Telegram Web
ወርቅ የሆንከው ጥበበኛው አባቴ ታሪክ ለመስራት አሁን ጥበበኛ እጆህን አንሳ : በቡሩሾችህም ቀለማትን 🖌️አሰባጥረህ ታሪክ ለመሥራት ተዘጋጅ . . . ! 🎨

🍂 በቃል የሚነገረውን ወንጌል በትውፊትም የተቀመመውን ሥርአት እና ቀኖናቸውን የጠበቁ ቅዱሳት ሥዕላትን በታሪካዊው እና ድንቅ በሆነው በኳታር ዶሀ ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንድትሥል እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ ጥበብ ማስተዋሉንም የስጥህ።

እኔም ልጅህ በዚህ ታሪካዊ ሥራ ከጎንህ ሆኜ አግዝህ ዘንድ ፍቃዱ የሆነ እግዚአብሔር ይመስገን 🙏🏽

ወንድሜ Biruk Thomas
ከ 2 ቀን በኋላ እንቀበልሀለን

እግዚአብሔር እረድቶን አግዞን
የምንሄድበትን አላማ በተሳካ ሁኔታ አጠናቀን እንደምንመለስም ሙሉ እምነት አለኝ

👉🏽 ጉዟችን የተቃና ይሆን ዘንድ በመንገዳችንም ሁሉ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ይሆን ዘንድ

በጸሎታችሁ አስቡን !🙏🏽


ሰኔ 22 / 2017 ዓ/ም
June 29 / 2025


ዲያቆን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
+251923075264
" 🔥 አቤት ደስታዬ እናንተም ደስ ይበላችሁ 🔥 እኚህን ቅዱሳት እጆች ያሏቸውን ሠዎች ማየትም ማግኘትም ምንኛ መታደል ነው ::

ታላቁን የኳታር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴን ቤተ ክርስቲያንን ቅዱሳት ሥዕላትን በተቀላቀሉ ውብ ቀለሞች በመስቀላቸው ብዕርነት በዕንቁ እና በወርቅ ሊያሽቆጠቁጡት እጅግ የተወደዱ ሊቅ የቤተ ክርስቲያኒቷን መዓዛ ያጣጣሟት የአባታቸውን የክህነት ዘር ያስቀጠሉ በሥዕላቸው ትንተና ከሁኔታ ከእይታ ከትርጟሜ ጋር አጣምረው ቅዱሳት ሥዕላትን አይምሮ ላይ ሁሉ ተስሎ እንዲቀር የሚያደርጉት ይህም ጸጋ በዘመናችን የተቸራቸው ዘራቸው በሙሉ ቤተ ክርስቲያኒቷን የሚያገለግሉ ካሕናት የሆኑላት Kesis Amare Kibret ከተወደደው የእርሳቸውን ፈለግ ተከትሎ እየቀደሰም እየሳለም የቤተ ክርስቲያናችንን ዘር ካስቀጠለ ልጃቸው ከሠዓሊ Dn Getabalew Amare ጋር ኳታር ገብተዋል ::
#እግዚአብሔር ፍጻሜውን ያሳምርልን እንኳን ደህና መጣችሁልን !! "

( ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ " )

ለተደረገለን መልካም አቀባበል እጅግ በጣም እናመሰግናለን #እግዚአብሔር ፍጻሜውን ያሳምርልን እንኳን ደህና ቆያችሁን "
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🔥 የደስታ ቀን 🔥 በእጃቸው የያዙት የወርቅ መስቀል እንደ ብዕር ሆኖላቸው የወርቅ እና የዕንቁ ቀለም አመንጭቶላቸው ቅድስት ቤተ ክርስቲያንን በሚያስደንቅ ጥበብ እያንቆጠቆጡ ያሉ ተወዳጅ አባታችን
ሠዓሊ ቀሲስ አማረ ክብረት እና
ተወዳጁ ወንድሜ ሠዓሊ ዲያቆን ጌታባለው አማረ

እንኳን በብዙዎች እንባ እና ጸሎት እየተገነባ ወዳለው ወደ ኳታር ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስትያን እናንተም የታሪኩ አካል ሆናችሁ እንኳን በሠላም መጣችሁልን::

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
📞 +251923075264.

