tgoop.com/eotcy/2305
Last Update:
የዓለማችን ድንቅ ሚስጢር❗❗❗
#ሼር
ስለ ቅድስት ኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተክርስቲያኔ ሳስብ ሁሌ የምደመምበትና የምደነቅበት አንድ ነገር አለ
ምን መሠላችሁ
ሁላችሁም እንደምታውቁት በተለምዶ Oriental Orthodox ተብለው የሚጠሩት ክርስቶስ አንድ አካል አንድ ባህርይ ነው ብለው የሚያምኑ አብያተክርስቲያናት የሚገኙት ( መንበረ ፕትርክናቸው የሚገኝበት ) በአምስት የተለያዩ ሐገራት ውስጥ ነው
አስቡት
👉 አምስቱም በተለያዩ ሀገራት ባህል ቋንቋና ማኀበረሰብ ውስጥ ነው ያሉት
👉 አምስቱም የየራሳቸው ፓትርያሪክና ቅዱስ ሲኖዶስ አላቸው
👉 አምስቱም ራሳቸውን የቻሉ Independent አብያተክርስቲያናት ናቸው አንዱ በአንዱ ጣልቃ አይገባም
👉 አምስቱም የየራሳቸው ቀኖናና አምልኮ ስርዓት አላቸው
👉 አምስቱም በየራሳቸው የጊዜ አቆጣጠር ዓመታዊ የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዓተ ጉባኤያቸውን ያደርጋሉ
በአጠቃላይ አምስቱም አብዛኛውን እንቅስቃሴያቸውን በግላቸው ወይንም እነርሱን በሚመለከት ነገር ላይ ብቻ ትኩረት ያደረገ ነው
💝 እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ ግን በአንድ አይነት ዶግማ ያምናሉ !!!
👉 የውላችሁ 👈
በአንድ አይነት ዶግማ ያምናሉ ሲባል ቀለል አድርጋችሁ በፍጹም እንዳታዩት ‼️❗️
Imagine
እነኚ አብያተክርስቲያናት በጋራ ለመጨረሻ ጊዜ የቅዱስ ሲኖዶስ ስብሰባ ያደረጉት በኤፌሶን ላይ በ425 ዓ.ም ላይ ነበር
ከዛ በኋላ 1600 አመታት በጋራ ያደረጉት Official ጉባዔ የለም ‼️❗️
ነገር ግን በያሉበት አካባቢ በየጊዜው Local Synod በማድረግ
ቤተክርስቲያናቸውን ይመራሉ ፣ በቤተክርስቲያናቸው ላይ ለሚነሡ ጥያቄዎች ምላሽ ይሰጣሉ ፣ የተለያዩ አስተዳደራዊና ሐይማኖታዊ ውሳኔዎችን ያሳልፋሉ ፣ ሐይማኖታቸውን አስጠብቀው ይጓዛሉ ...
👉 እጅግ በሚያስደንቅ ሁኔታ ግን
አምስቱም በየራሳቸው በሚያደርጉት ስብሰባ ላይ እርስ በርሱ የሚጣረስ አስተምህሮ አላመጡም
አንደኛው ያጸደቀው አንደኛው ያልተቀበለው ኃይማኖታዊ ውሳኔም ( ዶግማ ) የለም ‼️❗️
አምስቱም ሲኖዶሳት
በ325 በኒቂያ ጉባዔ
በ381 በቁስጥንጥንያ ጉባዔና
በ425 ኤፌሶን ጉባዔ ከተደነገገው ውሳኔና ና ቀደምት ሐዋርያነ አበው ካስተማሩት ትምህርት ላይ የጨመሩትም ሆነ የቀነሱት አንድም አስተምህሮ የለም !!!
በሚገርም መከራና ሂደትም ከጌታ ከሐዋርያትና ከሐዋርያነ አበው ያገኙትን ትምህርትና ስልጣንም በ Apostolic Succsition እኛ ዘመን ላይ እንዲደርስ አድርገውታል !!!
እናም ይሄንንና መሠል ጉዳዮችን በሚጥጥዬ የአስተሳሰብ አድማሴ ለመመርመር አስባለሁ እንዴት እንደዚህ ሊሆን ይችላል ብዬ እጠይቃለሁ ???
በተለያዩ ሐገራት በተለያየ ቋንቋና ባሕል ውስጥ ያሉ ሰዎች ሳይገናኙ እንደ አንድ ቃል ተናጋሪ እንደ አንድ ቃል መካሪ ሆነው እርስ በርስ ሳይጣረሱ ለሺህ አመታት እንዴት በአንዲት ሐይማኖት በአንዲት ዶግማ አምነው ሊኖሩ ቻሉ ????
እውን ይሄ በሰው ሰውኛ አመለካከት የሚቻል የሚታሰብ ነው ብዬም ደጋግሜ እጠይቃለሁ ???
እንኳንስ የተለያየ ሐገርና የተለያየ ቋንቋ ላይ ሆኖ ይቅርና በአንድ ሐገር እየኖሩ በአንድ ቋንቋ እየተናገሩ ለሺህ አመታት ተመሳሳይ አመለካከት ተመሳሳይ እምነት ማራመድ ምን ያህል ቀላል ነው ???
ብዬም አለማችን አሁን ላይ ካለችበት ሁኔታ አንጻርም ለመመዘን ሞክራለሁ
በመጨረሻም አውጥቼ አውርጄ ለራሴ ይሄንን ምላሽ እሰጠውና መመራመሬን እደመድማለሁ
ይሄ ሁሉ የሚሆነው ነብያት በተለያየ ሐገር ላይ ሆነው ተመሳሳይ መልእክትን ተመሳሳይ ሐሳብን ባናገረና ባጻፈው በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መሪነት ብቻ ነው !!!!
ለቤተክርስቲያኗ ራስ በሆነላት በክርስቶስ ኢየሱስ መለኮታዊ ጥበቃ ብቻ የሚመነጭ ነው !!!
ለዚያም ነው ክርስቶስ በቅዱስ ወንጌሉ
" እነሆም እኔ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ሁልጊዜ ከእናንተ ጋር ነኝ።” በማለት ቃል የገባው
— ማቴዎስ 28፥19-20
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2305