tgoop.com/eotcy/2271
Last Update:
➲ ልብ የሚነካ አሳዛኝ ታሪክ 😢
🚺 በጣም ከወደድኩት ታሪክ ላጋራችሁ
እናቱን የሚወድ ሁሉ ሊያነበው የሚገባ ፅሁፍ መልካም ንባብ
ከባለቤቴ ጋር ትዳር ከመሰረትን 21 ዓመት ሞላን ባለቤቴ አንድ እራሴን እንድፈትሽበት ያደረገኝን ጥያቄ አቀረበችልኝ ሃያ አንድ ዓመት ካንተ ጋር ስኖር አንድም ቀን ከእናትህ ጋር ለመዝናናት ስትወጣ አይቼክ አላውቅም ዛሬ ማታ እናትህን እራት ምሽት ጋብዛትና አዝናናት አለችኝ።
ውዷ ባለቤቴ ባቀረበችልኝ ሃሳብ ከመገረም በላይ መሰጠኝ ተስማማሁኝ እናም ወደ እናቴ ጋር ደወልኩላት እማ ዛሬ ካንቺ ጋር ሽርሽር መውጣት ፈልጋለሁ አልኳት ደነገጠች "ምነው ሰላም አይደል ልጆችሕ ምን ሆኑ ባለቤትህስ ሰላም አይደለች እንዴ ?" በማለት የድንጋጤ ጥያቄዎቿን አርከፈከፈችብኝ።
አብሽሪ እማ ሁሉም ሰላም ነው ካንቺ ጋር ለመዝናናት ፈልጌ ነው"አልኳት በጣም ደስ አላት ተስማማች ወደማታ ተዘጋጅተሽ ጠብቂኝ አልኳት በቀጠሮዬ ሰዓት ወደ እናቴ ጋር ሄድኩኝ እናቴ በረንዳው ላይ ቆማ እየጠበቀችኝ ነበር እናቴ ሁለመናዋ ተቀያይሯል እርጅና ተጫችጭኗታል ሰላምታ ከተለዋወጥን በኋላ ወደ መኪናዬ አስገብቺያት ጉዞ ጀመርን።
እናቴ በጣም ደስታ ይነበብባታል "ልጄ ዛሬ ካንተ ጋር ሽርሽር እንደምወጣ ለሰፈር ሰዎች ሁሉ እንዲሁም ለዘመድ አዝማዶቼ በሙሉ ተናግርያለሁኝ" በጣም ከመደሰቷ የተነሳ አንድም የምታውቀው አልቀራትም ወሬውን ለሁሉም አዳርሳዋለች ወደ ሆቴል ይዥያት ሄድኩኝ አስተናጋጁ የምግብ ዝርዝር ወረቀት የያዘ ኩፖን ሰጠን "እማ ምረጪ" አልኳት ፈገግ አለች ከእርጅና የተነሳ ማየት እንደማትችል ተረዳሁ ላንብብልሽ አልኳት "ልጅ እያለህ ሆቴል ቤት ገብተን ልንመገብ ስንል የምግብ ዝርዝር አነብልህ ነበር አሁን እዳህን ክፈል" ብላ ፈገግ አለች እኔም ፈገግ ብዬ አነበብኩላት።
የለበሰችውን ልብስ ስመለከት ከአስራ ዘጠኝ ዓመት በፊት የሞተው አባቴ የገዛላት የመጨረሻ ልብሷ እንደነበር አስታወስኩ ምግቡ ቀርቦ እናቴ ከደስታ የተነሳ ምንም እየበላች አልነበርም ደስታ በደስታ ሆናለች
በሕይወቴ እኔም በጣም የተደሰትኩበት አጋጣሚ ነበር ከእናቴ ጋር ተዝናንተን ስናበቃ ይህ ምሽት እንዲደገም ፈልጌ "እማ መቼ ተመልሼ ልምጣና ልውሰድሽ..?" አልኳት በእንደዚ ቀን ና ነገር ግን እኔ ነኝ የምጋብዝህ ከተስማማህ ና " አለቺኝ ፈገግ አልኩኝ ትጋብዥኛለሽ አልኳትና ተለያየን።
በመሃል እናቴ ታመመች ከህመሟ ድናልኝ አብርያት የማሳልፍበትን
ምሽት ናፈቀኝ ነገር ግን ከእናቴ ጋር ዳግም አልወጣንም እናቴ ወደ
ማይቀረው የሞት ጉዞ ተጓዘች በጣም አዘንኩ አለቀስኩ ከእናቴ ጋር ቀጠሮ ይዘን ወደነበረው ምሽት ከአንድ ታዋቂ ሆቴል ቤት ተደወለልኝ ዛሬ እራት ከባለቤትህ ጋር በነፃ ተጋብዛቹሃል።
@eotcy
ግራ ተጋባው ማነው እንዴት ለማንኛውም እሺ እንመጣለን ብዬ ስልኩን ዘግቼ ምሽት ላይ ከባለቤቴ ጋር ሄድኩኝ ግብዣው ከደብዳቤው ጋር ቀረበልን ደብዳቤውን ከፈትኩት እንዲህ ይላል :-"ልጄ ሰላም ላንተ ይሁን የእራቱን ግብዣ ስንቀጣጠር መገኘት እንደማልችል አውቅ ነበር
የሞት ቀጠሮዬ እየተቃረበ እንደነበር ነፍሴ ይነግረኝ ነበር ልጄ ይኸው እኔ በቃሌ መሰረት ጋብዥሃለው በኔ ፋንታ ውዷባለቤትህ አብራህ እንድትሆን ፈቅጃለሁ!" ይላል ሳይታወቀኝ እንባዬ ወረደ አለቀስኩ 21 ዓመት ሙሉ የዘነጋሁትን ውድ ዕቃ አሁን ነው ማጣቴን ያወኩት...!
@eotcy
ስንቶቻችን ይሆን ካገባን በኋላ እናቶቻችንን ወላጆቻችንን የምናስታውሰው ? ...ስንቶቻችን ነን ለራሳችን ስንሯሯጥ ወላጆቻችንን የረሳነው..? ስንቶቻችንስ ነን የእናት ፍቅር ያልገባን
ወላጆቻችን በህይወት ያሉ መቼም አይደለም ጊዜው አሁን ነው
እባካቹህ ሀሳባቹህን አካፍሉን🙏✍ 👇👇 @eotcy_comment
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/UAYNVHcM-VruQgZy0cwyWGcquE69um8xiDF99VWKPO-l1C1brINNfrnb274DX9LulxuejuZ48QLEQ4dV04615vBbfsO-1mzL6yRxPTrxBokT5vN18S_2IsGD95O1Da1EV2Bp-iSzrD18dQLyGTR-3DMVvyLF3ULa6fmFgrKd5IFKucl93oOLuE4mcN9wLcAuKkHb5kBiPfwTfH4gxvtEMuSVvfRaIwAp3LPlM-LbYS1G5-bDVWARAbd80OI_ciDJGTQqGArXNxc1Jag6V-oAdCiMzQnbSWumCR5Ug1Ud7LGhfHH99BXvyqThzuOGmoKLtLBDUykMgeRNROj-Y8J9Tw.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2271