ሊቀ ዲያቆናት ጎርፉ ስጦታው " ዘኳታር ቅድስት ሥላሴ "

#ethiopianorthodoxtewahedochurch #ethiopian_tik_tok🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹 #fyp #orthodox #viral #fypシ#eriterianorthodox
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂 #በአሜሪካ ካሊፎርንያ ለሳክራሚንቶ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከሰራናቻው ሙሉ የቤተመቅደሱ ቅዱሳት ሥዕላት መካከል የጻድቁ አባታችን አቡነ #ተክለሐይማኖት ሥዕል

#ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂 P2, #በአሜሪካ ካሊፎርኒያ ለሳክራሚንቶ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከሰራናቻው ሙሉ የቤተመቅደሱ ቅዱሳት ሥዕላት መካከል የሰማእቱ #ቅዱስ_መርቆሬዎስ ሥዕል

#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂P3 #በአሜሪካ ካሊፎርንያ ለሳክራሚንቶ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከሰራናቻው ሙሉ የቤተመቅደሱ ቅዱሳት ሥዕላት መካከል

የሰማእቱ #ቅዱስ_ጊዮርጊስ ሥዕል

#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂P4 #በአሜሪካ ካሊፎርንያ ለሳክራሚንቶ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከሰራናቻው ሙሉ የቤተመቅደሱ ቅዱሳት ሥዕላት መካከል

#ዕርገታ_ለማርያም ሥዕል

#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
🍂 ከጓደኝነት በላይ ወንድምነትን ያየሁብህ ሠዐሊ Biruk Thomas ጉዟችን አብረን ቢሆን ምንኛ ደስ ባለኝ ነበር እግዚአብሔር ፈቅዶ ዛሬ በሰላም ስለመጣህ ደስ ብሎኛል ፣ እንኳን ደህና መጣህ

#Our_Defense እጅ በእጅ በተግባር ተጀምሮ
ለቅድስት ቤተክርስቲያናችንም ፣ ለሀገራችን
ኢትዮጵያም ትልቅ ታሪክ የምንሠራበት ነውና ፦

አጋእዝተ ዓለም ቅድስት ሥላሴ ኃይል ጸወን ሆነውን ሥራችንን በሚገባ ጨርሰናል የሚለውን ዜና ለምናበሥርበት ጊዜ በሰላም በጤና ያድርሱን ።

እናንተም በጸሎታችሁ አስቡን ! 🙏🏽
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
🍂 QATAR 🇶🇦 DOHA ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ : አጋእዝተ ዓለም #ቅድስት_ሥላሴ እያገዙን እየረዱን ሥራው ግሩም እና ውብ በሆነ መልኩ እየተሠራ ይገኛል :

ለሐምሌ ሥላሴ ክብረ በዓል የፊት ለፊቱን ገጽ እና የዶሙን የታችኛውን ክፍል ለመጨረስ በርትተን እየሠራን ነውና በጸሎታችሁ አስቡን

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት
#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የአንድ ሳምንት የሥራ አፈጻጸማችን ይህንን ይመስላል : ኳታር ዶሀ 🇶🇦 ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ : በጸሎታችሁ አስቡን 🙏🏽

#ሠዐሊ_ቀሲስ_አማረ_ክብረት #ሠዐሊ_ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
#ሠዐሊ Biruk Thomas
📞 +251923075264
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🍂P6 #በአሜሪካ ካሊፎርንያ ለሳክራሚንቶ መካነ ስብሐት ቅድስት ሥላሴ ቤ/ክ ከሰራናቻው ሙሉ የቤተመቅደሱ ቅዱሳት ሥዕላት መካከል

#ቅዱስ_ሩፋኤል ሥዕል

#ዲያቆን_ጌታባለው_አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞+251923075264

@deacongetabalewamare
🍂 ርእሰ : ጻድቃን : ዮሐንስ : መወለዱ : እንደምን : ደስ : አያሰኝ !

