tgoop.com/bookfor/1388
Create:
Last Update:
Last Update:
Am I the tree? Am I the river?
፟ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ግንዱን ነች ወይ እቺ ነፍሴ? አዲስ ፍሬ አዲስ ቅጠል ይበቅላል ብስል ጥሬው በገላዬ። በጋ ክረምት ደግሞ ይረግፋል ቀን ጠብቆ ። ሰው ይመጣል ሰው ይሄዳል በእድሜዬ።
ዛፉን ነሽ ካልከኝ አደራ፦ ከጎኔ የበቀለ ሁሉ ሳያብብ አይክሰም ። እስኪረግፍ ፀደይ መጥቶ ይፍካ ይመርበት አብሮኝ ሲኖር። ላካፍለው ካለኝ ሁሉ። እሱ እንጂ የኔ እንግዳ እኔ መሄዱን አውቃለሁና። ሲረግፍም ቀን ጠብቆ ‘ሂድ መጣሁ’ ልበለው ። እኔስ ብሆን ከመሬት ጎን የበቀልኩ ቅርንጫፍ አይደለሁ?
ምን ቢራራቅ ፍጠረተ አለሙ ሁሉ መርገፍ በሚሉት የጋራ ሃቅ የቆመ አይደለ?
፟ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ? የጠለቀኝ የጠለቅኩት ይሰራኛል ያለድካም ።የነካሁት የታከከኝ መልኬ ይሆናል ።
ወንዝ ነሽም ካልከኝ አደራ ፦ የሰው ልጅ ንፅህና እንደውሃ ብዙ ባለመፍሰስ አይለካምና በወንዝነት ትርምስ ውስጥ ስፈስ በመንገዴ ከምገጨው ተራራ ስር የምንጭነትን ንፅህና አቅምሰኝ። የወደደኝ ሁሉ ሊጠጣኝ አይጠየፈኝ። ከመቀመስ ኋላ የምጠላ የምተፋ አታድርገኝ።
ዛፍን ነው ወይ የኔ ህይወት? ወንዙን ነው ወይ ይሄ ልቤ?
إن معي ربي سيهدين
©Newal Abubeker
@Bookfor
@Bookfor
BY @Book for all
Share with your friend now:
tgoop.com/bookfor/1388