክል እየሆነ የሚጥላቸው አንዱ የዲያቢሎስ ፍልሚያ ራስን የመውቀስ መንፈሳዊነትን ከልቦና እውቀት ውስጥ መድምሰሱ ነው፡፡ ብዙዎቻችን "ኃጢአቶችን መክሰስ እንጂ ኃጢአታችንን መክሰስ" አይሳካልንም፡፡ ምክንያቱም ከሳሹ ባሕሪይ ከባሕሪያቶቻችን መካከል ተደባልቆ ገብቶአል፡፡

   ክፉ መንፈስ ማለት ያው ክፉ ረቂቅ ማለት ነው፡፡ ረቂቅ የሆኑ ክፉ ነገራት ሁሉ የዲያብሎስ ጠባያትና መገለጫዎች ናቸው፡፡ ክፉ አሳብ፣ ክፉ ምኞት፣ ክፉ ፍላጎት፣ ክፉ እቅድ፣ ክፉ ስሜት፣ ክፉ ቃል፣ ክፉ ዝንባሌ፣ .. ሁሉ በቀጥታም በተዘዋዋሪ የመናፍስት ሕልውና ማሳያዎች ናቸው፡፡ እሳቱ ከሌለ ጭሱ ከየት መጣ? እንዲሉ፤ ክፉ መንፈስ በሌለበት ቦታ ማንኛውም ክፉ ነገር አይኖርም፡፡ ሰማይ ቤት ሰላም የሰፈነው ለዚህ ነው፤ ዘንዶውና ሠራዊቱ ከሰማይ ስፍራ ስለተጣሉ፡፡ (የዮሐንስ ራእይ 12፥8)
   እነሆም ከክፉ ጠባያት ዝርዝር የሚመደበው ሌሎችን መወንጀል የክፉ መናፍስት ማንነትና ሥራ ነው፡፡ ደጉ ባሕሪይ ከራሱ ውጪ ማንንም አይከስም፡፡ ዓይኖቹ ወደ ውስጥ እንጂ ወደ ውጪ አያዩም፡፡ እጆቹ የሚለቅሙት የሕይወቱን እንጂ የወገኖችን አረም አይደለም፡፡ "ስሕተቱን" እንጂ "ስሕተታቸውን" አያፋጥጥም፡፡ እንደውም በዚህ ባሕሪይ የሚገለጥ ስብዕና ልዕልናው ሲጨምር፤ የሌሎችን መጥፋት እያሰበ የሚያዝንና ስለ ኃጢአት ሥራቸው ንስሐ የሚገባላቸው ታላቅ ምዕመን ይሆናል፡፡

   እኛና ዘመናችን ግን ከዚህ ባሕሪይ በእጅጉ የራቅን ነን፡፡ የግላችንን ገመና አለባብሰን የሰዎችን ማጀት አደባባይ ማውጣት ያስደስተናል፡፡ በኃጢአታችን ከመጸጸት ይልቅ ኃጢአታቸውን ማውራት ይቀለናል፡፡ የወደቅንበት ጉድጓድ የቱን ያህል እንደሚጠልቅ ሳናውቅ የሌሎችን ውድቀት መለካት ይዳዳናል፡፡ አያችሁ? .. ረቂቁ ክፉ ባሕሪይ ከሥጋችን ውስጥ ተሰውሮ ሥራውን በብቃት ይመራል፡፡

  በንስሐ መንገድ ላይ የሚያራምድ ጸጸት ከኛ ውስጥ ሊገኝ የሚችለው፥ ነግቶ በመሸ ቁጥር እኛን አትኩረን የምንከታተል የሆነ እንደሆነ ነው፡፡ እንደ ሥጋ ዓይኖቻችን ደረቅ ግንባር ላይ ተለጥፈን ወደ ዓለም (ሰዎች) ብቻ የምናይ ከሆነ፤ ለንስሐ የሚያበቃ የመንፈስ ስብራት ከቶውኑ አይኖረንም፡፡

   እግዚአብሔር የሚቀበለው የዘወትር መሥዋዕት የሆነው የመንፈስ መሰበር እንዳይኖር፤ አሳቹ ባሕሪይ ራሳችንን ሳይሆን ሌሎችን የምንሰብር ደንዳናዎች ያደርገናል፡፡ ሰዎችን የሚሰብር ሰው ደግሞ የተወደደውን ቅዱስ ኃይል የሚያስቀምጥበት የልብ ስንጥቃት አይኖረውም፡፡

   ዲያቢሎስ ሁልጊዜ ሽንፈትን በጣሙን እንደታገላት ይኖራል፡፡ መጸጸት፣ ራስን መውቀስ፣ ስሕተትን ማመን፣ ጥፋትን መቀበል የሚባሉ ጠባያትን ሳያቋርጥ ይዋጋቸዋል፡፡ ይህንን ግንዛቤ እናድርግና እስቲ ዝምብለን ራሳችንንና ዙሪያችንን እንቃኘው፡፡ ንስሐን የሚከለክሉ ባሕሪያትን ስንከባከባቸውና በአደገኛ ቅጥር (በቁጣ፣ በስድብ፣ በሽሙጥ፣ በትዕቢት) አጥረን ስንጠብቃቸው እንታያለን፡፡

   መንፈስ የጸጸትን ኃይል ከልቦና ውስጥ በማዳከም፤ በንስሐ ጌጥ አማኞች ኑሮአቸው እንዳያምር ሲታገል፤ ተስፋ የሚያደርገው መድረሻ ዓላማው እንዲህ የሚለው የሐኪሙ ወንጌላዊ ጽሕፈት ነው፦

"ንስሐ ባትገቡ ሁላችሁ እንደዚሁ ትጠፋላችሁ።" (የሉቃስ ወንጌል 13፥5)

   በአምላክ የምሕረት መዳፍ ያልተጎበኘው ትውልዳችን በእርግጥም እንዲሁ እንደ ዘበት መጥፋቱን እንኳ ሳያውቀው ከጠፋ ከ40 ዓመታት በላይ አለፉ፡፡ እንዲሁ ያልጠፋ ምን አለ እስኪ? እንዲሁ ፍቅር ጠፋ፣ እንዲሁ ሰላም ጠፋ፣ እንዲሁ ጤና ጠፋ፣ እንዲሁ አንድነት ጠፋ፣ እንዲሁ አገራዊ ክብር ጠፋ፣ እንዲሁ የታሪክ በረከት ጠፋ፣ እንዲሁ ሰብአዊ እሴት ጠፋ፣ .. እንዲሁ!

   ጠፍቶ የሚያጠፋው ክፉው ባሕሪይ፤ ባለመታየትና ባለመደመጥ መንፈሳዊነቱ ተጠቅሞ የሚታይና የሚደመጥ ጥፋትን ለማምጣት ከባሕሪያችን ጠጋ ብሎ ሲመሳሰል፤ እኛ ጀምረው በሰጡን አቅጣጫ ላይ በሰመመን እየተጓዝን ወደ ጥልቅ ጥፋት በየቀኑ እንሄዳለን፡፡ ባላጋራው ኃይልም ማንነታችንን ተዋሕዶ ማንነቱን ስላለማመደን፤ እርሱ ካከበበልን የሕይወት ልምድ ርቀን ለመሄድ እንዳንችል የገዛ አካላችን ጉልበት አውጥቶ እየተናነቀን፤ የብርሃን ጥሪዎችን በመሸሽና በግዴየለሽነት በማለፍ ሰውነታችንን ተጭኖ ያለውን ግርዛዜ "አትንኩብኝ!" እያልን ብዙ ዘመናትን አቆራርጠን መጣን፡፡ ኦ.. ! ቃሉ ተናግሮአል  .. "እንደዚሁ ትጠፋላችሁ!"

   ሰው "ሰው" ከሚያሰኙት በጎ ባሕሪያት ርቆ ከተገኘ በቁም ሳለም ጠፍቷል ማለት ነው፡፡ በንስሐ ሕይወት በኩል የሚመጡ የመንፈስ ቅዱስ ገጸ በረከቶችን የሚሸሽ ማንነት በዓለም ገደል ጠልቆ ጠፍቷል ቢባል ልክ ይሆናል፡፡ ከእውነት ጋር ለመታረቅ የዕድሜ ቀጠሮ የሚያራዝም አስተሳሰብ ከሐሰት ማሳ ገብቶ የጠፋ ነው፡፡ ይህንንም ጽሑፍ እየተመለከተ ወደ ኑሮው አጠንጥኖ "እንዴት ነው ነገሬ ግን?" ሲል የማያምሰለስል፤ ውስጡ በጥሞና እንዲያስብ የማይፈቅድ ሕልውና፤ መድኃኒቱ እንዳለው እንደዚሁ ጥፍት ብሎ ሌላ መጥፋትን ደሞ ይጠባበቃል፡፡ መንፈሳዊ ትምህርቶችን አልፎ አልፎ የምንከታተል ሰዎችም፥ ጊዜያዊ መጸጸት በተሰማን ቁጥር "ለንስሐ ሞት አብቃኝ" እያልን፤ ለንስሐ የማያበቃ ዓለማዊ መጋረጃን ሳንቀድድ ቀናቶች በላያችን ሲረማመዱ ዝምብለን እናያለን፡፡

ነብዩ ኢዮኤል፦

"አሁንስ፥ ይላል እግዚአብሔር፥ በፍጹም ልባችሁ፥ በጾምም፥ በልቅሶና በዋይታ ወደ እኔ ተመለሱ። ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ፤ አምላካችሁም እግዚአብሔር ቸርና መሐሪ፥ ቁጣው የዘገየ፥ ምሕረቱም የበዛ፥ ለክፋትም የተጸጸተ ነውና ወደ እርሱ ተመለሱ (ንስሐ ግቡ)።"

   ልባችሁን እንጂ ልብሳችሁን አትቅደዱ ተብለን ነበር፡፡ እኛ ጂንሳችንን ጉልበቱ ላይ እየቀደድን "ፋሽን ነው!" ነው ከማለት ውጪ የልብ ሸካራነትን የሚቀድድ የንስሐ ጸጸት እስከ አሁን አልተሰማንም፡፡ ቢሰማንም፥ የተቀደዱ ልብሶችን የሚለብሱ መዝናኛዎችን በተከታተልን ጊዜ፥ በኃጢአት የመቆጨቱ ዕድሜ ወዲያው ያጥርብናል፡፡

   የተሳካ ንስሐ እንገባ ዘንድ ልባችን (ለማንም የማንገልጠው አመለካከታችን) ግብዝነትን ለራሱ ታማኝ ሆኖ መፋለም አለበት፡፡ ማስመሰልን መናቅ አለብን፡፡ ፍቅርን ባከበረ መግፍኤ እየተመራን እውነትን መቀበል ይገባናል፡፡ ብዙዎች እንደሚሆኑት ላለመሆን መጀገን ይጠበቅብናል፡፡ የትክክልን መሥፈርት በመጠበቅ "አንበሳነት" ራስን ማክበር ይኖርብናል፡፡ ክርስትናን ከአሳብ፣ ከቃልና ከሕይወት በማዋሐድ፤ የንጉሥ ልጅነትን ከአንገት ክር በዘለለ በኑሮ ማዕረግ ማሳየት ያስፈልገናል፡፡ የነጠላ ያይደለ የልብ ንጽሕናን መጠበቅ ራሱን የቻለ ድንቅ ሰማእትነት ነው፡፡

