Telegram Web
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

ከልጅነታችሁ ጀምራችሁ #ያጎለበታችሁት ፤ በፍጹም #የማትጠራጠሩት ፤ በዚህ በፍጹም ሰይጣንም ይሁን ሁኔታ #ፈጽሞ_ሊያስተኝ አይችልም ያላችሁት ፤ ለሰዎች በኩራት #የምታወሩት ፤ ሰዎች እናንተን በዚህ አቋሟችሁ ጠንካራ እንደሆናችሁ #የሚመሰክሩሏችሁ ፤ በሰውና በእግዚአብሔር ፊት ያለኝ #ጠንካራ_ጎኔ ይህ ነው ብላችሁ #የምትናገሩት ፤ በልበ ሙሉነት ከአቋሜ ለአንዲት #ሰከንድ_ሸርተት አልልም ፥ የምትሉት ነገር አላችሁ?

#እኔ_ነበረኝ ግን ያ ሁሉ ነገር #እኔ ስለራሴ የማስበውና የምናገረው ውሸት ነበር😭

#እውነቱ_ይህ_ብቻ_ነበር👉 "ሰው በኃይሉ አይበረታምና።”— 1ኛ ሳሙኤል 2፥9

#ሃይሌ ባልኩት ነገር #ደከምኩ#ጉልበቴ ባልኩት ነገሬ #ደከምኩ#ብርታቴ ብዬ በማስበው ባሕሪይ #ዛልኩ😭

#ግን_እውነቱ_ይሄ_ነበር👉  “በገዛ ልቡ የሚታመን ሰው ሰነፍ ነው፤ በጥበብ የሚሄድ ግን ይድናል።”— ምሳሌ 28፥26

#ሰዎች ሲወድቁ እንዴት ይወድቃሉ ባልኩት ፤ #ሰዎች ሲደክሙ እንዴት ይደክማሉ ባልኩት ፤ #ሰዎች ሲያቅታቸው ባንጓጠጥኩበት ነገር ፤ #ሰዎች ሲሰበሩ በሳኩበት ነገር ፤ በዚህ #እኔ ከነሱ የተሻልኩ እንደሆንኩ #ባፏጨውበት ነገር ፤

#እኔ ወደኩ ፣ #እኔ ደከምኩ ፣ #እኔ አቃተኝ ፣ #እኔ ተሰበርኩ ፣ #እኔ ከነሱ በብዙ አንሼ ተገኘው 😭😭😭

#ግን_እውነቱ_ይሄ_ነበር 👉 “አንተ በሌላው ሎሌ የምትፈርድ ማን ነህ? እርሱ ቢቆም ወይም ቢወድቅ ለገዛ ጌታው ነው፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ሊያቆመው ይችላልና ይቆማል።” — ሮሜ 14፥4

#አሁን_ይሄንን_ተረድቻለሁ “ልጆቼ ሆይ፥ ኃጢአትን እንዳታደርጉ ይህን እጽፍላችኋለሁ። ማንም ኃጢአትን ቢያደርግ ከአብ ዘንድ ጠበቃ አለን እርሱም ጻድቅ የሆነ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።”— 1ኛ ዮሐንስ 2፥1

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#ህይወት ምንጊዜም #የትግል_አለም ናት። በዚህ #የህይወት_አለም ውስጥ #አሸናፊዎች ምንጊዜም አይኖቻቸውን #በእግዚአብሔር ላይ የሚያደርጉ #ሰዎች_ብቻ ናቸው።

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#አንዳንድ_ጊዜ ለመጓዝ አስቸጋሪ የሆነውን የህይወት መንገድ ለመምረጥ ትገደዳለህ።

#ሰዎች በዚህ አስቸጋሪ የህይወት መንገድ ስትጓዝ በምትቀበለው መከራ እና በምታስተናግደው ጉዳት የራሳቸውን የተለያዩ ድምዳሜዎችን ይሰጣሉ።

#ፈልገህና_መርጠህ ባልተጋዝክበት የህይወት መንገድ #ትነቀፋለህ#ትሰደባለህ#ትታማለህ#ትናቃለህ#ትንቋሸሻለህ እንዲሁም ትገፋለህ።

#የዚህ_ጊዜ #ወዳጄ የምትላቸው ጠላትህ ፤ #ቤተሰቤ የምትላቸው ተቃዋሚህ ፤ #ሚስጥረኛዬ የምትላቸው የምትቀበርበትን ጉድጓድ ቆፋሪዎች ፤ #የክፉ_ቀን መሸሸጊያ ይሆኑኛል ያልካቸው የውድቀትህ ሰበር ዜና ተናጋሪዎች ሆነው ታገኛቸዋለህ።

