tgoop.com/bookfor/1358
Last Update:
ለአንድ ሴት በተለይ "ቆንጆ ሴት ነን" ብለን ለምናስብ ሴቶች ፥ አቅማችንን እንዳንጠቀም እስር ቤት የሚሆንብን፤ የራሳችን ቁንጅና ነው። የራሳችን ቆዳ የራሳችን እስር ቤት ነው።
በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሴትነት እና ቁንጅና የሚባል የእስር ፍርግርጋችንን እያስዋብን ፥ ተሟሙቀን የወንዶችን ጭብጨባና አድናቆት እየጠበቅን እንድንኖር ሆነናል።
ማኅብረሰቡ አንዲትን ሴት "የብረት መዝጊያ" የሚሆን አማች የምትመጣ እንጂ ፥ የብረት መዝጊያ መሆን የምትችል አድርጎ አያስብም፤ ስለዚህ የነሱን የምኞት በር የሚዘጋ የብረት መዝጊያ ለማምጣት ፥ አንዲት ሴት ዓይኗን፤ አዕምሮዋን፤ ሳይሆን እግሯን እንድትከፍት ከህፃንነቷ ጀምሮ ሲያዘጋጃት ይኖራል።
እግር የተፈጠረበት የመጀመሪያ ዓላማው መራመድ ነው፤ ለሴት ልጅ ግን ከመራመድ በላይ እግር ውበት እንደሆነ እንድታስብ ፥ በስነ-ጽሁፍ፣ በፊልሙ፤ አዕምሮዋ ውስጥ ሲታጨቅባት ኖሯል።
ከመራመዷ በላይ የአረማመዷን እና የእግሯን ውበት ፥ እንድታስብ ስትሰበክ ኖራለች። ለዚህም ነው ከፊትሽ የተነጠፈውን እሾህም ይሁን ጠጠር ፥ ረግጠውና ዋጋ ከፍለው አዳሰቡበት ከሚራመዱ ሴቶች ይልቅ፤ ከየትም ባገኟት ሳንቲም በየውበት ሳሎኑ ተጎልተው ፥ እግራቸውን የጥፍር ቀለም ሲያስቀቡና ተረከዛቸውን ሲያስፈገፍጉ የሚውሉ ዘመነኞች የሚበዙት። እግራቸው ከለሰለሰ በኃላ ፥ አዝሎ የሚያሻግር ወንድ ሲጠብቁ ቁጭ ብለው ይኖራሉ።
ገጽ 182-183
(ከእለታት ግማሽ ቀን)
@Bookfor
@Bookfor
BY @Book for all
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/jIc1iJJi9WJw-lEkUVsTkxZwIe6YmPdloAktz540a-vAXHKPRfUJVA5hiFMGbU5UTL5xTxKFswLyx9BzJIoV5pve2AZ4rU1GJbCdEo4Qlg5dEOH6d_eklKcg4e-3ibz4-84hei_G2ePB-aEufPwLBbFKwAkn5oyuPeAivXwqdx9e3iQVQwHSWW9XlSJu4c2AdbNkDFRSj7Sse_bnCuXVm0-934vcvz8hL6hRSBhWMlRozoIghoM9E_yecAPrZp2N89aygHzaCozadKQ9IWolAVvm3nl2uOqY4cBI90AccOd4-2Vevd3s9eOrji71WKTpAH04cvkN1GYq5l4PAae7_Q.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/bookfor/1358