በዮሐንስ መወለድ ነቢያት ደስ ይላቸዋል እርሱ ከተወለደ ጌታ መወለዱ ነውና ። መላእክትም ደስ ይላቸዋል ። ዮሐንስ ከተወለደ ጌታ ተወልዶ ሊያዩት ነውና ፤ ወዲህም በንጽሕናው ሊመስላቸው #ተወለደ

መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ እርሱ ከሌሎች ነቢያት በተለየ ጌታውን ዳስሶ ያጠምቀው ዘንድ በፊቱ ይሔድ ዘንድ ይመሰክርም ዘንድ ፥ መንገድ ይጠርግ ዘንድ #ተወለደ

ዮሐንስን የልዑል አምላክን መምጣት ይሰብክ ዘንድ ፥ ጥምቀትን ለንሥሐ ለኃጢአት ይቅርታ ያስተምር ዘንድ #ተወለደ ፡፡

እነሆ ጌታችን መድኀኒታችን በማያልቅ ነገር በማይደክም ልሳን ይመጣል እያለ ያስተምር ዘንድ #ተወለደ ::

ነቢያት ብርሃን ጽድቁን እግዚአብሔር እንዲልክላቸው እየተማጸኑ አልፈዋል ነገር ግን ይህን ብርሃን በአካል ተገኝተው እንዳያዩ የዘመን መጋረጃ ጋረዳቸው ዮሐንስ ግን የዚህን ብርሃን የንጋት ኮከብ ሆኖ መንገድ ሊጠርግ #ተወለደ

ሌሎቹ የመሥዋዕቱ በግ ወዴት ነው እያሉ እየቃተቱ አልፈዋል ዮሐንስ ግን የዓለሙን ኃጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ እነሆ ብሎ የሁላቸውን ጥያቄ ሊመልስ ለዓለሙ ሁሉ የሕይወት ምግቡን ያሳይ ዘንድ የሕይወት መምህር ሊሆን #ተወለደ ፡፡

ከአዳም እስከ ሙሴ ያሉት ሁሉ የመርገሙን ሸክም እንደ ተሸከሙ አልፈዋል ዮሐንስ ግን እርሱ እያጠመቀ ጌታ በእግሩ ተረግጦ የዕዳ ደብዳቤያችንን ሲደመስሰው የነበረ የተመለከተ የዚህ ምስጢር ተሳታፊ ሊሆን #ተወለደ

ያዕቆብ ድንግልን በመሰላል ልጇን በንጉሥ ኃምሳል አየ ዮሐንስ ግን በእናቱ ቤት ንጉሡን በማኅፀኗ ተሸክማ መጣችለት ከማኅፀን ቃሏን ሰምቶ ዘለለ ፡፡ እርስዋን ሰምቶ አደገ ጣዕሟንም ጠገባት ንጉሡንም ሊያጠምቀው #ተወለደ

ያዕቆብ ንጉሡን ከመሰላሉ ጫፍ ላይ አየው መጥምቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ ግን ንጉሡን ከእጆቹ በታች ሊያተጠመቀ #ተወለደ ፡፡

ሙሴ እግዚአብሔርን በደመና ውስጥ ሰማው ፡፡ በዚያም ውስጥ ሰባቱ መጋረጃ ፣ ጉም ፣ መብረቅ ፣ ንውጽውጽታ ፣ ድልቅልቅ ነበር ፡፡ እስራኤልም ከዚህ የተነሣ ደንግጠው እንደ ሻሽ ተነጥፈው እንደ ቅጠል ረገፉ ፡፡ ዮሐንስ ግን ያንን የሚያስፈራ እሳት በእጆቹ ሊዳስሰው ፤ በውኃም ሊያጠምቀው #ተወለደ

#መጥምቀ_መለኮት_ቅዱስ_ዮሐንስ ሆይ አንተ ለአባትህ ያደረግከውን አድርግልኝ እንጂ ፤ አንተ የተዘጉ ነገሮቼን ሁሉ ክፈትልኝ እንጂ ስምህን ደግሜ ደግሜ እጽፈዋለሁ ፡፡ #ዮሐንስ_ዮሐንስ_ዮሐንስ_ዮሐንስ_ዮሐንስ !
©✎﹏ዳዊት ተስፋዬ


ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞 +251923075264
@deacongetabalewamare
ዲ/ን ጌታባለው አማረ
የቅዱሳት ሥዕላት ሠዐሊ
📞 +251923075264
@deacongetabalewamare
2025/07/07 05:37:58
Back to Top
HTML Embed Code: