BIRYALEW Telegram 834
የካቲት 12 ቀን የሰማዕታት ቀን
የካቲት ሚካኤል መቼ ተከበረ
ዶማ ይዞ ዋለ ሰው እየቆፈረ!!

<< ኢትዮጵያውያን ሁሉ በሰላምና በፍቅር ከቤተ መንግሥቱ ግቢ ተሰበሰቡ።ጥቂት ቆይቶ ግራዚያኒና መኳንንቱ ከተቀመጡበት ጠረጴዛ አጠገብ ቦምቦች ተወረወሩ። ቦምቡ እንደተጣለ ግራዚያኒ ጠረጴዛው ስር ተደበቀ።ሌሎች ኢጣሊያኖች ግን ከመሬት ተኙ። ቦምቡን የጣለው በኢጣሊያኖቹ ዘንድ በአስተርጓሚነት የሚሰራ የኤርትራ ክፍለ ሀገር ተወላጅ ነው።

<< ለጥቂት ጊዜ ፀጥ አለ።ኢጣሊያኖቹ ሌላ የሚወረወር ቦምብ እንደሌለ ካወቁ በኋላ ከተኙበት ተነሱ። ወዲያው ካርቴሲ ወደ ኢትዮጵያውያን መኳንንት ሽጉጡን አነጣጥሮ የመጀመሪያዋን አንድ ጥይት ተኮሰ። ካራቢኜሪዎችም ምሳሌውን ተከተሉ። በጥቂት ጊዜ ውስጥም በዚያ ግቢ 300 ሬሳዎች ተከመሩ።

<< ኃይለኛና ተገቢ ያልሆነ ጭፍጨፋ ነበር። ሽማግሌዎች፣ እውሮች፣ እግር የሌላቸው ለማኞች፣ ድሆች እናቶች ከነልጆቻቸው ነበሩበት። ባለጥቁር ሸሚዞች በግቢው እየተሯሯጡ በሕይወት ያለ ኢትዮጵያዊ ይፈልጉ ነበር።ከሬሳዎቹ መሀልም የሚተነፍስ እንዳለ እያሉ እየመረመሩ ይገድሉ ነበር። . . .<< ምን ዓይነት አጨካከን ነው? ደም እንደ ውሃ ሲፈስ በየመንገዱ ላይ ያየሁት የዚያን ጊዜ ነው። የወንዶች፣ የሴቶች፣ የልጆች ሬሣ በያለበት ተኝቷል።

ወዲያውም ከባድ የቃጠሎ ጭስ ተነስቶ ከተማዋን አጨለማት። የሕዝቡ ቤት ከተፈተሸ በኋላ ሰዎቹ በውስጡ እንዳሉ ቤቱ በእሳት ይቃጠላል። ቃጠሎው ቶሎ እንዲያያዝም በቤንዚንና በዘይት ይጠቀሙ ነበር። ሰዉ እሳቱን እየሸሸ ከቤቱ ሲወጣ በመትረየስ ይገድሉታል። ሌሊቱንም ሲገድሉና ሲያቃጥሉ አደሩ። . . .

<< መኪናዎች እየዞሩ ሬሣ ያነሳሉ። ባለጥቁር ሸሚዞች ወደ ኢጣሊያ ባንክ እየገቡ ሌሊት የሰረቁትን ብርና ወርቅ ያስቀምጣሉ። ዘረፋው በቤት ውስጥ ብቻ አልነበረም። ከሚገድሏቸው ሴቶች አንገትና ጆሮ ላይ የሚገኘውን ወርቅ ሁሉ ይወስዱ ነበር። << ሕክምና በምሰራበት ቦታ ብዙ ኢጣሊያኖች ይመጡ ነበር።

እያንዳንዱ ኢጣሊያም ምን ያህል ሰው እንደገደለ በኩራት ይናገራል። አንዳንዶቹ 80 ገደልኩ ሲሉ አንዳንዶቹ ደግሞ መቶ እንደገደሉ በኩራት ይናገራሉ። አንድ ኢጣሊያዊ ብቻ እያዘነ "እኔስ የገደልኩት ሁለት ብቻ ነው" ብሎ ሲናገር ሰምቻለሁ። ... የማልረሳው ነገር ግድያው እንዲቆም በተደረገበት ጊዜ "ታላቁ ግራዚያኒ ለሕዝብ በማዘን ግድያው ይቁም ብለዋል" ተብሎ የተነገረው ነው። ግሩም አዘኔታ፥ ...>>. . . . .

(ይህ በወቅቱ አዲስ አበባ የነበረው ሀንጋሪያዊ ሐኪም ዶክተር ላዲስላስ ሳቫ የዓይን ምስክርነት ነው።) የካቲት 12 ቀን በተጀመረው እልቂት በሶስት ቀን ውስጥ 30,000 ሰዎች በአዲስ አበባ ከተማ ብቻ ከተገደሉ በኋላ ሌላው እየታፈሰ ወደ በረሃ እሥር ቤቶች ተላከ።

የኢትዮጵያና የጣሊያን ጦርነት( ጳውሎስ ኞኞ)
@biryalew
@biryalew

tgoop.com/biryalew/834
Create:
Last Update:

BY ✍✍✍ብዕር ያለው ያውጋ/bir yalew yawga✍✍✍

Share with your friend now:
tgoop.com/biryalew/834

View MORE
Open in Telegram

Telegram News

Date: |

Healing through screaming therapy Step-by-step tutorial on desktop: Add the logo from your device. Adjust the visible area of your image. Congratulations! Now your Telegram channel has a face Click “Save”.! On Tuesday, some local media outlets included Sing Tao Daily cited sources as saying the Hong Kong government was considering restricting access to Telegram. Privacy Commissioner for Personal Data Ada Chung told to the Legislative Council on Monday that government officials, police and lawmakers remain the targets of “doxxing” despite a privacy law amendment last year that criminalised the malicious disclosure of personal information. The court said the defendant had also incited people to commit public nuisance, with messages calling on them to take part in rallies and demonstrations including at Hong Kong International Airport, to block roads and to paralyse the public transportation system. Various forms of protest promoted on the messaging platform included general strikes, lunchtime protests and silent sit-ins.
from us

Telegram ✍✍✍ብዕር ያለው ያውጋ/bir yalew yawga✍✍✍
FROM American