tgoop.com/eotcy/2254
Last Update:
🙊🙊ስድብ በቀጠሮ🙊🙊
▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️▫️▪️
🗣ሴትየዋ በሰፈሩ ውስጥ የታወቀች ተሳዳቢና ተንኳሽ ናት። ወቅቱ የአቢይ ጾም መግቢያ አካባቢ ነው "አሁንስ በጾም በጸሎት ተወስኜ መኖር አለብኝ" ብላ ለራሷ ቃል ትገባና የንስሐ አባቷን ታማክራለች።
🕯 የንስሐ አባቷም በውሳኔዋ ተደስተው መልካም ማድረጓን ገልጸው እንዲህ ሲል ይመክሯታል። "ልጄ አደራሽን ይህ የሱባዔ ወቅት ሁላችን በጾምና በጸሎት ወደ ፈጣሪያችን የምንመለስበትና ስለ ኃጥያታችን የምናለቅስበት ነው እኛ ክርስትያኖች በይኽ ጊዜ እንኳንስ እርስ በእርስ ልንጣላ ይቅርና ጠላታችንን የምንወድበት፣ ስንበድል ይቅርታን የምንልበት የንስሐ ጊዜ ነው።ስለይኽ እንኳን አንቺ ቀድመሽ ልትናገሪ ቢናገሩሽም እንኳን በትእግስት ማለፍ ይኖርብሻል። አደራ ልጄ በርቺ እግዚአብሔር ከአንቺ ጋር ይሁን። ብለው ባርከው ያሰናብቷቷል።
💎ጾሙ ተጀመረና በሦስተኛው ቀን ሴትየዋ የከሰዓቱን ቅዳሴ አስቀድሳ ወደ ቤቷ ስትገባ "አንዴ ሌባ ካሏት ብትቆርብም አያምኗት" እንደተባለው የመንደሩ ሴት በነገር ጠመዳት። እስኪ ተመልከቷት አሁን ላያት ሰው እውነተኛ ክርስቲያን አትመስልም?? ወገኛ......እያሉ ዘለፏት እሷ ግን የንስሐ አባቷ የመከሯትን አስታውሳ እንዳትሳደብም ጾም በመሆኑ እንዲህ አለች "እሺ አሁን ስደቡኝ ግድ የለም ይኽ ጾም ይፈታና እያንዳንድሽን ልክ አስገባሻለሁ። .......
😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊😊
ሁሌም ቢሆን ተናግሮ አናጋሪውን ያዝልኝ ማለት ደግ ነው ቢሆንም ግን የብዙዎች ክርስትና እንደ ፋብሪካ ሠራተኛ በሺፍት(በፈረቃ) ነው። በጾም ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ይገሰግሳሉ ለፋሲካ ግን የመጠጥና ጭፈራ ቤቱን ያጨናንቁታል።
👉👉የሁዳዴ ክርስቲያን የፋሲካ ዘፋኝ መሆን አይገባንም ።
"በጊዜውም አለጊዜውም ጽና "
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2254