tgoop.com/eotcy/2309
Last Update:
አባቶች ስለ እመቤታችን ካስተማሯቸው ❗❗
"ሴጣን በአንዳንዶች መስቀሉን ይክዱ ዘንድ በእነርሱ ዘንድ ስራውን ይሰራል የጌታችንን ሕማማቱን እና ሞቱን እንዲያፍሩበት እና ምትሐት ነው እንዲሉ በውስጣቸው ይሰራባቸዋል፣ ከድንግል መወለዱን እና ስጋ መልበሱን ፣ እንዲሁ ም የእኛን ባሕርይ እርኩስ እንደሆነ አድርጎ ይነቅፍል። ከአይሁድ ጋር ደግሞ ሰዎች መስቀሉን እንዲክዱ ቤተ ክርስቲያንን ይዋጋታል፣ ከአሕዛብ ጋር ደግሞ ድንግል ማርያምን ይነቅፍሉ ፣ ክርስቶስ ከእርሷ ባሕርይዋን ገንዘብ አድርጎ እንዳልተወለደ አድርገው ይናገራሉ ። የክፍት ሁሉ መሪ ፊት አውራሪ የሆነው ዲያብሎስ አሰራሩ ብዙ አይነት ነውና ። እርሱ የሰዎች ፈታኝ እና አታላይ እንደ መሆኑ ሰዎችን በተለያየ መንገዶች ከእውነት ይለያቸው ዘንድ ይፈትናቸዋል ። (ቅዱስ አግናጥዮስ ፣ መልእክት ኅበ ፈልጵስዮስ ፣ ምዕ.4)
"የሁላችን መሰረት አዳም የተገኘው ካልታረሰችና ድንግል መሬት እንደ ነበር ( እግዚአብሔር አምላክ በምድር ላይ አላዘነበም ነበርና፣ ምድርንም የሚሰራበት ሰው አልነበረም ፣ ዘፍ 2፥5) እንዲሁም በእግዚአብሔር እጅ ፣ ማለትም በእግዚአብሔር ቃል የተፈጠረ እንደ ነበር ሁሉ ፣ ሁሉ የሆነው በእርሱ ነውና ፤ እግዚአብሔር ከምድር አፈር ወስዶ እንዳበጀው ሁሉ ፣ ያው የእግዚአብሔር ቃል ዳግማዊ አዳም ሆኖ ሲወለድም ድንግል ከሆነች ከቅድስት ማርያም ተወለደ ። ( ቅዱስ ሄሬኔዎስ ፣ በእንተ መናፍቃን መጽሐፈ 3፣ ምዕ ፣ ቁ. 10)
👇👇 👇👇
https://www.tgoop.com/eotcy
https://www.tgoop.com/eotcy
BY ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች

Share with your friend now:
tgoop.com/eotcy/2309