tgoop.com/eotcy/2265
Last Update:
እውነት እስኪ ይችን እውነታ አንብቡልኝ
ኤልሳቤጥም የማርያምን ሰላምታ በሰማች ጊዜ መንፈስ ቅዱስ ሞላባት አሰምታም እንዲህ አለች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የማህጸንሽም ፍሬ የተባረከ ነው የጌታየ እናት ወደኔ ትመጣ ዘንድ እንደት ይሆናል❓
የሰላምታሽ ድምፅ ወደኔ በመጣ ጊዜ ጽንሱ በማህጸኔ ዘሏልና" ሉቃ.፩÷፳-፵፫🙏
#ልብ_በሉ ሰላምታዋ መንፈስ ቅዱስን የሚሞላ ሴት እንደት የተመረጠች ናት❓
በመንፈስ ቅዱስ የተሞላች አረጋዊት ሴት አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የምትባል ሴት እንዴት አይነት መመረጥ ነው በኤልሳቤጥ ብቻ አይደለም መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልም ይህንኑ ቃል አንቺ ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ ብሏታል ምን አይነት መመረጥ ነው❓
ሰላምታዋን በሰማ ጊዜ በማሕጸን ያለ ጽንስ እንኳ በደስታ የዘለለ ምን አይነት ቅድስና ነው❓
@eotcy
ታዲያ በመንፈስ ቅዱስ ተሞልታ ኤልሳቤጥ ካመሰገነች ድንግል ማርያምን ፕሮቴስታንት አላመሰግንም የሚል ምን ተሞልቶ ነው❓
በመልአኩ አንደበት ጸጋን የተሞላሽ ሆይ ደስ ይበልሽ እግዚአብሔር ካንቺ ጋር ነውና፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ የተባለችን እናት እኛም እንደመልአኩ እናመሰግናታለን።
እኛስ መንፈስ ቅዱስን ተመልታ እመቤታችንን
እንዳመሰገነቻች ኤልሳቤት እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል እናመሰግናታለን መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን እንድትመሰገን
ሲያደርግ አይተናል። የጌታዬ እናት እንላታለን በመንፈስ ቅዱስ ሆና የጌታዬ እናት አንች ወደኔ ትመጭ ዘንድ እንደት ይሆንልኛል፤ አንች ከሴቶች መካከል ተለይተሽ የተባረክሽ ነሽ፣ የማህጸንሸ ፍሬ የተባረከ ነው.....እያልን እናመሰግናታለን
ይህን ያደረገ መንፈስ ቅዱስ እንደሆነ በግልፅ አይተናልና።
@eotcy
❤ ሰማያዊ መልአክና ምድራዊት ሴት ተባብረው በአንድ ቃል በአንድ መንፈስ ቅዱስ ያመሰገኗትን አላመሰግንም የሚሉ በምን መንፈስ ሆነው ነው❓መንፈስ ቅዱስ እመቤታችንን አስመሰገነ እንጅ ሲከለክል አላየንም። አላመሰግንም የሚሉ ከምን እንዳገኙት እንኳ አይነግሩንም።
ሰይጣንና ክፉ የገንዘብ ፍቅር ክብሯን ሸፍኖባቸዋልና።
እኛ ግን ከመጽሐፍ ቅዱስ እንደተረዳነው እንደ መልአኩ ቅዱስ ገብርኤልና ቅድስት ኤልሳጼጥ እናመሰግናታለን።
ሁላችችንም እንደ ቅዱስ ዮሐንስ በእምነት ወደቤታችን ወስደናታል
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
@eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy
@eotcy @eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2265