tgoop.com/concepthubeth/14
Last Update:
#ConceptHub
ሁለኛው ዕትም የሀሳብ አለኝ መጽሔት በዝግጅት ላይ ነው። በርካቶች ጹሑፍ እንዴት መላክ እንደሚቻልና እንዴት መሳተፍ እንደሚቻል ጠይቃችሁናል። የተነሱትን ጥያቄዎች በተወሰነ መልኩ ለመዳሰስ እንሞክራለን።
1. እንዴት መመዝገብ እችላለሁ ?
በኮንሰብት ሀብ ላይ በጸሐፊነት ለመመዝገብ ቢያንስ አንድ ጹሑፍ ማሳተም ግድ ይላል። ጹሑፎችን ያሳተሙ ጸሐፊያን በስማቸው ስለሚለቀቅ ሥራቸውን የራሳቸውን ሊንክ በመጠቀም ለሰው ማድረስ ይችላሉ።
ከዚህም ባለፈ አድራሻዎቻቸው ስለሚገኙ በጹሑፋቸው ላይ አስተያየት መቀበልና ከሰዎች ጋር መወያየት እንዲሁም በዚሁ አጋጣሚ የሥራ አማራጮች ጭምር የሚፈጠርበት አማራጮች ይኖራሉ። ይህንን እድል በመጀመሪያው ዙር ከተሳተፉ ጸሐፊያን በአንዳቸው መመልከት ችለናል 🙏
2. በምን መልኩ መሳተፍ እችላለሁ
በኮንሰብት ሀብ ሁለት አይነት አማራጮች አሉ። አንደኛው ጠለቅ ያሉ፣ ጥናትና ምርምር የተደረገባቸው ጹሑፎች የሚቀርቡ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በጦማር (Blog) ሊተላለፉ የሚችሉ የተለያዩ ምልከታዎችና የጥበብ ሥራዎች የሚቀርቡበት ነው።
3. ክፍያ አለው
- ለሐሳብ አለኝ መጽሔት፦ አዎ ከ2000 እስከ 5000 የሚደርስ ክፍያ ለጸሐፊያን ይከፈላል።
- ለጦማር(Blog)፦ አይከፈልም። ይህ ወጣቶች እንዲጽፉ ለማበረታታት የቀረበ ነው።
- ለውድድር የሥራዎች ፦ አዎ! የተለያዩ ተቋማት በተለየያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ላይ ወጣቶችን ያሳተፈ የጥናትና ምርምር እንዲሁም የጹሑፍ ውድድሮች ሲዘጋጅ እንደውድድሩ ይዘትና ስፋት መጠን ታይቶ ይከፈላል።
NB: ለውድድር ሥራዎች ቅድሚያ የሚያገኙት በርካታ ጹሑፎችን ያሳተሙ እና ተሳትፏቸውና ጹሑፋቸው ተገምግሞ ይሆናል።
4. መስፈርቱ ምንድን ነው ?
በተለይ ለመጽሔትና ለውድድር የሚቀርቡ ሥራዎች ልዩ ምልከታ ያላቸው፤ ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፤ መሰረታዊ የጋዜጠኝነትና የጥናታዊ ጹሑፍ መስፈርቶችን የሚያሟሉ እንዲሆን ይጠበቃል።
ቢያንስ መረጃዎችን ከሦስት ምንጮች ተጣርተው መቅረብ እና ያልተኮረጀ፤ ያልተገለበጠ ወጥ የግል ሥራ እንዲሆንም ይጠበቃል።
በተጨማሪም ጹሑፉ ወቅት የገምጋሚ ቡድኑ የሚሰጠውን አስተያየት ለማየት መሞከር፤ ማስረጃዎችን ማያያዝና ሙያዊ ክህሎት (professional) መሆን ይጠበቅበታል። ከዚህም ባሻገር ጸሐፊው በሚጽህፈው ርዕሰ ጉዳይ ላይ ሞያዊም ሆነ የእውቀት ዝግጁነት ቢኖረው ይበልጥ ይመረጣል።
5. ጹሑፍ ማስገባት ያለብን መቼ ነው ?
በየጊዜው የሚወጡ መጽሔቶች የጹሑፍ ማስገቢያ ቀነ ገደብ ይኖራቸዋል። ሆኖም አንዳንድ የጹሑፍ ሥራዎች ጊዜ የሚወስዱና ሰፋ ተደርገው መሰራት ያለባቸው ይሆናሉ።
በዚህ ምክንያት ጹሑፍ መነሻ ሐሳቦችን በማንኛውም ወቅት ማስገባት የሚቻል ሲሆን የጹሑፍ ሥራው ግን በየዕትሙ በሚቀመጡ የጊዜ ገደቦች ተጠናቀው መግባት ይጠበቅባቸዋል።
6. ዓላማው ምንድን ነው ?
- የሚጠቅም ሐሳብ ይዘው ለተቀመጡ ወጣት ባለሞያዎች እንዲጽፉ እና ሐሳባቸውን እንዲያወዳድሩ እድሉን ማመቻቸት፤
- ለንባብ አማራጭ መንገድ መክፈት፤
- አቅም እና ችሎታ ያላቸውን የተደበቁ ወጣቶችን በማስተዋወቅ ሥራዎቻቸውን በማቅረብ የልምድ፤ የሥራና የክህሎት ትስስርን ማጠንከር፤
- ከተለያዩ ተቋማት እንዲሁም ድርጅቶች ጋር አብሮ በመስራት ወጣቶች በሚሰሩት ሞያዊ ክህሎት በተላበሰ እንዲሁም ማኅበረሰቡን የሚጠቅም ሥራ አማራጭ የገቢ ምንጭ መፍጠር፤
- በቀጣይ የመማማሪያ፤ የውይይት እንዲሁም የዲጂታል መድረካችንን በማሳደግ አድማሱን ማስፋትና አማራጭ የሐሳብ መገበያያ መድረክ እንዲሆን ማስቻል።
7. ማን መሳተፍ ይችላል ?
ማንኛውም ወጣት መሳተፍ ይችላል። በተለይ ለጹሑፍ ዝንባሌ ያላቸው ወጣት ጋዜጠኞች፤ መምህራን እና በየትኛውም የሥራ ዘርፍ የተሰማራችሁ ባለሞያዎች መሳተፍ ትችላላችሁ።
ተጨማሪ ጥያቀዎችን 👇 ያቅርቡ ምላሽ የምንሰጥበት ይሆናል።
@Concepthubeth
BY Concept Hub Ethiopia
Share with your friend now:
tgoop.com/concepthubeth/14