tgoop.com/dirsanetibeb/90
Last Update:
ሦስት የታሪክ ዓይነቶች
Three Story Types
በቀላሉ የምንረዳቸው ሦስት የታሪክ ዓይነቶች አሉ፡፡
እነሱም - የክዋኔ | የውሣኔ | የጭብጥ ታሪኮች፡፡
፩ኛ • የክዋኔ ታሪክ •
————————
የክዋኔ/የድርጊት ታሪክ አንድ ገፀ-ባሕሪ ችግሯን ለመፍታት ወይም አላማዋን ለማሳካት የምታደርገውን ትግል የሚያሳይ በመሆኑ ማንኛውም የዕድሜ ክልል ባሉ ተመልካቾች ዘንድ ይታወቃል፡፡ አንድ ሰው ከጠንካራ ተቃዋሚው ጋር ታግሎ በመጨረሻ ድል ሲቀናጅ ተመልካች ይደሰታል፡፡
💡👇🏽
በ Clint Eastwood ዳይሬክት በተደረገው Million Dollar Baby በሚለው ፊልም ላይ የ Maggieን ገፀ-ባሕሪ ወክላ የምትጫወተው Hilary Swank የቦክስ ተጋጣሚ ተቀናቃኞቿን ለማሸነፍ የምታረገው ትግል ፤ Gladiator በተሰኝው ፊልም ላይ የ Maximusን ገፀ-ባሕሪ ወክሎ የተጫወተው Russell Crowe ቤተሰቦቹ ተገለው እንደ Galadiator እንዲሰለጥን በባርነት ከተሸጠ በኃላ ከእኩይ ተቀናቃኞቹ ጋር የሚያደርጋቸው በጀብዱ የተሞሉ ፍልሚያዎች እንደክዋኔ ታሪክ መውሰድ ይቻላል፡፡
በነገራችን ላይ ሁለቱም Hilary እና Russell በድንቅ ትወናቸው የAcademy Award for Best Actress
2005 እና Best Actor 2001 በቅደም ተከተል አግኝተዋል፡፡
ለመጨመር ያክል አሳሽ : የጠፋች ከተማ ፍለጋ ሲንከራተት፤ ተራራ የሚወጣ ስፖርተኛ ጓደኛውን አጥቶ መንገድ ሲስት፤ ፖሊስ ወንጀለኛውን ለመያዝ ሲሯሯጥ . . . ክዋኔ ታሪክ ይፈጥራል፡፡ በመሆኑም ክዋኔ ታሪክ ዋናው ገፀ-ባሕሪ የሚፈልገውን እስኪጨብጥ ድረስ ከባላንጣዎቹ ጋር የሚያደርገውን ግብግብ ያሳያል፡፡
የተቀሩትን ሁለት የታሪክ ዓይነቶች ደሞ በሚቀጥለው ፅሑፋችን ይዘን እምንቀርብ ይሆናል፡፡
———
ድርሳነ-ጥበብ / DIRSANE TIBEB @dirsanetibeb
BY DIRSANE TIBEB
Share with your friend now:
tgoop.com/dirsanetibeb/90