tgoop.com/betelhem29/538
Last Update:
የ ኢንስታግራም ገፃችንን ይጎብኙ። አብሮነታችሁ አይለየን https://www.instagram.com/p/CcgAfLBIFww/?igshid=YmMyMTA2M2Y=
ሐዋርያት በጽርሐ ጽዮን ተሰባስበው ሳሉ መንፈስ ቅዱስ በእሳት አምሳል ወርዶ ሰማያዊ ሀብትን፣ ዕውቀትና ጸጋን አድሏቸዋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ ከወረደላቸው በኋላም በአእምሮ ጐልምሰዋል፤ ጥቡዓን (ቈራጦች)፣ ጽኑዓን ሆነዋል፤ ለስብከተ ወንጌል የሚፋጠኑበትንና ለሰማዕትነት የሚዘጋጁበትን ልቡና ታድለዋል፡፡ ቀድሞ ይናገሩት ከነበሩት ቋንቋ በተጨማሪ ፸፩ [71] ቋንቋዎች ተገልጠውላቸው ምሥጢራትን በልዩ ልዩ ቋንቋ መተርጐም ጀምረዋል፡፡
ሐዋርያት በየሀገሩ ቋንቋ ሲናገሩ የሰሙ በዚያ የነበሩ ሰዎችም በሐዋርያት ተገረሙ፡፡ አንዳንድ የአይሁድ ወገኖች ግን በሐዋርያት ላይ ያዩት ክሥተት አዲስ ነገር ስለሆነባቸው ‹‹ጉሽ ጠጅ ጠጥተው ሰክረው የሆነ ያልሆነውን ይቀባጥራሉ›› እያሉ ሐዋርያትን ያሟቸው ነበር፡፡
ቅዱስ ጴጥሮስም ይህንን ሐሳባቸውን በመንፈስ ቅዱስ አውቆ ‹‹ሰክረዋል የምትሉ እናንተ እንደምትጠራጠሩት አይደለም፡፡ ጊዜው ማለዳ፣ ሰዓቱም ገና ሦስት ሰዓት ነውና፡፡ ግን በነቢዩ ኢዩኤል ‹ከዚህም በኋላ እንዲህ ይሆናል፤ መንፈሴን በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ አፈሳለሁ፤ ወንዶችና ሴቶች ልጆቻችሁም ትንቢት ይናገራሉ› ተብሎ የተነገረው ትንቢት ይፈጸም ዘንድ
°°°°°°°°° ይህንን ድንቅ ተአምር ያደረገው እናንተ የሰቀላችሁት ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፤››በማለት ሰፊ ትምህርተ ወንጌል ሰጥቷቸዋል፡፡ (ኢዩ.2፥28)•••••°°°°°°°°
BY ✝🕊አ͍ባ͍ ጊ͍ዮ͍ር͍ጊ͍ስ͍ ዘ͍ጋ͍ስ͍ጫ͍(ሰግላዊ)🕊✝
Share with your friend now:
tgoop.com/betelhem29/538