tgoop.com/eotcy/2288
Last Update:
እውነተኛ ማንነታችን በስም ፣ በማዕረግ በዕውቀት ፣ በዕድሜ....ተሸፍኖ ሊኖር ይችላል፣ ዛሬ ብዙዎቻችን ጋር ያለው ከልብ ያልኾነ የማስመሰል ክርስትና ነው።
ቤተ ክርስቲያን ሄደን
ስለ ተሳለምን
ስለ ተማርን
ስላስተማርን
ስላስቀደስን
ስላነበብን
ስለ ዘመርን
ገዳማት ስለጎበኘን
ስላደነቅን
ክርስትናን እየኖርን ከመሰለን ተሳስተናል።
ይኽ የሥርዓተ አምልኮ ክፍል እንጂ ፣ በራሱ ብቻውን ክርስትናዊ ሕይወት መገለጫ አይደለም።
የተክል ፍሬ እንዲያፈራ
ውሃ፣
አፈር
የፀሐይ ብርሐን እንደሚያስፈልገው፣
ከላይ የተዘረዘሩትን (መሳለሙ ፣ ማገልገሉ)
መንፈሳዊ ፍሬ እንዲናፈራ የሚያደርገን ናቸው እንጂ በራሳቸው ግብ አይደሉም።
አብዛኞቻችን ግን በእነዚህ ብቻ ታጥረን (ረክተን) ቆመናል)
የክርስትና / የመንፈሳዊ ሕይወት መገለጫው
ፍቅር፣
ቅድስና፣
ንጽሕና፣
ትሕትና፣
ትዕግስት፣
ቅንነት፣
ይቅር ባይነት፣
በሌላ አለመፍረድ፣
.....የመሳሰሉት ናቸው።
በመመላለሳችን እነዚህ ኹሉ ከሌሉ (ቢያንስ ለመተግበር ካልቀረብን) የክርስትና ጭምብልን አጥብቀን እየተወንን እንጂ ክርስትናን እየኖርነው አይደለም።
ብርሃን ከጨለማ በቀላሉ እንደሚለይ ክርስትናንም በግብሩ (በምግባሩ) በሥራው ከአሕዛብ በቀላሉ ይለያል።
መለያው ደግሞ "ሕይወቱ" እንጂ የአገልግሎት ተሳትፎው አይደለም።
ይሄን ለይተን ክርስትናን የምንተገብርበት ጥበብ ያድለን
ብርሃን
"...........እነሆ፥ የተወደደው ሰዓት አሁን ነው፤ የመዳን ቀን አሁን ነው"
--2ኛ ቆሮ 6፥2
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች
![](https://photo2.tgoop.com/u/cdn4.cdn-telegram.org/file/Eqih0Aq0mMNzTW4_vKLrSi0SmiupSGhdIcmcHRjwsfpBMD4EjTg4JwUO55zGfGBHZanjEQKRUFUdSW__j-LmoUYXSyBU0XS8QH8D8Iwz_tyUV-b5i6U-xxlA-anX-51S3c7413PRjKDv8U36ZiddVVxNAhsdcRAERpNRe7nwn36jWnp8IkOayC7rbUVpgJmh81BBjBaiXOkPBTToAHP-j5R4xXEvH4yoKvJpiaS_tbIwizIAOk0GmHSinrnb3Yq_M0TIrYt8KfqyC0c23gkOPABeN6Kt_9B1gQXASS5iCC8EnyAXGAYDQy2WGrMhlXL7XgNz8jlIPL7lH2EQZxb54g.jpg)
Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2288