tgoop.com/eotcy/2257
Create:
Last Update:
Last Update:
እስኪ ልጠይቃችሁ ❔
አንድ ሰው የተጣራ ወርቅ ልሰጣችሁ እመጣለሁና የሆነ ቦታ [ ለምሳሌ ተራራው ሥር ] ጠብቁኝ ቢላችሁ ምን ታደርጋላችሁ ? ወደዚያ ቦታ [ ወደ ታራራው ለመውጣት ] ለመሔድ አስፋላጊ ነው የምትሉትን [ ቅድመ ዝግጅት ] ሁሉ አታደርጉምን ? [ እንዳያመልጣችሁ በጊዜ ሔዳችሁ ] ቀኑን ሙሉም ቢሆን ቁጭ ብላችሁ አትጠብቁትምን ?
እግዚአብሔር እሰጣቹዃለሁ ያለው አንድ ሺህ ቅንጣት ወርቅ አይደለም ወይም ምድርን ሁሉ አይደለም። ከእነዚህ ሁሉ የምትበልጠዋን መንግስተ ሠማያትን ነው እንጂ ...
ታድያ ከዚያ የሚበልጥ ስጦታ ምን አለ ? 🤷🏾♂
[ ምንም የለም ] ይሕን ስጦታ ለማግኘት የማይደክሙ [ ወደ ተራራው የማይወጡ ] ሰዎች እንደምን ያሉ ምስኪኖች ናቸው❓
| ቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2257