tgoop.com/dxnproductknowledge/175
Last Update:
ለምፅ ምንድነው?
ለምፅ ከተወለድን በኋላ የሚከሰት እና የቆዳ ቀለም ባለመመረቱ ምክንያት የሚመጣ የቆዳ ህመም አይነት ነው፡፡
ይህ ህመም በማንኛውም የሰውነት አካል ላይ ቆዳን ሊያጠቃ የሚችል ነው፡፡ ቪታሊጎ (ለምፅ) የሚከሰተው ሜላኒን የሚያመነጩ ሴሎች ሲሞቱ ወይም ሥራቸውን ሲያቆሙ ነው ፡፡ በመደበኛነት የፀጉር እና የቆዳ ቀለም የሚወሰነው በሜላኒን ነው፡፡
ለምፅ ሁሉንም የቆዳ አይነት ሊያጠቃ ይችላል ፤ ነገር ግን ጥቁር ቆዳ ባላቸው ሰዎች ላይ የበለጠ ሊታይ ይችላል፡፡
ቀለም የቀየሩት የሰውነት ክፍሎች አብዛኛውን ጊዜ እየሰፉ የሚሄዱ ሲሆን በተጨማሪም በፀጉር እና በአፍ ውስጥ ሊታዩ ይችላል፡፡
ለምፅ የሚተላለፍ በሽታ የሚመስላቸው ብዙ ሰዎች አሉ፤ ነገር ግን ለምፅ የቆዳ ቀለም እንዲጠፋ የሚያደርግ በሽታ ሲሆን በንክኪ አይተላለፍም፡፡
ለዚህ ህመም መነሻ ይሄ ነው ተብሎ በእርግጠኝነት መናገር ባይቻልም ፤ የተለያዩ መላምቶች እንደምክንያት ይጠቀሳሉ፤ ከነዚህም መካከል የሰውነታችን በሽታ የመከላከያ ስርዓት (immunity system) የራሳችንን የቆዳ ቀለም አምራች ህዋሳትን (melanocytes) በሚያጠቃበት ጊዜ የሚከሰት የቆዳ ህመም ነው የሚለው መላምት በይበልጥ ተቀባይነት አለው።
በዚህም ምክንያት ለምጽ በተመሳሳይ ሁኔታ ከሚከሰቱ ሌሎች ህመሞች (autoimmune diseases) ጋር ተያያዥነት አለው ተብሎ ይታሰባል ፤ ለምሳሌ ከስኳር ህመም፣ የእንቅርት ህመም (autoimmune type)፣ ላሽ (alopecia areata) ይጠቀሳሉ፡፡
ለምፅ ከጭንቀት (emotional stress)፣ ከእርግዝና እንዲሁም ከአደጋ ጋር ተያይዞ ሊከሰት ይችላል፡፡
ምልክቶች ምንድናቸው?
* የቪቲሊጎ ምልክቶች ብዙውን ጊዜ በአይን የሚታዩ ናቸው በመሆኑም በመጀመሪያ በእጅ ፣ በፊት እና በብልት አካባቢዎች ላይ ይታያል።
*የራስ ፀጉር ፣ ቅንድብ ወይም ጺም ላይ ያለጊዜው መንጣት ወይም ሽበት መታየት።
* ቪቲሊጎ በማንኛውም ዕድሜ ሊጀምር ይችላል ፣ ብዙውን ጊዜ ግን ከ30 ዓመት በፊት የሚታይ ነው ፡፡
* በሽታው እንዴት እንደሚስፋፋ ለመተንበይ አስቸጋሪ ነው ፡፡ በአብዛኛዎቹ ተጠቂዎች ዘንድ ህመሙ እየተሰራጨ የሚሄድ እና በመጨረሻም አብዛኛውን የቆዳዎን ክፍል የሚያጠቃልል ነው፡፡ አልፎ አልፎ ቆዳው ወደነበረበት ቀለም ሊመለስ ይችላል፡፡
ሕክምናው
የሕክምናው አሰጣጥ በእድሜ ፣ በቆዳ ላይ ምን ያህል እንደተስፋፋ፣ ቦታው ፣ በሽታው በምን ያህል በፍጥነት እየተሰራጨ እንደሆነ እና በህይወትዎ ላይ ምን ተጽዕኖ እያሳደረ እንደሆነ ይወሰናል ፡፡
