tgoop.com/deacongetabalewamare/1841
Last Update:
✨ #በታኅሳስ_ወር_በ6ኛው_ቀን የቅድስት አርሴማ ቤተክርስቲያኗ ቅዳሴ ቤቷ በአርማንያ ሀገር ፣ በኪልቂያ ፣ በሶርያ ፣ በአንጾኪያና በግብጽ አውራጃዎች ሁሉ ሆኗል።
« ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳኔን አደረግሁ » እንዳለ እግዚአብሔር አምላክ ለእናታችን ቅድስት አርሴማ ስለ አምላኳ ስትል ከብዙ ጽናትና ተጋድሎ በኋላ እንዲህ የሚል ቃል ኪዳን ገባላት
« በእኔ ስም አምነሽ የዚህን ዓለም ተድላና ደስታ ሳያታልልሽ አንገትሽን ለሰይፍ ሰጥተሽ ተሰይፈሻል የሰማዕትነት ተጋድሎ ፈጽመሻልና ስምሽን የጠራ ፤ በዓልሽን ያከበረ ፤ ዝክርሽን የዘከረ ፤ ገድልሽን የጻፈና ያጻፈ ፤ የሰማና ያሰማም እስከ 12 ትውልድ ድረስ እምርልሻለሁ » ሲል ቃል ኪዳን ገብቶላታል ፡፡
በዚህም መሠረት በሷ አማላጅነት አምኖ በገዳሟም ሄዶ በጸሎት የተማጸናት ሁሉ ለችግሩ መፍትሄ አግኝቶ እንደሚመለስ እሙን ነው ፡፡
የሰማዕቷ : ቅድስት : አርሴማ : ረድኤት : ከሁላችን : ጋር : ይሁን : የቅድስት : አርሴማ : ቃልኪዳኗ : ሀገራችንን : ኢትዮጵያን : ከክፉ : ይሰውርል ።
© ✎﹏ዳዊት ተስፋዬ ✍🏽 Daweit Tesfay
ታኅሳስ 6 20 17 ዓ.ም
ሠዐሊ ቀሲስ አማረ ክብረት
እንደሳሉት
📞 +251913684351
ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
@deacongetabalewamare
BY Dn Getabalew Amare Kibret /ሰዐሊ/
Share with your friend now:
tgoop.com/deacongetabalewamare/1841