   ተወዳጁ ቸርና መሐሪ፥ ከቁጣም የዘገየ ባሕሪይ ነው፡፡ የልብ እውነትን እጅ መንሻ አድርገን እስክናሳልፍ ድረስ ምሕረቱን እያበዛ ይጠብቀናል፡፡ በኃጢአት ጽሕፈት ያጠራቀምነውን የዓመፃ ወረቀት ከልባችን እንድንቀድድ በየአጋጣሚው ሳያርፍ "ተመለሱ" ይላል፡፡ እርሱ አብዝቶ የሚፈልገውና ሊቀበለው የሚወደው ከልብ ተነሥቶ የወጣውን ነው፡፡ ምክንያቱም የማንነት መዝገብ ተቀምጦ ያለው በልብ ውስጥ ነውና፡፡

   እግዚአብሔር ልባችንን አጥብቆ ፈለገው ማለት፤ እንደ እግዚአብሔር ለመሆን የሚደክመው መንፈስም ልባችንን ፍለጋ ይኳትናል ማለት ነው፡፡ በሌላ አገላለጽ "ዘንዶው ከሴቲቱ ፊት" ይቆማል፡፡ (የዮሐንስ ራእይ ምዕ. 12) ሐሰትን የሚኖረው ኃይል ከእውነት አንጻር ይታያል፡፡ ውድቀትን የሚከተለው ባሕሪይ ከምዕመናን ትይዩ ይገለጻል፡፡ ጥፋትን የሚመራው ዲያቢሎስ እግዚአብሔር ከሚሰጠን ማንኛውም ጎን መሽጎ አይጠፋም፡፡ ወዳጄ በደንብ አስብበት! ትኩረት የሰጠኸው፣ ዘወትር የምትገሰግሰው፣ ፈቅደህ የምትጋብዘው፣ ወደህ የምትመርጠው ሁሉ ሲጠቀለል የአንተነትህን መጽሐፍ ያትማልና፤ እንደገና መለስ በልና፥ የመጣህበትን፣ አካሄድህንና የምትሄድበትን ሰክነህ መርምር!


(በአብ ምሳሌ ተፈጥረናልና እናስባለን፥ ስለዚህ ስታነቡ በተለይ የተሰመሩባቸውን ለብቻቸው በሌላ ቦታ ላይ ጻፏቸውና፥ አንድ በአንድ አምሰልስሏቸው፡፡ ስለ እውነት በእውነት ስናስብ፥ እውነት ከልባችን ይነቃል፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሔር በነፍስ ደምፅ በኩል ያስተምረናል!)
ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.3•  ንስሐ እንዴት ብለን እንግባ? ክፍል - ፮                 ✞ ንስሐ መጸጸት ነው ✞   ንስሐ የሚለው ቃል ራሱ በአንድምታ ፍቺው ጸጸት ማለት ነው፡፡ እንግዲያስ፥ ንስሐ እንዴት እንግባ ስንባል፤ ከስሙ ቀጥተኛ ትርጓሜ ተነሥተን ስለ ኃጢአት በመጸጸት ብለን እንመልሳለን፡፡   የጥፋተኝነት ስሜት፣ በራስ ላይ ማዘን፣ ባለፈው ጉዳይ መቆጨት፣ በፈጸሙት ስሕተት ማፈር፣…
2•  ንስሐ

   2.4•  ለንስሐ እንዴት እንዘጋጅ?

ክፍል - ፯

   የንስሐ መንገዳችን እነሆ ወደ መገባደዱ ደርሷል፡፡ ከ"ፍቅር" ተቀብሎ፤ ፍቅርንም በውስጡ ይዞ በራሱ ጎዳና ያንሸራሸረን "ንስሐ" እዚህ ድረስ ካመጣኋችሁ ለአሁኑ ይበቃል ብሎናል፡፡ ያላስጎበኘን ቦታዎች ስለሚኖሩ፤ ሌላም ጊዜ ወደርሱ መለስ እያልን እንድንጠይቀው የአደራ መልእክት አስቀምጦአል፡፡ የመጨረሻውን የጉዞአችንን ክፍሎች ያሳየንና፤ ገና ለመንገድ ስንነሳ ለመሄድ ወዳቀድነው "ቅዱስ ቁርባን" አድርሶን ይመለሳል፡፡ አልፋችን ፍቅር አብሮን እንዳለ ነው፡፡ በባሕሪይው አልፋ ብቻ ሳይሆን ዖሜጋም ጭምር ስለሆነ እስከ ማብቂያችን ድረስ ተከትሎን ይመጣል፡፡ በብያኔ ደረጃ ስንነጋገር፤ ጉዞአችንን ስንጨርስ የምናርፈውም በፍቅር ቤት ነው፡፡ ፍቅር ለሁሉም መልካም ነገር መነሻም መድረሻም በመሆኑ፤ ይሄ ለሁሉም መንፈሳዊ ጉዞ የሚሠራና የሚሆን እውነት ነው፡፡ የንስሐ የመጨረሻ ጉብኝነት ሦስት ክፍሎች አሉት፡፡ እነርሱን እንመልከትና ንስሐን እንሰናበት!

     ✞ ንስሐ ከመግባታችን በፊት ምን እናድርግ?

    ንስሐ ሂደት ነው፡፡ መጀመሪያና መጨረሻ ያለው ሂደት፡፡ ይህ ከሆነ ከንስሐ በፊትና በኋላ የሚኖር ራሱን ችሎ የሚቆም የአካሄድ መልክ አለ ማለት ነው፡፡ አስቀድመን ስለፊተኛው የንስሐ መንደርደሪያ ገጽታ እንጨዋወት፡፡

   ወደ መንፈሳዊ አኗኗር ለመግባት ንስሐን በር አድርገን ስንዘልቅ፤ ኃጢአትን መጥላትና ስለ ኃጢአት መጸጸትን እንደምናገኛቸው ባለፉት ሁለት ክፍሎች ላይ አይተናል፡፡ ወደ ውስጠኛው ክፍል ስንገባ የምናገኘው ሦስተኛ ጉዳይ ታዲያ ኃጢአትን መናዘዝ ይሆናል፡፡

   እውነተኛ ንስሐ ኃጢአትን ፊት ለፊት ለራስ ከመናዘዝ ይጀምራል፡፡ ስሕተትን ማመን፣ ጥፋትን መቀበል፣ ውድቀትን አለመደበቅ፣ የዓመፃን ውጤት የማረም ፍላጎት ኃጢአትን ከጠላና በኃጢአቱ ከተጸጸተ ሰው ይጠበቃል፡፡ ነገሩን "ራስን መውቀስ" ብለን ልንጠራው እንችላለን፡፡ "እኔ ትክክል አልሠራሁም" ሲል ኃጢአቶቹን ሁሉ ተጋፍጦ ከራሱ ጊዜ ጋር ያልተወያየ ሰው፤ የነፍስ አባት ፊት ቀርቦ ኃጢአቱን ሊናዘዝ ድፍረትና አንደበት አይኖረውም፡፡

    ኃጢአትን በመዘርዘር ራስን የመውቀስ ልምድ፤ የተፈጸሙት ኃጢአቶች በምክንያት በኩል እንዳይደገፉ"ምን ላድርግ ታዲያ ወድጄ ነው?" እንዳያሰኙ ይከላከላል፡፡ ለየትኛውም የኃጢአት ክስ ምንም አይነት ሰበብ ማስተባቢያ ሊሆን አይገባም፡፡ ለምሳሌ ሰዎች "ለማስታረቅ ሲባል መዋሸት ምንም ማለት አይደለም" ሲሉ ይደመጣሉ፡፡ ሆኖም ግን እውነት ላይ ያልተመሠረተ እርቅ ቀድሞውኑ እርቅ አይደለም፡፡ ስለዚህ ይፈርሳል፡፡ በውሸት ላይ የተገነባ ይቅርታ ሊጸና አይቻለውም፡፡ ምክንያቱም ሐሰት በባሕሪይዋ ሳትለዋወጥና በአመክንዮቶች ሳትደበቅ መቆም አይቻላትም፡፡ በተቃራኒው እውነት መለኮታዊ ባሕሪይ ስለሆነች ከጊዜና ከሁኔታዎች ጋር አትለዋወጥም፡፡ ትናንትም፣ ዛሬም፣ ነገም ስትገለጥ በራሷ እምነትና ኃይል ተደግፋ ነው፡፡

    በእንደዚህ አይነት ምሳሌ በኩል ሌሎችንም ኃጢአቶች ማየት ያስፈልገናል፡፡ በአደንዛዥ ዕፅ ሰክሬ ነው፣ በፍርሃት ተውጬ ነው፣ በችግር ተይዤ ነው፣ .. የሚሉ ምክንያቶችን ለኃጢአት ማምለጫ አድርገን ለራስ ይቅርታ ማድረግ ንስሐን የሚቃወም አካሄድ ነው፡፡ ኃጢአትን መፈጸም በምክንያት ወንበር ላይ አኑረን ካባበልነው፤ ጸጸት የምንለው የንስሐ ገጽ ይቀደዳል፡፡ ይህን በኦሪት ዘልደት ታሪክ ላይ እናገኘዋለን፡፡

   አዳም የአምላኩን ሕግ ሽሮ ፈቃዱን ከፈጸመ በኋላ ስለ ሠራው ዓመፅ ሲጠየቅ በሔዋን ላይ አሳብቦ ነበር፡፡ ሔዋንም ተራዋ ሲደርስ ወደ እባቡ አመካኘች፡፡ ሦስቱም ግን የሥራቸውን ደመወዝ ተቀብለዋል፡፡ (ኦሪት ዘፍጥረት 3፥11-19)

    ኃጢአት በምክንያት መጋረጃ ከተጀቦነች ሳትገለጥ ትቆያለች፡፡ በተሸፈነችበት የሰበብ ጀርባ ሆናም ቀስ በቀስ ታድጋለች፡፡ ለዚህ ለእድገቷም የሚቀርቡ ሌሎች ምክንያቶችን ደግሞ በእያንዳንዱ ደረጃዋ ላይ ታስቀምጣለች፡፡ ይህን ከመናፍስቱ አንጻር ስንገልጸው፤ አማኞች በንስሐ ሕይወት ተይዘው ከኃጢአት ኃይል እንዳይላቀቁ ክፉው መንፈስ ከሥጋ ምክንያት በስተኋላ ተከልሎ ይሠራል፡፡

