tgoop.com/eotcbete/449
Create:
Last Update:
Last Update:
✞ ለስንቱ እንጀራ ሆንክ
ለስንቱ እንጀራ ሆንክ ለስንቱ መጠጥ (2)
ኢየሱስ ስምህ ሲጣፍጥ
የበላነው በለስ ገድሎን ሰለነበር
የሕይወት እንጀራን ስንናፍቅ ነበር
ከሰማያት ወርደህ ታርደህ የበላንህ
ኢየሱስ ክርስቶስ ይጣፍጣል ስምህ
አዝ__________
የሕይወት ውሃ ምንጭ ከሆድህ ይፈልቃል
ሰማርያ ወርዶ ውሃ ማን ይቀዳል
በልብ እየፈሰስክ ነፍስ የምታረካ
ቅዳልን ኢየሱስ ጔዳችንን እንካ
አዝ__________
ከያዕቆብ ጉድጔድ ለዘመናት ጠጣን
አመታት አለፉ እጅግ እየጠማን
አይደለም ለእንስራ ለልብ የምትደርስ
የወይኑ ዘለላ በነፍሳችን ፍሰስ
አዝ__________
በሲና የነበርክ የጉዟችን አለት
በረሃው ቀዝቅዞ ረክተን አለፍንበት
ከጥልቅ እንደሚፈልቅ ከአለቱ ላይ ጠጣን
ስምህ እርካታ ነው ከእንግዲህ ላይጠማን
አዝ__________
ሳምሪት ታመኝበት መቅጃ አትጠይቂው
ጉድጔዱም ጥልቅ ነው ብለሽ አትንገሪው
የሕይወትሽ ውሃ መፍሰሻ ነው እርሱ
ለልብ የሚቀዳ እርሱ ነው ንጉሱ
ለስንቱ እንጀራ ሆንክ ለስንቱ መጠጥ x2
ኢየሱስ ስምህ ሲጣፍጥ
ሊቀ-መዘምራን
ዲያቆን ቴድሮስ ዮሴፍ
✥••┈┈••●◉ ✞◉●••┈┈••✥
⛪@eotcbete✝✝✝
⛪@eotcbete✝✝✝
⛪@eotcbete✝✝
BY የተዋህዶ መንፈሳዊ ምስሎች ✝
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcbete/449