በዚህ አስቸጋሪ #የህይወት_መንገድ ህመሙን የምትቀበለውም ሆነ የምታስታምመው #አንተና_አንተ ብቻ ነህ።

#በዚህ_አስቸጋሪ_የህይወት መንገድ የብቸኝነት ስሜት ፣ የመተውና የመረሳት ስሜት አንዲሁም የበታችነት ስሜትና የአቅመቢስነት ስሜት በዙሪያህ እንደ ድቅድቅ ጭለማ ይከብሃል።

የዚህ ጊዜ ከዚህ አስቸጋሪ የህይወት መንገድ ማምለጫ አንድ ምርጫ ብቻ አለ እርሱም በአምላክህ #በእግዚአብሔር መታመንና እርሱን ብቻ ተስፋ ማድረግ ነው።

#አሁን_እኔ በዚህ አስቸጋሪ የህይወት መንገድ በመጓዝ ላይ ነኝ። ነገር ግን አንድ ነገር ወስኛለሁ ይህንን አስቸጋሪ የህይወት መንገድ እስክጨርስ ድረስ ለአንዲት ሰከንድ ወደ ሃላ አልመለስም።

ነገር ግን #አንድ_ነገር_ባለማቋረጥ አደርጋለሁ እርሱም #በአምላኬ_በእግዚአብሔር እታመናለሁ #አግዚአብሔር ወዳዘጋቸልኝ ወደ #ክብር_ተራራ_ጫፍ እወጣለሁ።

✍️ @Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#መሆን እፈልጋለሁ ነገር ግን መሆን አቃተኝ😣
#ብዙ ሰዎች ጋር ያለ ነገር ግን የጎደለኝን ነገር አለ😣
#የምፈራውና_የምሸሸው ግን የምፈልገው ነገር አለ😣
#ብዙዎች ጋር ሳየው በኖረኝ የምለው ሲመጣ የምርቀው ነገር አለ😣
#ጥሩ የሆነ እኔ ግን ሸሽቼ የተደበኩበት መጥፎ ነገር አለ😣
#ይሄ የሁልጊዜ ከልጅነቴ ጀምሮ እስካሁን ለእኔ ያልተመለሰ ጥያቄዬ ነው😣

#ፈላስፍው ሲናገር እንዲህ ይላል < ሁሉም ሰው የሚፈልገው ብርሃን አለ ነገር ግን ሁሉም ሰው ከብርሃኑ ሸሽቶ የሚደበቅበት የራሱ ጭለማ አለው>

ለዚህ ነው በረጅሙ የህይወት ጉዞ ' የሚያሳድደን እውነታ ቢኖርም የምንደበቅበት ውሸት ያለን። '

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

እስከ #ዛሬ የሆናችሁትና ያደረጋችሁት ሁሉ #ህልም ቢሆንና #ከህልማችሁ አሁን ብትነቁ #የትና_በምን_ሁኔታ ውስጥ #እራሳችሁን የምታገኙት ይመስላችኋል?

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

በርግጠኝነት ሁላችንም #አሁን በጣም #የምንገበገብላቸው#የኛ ለማድረግ #የምንታገልላቸው#በኖረን ብለን #የምንመኛቸው#እንደ_ብርቅ አይተን #የምናደንቃቸው እና #እድሉን ባገኘው ብለን #የምንጓጓላቸው ነገሮች በሙሉ #ትርጉም_አልባ የምታደርግ አንዲት #ወሳኝ_ቀን ከፊታችን በጉጉት #እየጠበቀችን ትገኛለች።

እናም #እርሶን_መጠየቅ የምፈልገው ጥያቄ #ያቺ እርሶን #በጉጉት የምትጠብቆትን ቀን #በደስታ ወይስ #በሃዘን ለመቀበል ወስነዋል??

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

' #ሰው በህይወት የሚኖርበት ብቸኛው ምክኒያት #እንደአሸዋ ከበዛው የምሞትበት ምክኒያት ይልቅ #እንደጥላ የሚታየውን #ነገን የተሻለ እንደሚሆን #ተስፋ ማድረጉ ነው'

#በሰው_ህይወት_ሁሌም 'እየሳቁ ማልቀስ ፥ እያለቀሱ መሳቅ ፥ እየወደቁ መቆም ፥ እየቆሙ መውደቅ ፥ እየሞቱ መኖር ፥ እየኖሩ መሞት ፥ የሚባል ነገር አለ።

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

ይቺህ #አለም_ፍትሃዊ አይደለችም!!!

#ምክኒያቱም

#እራስ ወዳዶችና ስግብግቦች ብቻ #ሆዳቸውን ሞልተው የሚኖሩባት...
#ጉልበተኞች እና #ጨካኞች ደረታቸውን ነፍተው ያለአንዳች #ስጋት የሚገማሸሩባት....
#ተንኮለኞች እና #ክፉዎች አትርፈው የሚስቁባት....
#ዘመን የሚቀሙ ዘመነኞች አስፈራርተው የሚንቀባረሩባት...
#አሳፋሪዎች ኮርተው...
#ተሸማቃቂዎች ደንፍተው...
#ማቅ ለባሾች ጥበብ ለብሰው #እልል ብለው የሚኖርበት...

#ሚዛናዊ_ያልሆነች የእግዚአብሔር የእርግማን #በትር የመታት...
#በክፉት የተሞላች....
#ሰላምና እረፍት ፥ #ሳቅና ሀሴት የማይሰነብትባት...
#የስጋትና የጭንቀት መፈልፈያ ኢንኩቤተር....
#በየዘርፉና_በያይነቱ ፍርሀትን ያለማቋረጥ የምትፈለፍል....
#በጭለማ የተሞላች...
#ሀጢያተኛውን የምታነግስ
#እግዚአብሔርን ያማይፈሩትን የምታቆለጳጵስ
#በሙገሳ ዙፋን ላይ የምታስቀምጥ

#አለም_እንዲህ_ናት...

#ደጎች እንደ ክፉ
#የዋሆች እንደ ሞኝ
#አፍቃሪዎች እንደ ጅል
#ጻድቃኖች እንደ ዘመኑን ያልተረዱ ባዳዎች
#ተስፈኞች እንደ ሰነፍ
#አማኞች እንደ ግትር*የሚታይባት

ብቸኛዋ ፕላኔት #እኔና_እርሶ የምንኖርባት #አለም እንዲ ናት.....

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

➊. አራት አይነት ሰዎችን አክብር
1➳ የእውቀት ባለቤቶችን
2➳ ቤተሰብህን
3➳ አዛዉንቶችን
4➳ ባለ ስልጣናትን

❷. አራት ነገሮች ይኑሩህ
1➳ ኢየሱስ
2➳ ታማኝነት
3➳ እምነት
4➳ መልካም ስራ

❸. ራስህን ከ አምስት ነገሮች አርቅ
1➳ ሰዎችን ከመናቅ
2➳ ከማጭበርበር
3➳ ከብድር
4➳ ከዝሙት
5➳ ጣኦትን ከማምለክ

❹. ሶስት ነገሮችን ተቆጣጠር
1➳ ምላስህን
2➳ ቁጣህን
3➳ ስሜትህን

❺. ከ አራት ነገሮች ራስህን ጠብቅ
1➳ ከመጥፎ ስራ
2➳ ሰዎችን ከማማት
3➳ ከምቀኝነት
4➳ እግዚአብሔር ከማሳዘን

❻. አራት ነገሮችን ፈልግ
1➳ እዉቀትን
2➳ ጥሩ ስነምግባርን
3➳ ታዛዥነትን
4➳ እግዚአብሔርን

❼. ሶስት ነገሮችን ንጹህ አድርግ
1➳ ሰዉነትህን
2➳ ልብስህን
3➳ ንግግርህን

❽. ሶስት ነገሮችን አስታዉስ
1➳ ሞትን
2➳ ሰዎች የዋሉልህን ዉለታ
3➳ ሰዎች የሰጡህን ምክር

@Hiskelboy
Group @Covenantsons
Channel @christsbelievers
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇


#የኢየሱስን_ሰባት_እኔዎች

1. #እኔ የሕይወት እንጀራ ነኝ (ዮሐ 6:35)
2. #እኔ የዓለም ብርሃን ነኝ (ዮሐ 8:12)
3. #እኔ የበጎች በር ነኝ (ዮሐ 10:7)
4. መልካም እረኛ #እኔ ነን (ዮሐ 10:11)
5. ትንሳኤ እና ሕይወት #እኔ ነኝ (ዮሐ 11:25)
6. መንገድ፣ እውነት እና ሕይወት #እኔ ነኝ (ዮሐ 14:6)
7. እውነተኛ የወይን ግንድ #እኔ ነኝ (ዮሐ 15:1)
     
     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#ውሎህን ከነዚህ 5 (አምስት) ሰዎች ጋር አድርግ

1. ንቁ (አዋቂ)
2. ለለውጥ የተነሳሱ
3. ቀና አመለካከት ያላቸው
4. የፍቅር ልብ ያላቸው
5. አመስጋኝ
     
በእርግጥም ውሎህ ከነዚህ አይነት ሰዎች ጋር ከሆነ አንተ የነዚህ ባህሪያት ባለቤት ትሆናለህ።

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
Live stream started
Live stream finished (41 seconds)
Live stream started
Live stream finished (28 seconds)
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#ዛሬ ላይ የምንኖረው #የህይወት_አይነት #ያለፈው ጊዜያችን የህይወት ልምምድ #ድምር_ውጤት ነው።

#ዛሬ ላይ ያለ #መልካም ሆነ #ክፉ የህይወት መልክ #የትላንትና_እርምጃችን የቀየሰው ጎዳና ነው።

#ዛሬ ፦ ዛሬ ብለን ስንል በዛሬ ውስጥ #ጊዜ#ውሳኔና#ተግባር እነዚህ ሶስቱ እጅግ ወሳኝ ሆነው #ትናንት በሚባል #ሚዛን_እየተመዘኑ #ነጋችንን_እንድንሰራ ይረዱናል።

     #የተመቸው_ለሚወደው_ሼር
         ━━━━━⊱✿⊰━━━━━

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#ሰው_ሁሉ_ከእግዚአብሔር_የተቸረው ሁለት ዋና ነገሮች አሉ። እነርሱም #አእምሮ እና #ልብ ናቸው።

ሰው #በአእምሮ እና #በልብ ላይ ተመስርቶ #ነገሮችን የመለየት ፣ የመምረጥ ፣ እውቅና የመስጠት እና የመወሰን #አቅሞች_እንዲኖሩት ያደርጉታል።

ሰዎች #በየትኛውም እና #በማንኛውም ምርጫና ውሳኔ ላይ የሚጠቀሙት #አእምሮአቸውን እና #ልባቸውን ነው።

አንድ #እውነት_እንድታውቁ እፈልጋለሁ #አእምሮ እና #ልብ ፍጹም የተለያየ #የስራ_ዘርፍ ቢኖራቸውም #ፍጹም_የጠበቀና ሊለያይ #የማይችል_ህብረትም አላቸው።

#አእምሮ_ፈጽሞ_ማፍቀር አይችልም። ነገር ግን #ፍቅር_ምን_እንደሆነ_እውቀቱ አለው።
#ልብ_ፈጽሞ የነገሮችን #ምስል ማከማቸት አይችልም። ነገር ግን ነገሮችን  #በመልካምም_በትዝታ ይሁን #በመጥፎ_በትዝታ  የመያዝ #ብቃት አለው።

#አእምሮ ሁል ጊዜ #ውጤት_ተኮር ሲሆን
#ልብ ደግሞ #እርካታ_ተኮር ነው።

ሁልጊዜ #አእምሮ_በእውቀት ይታደሳል።
ሁልጌዜ #ልብ_ከአእምሮ በሚያገኘው #እውቀት_አይኑ_ይበራል

@Hiskelboy
Group 👉 @Covenantsons
Channel 👉 @christsbelievers
.    #አእምሮን_ማንቃት
                  👇

#አንዳንድ_ሰዎች_አሉ

#በመንገዳቸው እንድትሄድ #መንገድህን የሚቀሙ ፤ #እነሱ በፈሰሱበት ሸለቆ #እንድትፈስ ሸለቆህን የሚያፈርሱ ፤ #እነሱ የወጡትን ዳገት እንድትወጣ #ያንተን ቁልቁለት የሚቆፍሩ....

እንደዚ አይነት #ሰዎች የራሳቸውን ስኬት ማሳካት #ያልቻሉ ፤ ህልማቸውን መኖር #ያቃታቸው ፤ ማንነታቸው #የተቀሙ ፤ እራሳቸውን በሰው ህይወት ደግመው መኖር #የሚመኙ ሰዎች አሉ።

#እናንተ በፍጹም ሰዎች እራሳቸውን ደግመው በእናንተ ውስጥ እንዲኖሩ አትፍቀዱ። #እናንተ የራሳችሁን ህልም መኖር ጀምሩ። #እራሳችሁን ስትሆኑ ብቻ ነው እውነተኛ ስኬትን ማሳካት የምትችሉት።

@Ye_Fikr_Tebib
Channel @Christsbelievers
               @Christsbelievers
               @Christsbelievers
                 🔺🀄️🀄️ሉን🔺
#እናቴ ሁሌም እወድሻለሁ
እንኳን ለ 30ኛ የጋብቻ ክብረ በዓል እግዚአብሔር አደረሰሽ
#ሁሌም_ኑሪልኝ
2024/09/11 11:54:49
Back to Top
HTML Embed Code: