tgoop.com/bookfor/1389
Last Update:
የአስቻለው ፈጠነ አልበም ተለቀቀ!
#Ethiopia | የድምጻዊ አስቻለው ፈጠነ (አርዲ) "አስቻለ" የሙዚቃ አልበም ዛሬ አርብ ጥር 3 2016 ዓ.ም በብርቧክስ ሪከርድስ በኩል ተለቋል።
እናትዋ ጎንደር እና ካሲናው ጎጃም በሚሉት ነጠላ ዜማዎቹ ተወዳጅነትን ያተረፈው አስቻለው ፈጠነ ( Aschalew Fetene Ardi ) "አስቻለ" የተሰኘውን የመጀመሪያውን አልበም ለህዝብ ደርሷል።
እመት ሸዋ እና ወሎ የሚሉትን ትራኮች ለቅምሻ ያሰማን ሲሆን ጣፋጭ ጠላ ተገፈቱ እንደሚያስታውቀው ሁሉ አልበሙም የተዋጣለት እንደሚሆን ያሳብቃል።
አስቼ ትክክለኛ መንገዱን ይዞ እየተጓዘ የሚገኝ ባለ ተሰጥኦ ህልመኛ ነው ።
"እናትዋ ጎንደር" በሚለው ስራው አስደምሞኛል።
"እነ እቴቴ ጉርሻ ኧረ እንደምን ናችሁ
ጉብ ጉብ አለብኝ አፈር ልብላላችሁ " ብሎ አንጀትን ሰፍፍፍ የሚያደርግ ስራ ሰርቷል ።
ቃላት እርሷን ለመግለፅ ለሚሽመደመዱላት ሙሽራዋ ጎንደር
"እናትዋ ጎንደር
ትንፋሽዋ ጎንደር
እህልዋ ጎንደር " እያለ በሚያስገመግም ድምፁ ተቀኝቶላታል ።
"እናትዋ ጎንደር" አዕምሮዬ ላይ ላይወርድ ተቀርፆ የተቀመጠ ድንቅ ስራ ነው።
ከግጥም እስከ ዜማ ፣ ከአጀማመር እስከ ፍፃሜው ከሲኒማቶግራፊ እስከ ክሊፕ ትወናው ጥንቅቅ ያለ ስራ ነው።
በ "ካሲናው ጎጃም"
"ድግሱን ደግሶ አይነግሩም አዋጅ
መንገደኛው ሁሉ ሰተት ነው እንጅ " እያለ
መሬት ላይ በአይኔ ያየሁትን ሃቅ በጥበቡ ከፍ አድርጎ አሳይቶኛል።
"የነካኸው ይጣፍጥልህ" ተብሎ የተመረቀው ሰው መሆን ይስማው ሰርቶት ደግሞ እንዴትስ የተዋጣለት ላይሆን ይችላል ?
እንኳን ደስ አለህ ወንድሜ አስቼ😍
ብራቮ ሶሚክ Sewmehon Yismaw
Aschalew Fetene Ardi እንኳን ደስ አለህ!
https://youtube.com/BirbauxRecord
BY @Book for all
Share with your friend now:
tgoop.com/bookfor/1389