መድኃኒቶችን እና ብርሃንን መሠረት ያደረጉ ሕክምናዎች(phototherapy) የሚሰጡት ውጤት ቢለያይም የቆዳ ቀለምን ምርት ለማገዝ ይረዳሉ፡፡አንዳንዶቹ ህክምናዎች ከባድ የጎንዮሽ ጉዳቶች እንዳሏቸው የጤና ባለሞያዎች ይናገራሉ፡፡
በመሆኑም መዋቢያ (ሜካፕ) በመጠቀም የቆዳዎትን ለምፅ ለመሸፈን መሞከር ሌላኛው የሚመከር አማራጭ ነው፡፡
የመድኃኒት ህክምናው ሂደት ውጤታማነቱን ለማወቅ ብዙ ወራትን ሊወስድ የሚችል ሲሆን፤ ምንም እንኳን ህክምናው ለተወሰነ ጊዜ ስኬታማ ቢሆንም የሚያስገኘው ውጤት ላይቆይ ይችላል፡፡
በሌሎች ህክምናዎች የቆዳ ቀለምን መመለስ ካልተቻለ፤ ቀዶ ጥገና አማራጭ ሆኖ ሊቀርብ ይችላል ፡፡
ለምፅ ለማከም ሁለት ዓይነት ቀዶ ጥገናዎች ጥቅም ላይ የሚሆኑ ሲሆን፤ የቆዳ ንቅለ ተከላ(skin graft) እና
የሕዋስ ንቅለ ተከላ (melanocyte transplant) ናቸው፡፡
ቀዶ ጥገና የሚከናወነው ለማይስፋፋ እና ባለበት ለቆመ የለምፅ አይነት (stable vitiligo) ነው።
እነዚህ አማራጭ ህክምናዎች በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በ መቐለ በቅርብ እንደሚጀመር የህክምና ባለሞያዎች ተናግረዋል።
መከላከያዎቹ ምንድናቸው?
*ቆዳዎን ከፀሀይ ብርሃን ይከላከሉ ፤ የፀሐይ መከላከያ ክሬም (sunscreen) መጠቀም ፣ ቆዳዎን ከፀሀይ የሚከላከል ልብስ በመልበስ እና እና ዣንጥላን መጠቀም፡፡
*ከቆዳዎ ገፅታጋ የሚመሳሰል መዋቢያዎችን (makeup)መጠቀም።
*ብዙ ውሃ መጠጣት የሰውነት በሽታ የመከላከል ስርዓትን ያሻሽላል፡፡
*አረንጓዴ አትክልቶችን ፣ ፍራፍሬዎችን እንደ ሙዝ ፣ ፖም ፣ ሽምብራ እና ካሮት ያሉ ምግቦችን መመገብ ጠቃሚ ነው፡፡
የበሽታውን መስፋፋት ለመከላከል አልኮል ፣ ቡና ፣ ዓሳ እና ቀይ ሥጋን ከመጠቀም ይቆጠቡ ወይም ይገድቡ፡፡
ቫይታሚን ቢ፣ሲ፣አሚኖ አሲዶች እና ፎሊክ አሲዶችን የያዙ ምግቦችን መመገብ ጠቃሚ መሆኑን የህክምና ባለሞያዎች ይመክራሉ፡፡
ከለይ ያቀረብነው ከኢቢሲ ከ8 ወር በፊት የተለጠፈ ነው
በተፈጥሯዊ መንገድ እነዚህ ቀለም የሚያመርቱ ሜላኖሳይት ሴሎችን የቆዳ ቀለማችንን እንዲያመጣጥኑ የሚያግዙ ምርቶችን በመጠቀም ማዳን ይቻላል:: እነዚህሞ
መሽሩም ፓውደር https://youtu.be/lxeHgCBwq78?si=UGbtKRmxf6Yfmhpn
ስፒሩሊና https://youtu.be/tUO27-_V_jk?si=1QOARjF0WxW8xAPq
ጋኖዚ የማሳጅ ዘይት
ሞረንዚ ጁስ
የአሎ የቀን ክሬም የፀሀይ መከላከያ
ናቸው
ለማዘዝ በዚህ ይደውሉ +251917415102
BY Healthy Market-ጤናዬ ገበያ
Share with your friend now:
tgoop.com/dxnproductknowledge/175