tgoop.com/eotcy/2266
Last Update:
"ባልሽን የገደልሽው መርዟ አንች ነሽ"
ከለታት አንድ ቀን አንዲት ውብ የሆነች ልጃገረድ ባገባች በ ሁለተኛው ዓመት ትዳሯ ምርር ስላላት ባሏን ለመግደል ፈለገች።
ይህች ቆንጆ ልጅት አንድ ቀን ጠዋት ወደ እናቷ ቤት ብርር ብላ በመሄድ፦ "እማዬ የባሌ ነገር አድክሞኛል የሚያደርጋቸው የማይረባ ነገሮች ሰልችተውኛል ለኔ አያስብልኝም ዞር ብሎ አያየኝም እኔንጃ ከሌላ ሴት ጋር የጀመረው ነገር አለ እርሱን ገድዬ መገላገል ፈልጋለው በሌላ በኩል ህግ ያስረኛል ብዬ እፈራለው እባክሽ እርጂን " አለቻት።
እናቷም "እሺ ውድ ልጄ እረዳሻለው ነገር ግን አንዳንድ የምታደርጊያቸው ነገሮች አሉ"። አለቻት።
ልጅቷም " አንቺ ያልሽኝን ሁሉ አደርጋለው አለች"
እናትየውም "ባልሽ ሞቶ ሬሳው ከቤትሽ እስከሚወጣ ድረስ ከዛሬ ጀምሮ የምታደርገውን 6 ነገሮች በጥንቃቄ ፈጽሚው አለች፦
1. የገደለችው እሷናት ብለው ጎረቤት እንዳይጠረጥሩሽ ከአሁን ሰዓት ጀምረሽ ከባልሽ ጋር ሰላም ፍጠሪ
2. ሁልግዜ ውበትሽን ጠብቀሽ ወጣትና ቆንጆ ሆነሽ ታይ
3. በደንብ አድርገሽ ተንከባከቢው ጥሩ ሁኚለት አበረታችው
4. ትዕግስት አድርጊ ብዙም አትቅኚ ብዙ ግዜ አዳማጭ ሁኝ በማክበር ታዘዥው
5.በእጅሽ ያለውን ገንዘብ ለእሱ ጥቅም ብቻ አድርጊው እንዲች ብለሽ ለራስሽ እንዳትጠቀሚ ገንዘብ ከከለከለሽ አትናገሪ ዝም በይ
6. ማንም ገድላዋለች ብሎ እንዳይጠረጥርሽ የጭቅጭቅና የጩኸት ድምፅ አታሰሚ ሰላምና ፍቅር ብቻ ከአፍሽ ይውጣ ... እስከ ምትገላገይው ድረስ ብቻ ነው።
እናትዮዋ፦ በድጋሚ "ሳታዛንፊ ያልኩሽ ታደርጊያለሽ?" አለቻት።
ልጅቷም " እሱ ብቻ ሞቶ ሬሳው ይውጣልኝ እንጂ አደርገዋለሁ" አለች።
እናትየዋም የሆነ ብልቃጥ እየሰጠቻት፦ " ይህንን መርዝ ያዥው ቀስ እያለ ውስጡን አመንምኖ እንዲገድለው በየቀኑ ምግቡ ውስጥ ጠብ እያደረግሽ ስጭው" አለች።
ልጅቷም ድስ እያላት ወደ ቤቷ ተመለሰች።
ከአንድ ወር ብሓላ ልጅቷ ወደ እናቷ ቤት ተመልሳ መጣች። እንዲህ አለቻት" ወይ ጉድ ሰውዬው ወሬ ሰምቶ ይሁን ወይ ቀልቡ ነግሮት? ድሮ ዞር ብሎ የማያየኝ ሰውዬ ፣ ፍቅሬ፣ማሬ ፣ወለላዬ፣ ህይወቴ፣ ንግስቴ፣ በዓለም ላይ የምታክልሽ ሴት የለችም ይለኝ ጀምሯል ብቻ እኔንጃ ጸባዩ ልውጥ አለብኝ"
እናትየውም፦ መርዙን እየሰጠሽው ነው? አለቻት
ልጅቷም አይኗ ላይ እንባ እየቀረረ ፦ አዎ ግን አሁን ጸባየ ሸጋ ጣፋጭ አፍቃሪ ባል ሆኗል እንዲሞትብኝ አልፈልግም ማርከሻ ሌላ መድሃኒት ካለ ፈልጊልኝ እባክሽ ጸጸቱ ሊገለኝ ነው።
እናትየዋ፦ ልጄ በብልቃጥ የሰጠሁሽ መርዝ አይደለም የእርድ ዱቄት ነው። ነገር ግን ቀስ በቀስ ጸባየ መጥፎውን ባልሽን የገደልሽው "መርዟ አንቺ ነሽ" ማለቴ እሱን ማፍቀር ፣ መታዘዝ፣ መንከባከብ፣ መታገስ፣ ማክበር እና ውብ ሆነሽ ስትገኚ ባልሽን መለወጥ ችለሻል። አንቺ ለሌላው ሰው ምንም ነገር ሳትሰጭ እንዴት ከሌላ ሰው ያልሰጠሽውን ትጠቢቂያለሽ? ፍቅር ማለት ሰጥቶ መቀበል ነው። ቅድሚያ ግን መስጠት ያስፈልጋል ፍቅር ከሰጠሽው ፍቅር ታገኝያለሽ ጸብና ጭቅጭቅ ይዘሽ የምጠብቂው ከሆነ ያንኑ ታገኛለሽ።
ምላሽ ሳትጠብቂ ከራስሽ አስበልጠሽ በሁሉም ነገር ባልሽን አስቀድሚ ፍቅር ስጭው!
እንዲህ በጥበብ ትዳርን የሚያክል ተቋም የሚታደጉ እናቶችን፣ አባቶችን እግዚአብሔር ያብዛልን።አሜን!
ብታጋሩት መልካም ታደርጋላችሁ።
--2ኛ ቆሮ 6፥2
@eotcy
@eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2266