   ዘንዶው ሴቲቱ ፊት ይቆማል ብለናል፡፡ ከእግዚአብሔር የሆኑትን ሥራዎች በማየት ወደራሱ ሥርዓት አስገብቶ ለመጠቀም ሲሉ ዲያቢሎስ ሁልጊዜ በራሳቸው አንደኛ (መጀመሪያ) ሆነው የሚቆሙ ነገሮችን ይከተላል፡፡ ከፍቅር፣ ከእውነት፣ ከቸርነት፣ ከበጎነት፣ ከእውቀት፣ ከጥበብ፣ .. አንጻር ይቆማል፡፡ ከነዚህም ነገሮች ይወስድና "የኔ ነው" ሲል ራሱን ይሾምባቸዋል፡፡

   ባሕሪያችን በአዳም ዘመን ከእግዚአብሔር እቅፍ ተለይቶ ሲወጣ፤ የመንፈስ ቅዱስን ባሕሪይ ሳይተዋወቀው ነው የወጣው፡፡ በሌላ አገላለጽ አካላዊ መንፈስ ቅዱስ የሚያከናውናቸውን ነገሮች በቀጥታ መረዳት በማይችል ሥጋ ተወስነናል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔር ሲሠራ ለዚህ ሥጋችን (አእምሮአችን) የሚስማማ ምክንያትን ከሚፈጸመው ጉዳይ ጋር አያይዞ ያስቀምጥልናል፡፡

    ኖኅ ዓለምን ካጠፋው ውኃ የዳነው በመርከብ ስለተሳፈረ ነው፡፡ ግን በእርግጥ ነውን? .. እውነት ግዙፏ መርከብ ውኃውን ስለተቋቋመች ነው እነኖኅ የተረፉት? ብለን ስንፈትሽ፤ የእግዚአብሔር የፈቃዱ ኃይል እንጂ የመርከቢቱ ጥንካሬ ብቻውን ያንን ሁሉ ውኃ ሊቋቋም አይቻለውም፡፡ ዳዊት የሰማይ ስባሪ የሚያህለውን ጎልያድ በጠጠር ወንጭፍ መትቶ እንደጣለው ይነገራል፡፡ እዚህም ስንጠይቅ እውን አንዲት ጠጠር ይቅርና እንደ ጎልያድ ያለውን ቀርቶ አንድ አቅመ ደካማ አዛውንት እስከሞት በሚያደርስ ግፊት ልትጥል ይቻላታልን? .. አይቻላትም፡፡ ቢቻል ኖሮ ዛሬ ትልልቅ ድንጋዮች እንደ ሎሚ በሚወረወሩበት በዚህ ዘመን ብዙዎች ተፈንክተው ያልቁ ነበር፡፡

    መርከቢቱና ጠጠሯ ለኖኅና ለዳዊት (ለእኛም) ሥጋ የሚስማሙ ምክንያቶች ናቸው፡፡ የማይታየው ረቂቅ ኃይል የሚታይ ግዙፍ ሥራ ሲሠራ፤ ከፀሐይ በታች ላለው ሰብአዊ ባሕሪይ መግባቢያ ያደረጋቸው መንፈሳዊ ቋንቋዎች ናቸው፡፡

   ዘንዶው ደግሞ ከእግዚአብሔር ሥራ ፊት ይቆማል፡፡ አምላክ ሥራውን በምክንያት እየደገፈ ሲያከናውን ያየውን እርሱም ይደግማል፡፡ ክፉው መንፈስም ለክፉ ሥራዎቹ ምክንያትን ማስታከኪያ አድርጎ ይጠቀማል፡፡ ንዴትን ለጸብ፣ ቂምን ለበቀል፣ ቅናትን ለተንኮል ምክንያት እያደረገ ይሠራል፡፡ ለሰዎች ዓይንና አስተሳሰብ ተጨባጭ ከሚሆን ሥጋዊ ሰበብ ጀርባ ማንነቱን ይሰውራል፡፡ አንዳች ዝም የሚያደርገን (ማስተዋልን የሚነጥቅ) ምክንያት ባይኖር፤ ሥራው በቀጥታ በይፋ የሚከናወን ስለሚሆን በቀላሉ ልንነቃበት እንችል ነበር፡፡ መንገድ ላይ አንድ የማናውቀው ሰው ሮጦ መጥቶ አንገታችንን አንቆ ቢይዘን፤ "ሰውየው ምን ነካው? ሰይጣን ይዞታል እንዴ? እብድ ይሆን?" ብለን እንጠይቃለን፡፡ ራሱ ግለሰቡ ግን አንድን ጉዳይ ምክንያት አድርጎ ቢጣላን፤ ከዚህ ክስተት ጀርባ የክፉው እጅ አለበት ብሎ የማገናዘቡ አጋጣሚ በምክንያት ይሸፈናል፡፡

   የሙሴ በትር ለማይታየው የእግዚአብሔር ሥራ ምክንያት እንደሆነች ሁሉ፤ ኃጢአትም ከኑሮአችን ርቆ በንስሐ እንዳንታደስ ለዓመፃዎች ምክንያት እየሰጠ የማይታይ እስራትን ዲያቢሎስ በሕልውናችን ዙሪያ ይጠመጥማል፡፡

   ይህን በምክንያት ሽፋንነት የሚሠራ የክፉ መናፍስትን ውጊያ ለመፋለም የምንችለው ለራሳችን የመናዘዝ ባሕልን ስናዳብር ነው፡፡ በምክንያት የተደላደለ የዓመፃ ሥራችንን ስንወቅስ ነው፡፡ ለጥፋታችን ኃላፊነት የመውሰድ መንፈሳዊነት ሲኖረን ነው፡፡
 በተጨማሪ ለራስ በመናዘዝ ውስጥ ምን ምን ክህሎቶችን ልናገኝ እንችላለን?

ሀ)  ራስን የመመርመር ክህሎት
ለ)  ስሕተትን የመቀበል ክህሎት (ቅን ስነ ልቦና)
ሐ)  ለራስ ፈቃድና ውሳኔ ኃላፊነት የመውሰድ ክህሎት
መ)  ኃጢአት ሰክኖ እንዳይቀመጥ የመከላከል ክህሎት
ሠ)  ትሕትናን የመላበስ ክህሎት
ረ)  ግድየለሽነትን የመዋጊያ ክህሎት
ሰ)  ጥፋቶችን የማረም ፍላጎትና ክህሎት
ሸ)  ታማኝነትን ለራስ የማረጋገጥ ከህሎት
ቀ)  በሰው ሕይወት ላይ ያለመፍረድን ክህሎት

                       ✞  በርዕስ መጸለይ ✞

   ኃጢአቶቻችን ሁሉ አውጥተን በመዘርዘር ለራሳችን ከተናዘዝን በኋላ ቀጣዩ ሂደታችን መጓዝ ያለበት ወደ ርዕስ ጸሎት ነው፡፡ አስቀድሞ እንደጠቅሰነው (ምዕራፍ 1፤ ክፍል 7) የርዕስ ጸሎት ማለት አንድ ጉዳይን ለብቻ በመለየት፤ ስለጉዳዩ የሚመጥን ልዩ ትኩረትና ጊዜ ሰጥቶ መጸለይ ማለት ነው፡፡ ስለዚህ ንስሐ ከመግባታችን አስቀድሞ ስለሚከተሉት መሠረታዊ ምክንያቶች "ንስሐ ስለመግባት" በሚል ርዕስ መጸለይ ይገባናል፡፡

1)  የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለማስቀደም

   "ነገርን ሁሉ ውብ አድርጎ ሠራው" እንዲል መጽሐፍ፤ ንስሐ የምንገባበት ጊዜ በእግዚአብሔር ፈቃድ ተመርቶ ውብ ፍሬን እንዲያፈራ ስለ ንስሐ መግባት አስቀድመን መጸለይ አለብን፡፡ በተለይ "አምላክ ሰው ሆነ፥ ሰው አምላክ ሆነ" በሚል የተዋሕዶ ዶግማ የሚያምን ምዕመን፤ እግዚአብሔር ሰው ሆኖ ወገናችን ከሆነ ዘንዳ፥ እኛ ደግሞ የእርሱ ወገን ልንሆን ይገባናል በሚል መርህ ላይ ኑሮውን ይመሠርታል፡፡ በሌላ አባባል በሁለንተናው ላይ የእግዚአብሔር ፈቃድና ኃይል እንዲቀድም የራሱ የሆነውን ፈቃድና ውሳኔ አሳልፎ ይሰጣል፡፡ ሰው ንስሐ ልግባ ብሎ ሲወስን፤ ውሳኔው በራሱ የእግዚአብሔር መልካም ፈቃድ ሆኖ ሳለ፤ ይሄ ፈቃድ በምሪቱ ኃይል ታግዞ ወደ ተሳካ ፍጻሜ እንዲደርስ "አቤቱ አባት ሆይ፥ እኔ ስለንስሐ እንዲህ ወሰንኩ፤ አንተ ደግሞ ይህን እንዴት ታየዋለህ?" ብሎ መጠየቅ ያስፈልጋል፡፡ የእግዚአብሔርን ምሪት በነገር ሁሉ ማስቀደም፤ በውስጡ ራሱን የቻለ መለኮታዊ ክብር ይገለጥበታል፡፡ አምላክን እንደ አባት የማቅረብ የሐዲስ ኪዳን ተስፋ ይረጋገጥበታል፡፡ ፈጣሪ የሚገዛን ንጉሥ ብቻ ሳይሆን የሚያግዘን ወዳጅ ስለመሆኑ ይመሰከርበታል፡፡

2)  የመናፍስትን ቅደመ ዝግጅት ለማፍረስ

    በአካላዊ ገጽታ የማይዳሰሱት መናፍስት በሥጋ ስለማይጨበጡልን፤ በየዕለት የሕይወታችን ደቂቃ ውስጥ ጣልቃ ሊገቡ እንደሚችሉ ብዙዎቻችን እንዘነጋለን፡፡ በተለይ ደግሞ ምሽጋቸውን አፍርሶ ለሚጥለው እንደ ንስሐ ላለው መንፈሳዊ ሕይወት በቀላሉ እንደማይተኙልን አናስተውልም፡፡ ስለዚህ ንስሐ ለመግባት በወሰንን ጊዜ፤ ውሳኔያችን ወደ መሬት እንዳይወርድ በተለያየ ስልት (እንደ ጠባያችንና ኑሮአችን ሁኔታ) እንደሚዋጉ ስለማይገባን፤ እቅዳችንን ከዳር አድርሰን የኃጢአት ሥርየትን ማግኘት አልሆነልንም፡፡

   እንደ ዓይነጥላ ያሉ ከሩቅ የመመልከት ችሎታ ያላቸው መናፍስት በንስሐ መንገዳችን ላይ ከፊት ቀድመው ዕንቅፋት ያስቀምጣሉ፡፡ በኑሮ ምሳሌ ስናመጣው፤ ንስሐ ስለመግባት መወሰናችንን የሰሙ በዙሪያችን ያሉ ሰዎች ላይ በመሆን (ሠራዊት በመሳሳብ፣ ከውስጥ ወደ ውጪ በመናበብ)፤ ተቃራኒ ግፊት የሚያሳድር ተጽዕኖን ይፈጥራል፡፡ "ምንድነው በዚህ ዕድሜ ንስሐ የምትለው? መነኩሴ መሆን አማረሽ ወይ? ትንሽ ያካበድከው አልመሰለህም?" የሚሉ ይዘቶች ያሏቸውን አሳቦች ንግግር እያደረገ፤ በሰው እውቀትና ጠባይ ልክ እንደግለሰቡ ሆኖ ይዋጋል፡፡ ውሳኔን የሚሸረሽሩ፣ ሞራልን የሚያደቅቁ፣ የእምነትን ኃይል የሚያቃልሉ፣ መንፈሳዊነትን የሚያጣጥሉ፣ ሥጋዊ ብልጽግናን መለኪያ የሚያደርጉ፣ ነባራዊ ድርጊቶችን እንደ ምስክር የሚያቀርቡ ፈተናዎችን ያመጣል፡፡ አጠቃላይ የዚህ አይነት መልክ ያላቸው መሰናክሎች ሊታለፉ የሚችሉት በርዕስ ጸሎት ነው፡፡

    "ሊቀ ካህን ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ፥ ንሰሐዬን ጠብቅ፤ እኔ ያንተ እርሻ ነኝና ጠላት በእኔ እንርክርዳድ እንዳይዘራ ዙሪያዬን እጠረው፤ በምክንያትና በሰዎች ጀርባ እየተከለለ ክፉው እንዳያስታጉለኝ መንገዴን ምራኝ፤ ነፍሳት ሁሉ ይድኑና እውነቱን ወደማወቅ ጥግ ይደርሱ ዘንድ ሕያው ፈቃድ አለህና የመዳኔን ጉዞ አንተ ተረከብ፡፡ እውነትን ለማወቅ ስነሣ እውነት የመሰለ ሐሰት እንዳያታልለኝ በረድኤትህ ጋርደኝ፡፡ ሰማያዊ ባሕሪያትህን እውቀት አድርገህ አስተምረኝ፡፡ ወዳንተ የምመለስበትን ጎዳና ጠላት እንዳያጠፋብኝ፤ ከነፍስም ከሥጋዬም በኩል አብራልኝ" እያልን ስለ ንስሐ የተመለከተ አደራ ወደ አርያም መቅደስ ብንልክ፤ የውሳኔያችን ማሳ በዝንጀሮዎች እንዳይበዘበዝ "መልካሙ እረኛ" ኃላፊነቱን ይወስዳል (በነገራችን ክፉ መናፍስት በሕልም እይታ ዝንጀሮ ሆነው ብዙ ጊዜ ይገለጣሉ)፡፡

3)  ለንስሐ የምንሰጠውን ትኩረትና መሥዋዕት ይጨምራል

   የሰው ልጅ "ጉዳዬ" ብሎ ለይቶ የሚይዘው አጀንዳ ላይ ከፍተኛ ፍላጎትን፣ አስፈላጊ ጥረትን፣ የማይነዋወጥ ጽናትንና ተስፋ የማይቆርጥ ተጋድሎን ከባሕሪይው ውስጥ ለማንቃት አይቸገርም፡፡ ንስሐን እንደ ልዩ ጉዳይ በርዕስ ማክበር ያስፈለገው እንግዲህ ለዚህ ነው፡፡

   የንስሐችን ጊዜ ሥጋ ለብሶ በተጨባጭ እስኪሳካ ድረስ፤ በዕለት የግል ጸሎታችን ውስጥ ስለ ንስሐ እያነሱ በልዩ ትኩረት መጸለይ፤ ንስሐን አክብረን እንድንጠብቅ የሚያደርግ ስሜትን ይፈጥራል፡፡ መድኃኒቱ ባስተማረን ታላቁ ጸሎት ውስጥ "እኛ የሌሎችን በደል ይቅር እንደምንል፥ አቤቱ ኃጢአታችንን ይቅር በለን" በሉ ሲል ያሳሰበን አንድም ይሄንን ነው፡፡ በደልን የመሰረዝ፣ ኃጢአትን የመቃወም፣ ይቅርታን የመውደድ፣ ንስሐን የማክበር መንፈሳዊ አቋም እንዲኖረን ዘወትር እንዲህ ጸልዩ አለን፡፡

   ርዕስ አድርገን በተደጋጋሚ የምናነሳው የጸሎት ጉዳይ ሕልውናችን ውስጥ ዘልቆ የመዋሐድ ዕድሉ ሰፊ ነው፡፡ ወይንም በምናባችን ላይ እየተመላለሰ ከልቦናችን ርቆ የማይሄድ የአሳባችን አንድ ክፍል ይሆናል፡፡ እንዲህ ሲሆን ደግሞ፤ የንስሐን ዳገት (መቼም ኃጢአት ቀልቁለት ነው፤ አንዴ ከወረዱበት ቀሪውን እርምጃ ራሱ ይገፋፋል) ለመውጣት ጉልበት ማውጣት ስንጀምር ኃይል እየሆነ የሚያስቀጥለን ተስፋ ይሄ በልቦናችን የሚዋሐድ የንስሐ ርዕስ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር ንስሐ የምንገባበትን በሮች ሁሉ ዲያቢሎስ ጠርቅሞ ቢዘጋም፤ በተለሰነ ግድግዳ እንደማለፍ የሚተረጎም፥ በቀጭን መስመር ላይ ሳይንገዳገዱ የመራመድን ወኔ የምናገኘው ውስጣችን በሚመላለስ ብርቱ አሳብ ነው፡፡ ይህን አሳብ ለማስገኘት፣ ለማጠንከርና በእምነት ማኅተም ለማጽናት እንዲቻለን ነው የርዕስ ጸሎት ያስፈልጋል የተባለው፡፡


[በመጨረሻዎቹ ክፍሎች ንስሐን ለካህናት በመናዘዝ ጊዜና ከመናዘዝ በኋላ ምን እናድርግ፤ መቼ መቼስ እንናዘዝ የሚለውን ተመልከተን ምዕራፋችንን እንጠቀልላለን]

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.4•  ለንስሐ እንዴት እንዘጋጅ? ክፍል - ፯    የንስሐ መንገዳችን እነሆ ወደ መገባደዱ ደርሷል፡፡ ከ"ፍቅር" ተቀብሎ፤ ፍቅርንም በውስጡ ይዞ በራሱ ጎዳና ያንሸራሸረን "ንስሐ" እዚህ ድረስ ካመጣኋችሁ ለአሁኑ ይበቃል ብሎናል፡፡ ያላስጎበኘን ቦታዎች ስለሚኖሩ፤ ሌላም ጊዜ ወደርሱ መለስ እያልን እንድንጠይቀው የአደራ መልእክት አስቀምጦአል፡፡ የመጨረሻውን የጉዞአችንን ክፍሎች ያሳየንና፤…
2•  ንስሐ

   2.4•  ለንስሐ እንዴት እንዘጋጅ?

ክፍል - ፰

                 ✞ ለማንና እንዴት እንናዘዝ

   ከንስሐ ሂደት ውስጥ ወደ መጨረሻው አከባቢ የምናገኘው ክፍል "ኃጢአትን የመናዘዝ" ክፍል ነው፡፡ መናዘዝ በጥሬ ቃሉ አደራን መናገር፣ ሚስጢርን ማውጣት፣ ጥፋትን ማስረዳት፣ ስሕተትን መግለጥ ከሚሉ ግሶች ጋር አቻ ይገጥማል፡፡

   መናዘዝ የንስሐ መሠረታዊ አምድ ተደርጎ ቢወሰድ ትክክል ነው፡፡ ምክንያቱም ንስሐ ማለት የኃጢአት ሥርየት የሚገኝበት መንፈሳዊ ሕይወት በመሆኑ፤ በእግዚአብሔር ላይ ዓምፀን ያሳለፍናቸው ጊዜያት ሳይደበቁ ጥፋትነታቸውን መግለጥ ስንችል ነው ምሕረት የሚሰኘው ቀጣዩ የአምላክ ፍቅር የሚተረጎመው፡፡ ሆኖም ቀድሞውኑ በኃጢአታችን ተጸጽተን አውጥተን ልንጥላቸው ፈቃደኛ ካልሆንን፤ የይቅርታው መንፈስ በሕልውናችን ውስጥ ስፍራ የሚይይዝበትን ቦታ በማጣት ከኛ ለመራቅ ያለ አማራጭ ይገደዳል፡፡

   ስለመናዘዝ ስንነጋገር፤ አስፈላጊ ሆኖ የሚነሣው ጥያቄ "ኃጢአታችንን ለማን እንናዘዝ?" የሚለው ነው፡፡ እስቲ እንመልከተው፡፡

                  ሀ)  ለሰማያዊ ካህናት

"ንስሐ ከማያስፈልጋቸው ከዘጠና ዘጠኝ ጻድቃን ይልቅ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በሰማይ ደስታ ይሆናል።" (የሉቃስ ወንጌል 15፥7)

   በዕለተ እሁድ የተፈጠሩት ለባውያኑ ቅዱሳን መላእክት በሃይማኖታዊ አስተምህሮ ሰማያዊ ካህናት ተብለው ይጠራሉ፡፡ ምድር ላይ ሲሆን የምናየው ሁሉ የሰማዩን እውነት የተከተለ ነው፡፡ ይሄ መከተሉ ግን በሁለት አንጻር የሚገለጽ ነው፡፡ አንደኛ በጎ መንፈስ የሚመራው፤ የተቀደሰ ስብእና ባለቸው ሰዎች ውስጥ የሚገለጠው ቀጥተኛው መከተል ነው፡፡ ይሄኛው አንጻር "ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁ በምድርም ትሁን" ይላል፡፡ መለኮታዊው ኃይል በመላእክት ዘንድ የሚሠራውን ሥራ በእርሱም ላይ እንዲፈጽም ይለምናል፡፡ የአርያሙ ምስጋና በእርሱም አንደበት እንዲቀነቀን ይጠይቃል፡፡ መንፈሳዊው ሥርዓት በሕይወቱ ላይ እንዲታይለት ይማጸናል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የዘንዶው (ዲያቢሎስ) አካሄድ ነው፡፡

   ባሳለፉት ክፍሎች እንዳወሳነው፤ ክፉው መንፈስ ከሰማዩ ሥራ ፊት ይቆማል፡፡ ጻድቅ ነፍስ ያላቸው ሰዎች የሚፈጽሙትን እያየ የርሱን ሥራ ይሠራል፡፡ በእግዚአብሔር በኩል ሲተገበር ያስተዋለውን በራሱ አቅጣጫ ለውጦ በማከናወን "እኔ ፈጥርሁ" ይላል፡፡ ሐሳዊ መሲሕ ማለት ነው (መሲሑ የሠራውን ሥራ በራሱ የሐሰት መንገድ ተርጉሞ ይሠራና "የእኔ ነው" ይላል)፡፡

   ወደ ነጥባችን ስንመለስ፤ በቤተክርስቲያን የመቅደስ አገልግሎት ሲፈጸም የምናየው የክህነት ሥራ የሰማዩ ዓለም ነጸብራቅ ነው፡፡ በሌላ አባባል በጎው መንፈስ በሰማይ ያለውን ፈቃዱን በምድር በመግለጡ ነው፤ ቅዳሴን፣ ምስጋናን፣ ማኅሌትን፣ ኪዳንንና ሌሎች መንፈሳዊ ሥርዓቶችን በቤተክርስቲያን እንድንፈጽም የሆነው፡፡ ወይንም እዚህ በምድር የምንካፈላቸው መንፈሳዊ ሥርዓቶች የሰማዩ እውነት ምሳሌዎች ናቸው፡፡ ስለዚህ በምድር የምናያቸው ካህናት (የነፍስ አባቶቻችን) በሰማይ ያሉትን ካህናት (መላእክት) የሚወክሉ ናቸው፡፡ አክሲማሮስ አሳባችንን ያጸናልናል፦

"ሁለተኛም ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ኪሩቤል አላቸው፤ እነዚህም ካህናት ናቸው፤ የቀሳውስት አምሳል ናቸው"
"ሦስተኛም ዐሥሩን ነገድ ስማቸውን ሱራፌል አላቸው፤ የዲያቆናት አምሳል ናቸው፤ እነዚህም ዛሬ ዲያቆናት ተንሥኡ ለጸሎት ብለው እንዲጀምሩ ሁሉ የምስጋና ነቅዕ፣ የምስጋና ምንጭ በነዚያ ይጀመራል"

                                               መጽሐፈ አክሲማሮስ ዘእሑድ

የመላእክት መልክአ ጸሎት ደግሞ የሚከተለውን ይጨምራል፦

፴፫• ለከርሥከ፡፡ ... ሰማያዊው ካህን ሆይ በሰባተኛው ሰማይ የመሠዊያ አዳራሽ ቆመህ በጸሎትህ ኃጢአቴን ታስተሠርይ ዘንድ እኔ አጋልጋይህ ካህኑ ሚካኤል እያልኩ እማልድሃለሁ፡፡
                                                  መልክአ ሚካኤል

፭• ለገጽከ፡፡ ... ገብርኤል ሆይ በንጽሕና ልብሰ ተክህኖ የተሰየምክ አንተ በፍርድ ያይደለ በክርስቶስ ቸርነት እድን ዘንድ የነግሁንና የሠርኩን መሥዋዕት በምታሣርግበት ጊዜ የእኔን የኃጥኡን ኃጢአት አስተሠርይ፡፡
                                                  መልክአ ገብርኤል

፲፭• ለእመትከ፡፡ ... ሩፋኤል ሆይ የአምላክ ካህን ሚስጢረ ቅዳሴ ቀዳሽ አንተ ነህ፡፡
                                                   መልክአ ሩፋኤል

   ለምሳሌ ያህል ይህንን ካልን ይበቃል፡፡ ለማለት የተፈለገው መላእክትም እንደ ነፍስ አባት የሚያገለግሉን ሰማያዊ ካህናት ናቸው ነው፡፡ ስለዚህ ኃጢአታችንን ለእነርሱም በጸሎት መልክ መናዘዝ እንችላለን፡፡

   ባሳለፍነው ክፍል ላይ ኃጢአትን ለራስ መናዘዝና ስለ ንሰሐ በርዕስ መጸለይ ስንል ያነሣውን አሳብ እዚህ ከጠቀስነው የሰማያውያን ካህናት አገልግሎት ጋር ማያያዝ እንችላለን፡፡ ማለትም ራሳችንን የምንወቅስበትን ጸሎትና ስለ ንስሐ የምናቀርበውን ልመና አድራሻውን ወደ አንድ የተወደደ መልአክ ብናደርገው ብዙ እንጠቀማለን፡፡ (በነገራችን መጋቢ ሐዲሱ የኔ ነፍስ አባት ነው)

   መላእክትን እንደ ንስሐ አባቶች አድርገን ጸሎተ ኑዛዜን ማቅረብ በዋነኝነት ሁለት ጥቅም ይሰጠናል፡፡ አንደኛ መድኃኒቱ እንደተናገረው በአንድ ኃጥእ ነፍስ መመለስ በደስታ የሚሞሉት መላእክት፤ የንስሐ ጉዞአችንን አሳልፈን ስንሰጣቸው፤ በተሰጣቸው የተራድኦ አገልግሎትና በመንፈሳዊ ድጋፍ ንሰሐችንን በሰላም ጀምረን እንድንጨርስ ያግዙናል፡፡ ሁለተኛው ደግሞ የክፋት ካህን የሆኑት ክፉ መላእክት ከንስሐ ጎዳናችን ላይ ጋሬጣ ሊሆኑ መቆማቸው የማይቀር በመሆኑ፤ እነርሱን ይዋጉልናል፡፡

   እንደ ማሳሰቢያ የምትይዙልኝ፤ መላእክትን የነፍስ አባት አድርገን የመያዝ መንፈሳዊ ልምምድን ስንማር ምድራዊያን ካህናት አያስፈልጉንም ወደሚለው አሳብ በጭራሽ እንዳይመጣ፡፡ ምክንያቱም የረቂቃኑንም የግዙፋኑም ካህናት ሊቅ የሆነው ተወዳጁ፤ በሥጋ በተገለጠ ጊዜ ኃጢአትን የማስተሠረይ ሥራን በተጨባጭ ይሠራ ነበር፡፡ ይህንንም ሥልጣኑን ለተማሪዎቹ በመንፈስ ቅዱስ በኩል አቀብሏቸዋል፡፡ ስለዚህ የሥጋ አባቶች አያስፈልጉኝም የሚል ማንኛውም ሰው ይህንን የሐዲስ ኪዳኑን ሥርዓት እየከዳ ነው፡፡ እሰቲ ወደ ምድራዊያን ካህናቶች ደግሞ እንምጣ፡፡

                ለ)  ለምድራዊ ካህናት

"ኃጢአታቸውን ይቅር ያላችኋቸው ሁሉ ይቀርላቸዋል፤ የያዛችሁባቸው ተይዞባቸዋል አላቸው።" (የዮሐንስ ወንጌል 20፥23)

   መድኃኒቱ ክርስቶስ በሐዲስ ኪዳን የምሕረት ዘመን ከሰጠን አንዱ ሥርዓት መካከል የክህነቱ አገልግሎት ይገኝበታል፡፡

    መሲሑ ተሰቅሎ ከሞተ በኋላ ምስክሮቹ ሐዋሪያት ያስተማራቸውን የትንሣኤ ትምሕርት ዘንግተው፥ በፍርሃት የተነሣም ደጆችን ዘግተው፥ ሳሉ ሞትን ድል ያደረገው ጌታ በተዘጋ በር አልፎ በመግባት "ሰላም ለእናንተ ይሁን" አላቸው፡፡ ለጥቆም አስትንፋሱን በነርሱ ላይ አሳረፈና "መንፈስ ቅዱስን ተቀበሉ፤ በምድር የፈታችሁት ሁሉ በሰማይ የተፈታ ይሁን፤ በምድር ያሠራችሁት በሰማይም የታሠረ ይሁን" ሲል ቀደም ሲል በጴጥሮስ በኩል ሰጥቶአቸው የነበረውን ሥልጣነ ክህነት አጸደቀላቸው፡፡
  እግዚአብሔር በባሕሪይው ሕያው ነው፡፡ ከዚህ የተነሣ አሳቡም፣ ቃሉም፣ አነዋወሩም ሕያው ነው፡፡ ለአዳም የተናገረው ቃል እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ የሚደመጥ ሕያው ቃል ነው፡፡ የእግዚአብሔር ነገር በቦታና በጊዜ የተወሰነ ቢሆን ኖሮ መጽሐፍ ቅዱስ ውድቅ ይሆን ነበር፡፡ በነ'አብርሃም ሕይወት የሆነው የአምላክ ሥራ በኛ ላይ የማይሆን ከሆነ፤ ታሪካቸውን ማወቅ ብቻ ምን ይጠቅማል?

   ይህንንም ጉዳይ መድኃኒቱ ለደቀመዛሙርቱ ሲያረጋግጥላቸው እንዲህ ይላቸዋል፤ "እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።" (የማቴዎስ ወንጌል 28፥19-20)

   እስከ ምፅዓት ድረስ ከእናንተ ጋር አለሁ ካለ፤ የተናገራቸውና የሰጣቸውም ሥልጣን በባሕሪይ ሕያው ሆኖ ይቀጥላል ማለት ነው፡፡ እነ ጴጥሮስ በሥጋ ቢሞቱም፤ በነርሱ ባሕሪይ የተጻፈው ክህነት መንፈሳዊውን ሰንሰለት ጠብቀው በሚቀጥሉ ሰዎች ላይ መነበቡን ይቀጥላል፡፡ መድኃኒቱ በሐዋሪያቱ ላይ እፍ ያለው ሕያው እስትንፋስ የሚሠርጽበት ሰማያዊ ሥርዓት እስካልተቋረጠ ድረስ በካህናት ላይ ያለው ሥልጣን የመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን ነው፡፡

  እዚህ ጋር አንድ ነገር እናንሣ፡፡ በባሕሪይ የሚቀጥለው የነ'ጴጥሮስ ክህነት ብቻ አይደለም፡፡ የነ'ሐና (የኦሪቱ ሊቀ ካህን) ሥልጣንም እንደቀጠለ አለ፡፡ ክርስቶሳዊውን የመገለጥ ስብእና የሚያሳድዱ ከእውነተኞቹ አንጻር የቆሙ የብሉይ ካህናት እንደሚኖሩ ማስተዋል መልካም ነው፡፡ በዘልማድነት የሚታወቅ፤ አገልጋዮችን ክፉ መንፈስ አያጠቃም የሚል አስተሳሰብ፤ በብዙ ምዕመናን ላይ አለ፡፡ ግን ልብ እንበል፤ እንኳን "በሥጋቸው ቄሣር፥ በነፍሳቸው ዲያቢሎስ" የተቆራኛቸውን የብሉይ አገልጋዮች ቀርቶ፤ የሰማይ በሮች መክፈቻ የተሰጠውን ደቀመዝሙርም ሰይጣን እንዳሳተው መጽሐፍ ቅዱስ ይናገራል፡፡ (የማርቆስ ወንጌል 8፥33)

   ስለዚህም ነው ሰማያዊ ካህናትን ከጎን ማድረጉ ተገቢ ነው የሚያሰኘው፡፡ ዲያቢሎስ በአገልጋዮችም በኩል ሥጋዊ ምክንያትን፣ የእውቀት መጋረጃንና ድብቅ አጀንዳን ተገን አድርጎ ብዙ ፈተና ሊያመጣ ይችላል፡፡ ይህንን ፈተና የምናልፈው ደግሞ በሰማያውያኑ እርዳታ ነው፡፡

  እንዲህ ሲባል ካህናትን የመናቅ፣ አሳንሶ የማየትና የመራቅ አዝማሚያ በአእምሮ ምናብ እንዳይቀረጽ በማጤን አንብቡ እላለሁ፡፡ ካህናትን መሳደብና ማብጠልጠል የዚህ ዘመን አንድ "የማወቅ ፋሽን" መገለጫ ሆኗል፡፡ ይሄ ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ሲያልፍም የዲያቢሎስ ስልታዊ ምሪት ነው፡፡

   በተገቢው ሥርዓትና አካሄድ የሐዲስ ኪዳንን ሥልጣን የተቀበሉ ካህናትን ሁሉ ማክበር መንፈስ ቅዱስን ማክበር ነው፡፡ ምንም አይነት የግል ሕይወት ይኑራቸው፤ ለክህነታቸው ተገቢውን ቦታ መስጠት የክርስቲያኖች ኃላፊነት ነው፡፡ በኃጢአት ውስጥም እየተመላለሱ ሳለ፤ ሥልጣን የሰጣቸውን መንፈሳዊ እውነት እስካልከዱ ድረስ በንጹሑ ልቦና "ከኃጢአት ማሠሪያ ይፍታህ" ሲል የጸለዩለት ነፍስ ሁሉ ነጻ ይወጣል፡፡ ላጠፉት ጥፋታቸው ክህነታቸው ሳይሆን ራሳቸው በግል ይጠየቃሉ፡፡ ሲጠቃለል አገልጋዮች በተሰማሩበት መንፈሳዊ ሥራ ላይ ሁሉ ልበ ቀና ድጋፍን፣ ትሕትናን፣ ክብርንና መታዘዝን መሥዋዕት አድርጎ መግለጥ ታላቅ አስተዋይነትና ምዕመናዊ ድርሻም ጭምር ነው፡፡

   ይህን የማስተዋል ኃይል ይዘን ሳለ፤ የሴረኛውን መንፈስ ወጥመድ ለማክሸፍ ሰማያዊ ካህናትን ማሰለፍ ደግሞ ብልህነት ነው፡፡ ስለ ክፉ መንፈስ ባሕሪይና ውጊያ በቂ መረጃ የሌላቸውን ሰዎች ከለላ ያደረገ መሰናክልን ለመሻገር ረቂቃኑን ቀሳውስት መያዝ የማይታየውን ፍልሚያ የማየት ክህሎት ነው፡፡ ከዚያም በላይ ልበ ንጹሕ (በጎቹ) የሆኑ የነፍስ አባቶችን (እረኞችን) ምናልባት የገባንን ያህል የውጊያ ሕይወት ለማሳየት ዕድል የሚሰጥ አጋጣሚን ለመጠቀምም መላእክቱ ያስፈልጉናል፡፡ ፍቅር ተዓምረኛ ነው፤ የማይሠራው ሥራ የለም!

       ✞ ኃጢአትን እንዴት እናዘዝ ? ✞

  ግልጽ ነው፤ ለሰማያዊያን ካህናት የምንናዘዘው በንስሐ ጸሎት በኩል ነው፡፡ በነገራችን ላይ ቅዱሳንም የረቂቁ መቅደስ ተሳታፊዎች እስከሆኑ ድረስ የንስሐ ጸሎታችንን ተቀብለው ሊያግዙን ይችላሉ፡፡ የመናዘዝ እንዴትነት ዝርዝር የሚያስፈልገው ለምድራዊያን ካህናት ነው፡፡ የሚከተሉትን የመናዘዝ መሥፈርቶች ማወቅ ተገቢ ነው፦
  
ሀ)  ኃጢአትን ሁሉ ሳይደብቁ መናገር

  የንሰሐውን ጸሎት በግል ስናደርስ በሥጋ የምናየው አካል ስለሌለ፤ አእምሮአችን በግዙፍ መልክ የማያየውን ሕልውና እንደሌለ አድርጎ ስለሚወስድ፤ "የሚያሳፍሩ" የምንላቸውን ኃጢአቶቻችንን አውጥተን ለመናገር አንቸገር ይሆናል፡፡ ግን በሥጋ የምናያቸው ካህናት አጠገብ ስንሆን የማፈር፣ የመሸማቀቅና ምን ይሉኛል የማለት አሳብ ማመላለሳችን የሚጠበቅ ነው፡፡ አንድም ምድራዊ የነፍስ አባቶች ያስፈለጉት ለዚህ ነው፡፡

  አንድ አማኝ ሰው በኃጢአቱ ሊያፍር በእርግጥም ይገባዋል፡፡ የፈጸመው ጽድቅ አይደለምና ስሕተቱን ቢያዝንበት ተገቢ ነው፡፡ ይህ የሐፍረት ስሜት ንጹሕ መሆንን ከማመንና ከመፈለግ ጋር ተያያዥነት አለው፡፡ ስለዚህ አባቶች ፊት ኃጢአትን ሲናገሩ ማፈር ጤናማ ሰዋዊ ስሜት ነው፡፡

  ነገር ግን ይህ ስሜት ድንበሩን ጥሶ፤ ኃጢአቱን እስከ መሸሸግ የሚያድረስ ልክ ላይ ከደረሰ፤ በስሜት ውስጥ ገብቶ ጭንቅላት ላይ አሉታዊ ድምፅ እየሆነ ያለ የመንፈስ አሠራር  ስለመኖሩ ግንዛቤ ልናገኝ ያስፈልገናል፡፡

  የቱን ያህል አሳፋሪ ብለን ያስቀመጥናቸው የኃጢአት ታሪኮች ይኑሩን፤ ሁሉንም በመዘርዘር ለካህኑ መናዘዝ ይጠበቅብናል፡፡ ዲያቢሎስ ኃጢአትን እንደ ምሽግ አድርጎ ይቀመጥበታል ያለውን ትምሕርት እዚህ እናስታውስ፡፡ ባልተናዘዝነው ኃጢአት ውስጥ ገብቶ ለመደበቅ፤ መናገር ያለብንን እንዳንናገር የሐፍረትን ነገር ምክንያት አድርጎ ይፈታተናል፡፡

  ስለሆነ ካህን ፊት ቀርቦ ኃጢአትን ከመናዘዝ አስቀድሞ፤ የምናዘዛቸውን ሁሉ በሚገባ አሰታውሶና እንዳይጠፉም በወረቀት መዝግቦ መዘጋጀት፤ በኑዛዜ ጊዜ ያለውን የመንፈስ ውጊያ ያሸንፍልናል፡፡

ለ)  እግዚአብሔር ፊት እንደሚናገሩ ማሰብ

  ከላይ ባሉት አንቀጾች እንዳወጋነው፤ ኃጢአትን የመፍታት ሥልጣን በመድኃኒቱ እፍታ በኩል ለሰዎች ተሰጥቶአል፡፡ ማለትም መንፈስ ቅዱስ በካህናት ሥልጣን ላይ ሆኖ ኃጢአታችንን የሚያስተሠርይበት ሥርዓት ነው የተሠራው፡፡

  እንዲህ ከሆነ፤ ከካህናት ፊት ሆነን ስንናዘዝ፤ ከእግዚአብሔርም ፊት ቆመን ንስሐ እየገባን እንደሆነ ማመን ይገባል፡፡

  አንዳንድ ጊዜ ሰዎች በዓይን ሲመለከቱ የሚያዩት እንደነርሱ ያለን ሰው ስለሆነ፤ በካህኑ ሥልጣን ላይ የሚገኘውን መንፈስ ቅዱስ በመዘንጋት በቸልተኝነት "እንደ ነገሩ" ይናዘዛሉ፡፡ በሌላ አባባል ንስሐ እየገቡ እንደሆነ አምነው ሳይሆን የአዘቦት ቀን ጭውውት እያደረጉ እንደሆነ ያህል ለኑዛዜው የሚሠዋውን የእምነት ክብርና ቦታ ግዴለሸ ይሆኑበታል፡፡ ይሄ ደግሞ ለኃጢአቱ ሥርየት የሚታዘዘውን ቀኖና በአስፈላጊ ትጋትና ድካም እንዳንፈጽም ለክፉው በር የሚከፈት ጠባይ ነው፡፡

  "እንኳንስ ዘንቦብሽ.." የሚለው አባባል ለዲያቢሎስም ይሠራልና፤ እንኳንስ ግዴለሽ የመሆንን ጠባይ አግኝቶ አይደለም በንቃትና በቁርጠኝነት እየታገልነውም ሳለ፤ ጥቃቅን ስሕተቶችን ሰብስቦ ትልቅ ክምር የሚያህል ፍልሚያን የሚያመጣብን አደገኛ ፍጡር ነው፡፡ በመሆኑም ከካህናት ጋር ስንነጋገር፤ ለአምላክ መንፈስ በሚገባ "የአቤል መሥዋዕት" ልክ ትኩረት ሰጥተን ቢሆን መልካም ነው፡፡

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
@bemaledanek
በማለዳ ንቁ ቁጥር ! ፪
2•  ንስሐ    2.4•  ለንስሐ እንዴት እንዘጋጅ? ክፍል - ፰                  ✞ ለማንና እንዴት እንናዘዝ ✞    ከንስሐ ሂደት ውስጥ ወደ መጨረሻው አከባቢ የምናገኘው ክፍል "ኃጢአትን የመናዘዝ" ክፍል ነው፡፡ መናዘዝ በጥሬ ቃሉ አደራን መናገር፣ ሚስጢርን ማውጣት፣ ጥፋትን ማስረዳት፣ ስሕተትን መግለጥ ከሚሉ ግሶች ጋር አቻ ይገጥማል፡፡    መናዘዝ የንስሐ መሠረታዊ አምድ ተደርጎ…
2•  ንስሐ

   2.5• ንስሐ መቼ መቼ እንግባ ?

ክፍል - ፱

           ✞ ከትንሹ ወደ ትልቁ መሰብሰብ

   ልዑል እግዚአብሔር ተፈጥሮአዊ ዑደትን በጠበቀ አሠራሩ በአብዛኛው ጊዜ ነገሮችን ሲገነባ ከትንሹ ወደ ትልቁ በመሰብሰብ የመመሥረቱ ጉዳይ እሙን ነው፡፡ ትልልቅ ነገሮች የተገነቡበትን መድረሻ ፈለግ ተከትለን ወደ መነሻቸው ብንሄድ፤ የምናገኘው ትንንሽ ነገሮችን ነው፡፡ እኛም የሰው ልጆች በዘፈጥረታቱ ስድስት ቀናት (ባሕሪያት) ድምርነት የተገነባን ፍጡሮች ነን፡፡

   ከትንሹ ወደ ትልቁ የመሰብሰብ አሠራር ደግሞ የራሱ የሆነ  ልዩ ጊዜ ወይንም ሂደት ይኖረዋል፡፡ መንፈሳዊ ሕይወትም ሂደት ነው፡፡ የምንነጋገርበት የንስሐ ጉዳይም እንዲሁ መነሻና መድረሻ ያለው ጉዞ እንዳለው ባለፉት ክፍሎች አንስተናል፡፡ ሁሉን መንፈሳዊ ሂደት ስለሚጠቀልለው ጉዞ የሐዲስ ኪዳን መጽሐፍ እንዲህ ይላል፦ 

"እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እኔን ምሰሉ።" (1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 11፥1)


   በመግቢያው አንቀጽ ላይ ማሳያ እንዳደረግነው የሰው ልጆች በስድስቱ ቀናት በተሰበሰበ የባሕሪይ ውጤትነት ተፈጥረናል፡፡ ከኛ አስቀድሞ የተፈጠሩት ፍጥረታት ባሕሪይ በሙሉ በኛ ውስጥ አለ፡፡ እነዚህን የተለያየ ስብጥር ያላቸውን ባሕሪያት ሥርዓት ባለው ደንብና ቅርጽ ለማስተዳደር እንድንችል ደግሞ የአምላክ መለኮታዊ ባሕሪይ በእፍታ በኩል ተለግሶናል፡፡ "ምድርን ግዙአት" የሚለው የገነቱ ድምፅ የተደመጠው ለዚህ ባሕሪያችን ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በውስጣችን ያሉትን ባሕሪያት የመግዛት ሥልጣን የተጻፈልን በነፍሳችን ላይ ነው፡፡

   ይህች ነፍስ የእግዚአብሔር መንፈሳዊ አካል እንደመሆኗ፤ በአርአያውና በአምሳሉ እንድንቀረጽ መልክ ሆና የተቀመጠች ሕልውናችን ናት፡፡ በገጠመን ውድቀትም የተነሣ ጀርባችንን ለእግዚአብሔር ሰጥተን ፊታችንን ወደ ምድር  በማዞር ከፀሐይ በታች ወዳለው ሕይወት ስንሰደድ (በመጽሐፍ አገላለጽ ወደ አፈር ተመለሱ ስንባል)፤ ካጣናቸው (ከረሳናቸው) እውነታዎች መካከል አንዱ የአምላክ ምሳሌ ሆነን የተፈጠርንበትን የባሕርይ ልዕልና ነው፡፡

   አዳም ፊቱን ወደ ምድር አዙሮ ከአምላክ ፈቃድ ወደ ሥጋ ፈቃድ ሲወጣ፤ ስድስቱ የቀን ባሕሪያት በውሰጡ ተሰብስበው እንደሠሩት ዘንግቷቸዋል፡፡ ወይንም ከስድስተኛው ቀን (ሰብአዊነት) እየፈረሰ በመውረድ ወደ አንደኛው ቀን (አፈርነት) ይመለሳል፡፡ ከትልቁ ወደ ትንሹ መመለስ እንደማለት!

   ከትልቁ ወርደን ወደ ትንሹ ሄደን ከወደቅን፤ ለመነሣት ከፈለግን ይህንኑ ሂደት መከተል ይኖርብናል፡፡ ማለትም ከመጀመሪያው ቀን የአፈርነት ባሕሪይ ተነሥተን ወደ ስድስተኛው ቀን ሰብአዊነታችን መገሥገሥ አለብን፡፡ ይሄንን በራሳችን ልናደርገው አንችልም፡፡ ሰለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ የሰው ልጅ ሆኖ ወደኛ ይመጣ ዘንድ ግድ ሆነ፡፡ በመሆኑም ከአዳም (የመጀመሪያው ዘመን ትውልድ) እስከ ድንግል ማርያም (ስድስተኛው ዘመን ትውልድ) ድረስ በስድስቱ ቀናት በኩል ዳግም እየሰበሰበ በቃሉ ሲሠራን ቆየና፤ [በሰማይ] በተፈጠርንበት አርብ አጋማሽ ([በምድር] 5500ኛው ዘመን) ላይ ሲገነባን የቆየው ቃል ሥጋ ሆነ፡፡ የጠፋብን እግዚአብሔርን የመምሰል መልክ ስለመገኘቱም ማረጋገጫ የሚሆነው ሕያው ቃል "የሚወለደው ቅዱስ የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል" በሚለው የገብርኤል ብሥራት ውስጥ ተደመጠ፡፡ (የሉቃስ ወንጌል 1፥35)

   መድኃኒቱ በእግዚአብሔር ልጅነቱ በኩል ሁላችንን የእግዚአብሔር ልጆች ሊያደርገን ሰማያዊ ሥልጣንን ሲሰጠን፤ ከዙፏና የወረደቺው ነፍሳችን ወደ ቀደመ ክብሯ ተመለሰች ማለት እንችላለን፡፡ በሌላ አነጋገር በክርስቶስ መንገድነት እየተጓዝን ወደ ባሕሪይ ልዕልናችን የምንመለስበት ጉዞ ሐዲስ ኪዳን በተሰኘ የምሕረት ቃልኪዳን ተሰጥቶናል፡፡ ይህንን ነው እንግዲህ ሐዋሪያው "እኔ ክርስቶስን እንደምመስል እናንተንም እኔን ምሰሉ" ሲል ያሳሰበን፡፡

   በክርስቶስ መንገድነት (በክርስትና) እየተጓዝን ነው ማለት ፊታችንን (ሕልውናችንን) ወደ እግዚአብሔር ፈቃድና እውነት አድርገን አምላክን ወደ መምሰል ሰማያዊ ማንነት እያደግን ነው ማለት ነው፡፡ ይሄንን ሂደት የሚቃወመው እባብ በዚህ ጊዜ ከፊታችን መጥቶ ይቆማል (በሰማያዊው ጊዜም ላይ አዳም እግዚአብሔር አስቦ ወዳዘጋጀለት ከፍታ (ሰባተኛዋ ቀን) እየሄደ ሳለ ነበረ እባቡ በአካሉ (በሔዋን) ፊት መጥቶ የቆመው)፡፡

   ዲያቢሎስ እንደ አምላክ በመሆን የዓመፃ መሻቱ ውስጥ የአምላክን መለኮታዊ አሠራርና ድንቅ ጥበብ ለመኮረጅ በእጅጉ የሚጥር ቀናተኛ ፍጡር ነው (ዘንዶው ሴቲቱ ፊት ልጅዋን ሊበላ ይቆማል ያልነውን ካለፉት ክፍሎች አስታውስ)፡፡ እግዚአብሔር አምላክ ከትንንሽ ነገሮች ወደ ትልልቅ ገጽታዎች የሚመጡ ግሩም ነገራትን ሲሠራ፤ ክፉው መንፈስም ትንንሽ ጥፋቶችን ወደ ትልልቅ ውድመቶች ሰብስቦ ግዙፍ የሆነ የታሪክ ጉዳትንና የትውልድ ቁስለትን ያስከትላል፡፡

   ይሄ ማለት በክርስትና የእምነት ጎዳና ላይ (በሐዲስ ኪዳን) በሁለንተናችን ስንራመድ፤ እንደ ጥንቱ አዳም (እንደ ትውልድ ብሉይ ዘመን) ፊታችን ወደ ሥጋ ፈቃድ እንዲጠመዘዝ በየቀኑ ይታገላል፡፡ እነዚህ የየዕለት ፍልሚያዎቹ በዋነኝነት ኃጢአትን እንድንፈጽም በማስደረግ ላይ ያተኮሩ ናቸው፡፡

   ክፉው መንፈስ ከሰውነት ውስጥ ገብቶም ይሁን ከውጪ ባለ ሁኔታ፤ ፈተናዎቹን የሚያመጣው "በየቀኑ" ነው፡፡ ምክንያት? .. ዘወትር የተለያዩ ስልቶችን እየተጠቀመ ዓመፃ ላይ እንድወድቅ ፈተነ ማለት፤ ከትንሹ ወደ ትልቁ በመሰብሰብ ዑደት የሚዞር የጊዜ ሥርዓትን ሳያባክን በሥራ ላይ በመዋል፤ ሲታዩ ትንንሽ "የሚመስሉ" አጋጣሚዎችን ሰብስቦ እያጠራቀመ በመዋጋት፤ በፍጻሜው ነፍስን ከእግዚአብሔር እቅፍ እስከወዲያኛው መለየት የሚል ትልቅ ራእዩን እየተከተለ ነው ማለት ስለሆነ፡፡

   መናፍስት ጥፋትንና ኃጢአትን ወደ ሰው ልጆች ከማድረስ ጋር በተያያዘ ተልዕኮአቸው፤ ይሄ ትንሽ ፈተና ነው ብለው የሚንቁት፣ ይሄ ትንሽ ጽድቅ ነው ብለው የማይፋለሙት፣ ይሄ ትንሽ መሰናክል ነው ብለው የማያስቀምጡት፣ ይሄ ለውጥ የማያመጣ ትንሽ ትግል ነው ብለው የሚዘሉት፤ የየቀን አጋጣሚ የላቸውም፡፡ እንደው ምንም ዋጋ ባይኖረው እንኳ፤ የደቂቃ እምባ ማስለቀስ ለእነርሱ በእጅጉ ደስታን ይሰጣቸዋል (በቅዱሱ መንፈስ አንዲቱ በግ እስከ መስቀል ሞት ድረስ የተወደደችው በተቃራኒው መንፈስ በእጅጉ ስለተጠላች እንደሆነ ያስተውሏል!)፡፡

   እኛ ደግሞ በተቃራኒው ትንንሽ ብለን የመጠን ልክ ያወጣንላቸውን ኃጢአቶች፣ ጥቃቅን የሚመስሉ ስሕተቶችንና የተላመዱንን ጥፋቶች እንንቃለን (ግን ክርስቶስ የማይደስበት ትንሽ ጽድቅ፥ ሰይጣን የማይደስትበት ትንሽ ኃጢአት የለም!)፡፡ ትንንሽ አልከናወን ያሉ ችግሮችን ይዘናቸው እንጓዛለን፡፡ በዚህም ርኩሳን መናፍስት ለሚገነቧቸው ትልልቅ ዓመፃዎች የግንባታ ጡብ የሆኑ ትንንሽ ልማዶች የማንታረምባቸው ዝንባሌዎቻችን ሆነው አንዴ በትልቁ የምንፈርስበት ምክንያት፤ ያላስተዋልናቸው አሊያ በቸልተኝነት የምናልፋቸው የየዕለት ውድቀቶቻችን ናቸው፡፡

