tgoop.com/eotcy/2223
Last Update:
ምሴተ ሐሙስ እና ጉልባን ምን አገናኛቸወ❓
ጉልባን ከባቄላ ክክ ከስንዴ ወይንም ከተፈተገ ገብስ እና ከሌሎችም የጥራጥሬ እህሎች ጥሬውን ተከክቶ እንደ ንፍሮ ተቀቅሎ የሚዘጋጅ ሲሆን በዕለተ ሐሙስ የዕለቱ ሥርዓተ ጸሎት እና ስግደት አልቆ ቅዳሴው ተከናውኖ ከተፈጸመ በኋላ ምእመናን ወደ ቤታቸው ሄደው የሚመገቡት ነው ይሄውም ስለ ሦስት ነገር ይደረጋል
፩ የኦሪትን ምሳሌ ለመፈጸም
@eotcy
እስራኤላውያ ከግብጽ ባርነት በዘጠኝ መቅሰፍት በአስረኛ ሞተ በኩር መውጣታቸውን እናሳታውሳለን በመጨረሻው ሞተ በኩር ግን ፈርኦን እነርሱን ማስቀረት አልቻለም ነበር እሥራኤላውያንም ተቻኩለው ሲወጡ በቤተ ያለውን እህል ያልተፈጨውን ንፍሮ ቀቅለው የተፈጨውን ቂጣ ጋግረው በልተው ነው ጉዞ የጀመሩት ፡፡ ይህንን በዓል ( ፋሲካን ) ሲያከብሩ በግ አርደው ያልቦካ ቂጣ ጋግረው ንፍሮ ቀቅለው ከባርነት በወጡ ዕለት የነበረውን ሁኔታ ያስቡ ዘንድ ታዘዋል ፡፡ዘዳ 13፡-1
እኛም አስቀድሞ በሙሴ ላይ ህገ ኦሪትን የሠራ ህዝቡንም መርቶ ከነዓን ያስገባ እርሱ እግዚአብሔር የሰውን ሥጋ ተዋሕዶ በሥጋዌ መገለጡን በማመንና ጌታ ራሱ አዲሱን ኪዳን ከመሥራቱ አስቀድሞ ከደቀ መዛሙርቱ ጋር በዓለ ፋሲካን እንዳከበረ ሁሉ እኛም ሐዲስ ኪዳን የተመሰረተባትን ዕለት ስናስብ ቀድሞ የነበረውንና ለሐዲስ ኪዳን ጥላ (ምሳሌ) የሆነውን ሥርዓት ለመታሰብያ እናደርጋለን፡፡
ሌላው እስራኤላውያን ጉልባን በልተው ግብጽን ተሰናብተው እንደወጡና ወደ ተስፋይቱ ምድር እንደገቡ እኛም ከሰሙነ ሕማማት በኋላ የመከራውን ዘመን ተሰናብተን አማናዊውን ሥጋና ደም ተቀብለን ርስት መንግስተ ሰማያትን ለመውረሳችን ምሳሌ ነው ፡፡
፪ የሐዘን ሳምንት መሆኑን ለመግለጽ
@eotcy
እንደ ሀገራቸችን ባህል ንፍሮን ዕንባ አድርቅ ይሉታል ብዙ ጊዜ ለለቀስተኞች ይዘጋጃል ምክንያቱም ሞት ተናግሮ አይመጣምና በድንገት ሲመጣ ለእንግዳ መሸኛ ቶሎ ሊደርስ የሚችል ምግብ ንፍሮ ስለሆነ ለለቅሶ ቤት ይሰራል ስለዚህ ክርስቲያኖችም በክርስቶስ ሞትና በድንግል ማርያም ኃዘን ምክንያት ኃዘንተኞች ስለሆንን ይህንን ለማመልከት ጉልባን እናዘጋጃለን
፫ የጌታን መከራ እና ሕማም ለማሰብ
ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ለማዳን ብሎ ከተቀበላቸው ሕማማተ መስቀል መካከል አንዱ ሆምጣጤን መጠጣቱ ነው በጸሎተ ሐሙስ ይህንን መሠረት በማድረግ የሚዘጋጀው ጉልባን አንዲህም ቂጣ ጨው በዛ ተደርጎ ይጨመርበታል ጨው ውኃ የሚያስጠማ በመሆኑ የጌታን መጠማት ያስታውሰናል፡፡
******
ውድ የዚህ ቻናል ተከታታዮች የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ያልተበረዙ ስርዓቶች ሁሉም ሰው ያውቅ ዘንድ ካነቡ በኃላ ለሌላው ማስተላለፍ አይርሱ
@eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2223