tgoop.com/eotcy/2247
Last Update:
. ⛪️✍ #በዙፋኑም_መካከል: በዙፋኑም ዙሪያ በፊትና በሁዋላ ዓይኖች የሞሏቸው አራት #እንስሶች_ነበሩ:: ፊተኛውም እንስሳ አንበሳን ይመስላል:: #ሁለተኛውም_እንስሳ ጥጃን ይመስላል:: #ሦስተኛውም_እንስሳ እንደ ሰው ፊት ነበረው:: #አራተኛውም_እንስሳ የሚበረውን ንስር ይመስላል:: #አራቱም እንስሶች #እያንዳንዳቸው_ስድስት ክንፎች አሏቸው::(ራዕይ 4:6)🙇♀🦋
(፰🕯) አርባዕቱ እንስሳ ❤🙏
#አርባዕቱ_እንስሳ ማለት⁉⛪️
#የቅድስት_ሥላሴን_መንበር_የሚሸከሙ #የእግዚአብሔር_ሠረገላዎቹ ናቸው። ስለ እሳቸውም ወንጌልን የጻፈ ዮሐንስ እንዲህ ሲል እንደመሰከረ በዚያ #ዙፋን_ፊት_በረድ የሚመስል ባሕር አለ በዙፋኑም ዙሪያ አራት #እንስሶች_አሉ በፊትም በኋላም ዐይንን የተመሉ ናቸው።
አንድም የራሳቸውን #ክብርና_ተፈጥሮ ያስረዳል ገጸ ሰብእ አስተዋይነታቸውን ፤ ገጸ #አንበሳ_ግርማቸውን ፤ ገጸ ላሕም ተገዢነታቸውን ፤ ገጸ ንስር ተመስጧቸውን ያስረዳል ።https://www.tgoop.com/eotcy
አንድም ነገረ #እግዚአብሔርን_ያስረዳሉ ይኸውም ገጸ #ላሕም_ለሥጋዌው ፣ ገጸ ንስር ለተራዳኢነቱ ፣ ገጸ አንበሳ ለኀያልነቱ ፣ ገጸ ሰብእ ለመግቦቱ ምሳሌ ነው ።
አንድም ገጸ #ሰብእ_ሰው መሆኑን ፤ ገጸ አንበሳ ድል አድራጊነቱን ፤ ገጸ ላሕም #መሥዋዕትነቱን ፤ ገጸ ንስር #ትንሣኤውንና ዕርገቱን ያስረዳል
✍ አንድም #በዐራቱ_ወንጌላውያን ይመሰላሉ ገጸ ሰብእ #በማቴዎስ ፣ ገጸ አንበሳ #በማርቆስ ፣ ገጸ ላሕም #በሉቃስ ፣ ገጸ ንስር #በዮሐንስ ይመሰላላል❤🙏
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
🤲 🤲 🤲
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2247