tgoop.com/eotcy/2307
Last Update:
✨✨✨✨✨✨
ስንት ኦርቶዶክሳዊ ተረፈልን . . .❓
📌 ይነበብ
☞ማዕተብ ካሠረው 50-60? ሚሊየን፦
➊ከእግዚአብሔር ይልቅ ለራሱ አመለካከት የሚገዛ፤
➋በተለያየ ሱስ የታሠረ፤
➌ ቅዱስ ሥጋ ወደሙን ከሕጻንነቱ በቀር የማያውቅ፤
➍ስለ ቅድስና (ክርስትና) ተግባራዊ ሕይወትን ያላወቀ፤
➎ቤተ ክርስቲያን በመንገድ መሳለም (ብቻውን) እንደሚያጸድቀው የሚያስብ፤
➏ንስሃ መግባት ይቅርና የንስሐ አባት የሌለው፤
➐እኖራለሁ እንጂ እሞታለሁን (ኩነኔን) ያልፈራ . . .
ብለን ስናስበው፥ እውነቱን ተረድቶ ትክክለኛ ክርስቲያን የሆነ ስንት ኦርቶዶክሳዊ ይቀረናል . . .?
☞ከዚህ ተርፎ ወደ ደጁ የመጣውን ደግሞ፦
👉አጥማቂ
👉ባሕታውያን
👉ሰባኪ
👉ዘማሪ
👉Artist
ቀላጤ (Activist)
👉 ካድሬ፥ ጸሐፊ ፥ ለጣፊ፥ . . . ነን የሚሉ ዘርፈው ተከታይ አድርገውታል!
✍ ከእግዚአብሔር ይልቅ የነርሱን ድምጽ ይስቀድማል❗
✍ ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለነርሱ ክብር ጥብቅናን ይቆማል❗
እስመ በልዕዎ ለያዕቆብ"(መዝ. ፸፰)
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በታሪኳ እንዲህ የተዋረደችበት፥ ቅድስና እንኳን ግብሩ ስሙ የተረሳበት ጊዜ መኖሩን እጠራጠራለሁ፡፡
ጊዜው ደግሞ እንዳያያዛችን ታሪካዊ ጥፋት ላይ አድርሶናል
ከታላቁ ውርደት የመጨረሻ አፋፍ ላይም አቁሞናል።
በዚህ መንገድ መጨረሻን "ነበረ" ተብሎ በታሪክ እንደሚነገርላቸው አብያተክርስቲያናት እንዳያደርሰን ያስፈራል፡፡
አውቃለሁ፤ "ሐሳቡ" በራሱ ትልቅ ርዕስ ሆኖ አይሰማን ይሆናል፤
ከግል፥ ከቤተዘመድ፥ ከጓደኛ፥ ከጎሳና ከፖለቲካ ጉዳይ በላይ ገዝፎ ላያስጨንቀንም ይችላል፡፡ ግን እውነቱን መካድ አይቻለንም።
"አኃዊነ ምንተ ንግበር፤ ወንድሞቻችን ሆይ፥ ምን እናድርግ?" (ሐዋ. ፪:፴፯)
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2307