tgoop.com/eotcy/2213
Last Update:
በዛሬው መርሐ_ግብሬ እስኪ ይህን ልበላችሁ
የተለመደ ትብብራቹን ለሁሉም አድርሱልን
ከእርሱ ማንንም አታስበልጡ ልላችሁ እወዳለሁ ይነበብ👇👇👇
🔘 ከእግዚአብሔር በላይ ማንንም አታስቀድሙ❗❗❗
ከእግዚአብሔር በላይ የምቶዱት ሰው የለም?
የሆነ ነገር የለም? የምንወዳቸውን ሰዎች ላለማስቀየም ብለን እግዚአብሔርን አላስቀየምንም (ኀጢአት አልሰራንም?)፣ ለእግዚአብሔር ልንሰጠው የሚገባውን ጊዜ ለሰዎች ብለን አላቃጠልንም?
ለምን ይሆን ሰዎችን ከማስቀየም እግዚአብሔርን ማስቀየም የቀለለን?
🛑 ከክርስቶስ በላይ የምንወደው የሆነ ነገር ካለ በቃ ጣኦት አምላኪ ነን።❗
ለዛ ነገር ያለን ፍቅርም ፍቅር አይደለም የውሸት ስሜት ነው።ለአንድ ነገር ወይም ሰው ያለን ፍቅር ከክርስቶስ የበለጠ ከሆነ ውሸት ነው ተራ ነው።
ቅዱስ ጳውሎስ በወላጆችና በልጆች መካከል ሊኖር የሚገባውን ገደብ ሲያስረዳ ምን አለ "ልጆች ሆይ ወላጆቻችሁን #በጌታ ታዘዙ" ለምን በጌታ አለ ብንል የምንታዘዘው ትዕዛዝ በጌታ ቃል የተመዘነ መሆን እንዳለበት ሲነግረን ነው። እርግጥ ነው ቤተሰብን መታዘዝ እግዚአብሔር ማገልገል ነው።ግን እግዚአብሔር የሚያስደስተውና የማያስደስተው አለ ሁሉንም በእግዚአብሔር ቃል መዝኖ መፈፀም ነው የሚገባው። ለምሳሌ ደሞ እጮኝነት ላይ ከትዳር በፊት አንዱ ወገን ሩካቤ ስጋ እንዲፈፅሙ ጥያቄ ሲያቀርብ ሌላኛው ወገን ደሞ አይ ዝሙት ነው እግዚአብሔር ያዝንብላል ሲል አትወደኝም ማለት ነው? አትወጅኝም ማለት ነው? ብትወደኝ ብትወጂኝ ኖሩ አሽ ትይ/ ትል ነበር የሚል ምላሽ ሲሠጡ ይህን ሰው ከማጣ እግዚአብሔርን ልጣ የሚል ሀሳብ ያለው ድርጊት እንፈፅማል ለምን እንደው ባላውቅም ክርሰቶስን ካሶጣን ፍቅራችን የሚሠምር ይመሥለናል።ግን እህቴ ቆይ የእግዚአብሔር ህግ ለማክበር ፈቃደኛ እንዳልሆነ እየተረዳሽ አግብተሽው ልትኖሪ ያሠብሽው ምን ነካሽ?
ቅዱስ ጳውሎስ ባሎችን ሲመክር ክርስቶስ ቤተክርስቲያንን እንደወደዳት ውደዱ ያለውን የሚፈፅም ይመስልሻል? አንተስ ብትሆን ክርስቶስን ለመታዘዝ ዝግጁ ያልሆነችን ሴት ለማግባት ስታስብ ለባሎቻችሁ ተገዙ የሚለውን በትዳር ስትኖሩ ትፈፅመዎለች ብለህ ታስባለህ?
ምን አልባት እንዲህ አይነት ጥያቄ ቢቀርብላችሁ ያው ምን አልባት ሰይጣን እየፈተነው ስለሚሆን ልንፀልይለት በትህትና ልናስረዳ ይገባል ከዛ አቋማቸውን አልቀይር ካሉ ምን ይባላል አመሠግናለሁ ቻዉ ከማለት ውጭ። ከክርስቶስ ማንም ሊለየን ስለማይገባ።
✍ግን አንድ እንድታውቁ የምፈለገው ነገር ከትዳር በፊት ሩካቤ ስጋ እንፈፅም አለማለቱ ብቻ ኦርቶዶክሳዊ መርህን ያሟላል/ታሟላለች ማለት ነው ማለት አደለም እርግጥ ነው አንዱ የኦርቶዶክሳዊነት መገለጫ ነው ግን ብቻ አድርገን ከወሰድንው ትልቅ መሠረታዊ ስህተት ውስጥ እንገባለን።
❌ ማስጠንቀቂያ @eotcy
ከሆነ ጊዜ በኃላ ለወንድ ወይም ለሴት ብሎ ሃይማኖት መቀየር እየተበራከተ መጥቷል። #ክርስቲያኖች እስኪ አስቡት እንዴት አምላካችንን በወንድ ወይም በሴት እንቀይራለን?
ከአምላኩ በላይ ወዶሽ ወይም ወዳህ አምላኩን/ኳን/ የከዳ አንቺን/አንተን/ እንደማይከዳሽ/ህ/ ምን ዋስትና አለሽ/ህ/? ሁላችንም ከምንም በላይ እስከ ሞት ድረስ ያፈቀረንን ክርስቶስን እናስቀድም
ለሁላችሁም ክርስቶስን ያስቀደመ ህይወት ተመኘሁላችሁ 🙏🙏🙏
✍የወደቃችሁ ከጥፋታችሁ ተምራችሁ ወድቃችሁ ያልቀራችሁ ጀግኖች (አናትሽ ሄዎን በውሸት ቃል ተታላ ብትወድቅም ንስሀ ገብታ ዛሬ ቅድስት ሄዎን ተብላ ትጠራለች እግዚአብሔር ምሯት በገነት ነች አንችም ተነሽ ወንድሜ አንተም ተነስ አባታችን አዳም ከውድቀቱ ተነስቶ ወደ ቀደመ ክብሩ ተመልሷል) ያልወደቃችሁ በርትታችሁ እስከመጨረሻው ፀንታችሁ ትኖሩ ዘንድ።
ምንም ይሁን ምን ስናደርግ እግዚአብሔር ምን ይላል የሚለውን መርምረን ይሁን።
❤ https://www.tgoop.com/eotcy ❤
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2213