   ለምሳሌ፤ ሐሜት፣ ፌዘኝነት፣ ችኩልነት፣ ግንፍልነት፣ ግዴየለሽነትና መሰል ጠባያት በየቀን የኑሮ ልምምዳችን ውስጥ የጊዜያችን አካል ለመሆን የሚታጉሉ "ትንንሽ" የመናፍስት ፈተናዎች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜትን ተገን ያደረጉ የዕለት ተዕለት ግፊቶች፤ በአብዛኞቻችን አኗኗር ውስጥ የተካተቱና በቁጥር እጅግ የበዛ ሰው ስለሚገኝባቸውም እንደ ጥፋት ከመቆጠር የራቁ አሰናካይ "ጠጠሮች" ሆነዋል፡፡
   ከትንሹ ወደ ትልቁ በመስብሰብ ሂደት ውስጥ ብዙዎቻችን ከተጎዳንባቸው ነገራት መካከል አንደኛው ውሸት ነው፡፡ በየቀኑ ትናንሽ ውሸቶችን ቀለል አድርገን ስንዋሽ .. ስንዋሽ፤ እንግዲህ ዛሬ በዚህ ዘመን፥ በዚህ ትውልድ "የማይዋሽ ሰው" ውሸታም እስከሆነበት ጥግ ሁላችንም ሐሰትን የሕይወታችን ባለንጀራ ስናደርገው፤ እውነትን ብቻ እየተናገርን ያሳለፍናቸው ቀናት እየከሰሙ .. እየከሰሙ ሄዱ፡፡ ስለሆነም ከውሸት ጋር ተጣብቶ መኖርን ተላምደን (ከትንሹ ወደ ትልቁ የሚሰበሰቡ ነገራት ልማድ የመሆን ዕድላቸው በጣም ሰፊ ነው)፤ ንስሐ በተባለ ሽምግልና ከእውነት ጋር ታርቀን የመንፈስ ቅዱስ መግለጫዎች ለመሆን እስኪከብደን ድረስ በጣም ተቸገረን እንገኛለን፡፡

   ባለንበት የሐዲስ ኪዳን ዘመን ዲያቢሎስ የየዕለት ኃጢአቶችን ለሕይወታችን ለማሰልጠን በእልህና በትጋት ጥርሱን ነክሶ የሚሠራው ለዚህ ነው፡፡ ከኃጢአት ጋር ተስማምቶ በመኖር ውስጥ፣ ዓለማዊ እውቀትን ብቻ እንደ ኑሮ መርህ ተላምዶ በመቆየት ውስጥ፣ ከሥጋዊ ጊዜያት የሚፈልቅ ዓመፃን እንደ ሕይወት ገጠመኝ በመቁጠር አስተሳሰብ ውስጥ፤ በመድኃኒቱ ከትንሹ ወደ ትልቁ በመሰብሰብ ድንቅ ሥራ በኩል የተካፈልነውን ሰማያዊ ልጅነት እንዳናሳድግ (እግዚአብሔርን እንዳንመሰል) በመታገል ወደ ብሉይ ዘመን ውድቀት ሊመልሰን ቀን ከሌት ሳይደክም ይለፋል፡፡ አየተሃል ወዳጄ? .. ለዘመናት ከትንንሽነት ተነሥተው በመደጋገማቸው ምክንያትነት የለመድካቸው የኃጢአት ጊዜያት ተሰብስበው ትልቅ የበደል ክምር ሲሆኑ፤ ይሄንን ክምር ለመደርመስ የሚወጣ የንስሐ ጉልበት አጠረህ፡፡ ያ ማለት በዘመነ ምሕረት ሳለህ ዓመተ ፍዳን ትቆጥራለህ ማለት ነው፡፡ ከትንሹ ወደ ትልቁ ምን ማለት? .. መሰብሰብ!

   ስንት ውሸቶች እስከዛሬ ተሰብስበውብናል? ሰንት ዝሙቶች እስከዛሬ ተከማችተውብናል? ስንት የምቀኝነት ወቅቶችን እስከዛሬ አሳልፈናል? ስንት ጽድቅን የሚቃረኑ ቀናትን እስከዛሬ ኖረናል? ስንት የበደል ውጤት የተመዘገበባቸው ቆይታዎች እስከዛሬ ተገኝተውብናል? እስኪ በደንብ እናስብ! ዛሬ ወደ መንፈሳዊው ስፍራ ገብተን ጸንተን እንዳንኖር የሚታገሉ ስንት ትናንሽ ኃጢአቶች እስከዛሬ ተሰብስበው ትልቅ መሰናክል ሠርተው ይሆን?

   የርዕሳችንን ጥያቄ የምንመልሰው እንግዲህ እዚህ ቦታ ላይ ይሆናል፡፡ ንስሐ መቼ መቼ እንግባ ከተባለ፤ በየቀኑ የሚል ቁርጥ መልስ መገኘት ይኖርበታል፡፡ ትናንሽ የዲያብሎስ ምሪቶች ተሰብስበው ትልቅ የጥፋት መድረሻ ላይ እንዳያስቀምጡን፤ ትናንሽ "የአጋጣሚ" ክፍተቶች ተሰብስበው ትልቅ የሕይወት ገደል እንዳይፈጥሩ፤ ትናንሽ የየዕለት ኃጢአቶች ተሰብስበው ትልቅ የንስሐ መጋረጃ እንዳይዘረጉ ሲባል፤ በየዕለቱ "አውቄም ሆነ ሳላውቅ የፈጸምኳቸውን ኃጢአቶች ሁሉ ይቅር በል" በሚል የልብ ጸሎት መበርታት ያስፈልገናል (በዘወትር ጸሎት ላይ "እኛ የበደሉንን ይቅር እንደምንል፥ አቤቱ በደላችንን ይቅር በለን" የምንለው ለዚህ ነው፤ ከልብ እንጸልየው!)፡፡

   ብዙዎቻችን የየዕለት ኃጢአቶቻችንን በየዕለት ንስሐ አናጥባቸውም (የመጀመሪያ ምዕራፋችን ፍቅር ትዝ አለን፡፡ ፍቅር ቢኖረን ኖሮ..) ንስሐ ብዙ ጊዜ ስንገባ የምንገኘው ኃጢአቶቻችን "ከተጠራቀሙ በኋላ" ነው፡፡ በዘወትር የንስሐ ጸሎትና በተደጋጋሚ የንስሐ ስግደት፤ ትንንሽ የሚመስሉ ኃጢአቶችን ከሥር ከሥሩ አንሰርዛቸውም፡፡ በዚህም በየዕለቱ የሚከማቹ በደሎች፣ ስሕተቶችና ክፉ ጊዜዎች ራሳቸውን በመደጋገም አካሄድ ውስጥ ተላምደውን፤ ለዲያቢሎስ የእስራት ገመድ ማጥበቂያ እየሆኑ እንዳለ አልገባንም፡፡

   ዲያቢሎስ ለዘመናት ሕይወታችን ውስጥ አድፍጦ ቆይቶ፤ ባልተሰረዩ የየዕለት ነጠላ ኃጢአቶች በኩል ያገኘውን ኃይል፤ እነዚህ ትናንሽ ኃጢአቶች ተሰብስበው ትልቅ ውድቀት እንዲሆኑ ለዓመታት የለፋበትን ኃጢአትን የመደጋገም ሥራው፤ እንደገናም ወደፊት ሊያከናውናቸው ያቀዳቸውን የኃጢአት ጊዜዎች፤ ከንቱ ሆነው እንዳይቀሩበት በጥብቅ ስለሚፈልግ በየቀኑ በንስሐ መንፈስ እንዳንመላለስ ይፋለማል፡፡ ይቅር ባይነትና ይቅርታ ጠያቂነት አማናዊ መሥዋዕት ናቸውና፥ እነዚሀን ያስቀራል፡፡ በሌላ አገላለጽ ከልጅነት አንስቶ፤ ጥፋትን በመደጋገም፣ ኃጢአትን በማስለመድ፣ ከእግዚአብሔር የራቀ ሕይወትን የኑሮ አካል ለማድረግ የተጓዘባቸው ከትንሹ ወደ ትልቁ የመሰብሰብ ሂደቱ በቀላሉ እንዲከሽፍበት ፈጽሞ አይፈልግም፡፡ ስለሆነ የተጠመጠመውን በመፍታት ቆይታ ውስጥ (ነቅተህበት እየታገልከው ሳለ)፤ ነገ ተስፋ ልትቆርጥ እንደምትችል እያሰበ ዛሬን ይታገልሃል (ተስፋ የሌለው ተስፋ አድራጊ!)፡፡

   በመሆኑም፤ የየዕለት ንሰሐዎችን፣ የጸሎት ጊዜዎችን፣ የሰግደት ቆይታዎችን፣ የመቀደስ ልምምዶችን በማከናወን፤ እኛ ደግሞ ከጠላታችን አቅጣጫ በተቃራኒው ተጉዘን፤ ትናንሽ ጽድቆችን፣ ትናንሽ ቅድስናዎችን፣ ትንንሽ የአምልኮት ሰዓቶችን በመስብሰብ፤ በትልቁ እየተገለጠ የሚሄድ ከእግዚአብሔር ጋር የመገኘት አኗኗርን ለመኖር ቁርጠኛ አቋም ልንይዝ ያስፈልገናል፡፡

   በአጀማመራችን አካሄድ ለመጨረስ ያህል፤ ወደ አፈርነት እየተመለስን በሞት ቁጥጥር ሥር ውለን የነበርነው የሰው ልጆች፥ በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሞትን የምናሸንፍበት የባሕርይ አለኝታነት ሲሰጠን፤ ይህንን ስጦታ ጠብቀን ለመጓዝ የምንችለው በንስሐ ሕይወት ስንደገፍ ነው፡፡ የሥጋ ድክመት፣ እንደጋራ የተላመድነው ዓላማዊ አኗኗር እና ከነዚህ ጀርባ ሆነው የሚንቀሳቀሱ ክፉ መናፍስት እግዚአብሔርን ወደ መምሰል ታላቅ የቅድስና ተራራ እንዳንወጣ በየሰዓቱ በኃጢአት መዳፍ ስበው ቢጎትቱንም፤ ከተጎተትንበት ነጥብ ላይ ቀጥለን ወደ ሉዓላዊ ክርስትና እስክንደርስ ድረስ ምርኩዝ ሆኖ የሚያግዘን የአምላክ ክንድ ንስሐ ይባላል፡፡ "ዘወትር" እንጠቀምበት!

-------------------

ንስሐ እንዲህ እንዲህ እያለ እዚህ አድርሶናል፡፡ ወደ ቅዱስ ቁርባን ምዕራፍ መጀመሪያ ላይ ስንደርስ "በሉ በርቱ" ብሎ ተለይቶናል (እናመሰግናለን!)፡፡ የእኛም የሰማያዊው ማዕድ ጉዞአችን ይቀጥላል፡፡ ከአጠገባችን "ፍቅር" ስላለ ካሰብንበት እንደምንደርስ አንጠራጠርም፡፡ ስንጨርስም ፍቅር በዖሜጋነቱ መድረሻ ላይ ሆኖ እንደሚቀበለን እናምናለን፥ አምነንም እንኖራለን፡፡ አስጀምሮ ላስፈጸመን ለይቅር ባዩ አምላክ ምስጋና ይግባው፡፡

ወደ ሥጋና ደሙ መጓዛችንን እንቀጥላለን. . .
#ጸባኦት_ይከተላችሁ
@bemaledanek
2024/07/01 03:06:46
Back to Top
HTML Embed Code: