tgoop.com/eotcy/2285
Last Update:
ምክረ አበው
የማታምንበትን ነገር ለሰው ስትል አትስራው ከሰራኸው እንደምትጠፋበት እወቅ።(መጽሐፈ ምክር)
"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል። (አረጋዊ መንፈሳዊ)
ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)
‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል❓›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/
‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ፀጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/
‹‹በማንም ላይ ክፈትን አትስሩ አትፍረዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/
‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/
‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/
‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ንጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/
‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
‹‹የቤተክርስቲያን ህይወት በመስቀል ላይ ስለሆነ ፈተና ይበዛበታል ስለዚህ ከግል ህይወታችሁ ይልቅ የቤተክርስቲያናችሁን አቋም አጠንክሩ።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ/
‹‹ከመኝታህ በፊት የምታደርገውን ጸሎት ትተህ እንድትተኛ መንፈስህ ሲገፋፋህ እሺ ብለህ አትቀበለው፡፡ እንዲያውም መዝሙረ ዳዊትን ጨምርና ሌሊቱን በሙሉ ስትጸልይ እደር።›› /ቅዱስ ይስሐቅ ሶርያዊ/
‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ እንጦስ/
"አንደበቱን ከቧልት ያየውን ሚስጥር ከመናገር የሚከለክል ሰው ልቦናውን ከኅልዮ ኃጢአት ያርቀዋል። (አረጋዊ መንፈሳዊ)
ጸጋ ቢሰጥህ በተሰጠህ ጸጋ አመስግን ያልተሰጠህን እሻለሁ በማለት የተሰጠህን እዳታጣ " (ማር ይስሃቅ)
‹‹ራሱን የሚንቅ የሚያቃልል ሰው ከእግዚአብሔር ዘንድ እውቀትን ያገኛል አዋቂ ነኝ የሚል ሰው ከፈጣሪው ‹ጥበብ ይለየዋል።›› /አረጋዊ መንፈሳዊ/
‹‹እግዚአብሔር ሆይ አፈርና ትቢያ ሆኜ ሳለ ጻድቅ አድርገው ከሚቆጥሩኝ ሰዎች አድነኝ።›› /አባ እንጦንስ/
‹‹ፍጡራንን መርምሮ ማወቅ ካልተቻልን ሁሉን የፈጠረ እርሱን መርምሮ ማወቅ እንደምን ይቻልናል።›› /ቅዱስ አትናቴዎስ/
‹‹ወርቅ በእሳት እንደሚፈተን ሁሉ የክርስቶስንም ጸጋና ክብር ሳይፈተኑ ማግኘት አይቻልም የዚህ ዓለም ፈተናና እሳት ቶሎ ያልፋል ይጠፋል ኃጢያተኞች የሚገቡበት የገሀነም እሳት ግን ለዘላለም እንደ ነደደ ይኖራል።›› /ቅዱስ ሚናስ/
‹‹በማንም ላይ ክፋትን አትስሩ አትፍርዱ ይህንን ከጠበቃችሁ ርስቱን ትወርሳላችሁና።›› /ታላቁ አባ መቃርስ/
‹‹ብዙ ጊዜ ብዙ እናገራለሁ በመናገሬም አዝናልሁ በዝምታዬ ግን ያዘንኩበት ጊዜ የለም።›› /ቅዱስ አርሳንዮስ/
‹‹ቤተክርስትያን መጠጊያችን ነች ቤተክርስትያን የኖኅ መርክብ ነች በውስጧ እንጠለላልን ከውጭዋ ግን ማዕበልና ቀላያት ተከፍተዋል።›› /ቅዱስ እንድርያስ/
‹‹ልባችንን ጠፊና በስባሽ ከኾነው ከምድራዊው ምኞት አርቀን ከበደል በንስሐ ነጹሕ ካደረግነው በጸጋ መንፈስቅዱስ የተሞላን እንሆናለን።›› /አባ አብርሃም መፍቀሬ ነዳያን/
‹‹ስጋዊ ፍላጎቶችን ማሸነፍ ለአክሊለ ህይወት የሚያበቃ ሰማዕትነት ነው።›› /ብፁዕ አቡነ ጎርጎርዮስ ካልዕ
‹‹ኃጥያታችንን እኛ እያሰብን የምንፀፀት ከሆነ እግዚአብሔር ይረሳልናል ኃጥያታችንን እኛ እረስትን የምንፅናና ከሆነ እግዚአብሔር ያስብብናል።›› /ቅዱስ እንጦስ/
🟢 @eotcy 🟢
🟡 @eotcy 🟡
🔴 @eotcy 🔴
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2285