tgoop.com/eotcy/2283
Last Update:
ቃለ ሕይወት ያሰማልን ማለት ምን ማለት ነው?
ይህ አባባል በቤተ ክርስቲያናችን ውስጥ ከወንጌል ስብከት፣ ከመዝሙር ከምክር ተግሳጽ በኋላ ምእመናን በአንድነት ላቀረበው አካል ቃለ ሕይወት ያሰማልን፣ መንግስተ ሰማያት ያውርስልን አገልግሎት ዘመንዎትን ያርዝምልን በእድሜ እና በጸጋ ይጠብቅልን ፣ ዝማሬ መላእክትን ያሰማልን .... ወዘተ እያልን መንፈሳዊ ምርቃን እንመርቃለን! ምን ማለት ነው ቃለ ህይወት ያሰማልን? ቃለ ሕይወትስ ምንድን ነው??
በወንጌል በመዋዕለ ሥጋዌው፣ ለሥም አጠራሩ ክብር ይግባውና ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ብትወዱኝ ትዕዛዜን ጠብቁ (ዮሐ.14:15) እርስ በርሳችሁ ተዋደዱ በእኔ እመኑ በአባቴም እመኑ በሃይማኖት ኑሩ ጎልምሱም.....(1ኛቆሮ 16:13) በሃይማኖት ጤናማ
(ቲቶ 1:13-14) ሆናችሁ እኔ የዋህ በልቤም ትሁት እንደሆንኩ በእኔ አምናችሁ ለነፍሳችሁ እረፍት አግኙ
(ማቴ.11:29)..... ጆሮ ያለው መስማትን ይስማ... እስክመጣ ድረስ ትእዛዜን ጠብቁ ያለውን ይዘው በሃይማኖት ኖረው መልካም ተጋድሎን አድርገው በጌታ ለኖሩ በእሱና በቃሉ ላላፈሩ (ሉቃ.9:26) ንስሀ ገብተው ሥጋውን በልተው ደሙን ጠጥተው ለዘለዓለም ሕይወት ራሳቸውን ላዘጋጁ ትእዛዜን ብትጠብቁ በፍቅሬ ትኖራላችሁ እንዳለ
(ዮሐ.15:10) በፍቅሩ ለኖሩ በመጨረሻም ኩላሊትንና ልብን የምመረምር እኔ ለእያንዳንዳችሁ እንደ ሥራችሁ ለመክፈል (ራዕ.23:32) እስክመጣ ድረስ በፍቅር ኑሩ ያለውን ለፈፀሙ ...በአጠቃላይ በጌታ ለኖሩ ፍሬዎች የሰው ልጅ በክብር በሚመጣበት ጊዜ (ማቴ.25:31) በጎቹን ፍየሎቹን በሚለይበት ጊዜ (ማቴ.25:34) ኑ እናንተ የአባቴ ቡሩካን ኑ ዓለም ከተፈጠረበት ጊዜ ጀምሮ የተዘጋጀላችሁን መንግሥት ውረሱ።
ብሎ ጌታ የሚፈርደው ፍርድ የሕይወት ቃል ይባላል።
ሥለዚህ ቃለ ሕይወት ያሰማልን ማለት ይህን የተወደደ ለዘለዓለማዊ ሕይወትን የሚሰጥ ቃል ያሰማልን፤
በቀኙ ከሚቆሙት ቅዱሳን ይደምርልን እንደማለት ነው፤
ግሩም ምርቃት! አሜን እኛንም የጥምቀት ልጆቹን በመንግሥቱ በመጣ ጊዜ ኑ የአባቴ ብሩካን ከሚላቸው ጋር ይደምረን።
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/Eqih0Aq0mMNzTW4_vKLrSi0SmiupSGhdIcmcHRjwsfpBMD4EjTg4JwUO55zGfGBHZanjEQKRUFUdSW__j-LmoUYXSyBU0XS8QH8D8Iwz_tyUV-b5i6U-xxlA-anX-51S3c7413PRjKDv8U36ZiddVVxNAhsdcRAERpNRe7nwn36jWnp8IkOayC7rbUVpgJmh81BBjBaiXOkPBTToAHP-j5R4xXEvH4yoKvJpiaS_tbIwizIAOk0GmHSinrnb3Yq_M0TIrYt8KfqyC0c23gkOPABeN6Kt_9B1gQXASS5iCC8EnyAXGAYDQy2WGrMhlXL7XgNz8jlIPL7lH2EQZxb54g.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2283